EthioTech

EthioTech

Share

Technology solutions in Ethiopia

Photos from Ethiopian Artificial Intelligence Institute- የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት's post 12/01/2023
03/03/2021

በሽታ አነፍናፊው የሰው ሰራሽ አስተውሎት

በአግባቡ የሰለጠኑ ውሾች ብዙ አይነት በሽታዎችን በማነፍነፍ ውጤታማ መሆናቸውን ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡ ውሾች ከካንሰር እስከ ኮቪድ-19 ድረስ በሽታዎችን በማነፍነፍ የመለየት አቅም እንዳላቸው አሳይተዋል፡፡
ሆኖም እነዚህን መሰል ውሾች ለማሰልጠን ከፍተኛ ጊዜ ከመውሰዱም ባሻገር እንደ ልብ አንቀሳቅሶ ለመጠቀም አዳጋች ነው፡፡

በኤም.አይ.ቲ (Massachusetts Institute of Technology) የሚገኙ ተመራማሪዎች ከውሾችም በተሻለ በአየር ናሙና ውስጥ የሚገኙ ኬሚካሎችን እና ረቂቅ ተህዋሲያንን ማነፍነፍ የሚችል ግኝት አለን እያሉ ነው፡፡ ይህ ግኝታቸው ከማሽን ለርኒንግ ሂደት ጋር በመጣመር የሚቀርቡለትን ናሙናዎች የየትኛውን በሽታ ባሕርይ እንደሚያሳዩ መለየት እንዳስቻላቸው ተመራማሪዎቹ አሳውቀዋል፡፡

በተመራማሪዎቹ ትንበያ መሰረት ይህ ግኝት ወደፊት የበለጠ አድጎ እራሱን ወደቻለ የጠረን-አነፍናፊ አነስተኛ ሲስተም(ስርዓት) በማደግ በእጅ ስልኮቻችን ሳይቀር መካተት ይችላል፡፡
ይህ ሲስተም በየስልኮቻችን እንደምናገኛቸው ካሜራዎች ሁሉ ወደፊት ጠረን-አነፍናፊ መተግበሪያ ያላቸው ስልኮች አይቀሬ መሆናቸውን ከተመራማሪዎቹ አንዱ የሆኑት አንድሪያስ መርሺን ተናግረዋል፡፡ እንደ ተመራማሪው ገለጻ እነዚህ ሲስተሞች በማሽን ለርኒንግ አማካኝነት የበለፀጉ እና የተራቀቁ ስልተ-ቀመሮች ይኖራቸዋል፡፡

ይህም ከበሽታዎች ቅድመ-ምልክት ጀምሮ በቤት እና ስራ አካባቢዎች የሚፈጠሩ ጭሶችን እና አደገኛ የጋዝ ሽታዎችን በማነፍነፍ ማስጠንቀቂያ መስጠት ያስችላቸዋል፡፡
የመረጃው ምንጭ፡- ሳይ ቴክ ዴይሊ

26/02/2021
19/02/2021

የቴክኖሎጂ ግዙፋኑ ወደ ታዳሽ ኃይል ጉዞ
አማዞን፣ አፕል፣ ፌስቡክ፣ ጎግል እና ማይክሮሶፍት አምስቱ ታላላቅ በመባል ይጠራሉ፡፡ ባለንበት የዲጂታል ዘመን እነዚህ ግዙፍ የቴክኖሎጂ ተቋማት ከፈጠሩት ምህዳር ውጭ መኖር የማይቻል ነው በማለት አንዳንዶች ስለ ታላቅነታቸው ማሳያ አድርገው ያነሳሉ፡፡
እነዚህ ግዙፍ ተቋማት የታዳሽ ኃይልን በመግዛት ረገድ ከሌሎች የዓለማችን ተቋማት ቅድሚያውን ይዘዋል፡፡ ተቋማቱ በዳታ ማዕከሎቻቸው ምክንያት ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይልን ይጠቀማሉ፡፡ እነዚህ የቴክኖሎጂ ኃያላን በየዓመቱ ጥቅም ላይ የሚያውሉት የኃይል መጠን በድምሩ ከ45 ቴራዋት አወር በላይ ነው፡፡

በፍጥነት እያደገ የመጣው አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እና ማሽን ለርኒንግ የሚጠይቁት ከፍተኛ የሆነ የማስላት ኃይል ፍላጎት ሲጨምር፤ የተቋማቱም የኃይል መጠን ጥያቄ እንደሚጨምር ይጠበቃል፡፡

ይህን ከፈተኛ የሆነ የኃይል ፍላጎት ለማሟላት የተለጠጠ የአየር ንብረት ግብ አስቀምጠው ለተግባራዊነቱ እየተጉ ይገኛል፡፡ በታዳሽ ኃይል ዙሪያ የሚያደርጉት ስምምነት እና የሚያስቀምጡት ግብ በተቋማቱ መካከል የፉክክር ምንጭ እስከመሆን ደርሷል፡፡

በዚህም መሰረት ማይክሮሶፍት በ2030 (እ.ኤ.አ) የበካይ ጋዝ ልቀቱን ሙሉ ለሙሉ ለማቆም ቃል ገብቷል፡፡ ይህም ማለት በየዓመቱ ወደ ከባቢ አየር ከሚለቀው በካይ ጋዝ በላይ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ከከባቢ አየር ካርበን ዳይኦክሳይድ ለመውሰድ ቃሌ ነው ብሏል፡፡
በሌላ በኩል ጎግል በ2030 (እ.ኤ.አ) ሁሉንም የዳታ ማዕከሎች ከካርበን ነጻ በሆነ የኤሌክትሪክ ኃይል ለማንቀሳቀስ እንደሚሰራ አስታውቋል፡፡

ዘግየት ብሎ ፉክክሩን የተቀላቀለው አማዞን በ2040 (እ.ኤ.አ) ከበካይ ጋዝ ልቀት ነጻ የመሆን ግብ አስቀምጧል፡፡

በተጨማሪም የማሕበራዊ ትስስር ድረ-ገጹ ፌስቡክ የታዳሽ ኃይል በመግዛት ከአለም የሶስተኝነትን ደረጃን ለመያዝ በቅቷል፡፡

በስማርት ስልክ ምርቶቹ ከፍተኛ ስኬትን ያስመዘገበው አፕል በ2030 (እ.ኤ.አ) የካርበን ልቀቴን ዜሮ አደርሳለሁ በማለት የአቻዎቹን ፈለግ ተከትሏል፡፡
በዚህም የአየር ንብረት ለውጥ የመንግስታት ጥምረት IPCC በ2050 (እ.ኤ.አ) አሳካዋለሁ ብሎ ካስቀመጠው 20 ዓመታት ቀድሞ የካርበን ልቀቱን ወደ ዜሮ ለማውረድ መስራት የአፕል ግብ ነው፡፡
የመረጃው ምንጭ፡- ፋይናንሺያል ታይምስ እና አፕል

10/02/2021

አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የሕዋ አካላትን በቅርበት ለመረዳት

የቴክኖሎጂን ከፍተኛ ግብአት ከሚፈልጉ ዘርፎች አንዱ የሕዋ ሳይንስ ነው፡፡ በዘርፉ ከፍ ያለ ደረጃ የደረሱ አካላት የጠፈርን መዳረሻዎች ከምድር እና ከሕዋ ሆነው በመቃኘት በዘርፉ ከፍተኛ ፉክክር ላይ ናቸው፡፡ በሕዋ አዳዲስ አካላትን ለማግኘት፣ ከመሬት ውጭ ያሉ ስልጣኔዎችና ፍጡራን ጋር ለመድረስ፣ ከመሬት ሌላ ምቹ የሰው ልጅ መኖሪያ ለማፈላለግ እና አሁን ደግሞ ለመዝናኛ ጭምር ጥቅም ላይ እየዋለ ይገኛል፡፡

የዚህን ዘርፍ እድገት አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ በምን መልኩ እያገዘው እንደሆነ ጥቂት ማሳያዎችን በማንሳት እንዳስሳለን፡፡


ሳይንቲስቶች አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን በመጠቀም፤ ምናልባትም ቴክኖሎጂውን ባይጠቀሙ ሊያልፏቸው የሚችሉ ከዚህ በፊት ያልመዘገቡትን ጋላክሲ፣ ሱፐርኖቫ፣ ከዋክብት፣ ብላክ ሆል እና ሌሎች የጠፈር ሁነቶችን ለማጥናት ጥቅም ላይ እያዋሉት ነው፡፡

ለዚህም ማሳያ የሆነው CHIRP (Continuous High-Resolution Image Reconstruction using Patch Priors) የተባለው ስልተ-ቀመር ከዓለም ዙሪያ ከተውጣጡ ስምንት ሬዲዪ ቴሌስኮፖች የተወሰዱ መረጃዎችን በመጠቀም የመጀመሪያውን ምሉዕ የሆነ የብላክ ሆል ምስል ለመፍጠር አስችሏል፡፡

ከግዙፍ የሕዋ ቴሌስኮፖች የሚወሰዱ ምስሎችን በዲፕለርኒንግ አማካኝነት በማጠናቀር የጋላክሲ አፈጣጠሮችን ለማስመሰል እና ለመመደብ ጥቅም ላይ እየዋለ ይገኛል፡፡


አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የጠፈር አካላትን ለመለየት አስተማማኝ መሳሪያነቱ በሳይንቲስቶች ተረጋግጧል፡፡ ሳይንቲስቶች የሰው ሰራሽ አውታረ መረብ ስልተ-ቀመር (Artificial Neural Network Algorithm) በማበልፀግ ከመሬት ጋር ተመሳሳይነት ያላቸው ፕላኔቶችን ለመለየት ጥቅም ላይ አውለውታል፡፡

በናሳ የሚገኙ ተመራማሪዎች ጄኔሬቲቭ አድቨርሰሪያል ኔትዎርክ (Generative Adversarial Networks) ተጠቅመው ከኬፕለር እና ከአውሮፓ ስፔስ ተቋም ቴሌስኮፖች የተገኙ መረጃዎችን በግብዓትነት በመውሰድ የእንግዳ ፍጡራንን መኖር/አለመኖር እየተመራመሩ ይገኛል፡፡


Earth Observer 1 (EO-1), SKICAT, ENVISAT በመባል የሚታወቁ ሳተላይቶች አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን በመጠቀም ወደ ተግባር መለወጥ የሚችሉ እና ትክክለኛ ውሳኔዎችን ለመስጠት የሚያግዙ መረጃዎችን ለተቋማት እና መንግስታት በማድረስ ይታወቃሉ፡፡


በጠፈር አካላት ላይ የሚደረጉ የማዕድን ማውጣት እንቅስቃሴዎች በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ማሽኖች አማካኝነት ማከናወን እንደሚቻል የዘርፉ ባለሞያዎች እምነት ነው፡፡ በዚህም ጠቃሚውን ማዕድን ከጎጂው በመለየት እና ማሽኖቹ የሚገጥማቸውን ችግር ያለ ሰው እርዳታ መፍታት መቻላቸው ተመራጭ ያደርጋቸዋል፡፡
የመረጃው ምንጮች፡- analyticsinsight. net እና techcrunch. com

This Company Uses a Wall of 100 Lava Lamps to Encrypt Data 18/01/2018

https://interestingengineering.com/this-company-uses-a-wall-of-100-lava-lamps-to-encrypt-data

This Company Uses a Wall of 100 Lava Lamps to Encrypt Data Lava lamps are finally being put to good use thanks to the efforts of Cloudflare, who is utilizing them as unique data encryption tools.

Sir Tim Berners-Lee: The Man Who Invented the World Wide Web 09/06/2017

http://interestingengineering.com/sir-tim-berners-lee-who-invented-world-wide-web/

Sir Tim Berners-Lee: The Man Who Invented the World Wide Web The World Wide Web has changed our lives as we know it, let's take some time to honor its creator Sir Tim Berners-Lee on his 62nd birthday.

Could an app help you study? - CNN Video 29/04/2016

Could an app help you study? - CNN Video It's a unique technology start-up in Ethiopia. Co-founders Eskinder Mamo and Amanuel Abrha combined their passions and created a company, called AhadooTec, that makes apps, from travel to education.

Use YouTube to record screencasts for free 28/01/2016

YouTube ተጠቅመው ዴስክቶፕዎን መቅዳት (record) እንደሚችሉ ያውቃሉ?

እስቲ ተከታዩን ሊንክ በመጫን እንዴት እንደሆነ ይከታተሉ::

Use YouTube to record screencasts for free

Want to record your desktop? A little-known YouTube option makes it possible, no extra software required.

Use YouTube to record screencasts for free Want to record your desktop? A little-known YouTube option makes it possible, no extra software required.

The Ethiopian AI Geeks Building Cutting-Edge Robots 26/01/2016

The Ethiopian AI Geeks Building Cutting-Edge Robots

Discover iCog-Labs in 's university district, the first Ethiopian research and development laboratory specializing in artificial intelligence.
Worldcrunch

The Ethiopian AI Geeks Building Cutting-Edge Robots ADDIS ABABA — The black-and-white robot stopped and its eyes, two small red lights, suddenly lit up. Rotating about 90 degrees, it recognized the blue plastic ball a few centimeters away, came forward and kicked it.

Why successful people wear the same thing every day 26/01/2016

Why Mark Zuckerberg and other successful men wear the same thing every day?

Why successful people wear the same thing every day

Want your business to be the top-listed Computer & Electronics Service in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address


Bole Road
Addis Ababa
1032