EthioPost

EthioPost

Share

Ethiopian News,information & Entertainment portal Entertainment ....

Photos from EthioPost's post 26/04/2020

ነብስ ይማር 😭😭😭

እህታችን ወገኔ

በዋሽንግተን ዲሲ ሜሪላንድ በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ሕይወቷ ያለፈው

የአራት ልጆች እናት የሆነችው ወ/ሮ ወገኔ ደበሌ የቀብር ስነስአት ከሰአታት በፊት ተፈፅሟል።

በድጋሚ ነፍስ ይማር እያልን ለቤተሰቦቿ መፅናናትን እንመኛለን።

ምንጭ voa

Photos from EthioPost's post 26/04/2020

በኢትዮጵያ ዛሬ ተጨማሪ 12 ስዎች:-

* 12ቱ ከአዲስ አበባ

ከኮሮናቫይረስ የተሻላቸው ሲሆን

* በአጠቃላይ ከ123ቱ ስዎች ውስጥ

* 41 ስዎች ከኮሮና ቫይረስ በሽታ አገግመዋል

እስቲ ይሄ መልካም ዜና ሼር አድርጉት

ምንጭ :- የኢትዮጵያ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር

26/04/2020

ምከሩት ከማፈያ ቡድን ጋር አንሶላ እየተጋፈፈ ነው ተባለ ሲሉ ምንጮቻችን አስታወቁ

"ምከሩት!!! ከስር ያለውን ፎቶ ያገኝሁት ከSintayehu Chekol ገጽ ላይ ነው፣ ከእስክንድርን ጋር በፎቶ የሚታየው ዘርፉ ነው፣ ዘርፉ ቦክሰኛው ይባላል፣ የፈንሳይ ልጅ በሚገባ ያውቀዋል!! ህግ የማይመልሰው እጅግ አደገኛ የማፍያ ቡድን መሪ ነው፣ ህዝብን ደም እንባ ያስለቀሰ!! don't take my words! ጌታቸው ሽፈራው በደንብ ያውቀዋል፣ ጌታቸው ፈረንሳይ እንደኖረ አውቃለሁ፣ ስለዚህ እሱን ጠይቁት!! እረ ፈረንሳይ መኖር አይጠበቅብህም ዘርፉን ለማወቅ፣ he is famous for wrong reasons!!!

ከዚህ በፊት የስድስት ኪሎ፣ የ05 እና የፈረንሳይ ማጅራት ቆልማሚዋችን የባልድራስ መስራች ብሎ በፎቶ ይዟቸው ወጥቷል፣ እነዚህን ሰዋች እስር ቤት እንደተዋወቃቸው መጠርጠር ይቻላል፣ ሰውየው ለነዚህ ሰዋች ሽፋን እየሰጠ ነው፣ ወንጀለኛን እያበረታታ ነው፣ empower እያደረጋቸው ነው፣ ነገ ጠዋት ሰው ገለው በቁጥጥር ስር ቢውሉ የባልድራስ አባላት በፖለቲካ አመለካከታቸው ታሰሩ መባሉ አይቀርም፣ this is so personal to me as my whole families are in the visinity!!!"

05/04/2020

የጣረ-ሞት ስም የያዙ ህፃናች >>> አጀብ ነው ዘንድሮ
------
በህንድ የተወለዱ ሴትና ወንድ መንትዮች ኮሮና እና ኮቪዲ የሚል ስም እንደወጣላቸው ተሰማ።

በኮሮና ቫይረስ ስርጭት ስጋት ህዝባችን ከቤት እንዳይወጣ በመታዘዙ እኛም በዚህ ጭንቅ ሰአት ልጆች ስለወለድን ልጆቻችን የተወለዱበትን ግዜ ለማስታወስ ኮሮና እና ኮቪዲ በማለት ሰይመናቸዋል ሲሉ በማእከላዊ ህንድ ቻቲስጋሪ ግዛት የሚኖሩት የመንትዬዎቹ ወላጆች መናገራቸውን አልጀዚራ ዘግቧል።

ህንድ ከቤት በኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ከቤት አለመውጣት ባዘዘች ከሁለት ቀን በኋላ ባለፈው ሳምንት የተወለዱት መንትዬዎቹ ከወጣላቸው ስም በፊት ሌላ ስም የወጣላችው ቢሆንም ባልና ሚሰቱ ቪናይ ቬርማ እና ፕሪቲ ቬርማ ስማቸውን አስቀይረውታል።

እናት ፕሪቲ ቬርማ እንዲህ አለች " በኮሮና ምክንያት ህንድ ጭንቀት ውስጥ ናት የልጆቻችን ስም ነገ በሽታው ሲጠፋ ሀገራችን የነበረችበትን ጭንቀት ያስታውሰናል " ብላለች።

አባት ቪናይ ቬርማ በበኩሉ " የልጆቻችን ስም ከኮሮና መጠበቅ ንፅህናንና እጅ መታጠብን እንደሚጠይቀው ይሄን ተግባር በሽታው ቢጠፋም የሁል ግዜ ተግባር እንድናደረገው ያስተዋስናል " ብሏል።

05/04/2020

በኮሮና ምክንያት ህይወታቸው ያለፈው የ60 ዓመት እናት : -ነብስ ይማር ->> RIP

Photos from EthioPost's post 05/04/2020

እህተ-ማርያም...

በእሷና በተከታዮቿ የቀን አቆጣጠር መሰረት የፋሲካን በዓል በዛሬው እለት ስታከብር

ምንጭ፣ አሉ .....ተባለ
እንኳን ለበዓሉ በሰላም አደረሰሽ እህተ ማሪያም
--------
የዝግጅት ክፍሉ

Photos from EthioPost's post 05/04/2020

ሟቿ የጋዜጠኛዋ አክስት ነበሩ!
----------------------
->>የኮሮና ሟች ኑዛዜ " የሃገሬ ህዝቦች ሆይ እራሳችሁን ከአስከፊው ቫይረ ስጠብቁ "
•••••
በአሁኑ ስዓት በኦሮሚያ ቴሌቭዥን ውስጥ እየሰራች የምትገኘው ጋዜጠኛ ቢሊሴ ኢሬና የ60 ዓመት አዛውንት አክስቷ በኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ የኮሮና ቫይረስ ሟች መሆኗን ተከትሎ በፌስቡክ ገጿ የሚከተለውን አስፍራለች።

“Biyya France turtee gara biyyaati Kan deebite adaadaankoo dhukuba koronaan qabamtee biyya keessati yaalamaa erga turtee booda hara boqoteetii. Waan jeenuu hinqabnuu nagaan boqodhu.
Yaalamiikoo maaloo dhukuba kanairraa of eegaa.”

"ፈረንሳይ ሐገር ቆይታ በቅርቡ ወደ ሐገር ቤት የተመለሰችው አክስቴ በኮሮና ቫይረስ ተይዛ የህክምና ርዳታ ሲደረግላት ከቆዬች በኋላ በዛሬው እለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች። ሰዎች ሆይ እባካችሁ ከዚህ ገዳይ ቫይረስ ራሳችሁን ጠብቁ"

Photos from EthioPost's post 05/04/2020

በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ሞት ተመዘገበ ->>ሁለት ሰዎች ዛሬ ተቀበሩ->>43 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘው አይሲዩ ውስጥ ናቸው
*******************
የጤና ሚኒስቴርና ኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የኮሮና በሽታ (ኮቪድ-19) በቻይና ውሃን ከተማ ከተቀሰቀሰበት ግዜ አንስቶ ወደ ሀገራችን ቫይረሱ እንዳይገባ እንዲሁም ከገባ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል ዝግጅት እያደረጉ መቆየቱ ይታወቃል፡፡

ቫይረሱ ወደ ሀገራችን ከገባ ጀምሮ ህብረተሰቡ የጥንቃቄ እርምጃዎችን ተግባራዊ እንዲያደርግ ቅስቀሳዎችን እያደረገና የተጠቂዎችን ቁጥርና የጤና ሁኔታቸው እያሳወቀ ነው፡፡ አንዲት የ60 ዓመት ታማሚ መጋቢት 19 ፣2012 ዓ.ም በኮሮና ቫይረስ በሽታ ምልክት ታይቶባቸው በለይቶ ማከሚያ ገብተው የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው የነበረ ሲሆን በመጋቢት 22፣2012 ዓ.ም በኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው መረጋገጡ ይታወሳል፡፡

ይሁንና ከመጋቢት 22 አንስቶ ላለፉት ስድስት ቀናት በፅኑ ህክምና ላይ የነበሩ ሲሆን በዛሬው እለት ህይወታቸው አልፏል፡፡ የጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በህልፈተ ህይወታቸው የተሰማውን ሀዘን እየገለፀ ለቤተሰቦቻቸው መፅናናትን ይመኛል፡፡

ህብረተሰቡ በዚህ ሳይደናገጥ ለተለያዩ ጉዳዮች በአንድ ቦታ መሰባሰብን በማስወገድ፣ እጅን አዘውትሮ በመታጠብ፣ በአካል ንክኪ የሚደረግ ሰላምታን በመተውና አካላዊ መራራቅን (ቢያነስ አንድ ሜትር) ተግባራዊ በማድረግ የበሽታውን ስርጭት እንዲከላከል በጥብቅ እናሳስባለን፡፡

05/04/2020

በኮሮና አይሲዩ(ICU) ውስጥ የገባው የመጀመሪያው ከብት
ምንጭ:- ፌክ ኒውስ አለርት ፣ከአለርት ሆስፒታል

Photos from EthioPost's post 02/04/2020

መሃል አዲስ አበባ ኮሮና ተብሎ የተበደበ ነጫጭባ ( ኩርድ ነጭ ካውካሺያን ስላልሆነ ነው; ) ) =>> መልእክት
ተመልከቱ ወገን

ይህ ወጣት ኢትዮጵያውያን ውስጥ የሚኖር የቱርክ ኮርዳዊ ነው ስሙም ሞ ጃርክስ ይባላል

በዩኒት ዩኒቨርስቲም በሲቪል ኢንጀርነት እየተማረ ይገኛል

ዛሬ በፌስብኩ ፔጅ ይህን አለ:-

መብራት ይዞኝ መኪና አቆሜ ነበር ከዛ ስዎች መጥተው በብረት አንተ ኮሮና እያሉ ጭንቅላቴን ፈነከቱኝ

እንደምታዩኝ ደም በደም ሆኛለው ግን ደሞ ፈጣሪ አትርፎኛል

እኔ አማረኛ እናገራለው የኢትዮጵያ ባህልም አውቃለው እዚህ ሀገርም ነው የምኖረው

ነገር ግን ነጭ ስለሆንኩ ብቻ ኮሮና ቫይረስ አንተ ነህ ያመጣህብን እያሉ ፈነከቱኝ

ምንም ያደረጉትን ነገር የለም ግን እንዲዚ አደረጉኝ

ምንጭ : - Mo Jarkas

Photos from EthioPost's post 02/04/2020

ስለኮሮና ጥንቃቄ ምክር የለገሰው ግለሰብ ደመ ከልብ ሆነ

♦ መሸለም የነበረባቸውን ሰው ደበደቡት !!!

ያሬድ አማረ ፦ ሰፈሩ ብሔረ ጽጌ አካባቢ ሲሆን ፤ በትላንትናው ዕለት ሰፈሩ አካባቢ ሲንቀሳቀስ ብዙ ሰዎች በአካባቢው ባሉ መጠጥ ቤቶች ተሰባስበው፣ ሳይራራቁ ሲጠጡ በማየቱና ለሁሉም ስጋት የሆነው ኮሮናን ለማስተላለፍ ምቹ መሆናቸውን በማየትና በመታዘብ ፤ ይሄ ድርጊት መታረምም እንዳለበት በማኅበራዊ ሚዲያ በራሱ ገጽ ላይ በመግለጽ ፣ እንዲሁም የሚመለከተው አካል የመፍትኄ እርምጃ እንዲወስድ ጥሪ አስተላልፉ ነበር።

ይሁን እንጂ ፤ ጠዋት ላይ ከዚህ በፊት የሚያውቃቸው ሁለት ወጣቶች ዛቻና ማስፈራሪያ አድርሰውበት የሄዱ ሲሆን ፤ አመሻሽ ላይ ደግሞ በድጋሚ መጥተው ደብድበውት ሄደዋል። እሱም የደረሰበትን በደል አካባቢው ለሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ አመልክቷል ።

02/04/2020

እህታችንን እናድናት........

(ሁሉም ሰው በማድረግም ይተባበር)

ይህቺ በፎቶ ላይ የምትመላከቷት ወጣት ትግስት ፋንቱ ትባላለች በአሁኑ ሰዓት ሁለቱም ኩላሊቶቿ የመስራት አቅማቸው ስለተዳከመ የኩላሊት ንቅለ ተከላ በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ማድረግ እንዳለባት ተግሯታል ቢሆንም ንቅለ ተከላው እስኪደረግላት ድረስ ቢያንስ እስከ ከስድስት ወር በላይ ስለሚቆይ እስከዛ ዲያሌስስ በሳምንት ሶስት ጊዜ እያደረገች መቆየት አለባት ወጪውም በአጠቃላይ 250.000 ብር በላይ ስለሚያስፈልጋት እባካችሁ በእግዚአብሔር ስም ከጎኗ እንቁም እላለው?ትግስት በተማረችበት ሙያ ሀገርዋን እና ወገንዋን የማገልገል፣ ህልም አላት ህልሟን ከእግዚአብሔር ጋር እውን እናድርገው።ተባረኩ።

ለመርዳት ምትሹ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000174062823 ትግስት ፋንቱ ብላችሁ ማስገባት ትችላላችሁ።በአካል ለማግኘት ለምትሹ 0920707352 ካሌብ ብላችሁ መደወል ትችላላችሁ።

Want your business to be the top-listed Media Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Website

Address


Addis Ababa