Sport View
sport tips
07/01/2026
♦️ለግማሽ ቀን ውድድር ፕሬዝዳንቱን ጨምሮ ሶስት ስራ አስፈፃሚ መጓዙ ተቃውሞ አስነስቷል
♦️የትኬትና የሆቴል ወጪን ሳይጨምር ለሶስቱ አመራሮች ከ4,200 የአሜሪካን ዶላር በላይ ወይም ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ ተመድቧል
♦️ውድድሩ ግማሽ ቀን የተያዘው አበል ለ7 ቀን መሆኑም አነጋጋሪ ሆኗል
♦️የአትሌቲክስ ቡድኑ በአውቶቡስ የ6:00 ጉዞ አድርጓል
✍️✍️በጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ(ሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል)
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን ትናንት ማምሻውን ውድድሩ ወደሚካሄድባት አሜሪካ ፍሎሪዳ ታላሃስ ከተማ ለመድረስ ትናንት ማምሻውን ወደ አታላንታ ያቀና ሲሆን አታላንታ ከተማ ከገባ በኃላ ወደ ውድድሩ ቦታ የሚወስድ በረራ ላይ ከአዲስ አበባ ሳይነሱ ተገቢው ግንኙነት ባለመፈጠሩና በኮኔክሽን ፍላይት ለመጠቀም ረዥም ሠዓት ኤርፖርት ውስጥ ለመቀመጥ ይገደዳሉ ከዚህ ይልቅ ወጥተን አውቶብስ ብንጠቀም ታላሃስ ፕሌኑ ከመነሳቱ በፊት ስድስት ተጉዘን ታላሃስ የውድድሩ ስፍራ እንደርሳለን የሚል አቋም በመያዛቸው የግማሾቹ የተከፈለበት የአውሮፕላን ትኬት ተሠርዞ የልዑካን ቡድኑ ከ4:30 እስከ 6:00 የሚፈጅ ጉዞ በአውቶቡስ ለማድረግ መገደዳቸውና በተለይ አትሌቶቹ ላይ ከረዥሙ የአውሮፕላን ጉዞ ወደሌላ የአውቶቡስ ጉዞ በማድረግ ለከፍተኛ ድካምና መንገላታት እንደዳረጋቸው ነው ከስፍራው እየደረሱን ያሉት ታማኝ የመረጃ ምንጮቻችን የሚጠቁሙት።
በቪዛ ችግር ሲታመስ የነበረው የአትሌቲክስ ቡድኑ ቀድሞ አዲስ አበባ እያሉ በኮኔክሽን ፍላይት እንዲጓዙ የሚያደርግ ዕውቀትም ልምድም ያለው የቡድን መሪን ባለማካተቱ ለአትሌቶቹ መንገላታትና በጉዞ መዳከም ትልቁን ቦታ እንደሚይዝ ነው እየተነገረ ያለው፤
አስገራሚው ነገር ግማሽ ቀን ከሚወስደው ውድድር በላይ ጉዞው ለሚበልጠው የፍሎሪዳ ታላሃስ አገር አቋራጭ ሻምፒዮና ሶስት የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት መጓዛቸው ብዙዎችን እያነጋገረ ነው።
በሠዎች ህገ-ወጥ ዝውውር(Human Trafficking)፣በገንዘብ ብክነትና በብልሹ አሠራር የምርመራ ዶክመንተሪ የተሠራበትና በጀግኖች ላብና ደም ተገንብቶ መመኪያ የነበረው ፌዴሬሽን ስሙ ጠልሽቶና በክፉ እየተነሳ ባለበት በዚህ ሠዓት ለግማሽ ቀን ውድድር ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ፌዴሬሽኑን ለአላስፈላጊ ብክነት በሚዳርግ ሁኔታ ሁለት የቡድን መሪ(ዋናና ምክትል በማለት) በተጨማሪ ፕሬዝዳንቱ ወደ ውድድሩ ስፍራ መጓዛቸው በርካቶችን አስቆጥቷል።
ታማኝ የመረጃ ምንጮች በተለይ ለሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል እንደጠቆሙት ከውድድሩ ይልቅ ጉዞው ለሚበልጠው ለግማሽ ቀን ውድድር ሁለት የቡድን መሪና ፕሬዝዳንቱ ሙሉ ወጪያቸውና አበል ተመድቦላቸው(ይውሠዱ አይውሠዱ መረጃው ባይኖረንም) መሄዳቸው ፌዴሬሽኑን ለከፋ የገንዘብ ብክነት አያዳርገውም ወይ?ደግሞስ ለግማሽ ቀን ውድድር አንድ ሠው አይበቃም?በማለት ከጠየቁ በኃላ ለአውሮፕላን ትኬት፣ለአበል የወጣው ገንዘብ ሲደመር ብክነቱን ያንረዋል።
በዚህም በህገ-ወጥ የሠዎች ዝውውርና በገንዘብ ብክነት ስሙ የጠለሸው የኦዲተሮችና አይን ያረፈበትና ዘገናኝ የኦዲት ሪፖርት የተሠማበት ፌዴሬሽኑ ካለፈው ውድመትና ስህተቶቹ ከመማር ይልቅ ጥፋትን አሻሽሎ መቀጠልን እንደመረጠ ይጠቁማል ሲሉ ድርጊቱን ኮንነዋል።
ለግማሽ ቀን ውድድር ሁለት የቡድን መሪና ፕሬዝዳንቱ በአጠቃላይ ሶስት ስራ አስፈፃሚ የተመደበላቸውን አበል ይውሠዱ አይውሠዱ ለማረጋገጥ ያደረግነው ጥረት ባይሳካም እንደ ታማኝ ምንጮቻችን ከሆነ በቀን 200፣በአጠቃላይ ከ4,200 የአሜሪካን ዶላር በላይ ወይም ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ ለ7 ቀን አበል እንደተያዘላቸው መሰማቱ ብዙዎችን እያነጋገረ ነው፤
ይሄ የገንዘብ መጠን የአውሮፕላን ትኬትንና የሆቴል ወጪን ሲጨምር ከአንድ ሚሊየን ብር በላይ ከፌዴሬሽኑ ካዝና እንዲወጣ ያስገድዳል በማለት በአንድ ሠው ማለቅ የሚችለውን ሶስት ስራ አስፈፃሚ በመሄዱ ድርጊቱን ከአላስፈላጊ ብክነት ጋር አያይዘው ተችተዋል።
ሁለቴ ቪዛ ለማግኘት ኤምባሲ ገብተው ወደ 60ሺ ብር ወጪ ከፌዴሬሽኑ ካዝና አስወጥተው ለኪሳራ የዳረጉትና ሁለቴ ቪዛ በተከለከሉት የፅ/ቤት ኃላፊው አመንሲሳ ከበደ(ዶ/ር) ምትክ እንደሄዱ የተነገረላቸው ፕሬዝዳንቱ ጉዞም አላማው ምንድነው?በማለትም በርካቶች ጥያቄ መዘዋል።
በክልል በሚካሄዱ ውድድሮችና በአፍሪካ ውድድሮች ብዙም ሲጓዙ የማይታዩትና ጉዞን እንደፊልም እየመረጡ ሲጓዙ የሚስተዋሉት ፕሬዝዳንቱ አሜሪካ ሲሆን ከፊት መገኘታቸው ጥያቄ የፈጠረባቸው ታዛቢዎች የአለም ሻምፒዮና ወይም ኦሎምፒክ ቢሆን የኮንግረስ ስብሠባ ስለሚኖር ፕሬዝዳንቱ መጓዛቸው ጥያቄ አያስነሳም፣ተገቢም ነው ካሉ በኃላ ለግማሽ ቀን ውድድር ያለበቂ ምክንያት ሶስተኛ ሠው ሆነው መሄዳቸው ግን ከብክነት ውጪ ሌላ ፋይዳ የለውም ሲሉም ተናግረዋል።
ከምንም በላይ ደግሞ በፌዴሬሽኑ ቀድሞ ባልተሠራ ደካማ ዲፕሎማስያዊ የኤምባሲ ግንኙነትና የፌዴሬሽኑ ሠዎች ባድበሠበሱት የሠዎች ህገ-ወጥ ዝውውር ኤምባሲው ጥርስ ነክሶ ቪዛ የከለከላቸው፤ ነገር ግን ሞራላቸው ሳይነካ፣እንደማይሄዱ እያወቁ ለ47 ቀናት ከተጓዦች ጋር እስከ መጨረሻው ዝግጅት ሲያደርጉ የነበሩ አትሌቶችና አሠልጣኞች ሞራላቸው ሳይጠበቅ፣ ማበረታቻም፣ተገቢው ክብር ባልተሠጠበት ሁኔታ ሶስት ስራ አስፈፃሚዎች ቡድን መሪና ምክትል ቡድን መሪ በሚል ማዕረግ ከፍተኛ ወጪ ወጥቶ ተንጋግተው መሄዳቸውን በርካቶች ቅሬታ እንዲያሠሙ ምክንያት ሆኗል።
በቀጣይ ጋዜጠኛ ጠል ስለሆኑትና አንዱን ልጅ ሌላኛውን የእንጀራ ልጅ በማድረግ ጋዜጠኛውን ስለሚከፋፍሉት የፌዴሬሽኑ አመራሮችና አሜሪካ ኤምባሲ ሁለቴ የቪዛ ጥያቄያቸውን ውድቅ ያደረገባቸው የፅ/ቤት ኃላፊ ወንበራቸው ላይ ሁለት ወር እንኳን በቅጡ ሳይደፍኑ በአለም አቀፍ ውድድሮች ላይ ለመሳተፍ ለማመልከት የሚረዳውን፣የጋዜጠኛው መብት የሆነውን አክሠስ ኮድ በመቆጣጠራቸው ዙሪያ የምመለስበት ይሆናል።
መልካም ዕድል ለጀግኖች አትሌቶቻችን💪💪
07/01/2026
መርህ የማይገዛው ፌዴሬሽን አሁንም የኃልይዮሽ ጉዞ እንደቀጠለ ነው።
አንድ ወደፊት ሁለት ወደኋላ የሚጓዘው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከስተቱ መማር ከብዶታል።
እንደሚታወቀው በታላሀሲ - ፍሎሪዳ በሚካሄደው 46ኛው ዓለም አገር አቋጭ ሻምፒዮናን አራት የሚዲያ ተቋማት ሽፋን እንዲሰጡት በማሰብ የሚዲያ አክሪዴሽን መስጠቱ ይታወሳል።
ሆኖም አክሪዴሽኑን ከሰጠ በኃላ ወትሮ የሚያደርገውን የጋዜጠኞችን ወጪ እንደማይሸፍን አስታውቋል ።
ነገሩ ወዲህ ነው ይህንን ውሳኔ ካስተላለፈ ሳይውል ሳያድር ሌላ ውሳኔ ሰማን ሰማን ።
ለአትሌቲክሱ ብዙ የለፉ እና የዘወትር ስራቸው አትሌቲክስ የሆኑት ጋዜጠኞችን ወጪ አልሸፍንም ያለው ፌዴሬሽኑ ከስፖርት ጋዜጠኝነት የወጣ ግለሰብን ወደ ፍሎሪዳ ይዞ መጓዝን መርጦል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲ ከሚዲያ ጋር የነበረው ግንኙነት እየተሻሻለ እየመጣ የነበረው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በጥቅም አባዜው አሁንም አለመውጣቱን ያሳየ ውሳኔ አስተላልፏል።
በተቋሙ የሚገኙ ግለሰቦች በጥቅም ከነሱ ጋር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚገናኙ ግለሰቦችን ከመመሪያ እና ከደንብ ውጪ ለመጥቀም ሲንቀሳቀሱ እያየን ነው።
ይሄም ወትሮውንም ቢሆን በቋፍ ላይ የሚገኘውን የፌዴሬሽኑ እና የስፖርት ጋዜጠኞች ግንኙነት መልሶ የሚያሻክር ነው።
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከወትሮ ስህተቱ ከመማር ይልቅ ስህተቱን መድም ምርጫው ማድረጉን በተደጋጋሚ እየተመለከትን እንገኛለን።
ይህ አካሄድ በፌዴሬሽኑ ውስጥ ተቋማዊ አሰራር ለመዘርጋት የሚደረገው ሂደት የሚያደናቅፍ መሆኑን ስፖርት ኮርነር ኢትዮጵያ አትሌቲክስ ተመልክቷል ።
ምንጭ ፦ ስፖርት ኮርነር ኢትዮጵያ አትሌቲክስ
14/09/2025
የአሰልጣኞቹ ሪሲሊንግ!!!
በዓለም ሻምፒዮና የሚሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ቡድን ወደስፍራው በሚያቀናበት ወቅት በጃፓን ኢንተርናሽናል ኤርፖርት ዉስጥ አሰልጣኝ ህሉፍ ይህደጎ እና ቶሌራ ዲንቃ ለግጭት ተጋብዘዋል።
ሁሌም ቢሆን የአሰልጣኞች የግጭት መንስኤ በሚሆነው የአትሌቶች መነጣጠቅ የግጭታቸው መንስኤ ነው።
ሁለቱ አሰልጣኞች በሚጣሉበት ሰዓት የአሰልጣኝህሉፍ ይህደጎ ባለቤት አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ተደርባ ግጭቱ ላይ ለመሳተፍ ሞክራለች።
በዚህም አሰልጣኝ ቶሌራ ዲንቃ የግል ሞባይ በአሰልጣኝ ህሉፍ ላይ ወርውሮበት ከአገልግሎት ዉጪ ሆኗል።
ይሁሉ ሲሆን የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ባለበት ሲሆን ለተቋሙ እና ለፕሬዝዳንቱ ያላቸውን ዝቅተኛ ክብር የሚያሳይ ነው ።
እንደዚ አይነት ግጭቶችን የማስቆም እና ዘላቂ መፍትሔ መስጠት የተሳነው ፌዴሬሽኑ ፤ መረጃዎች ማፈንን መርጧል።
15/04/2025
Ethiopian Athletics Federation’s new rules upset coaches The requirement for a master's degree in sports for the position of the head coach of the Ethiopian national team sparks discontent among current coaches
09/11/2024
ትራምፕ እና ስፖርት በቀጣዮቹ 4 አመታት ምን አይነት ግንኙነት ይኖራቸው ይሆን?
አሜሪካ በትራምፕ ዘመን ኦሎምፒክና የአለም ዋንጫን ታዘጋጃለች፡፡ ትራምፕ ስለ ስፖርት ያላቸው አቋም ምን ይመስላል? USA will host the Olympics and World Cup in the Trump era. What is Trump's stance on sports?
ይህንን አስገራሚ ዝግጅት እንድትከታተሉ ጋበዝናችሁ!
👇👇👇👇👇
አሜሪካ በትራምፕ ዘመን ኦሎምፒክና የአለም ዋንጫን ታዘጋጃለች/ What is Trump's stance on sports? ትራምፕ እና ስፖርት በቀጣዮቹ 4 አመታት ምን አይነት ግንኙነት ይኖራቸው ይሆን?አሜሪካ በትራምፕ ዘመን ኦሎምፒክና የአለም ዋንጫን ታዘጋጃለች፡፡ ትራምፕ ስለ ስፖርት ያላቸው አቋም ምን .....
07/11/2024
የሲሳይ ማስሬ የአትሌቲክስ ህይወት #ፋና #ኢትዮጵያ
06/11/2024
ሲያሳዝኑ
አግኝተው ያጡ የአውሮፓ እግር ኳስ ተጨዋቾች ታሪክ / Bankrupted european footballer amazing stories For how mind-blowingly lucrative a career in top-level football can prove, even if a player doesn’t fulfil their potential, stories of post-playing career ba...
06/11/2024
ለአትሌት ታምራት ቶላ ድምፅ እንስጥ
*በሶሻል ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪ የሆናቹ ብዙ ተከታይ ያላችሁ እና በመገናኛ ብዙሃን የምትሰሩ ህዝቡ ድምፅ እንዲሰጥ ቅስቀሳ አድርጉ።
ድምፅ መስጫ ሊንኩ
Link to vote 👉 bit.ly/3YxLVx8
05/11/2024
ሩበን አሞሪም ፔፕ ጋርዲዮላን የካውንተር ፕረሲንግ እንዴት እንደሆነ ዛሬ አሳይቶታል:: አሞሪም ቀጣዩ ፈርጉሰን ወይስ special 2 ?
ይህንን ዶክመንትሪ በአማርኛ ይከታተሉ!
አዲሱ የማንቸስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ማን ናቸው? Ruben Amorim to Man Utd? Ruben Amorim has long been of interest to Europe's top clubs following his success with Sporting in Portugal but what would the 39-year-old coach
05/11/2024
ለ2024 የዓለም ከስታዲየም ውጪ የአመቱ ምርጥ አትሌት ድምፅ ስጡ ።
በዓለም አትሌቲክስ በእያንዳንዱ ዘርፋ በዕጩዎች ከቀረቡ የመጨረሻ አትሌቶች መካከል ከ24 አመት በኃላ በኦሊምፒክ ለኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳሊያ ያስገኘው ታምራት ቶላ ነው ።
የአለም የአመቱ ምርጥ አትሌት ማን እንደሆነ ለመወሰን የመጨረሻው ዙር የድምጽ አሰጣጥ በደጋፊዎች ከጥቅምት 25 እስከ ህዳር 1 እየተካሄደ ስለሚገኝ የስፖርት ቤተሰቡ ለአገር ባውለታው ታምራት ቶላ ከታች በተቀመጠው ሊንክ ድምፃችንን እንስጥ ።
Who is your Male Athlete of the Year? 🤩
Vote for your 2024 World Athlete of the Year amongst these finalists in the .
Voting closes on Sunday 10 November at 11:59PM CET.
Link to vote 👉 bit.ly/3YxLVx8
04/11/2024
የ2024 የአመቱ ምርጥ አትሌት የመጨረሻ ዕጩዎች ሽልማቶች ይፋ ሆኗል ።
ከአለም አትሌቲክስ ካውንስል አባላት ፤ የአለም አትሌቲክስ ቤተሰቦችና የህዝብ ድምፅ ባካተተ ምርጫ በእያንዳንዱ ምድብ ሁለቱ ምርጥ መሪ አትሌቶች ፣ የትራክ፣ የሜዳ እና የስታዲየም ውጭ ዘርፎች አትሌቶች በመጀመሪያው ዙር ምርጫ ተመርጠዋል።
ከእነዚህ አትሌቶች መካከል አንዳቸው በዘርፋቸው በቀጣይ ህዳር 22 አሸናፊዎች ይለያሉ ።
ዘንድሮ በተጨመረው አዲስ ሂደት መሠረት አጠቃላይ የአለም የአመቱ ምርጥ አትሌት ማን እንደሆነ ለመወሰን የመጨረሻው ዙር የድምጽ አሰጣጥ በደጋፊዎች የሚካሄደው ከጥቅምት 25 እስከ ህዳር 1 ባለው ጊዜ ውስጥ ነው።
የመጨረሻ ዕጩዎች
ከስታዲየም ውጪ ሴቶች የአመቱ ምርጥ አትሌት
ሩት ቼፕንጌቲች (ከኬኒያ ) - የዓለም ማራቶን ሪከርድ ያዥ
ሲፋን ሀሰን (ከኔዘርላንድ ) - የኦሊምፒክ ማራቶን ሻምፒዮን
በወንዶች ከስታዲየም ውጪ የአመቱ ምርጥ አትሌት
ብሪያን ፒንታዶ (ከኢኳዶር ) - የሊሎምፒክ የ 20 ኪሎ ሜትር የእርምጃ ውድድር ሻምፒዮን
ታምራት ቶላ (ከኢትዮጵያ ) - የኦሊምፒክ ማራቶን ሻምፒዮን
የአመቱ ምርጥ ሴቶች የትራክ አትሌት
ጁሊን አልፍሬድ (ከሴንት ሉሲያ) - የኦሊምፒክ 100 ሜትር ሻምፒዮን
ሲድኒ ማክላውሊን-ሌቭሮን (ከአሜሪካ) - የኦሊምፒክ 400ሜ መሰናክል ሻምፒዮን
የወንዶች የአመቱ ምርጥ የትራክ አትሌት
ጃኮብ ኢንግብሪትሰን (ከኖርዌይ) - የኦሊምፒክ 5000ሜ ሻምፒዮን
ሌሳሌይ ቲቦጎ (ከቦትስዋና ) - የኦሊምፒክ 200 ሜትር ሻምፒዮን
የአመቱ ምርጥ የሴቶች የሜዳ ተግባራት አትሌት
ያሮስላቫ ማሁቺክ (ከዩክሬን ) - የኦሊምፒክ ከፍተኛ ዝላይ ሻምፒዮን
ናፊነሳታው ታያም (ከቤልጅየም ) - የኦሊምፒክ የጦር ውርወራ ሻምፒዮን
የአመቱ ምርጥ የወንዶች ሜዳ ተግባራት አትሌት
ሞንዶ ዱፕላንቲስ (ከሲውዲን) - የኦሊምፒክ የምርኩዝ ዝላይ ሻምፒዮን
ሚቲያዲስ ቴንቶግሎ (ከግሪክ ) - የኦሊምፒክ የርዝመ ዝላይ ሻምፒዮን
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Website
Address
Addis Ababa
1000