AMN-Addis Media Network
This is the official page of AMN- Addis Media Network ‘Voice of generation.’ stay connected🤳
07/06/2026
19ኛው ግማሽ ማራቶን ለሐገር ዓቀፍ ውድድሮች መነቃቃት አስተዋጽኦ አለው - አትሌት ስለሺ ስህን
AMN ግንቦት 30/2018
በአዲስ አበባ በታላቅ ድምቀት የተካሄደው 19ኛው የኢትዮጵያ ግማሽ ማራቶን የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ከፍተኛ ፉክክር የተደረገበት መሆኑን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አትሌት ስለሺ ስህን ገለጹ።
ፕሬዝዳንቱ በተለይ ለኤ ኤም ኤን በሰጡት ማብራሪያ የዘንድሮው ውድድር ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የተሳታፊዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ የጨመረበትና ለሀገር ዓቀፍ ውድድሮች መነቃቃት አስተዋጽ ያለው ነው ብለዋል፡፡
ውድድሩ አትሌቶች በጉጉት የሚጠብቁትና ክለቦች እንዲሁም ክልሎች ከፍተኛ ፉክክር የሚያደርጉበት መሆኑን ነው አትሌት ስለሺ የገለጹት፡፡
ተተኪ አትሌቶች ከነባርና ልምድ ካላቸው አትሌቶች ጋር አብረው በመወዳደር ራሳቸውን እንዲመዝኑ እና ብቃታቸውን እንዲያሳድጉ ዕድል የሚፈጥ ነው ብለዋል።
ውድድሩ ዓመታዊ እንደመሆኑ መጠን ከሁሉም የሀገሪቱ ክልሎች የመጡ አትሌቶች የተሳተፉበት መሆኑንም ገልጸዋል።
ይህ አገር አቀፍ ውድድር በዴንማርክ ኮፐንሀገን ለሚካሄደው ማራቶን ኢትዮጵያን ወክለው የሚሳተፉ አትሌቶች የሚመረጡበት መሆኑን ፕሬዝዳንቱ አስገንዝበዋል።
በዘንድሮው ዓመት በአጠቃላይ የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድሮችን የማዘጋጀት እንቅስቃሴ ከሌላው ጊዜ በበለጠ መልኩ ከፍተኛ መነቃቃት የታየበት እና ደረጃው ከፍ ያለ እንደነበር አትሌት ስለሺ ስህን በጥንካሬ አንስተዋል።
በፍሬሕይወት ብርሃኑ
አሁን
AMN - ግንቦት 30/2018 ዓ.ም የቀን 6፡00 ዜናዎቻችንን በቀጥታ ይከታተሉ፤ 👇👇👇👇👇👇👇
ትክክለኛውን የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ የትስስር አውታሮችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑን!
https://linktr.ee/AddisMediaNetwork
AMN - ግንቦት 30/2018 ዓ.ም
19ኛው የኢትዮጵያ የግማሽ ማራቶን የወንዶች ውድድር አሸናፊ አትሌት ጌታቸው ማስረሻ
👇👇👇👇👇👇👇
ትክክለኛውን የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ የትስስር አውታሮችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑን!
https://linktr.ee/AddisMediaNetwork
መንግሥት የሚሊሻውን ኃይል አደረጃጀት ዘመናዊ ለማድረግ፣ በዕውቀትናበሥልጠና ለማበልጸግ፣ እንዲሁም ትጥቅና አቅርቦቱን ለማሻሻል የጀመረውንተቋማዊ የሪፎርም ሥራ አጠናክሮ ይቀጥላል። - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
👇👇👇👇👇👇👇
ትክክለኛውን የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ የትስስር አውታሮችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑን!
https://linktr.ee/AddisMediaNetwork
07/06/2026
አዲሷ የስፖርት ቱሪዝም መዳረሻ - አዲስ አበባ
AMN ግንቦት 30/2018
አዲስ አበባ ዛሬ በፈጠነ የልማት ምዕራፍ ውስጥ ትገኛለች። ከተማዋን ያስዋባት የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ዘመናዊ የስፖርት መሰረተ ልማቶችን ያካተተና ያቀናጀ በመሆኑ አዲስ አበባን ለዓለም አቀፍ ስፖርታዊ ውድድሮች ምቹ ከተማ እንድትሆን አስችሏታል።
የስፖርት ማዘውተሪያዎች መስፋፋት ፣ ዓለም አቀፍ ስፖርታዊ ሁነቶችን ማካሄድ የሚያችሉ አማራጭ አውዶች መኖራቸው የጎዳና ላይ ውድድሮች ፣ የቤት ውስጥ እና የሜዳ ላይ ውድድሮች ማዘጋጀት የሚያስችል አቅም ተፈጥሯል፡፡
አዲሶቹ የእግረኛ መንገዶች ፣ የብስክሌት መጋለቢያዎች፣ የስፖርት ማዝወትርያዎች እና አረንጓዴ ስፍራዎች ለአትሌቶች ልምምድ ምቹ ከመሆናቸውም በላይ፣ ከተማዋን ለዓለም አቀፍ የማራቶን እና የብስክሌት ውድድሮች መድረክ እያደረጓት ይገኛሉ።
እየተገነቡ ያሉት ዘመናዊ ስታዲየሞች እና የተገነበቡት ሁለገብ የስፖርት ማዕከላት እንደ የመዋኛ፣ የቅርጫት ኳስ እና ቴኒስ የመሳሰሉት ለዓለም አቀፍ ውድድሮች የሚያስፈልገውን መስፈርት የሚያሟሉ ናቸው።
በርካታ ዓለም አቀፍ ደረጃ ያላቸው ሆቴሎች እና የዲፕሎማሲ ማዕከል መሆኗ፣ ለውድድር የሚመጡ እንግዶችን በብቃት ለማስተናገድየሚያስችል አቅም ፈጥሮላታል፡፡
ከዓለም አቀፍ ከተሞች ጋር ያላት የበረራ ቀጥተኛ ትስስር ለስፖርት ልዑካን የጉዞ ምቾት የሚሰጥ በመሆኑ ተደራሽ ደርጋታል፡፡
የኮሪደር ልማቱ አዲስ አበባን በአፍሪካ ደረጃ ቀዳሚ የከተማ ልማት ሞዴል ብቻ ሳይሆን፣ የስፖርት ኢኮኖሚን የሚያነቃቃ ማዕከል አድርጓታል።
ይህ የተቀናጀ ስራ አዲስ አበባን ለቀጣይ ታላላቅ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፍ ውድድሮች በግንባር ቀደምትነት ማስተናገድ የሚያስችላት ነው፡፡
በፍሬሕይወት ብርሃኑ
07/06/2026
የኢቦላ ቫይረስ ወረርሽኝ በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና በዩጋንዳ ከተከሰተ ጊዜ ጀምሮ ጥብቅ የቅኝት እና የልየታ ሥራ እየተሰራ ነዉ
AMN ግንቦት 30/2018 ዓ.ም
የኢቦላ ቫይረስ ወረርሽኝ በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና በዩጋንዳ ከተከሰተ ጊዜ ጀምሮ የኅብረተሰብ ጤና አደጋ ማስተባበሪያ ማዕከልን በማጠናከር ጥብቅ የሆነ የቅኝት እና የልየታ ሥራ እየተሰራ ነዉ መሆኑን የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ገለጹ፡፡
የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ የኢቦላ በሽታ ወረርሽኝን ለመከላከል የሚያስችል የባለሙያች የተግባር ልምምድ ተመልክተዋል፡፡
የኢቦላ ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል ዝግጁነት ለማጠናከር ይቻል ዘንድ በኅብረተሰብ ጤና አደጋ ቁጥጥር የመግቢያ እና መውጫ የጤና ቁጥጥር ባለሙያዎች በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ የጤና ልየታ፣ የቁጥጥር እና የቅኝት ሥራዎች ላይ ትኩረት ያደረገ የባለሙያዎች ተግባራዊ ልምምድ (Simulation exercise) እየተደረገ ይገኛል።
ልምምዱን የተመለከቱት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ፣ ኢቦላ ቫይረስ ወረርሽኝ በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና በዩጋንዳ ከተከሰተ ጊዜ ጀምሮ የኅብረተሰብ ጤና አደጋ ማስተባበሪያ ማዕከልን በማጠናከር ጥብቅ የሆነ የቅኝት እና የልየታ ሥራ እንዲሠራ የተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
ወረርሽኞችን ከመከላከል እና ከመቆጣጣር አንጻር ከዚህ በፊት የነበሩትን ልምዶች እና አሁን የተገኘውን እውቀት መሠረት በማድረግ በቀጣይ እስከ ታችኛው የጤና ተቋም እና የኅብረተሰብ ጤና አደጋ ቁጥጥር ባለሙያዎች በማውረድ ሁሉም ዝግጁ እንዲሆን ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።
ሀገራችንን፣ ቤተሰባችንን፣ ኅብረተሰባችንን ከማንኛውም የኅብረተሰብ ጤና አደጋ ችግሮች በመጠበቅ እና በመታደግ ለትውልድ የሚሻገር ሥራ በመሥራት ኃላፊነታችንን ልንወጣ ይገባል ሲሉም ማሳሰባቸውን ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
የጥበብ ፍለጋ በውብ አዲስ!!
👉የፊልም ባለሙያዎች ውድድር (Film Reality Show)
ዛሬ ምሽት 2:00 ሰዓት ይጠብቁ
አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ
የትውልድ ድምፅ
07/06/2026
ኑ ሃገር እንስራ !
👇👇👇👇👇👇👇
ትክክለኛውን የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ የትስስር አውታሮችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑን!
https://linktr.ee/AddisMediaNetwork
አትሌት መሰለች አለማየሁ የ19ኛው የኢትዮጵያ የግማሽ ማራቶን የሴቶች ሩጫ ዉድድር አሸናፊ
👇👇👇👇👇👇👇
ትክክለኛውን የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ የትስስር አውታሮችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑን!
https://linktr.ee/AddisMediaNetwork
ኑ... ሀገር እንስራ!
የህዝባችንን ፅናት፣ የዴሞክራሲ ልዕልና እና ያልቆመውን የልማት ጉዞ የሚያሳይ ዶክመንተሪ።
ዛሬ ምሽት 3፡00 ሰዓት ይጠብቁን!
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Telephone
Website
Address
5 Kilo
Addis Ababa
251