Cbe/ats
Cbe/ats is a financial company, which dedicate itself to facilitate the gap of online payments in Ethiopia.
12/09/2025
❗
የኢፌዲሪ ፕላንና ልማት ሚንስትሪ የነበሩት ክብርት ዶ\ር ፍፁም አሰፋ የብሄራዊ ባንክ ዋና ገዢ ተደርገው ተሾሙ!!
የኢፌዲሪ ፕላንና ልማት ሚንስትሪ የነበሩት ክብርት ዶ\ር ፍፁም አሰፋ የብሄራዊ ባንክ ዋና ገዢ ተደርገው ተሾመዋል!!
መልካም የስራ ጊዜ ይሁንልዎ❗
⛔️ This news is not independently verified by Banking Matters ‼️
Subject: Congratulations on Our Outstanding Achievement!
Dear ............
I am thrilled to share some exciting news that reflects our collective hard work and dedication. The CBE Board of Management and Executive Management has approved a 3-month bonus and a 2-step salary scale increase for all employees in recognition of our extraordinary performance in 2024/25 across all major KPIs.
This achievement is a testament to the commitment and excellence each of you brings to our organisation. Your efforts have contributed to our success and set a remarkable standard for our branches.
As we celebrate this milestone, let us continue to strive for excellence and maintain the momentum that has brought us here. Together, we will ensure that CBE remains as strong and strategic as ever.
Thank you for your hard work and dedication!
Congratulations again!
Best regards,
........
VP- CR
12/07/2025
እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ አለን!!
14ኛ የሕብረት ስምምነት ተፈረመ፡፡
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ማሕበር መካከል በድርድር ላይ የነበረዉ 14ኛዉ የሕብረት ስምምነት ተጠናቆ ዛሬ ሐምሌ 5 ቀን 2017 ዓ.ም ተፈርሟል፡፡
በዕለቱም የገንዘብ ሚንስቴር ሚንስትር እና የባንካችን ዳይሬክቴሮች ቦርድ ሰብሳቢ ክቡር አቶ አህመድ ሽዴ ፣ የባንካችን ፕሬዝደንት ክቡር አቶ አቤ ሳኖ ፣ሰራተኞችን በመወከል የስራ አመራር ቦርድ አባል የሆኑት ክቡር አቶ ኦላኒ ሴቃታ፤ የኢሠማኮ ፕሬዝደንት አቶ ካሳሁን ፎሎ፣የኢትዮጵያ የፋይናንስ ተቋማት እንዱስትሪ ፌዴሬሽን ፕሬዝደንት አቶ ደስታ በርሃ፣ የባንኩ ከፍተኛ አመራሮች ፤ የዲስትሪክት ዳይሬክቴሮች ፤ የሁሉም ቅርንጫፍ ማኔጄሮች ፣ የማሕበራችን ስራ አስፈፃሚ እና ኦዲት ኮሚቴ አባላት ፣ የቀድሞ የማሕበራችን አመራሮች እና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት የፊርማ ስነስርዓት ተከዉኗል፡፡
12/07/2025
ሀሳብ ስጡበት👇👇👇
12/07/2025
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብድር ጠይቆ የሚያጣ አንድም ኢትዮጵያዊ እንዳይኖር ስትራቴጂ ተቀምጧል ። አቶ አቤ ሳኖ
10/07/2025
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተለያዩ የአፈፃፀም መለኪያዎች የገበያ ድርሻውን ከ49.6% -50.1% አሳድጓል ። ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ
**************
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተጠናቀቀው የ2017 በጀት ዓመት ከ515 ቢሊየን ብር በላይ ተጨማሪ ተቀማጭ ገንዘብ በማሰባሰብ አጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘቡን 1.69 ትሪሊዮን ብር ያደረሰ ሲሆን፣ የገበያ ድርሻው 49.6 በመቶ ሆኗል።
የባንኩ ጠቅላላ ሀብት 2.3 ትሪሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን፣ ይህም የገበያውን 50.1 በመቶ የገበያ ድርሻ እንዲይዝ አስችሎታል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአሁኑ ጊዜ ከ43.1 ሚሊዮን በላይ ደንበኞች አሉት።
እንኳን ደስ አለን!! እንኳን ደስ አላችሁ!!
ባጠናቀቅነው በጀት ዓመት ብቻ ከ515 ቢሊየን ብር በላይ ተጨማሪ አዲስ ተቀማጭ ገንዘብ አሰባስበን አጠቃላይ ተቀማጭ 1.69 ትሪሊዮን ብር በማድረስ ታላቅ ስኬት አስመዝግበናል
የተከበራችሁ ደምበኞቻችንና የተወደዳችሁ የባንካችን ሰራተኞች!፤
ሰላምታዬ በያላችሁበት ይድረሳችሁ፤
ባጠናቀቅነው የ2024/25 በጀት ዓመት በፈረንጆቹ ጁን ወር መጨረሻ፤ ባንካችን ከ515 ቢሊየን ብር በላይ ተቀማጭ ገንዘብ የማሰባሰብ ተግባር በማሳካቱ የተሰማኝን ከፍ ያለ ደስታ ልገልጽላችሁ እወዳለሁ፡፡ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ በባንካችን የተመዘገበ አዲስ ታሪክ ነው፡፡ ለዚሁ ታላቅ ስኬት አሻራችሁን ላኖራችሁ ሁሉ እንኳን ደሰ አላችሁ እላለሁ፡፡
በተለይም ባንካችን ላይ እምነታችሁን አሳድራችሁ አብራችሁን ለሰራችሁ ውድ ደንበኞቻችን ምስጋናዬ ይድረሳችሁ፡፡ ይህ ስኬት የናንተ እገዛና ያላሰለሰ ጥረት ድምር ውጤት ነው፡፡ የባንካችን የዳይሬክተሮች ቦርድ አመራሮችና አባላት ለውጤቱ መሳካት ያደረጋችሁት ክትትልና ድጋፍ የነበረው አስተዋጽኦ ከፍ ያለ ነው፡፡ ድካማችሁ ፍሬ አፍርቶ ለማየት ስለበቃችሁ እንኳን ደስ አላችሁ፡፡ የባንካችን የስራ አመራር አባላት፣ የሪጅን እና የዋናው መ/ቤት ሰራተኞችና የሥራ ኃላፊዎች፣ የዲስትሪክቶችና የቅርንጫፍ ሰራተኞቻችን፣ የባንካችንን ስትራቴጂዎች እና አቅጣጫዎች ለመተግበር ያሳያችሁት ቁርጠኝነት ለስኬቱ ከፍ ያለ ሚና አበርክቷል፡፡
እዚህ ስኬት ላይ ለመድረስ ያሳየነው ታታሪነት እና ትጋት ፍሬ ሰጥቶን ለማየት በመብቃታችን ስሜቱ ጥልቅ ነው፡፡ በየደረጃው ያሉ የስራ ክፍሎቻችን በትብብርና በትጋት የመስራት ውጤት አስረጅ ነው፡፡ የባንካችን ሰራተኞች በጋራ ሆነን እና ተናበን ያሳየነው ጥረት ውጤት ለመሆኑም ጥርጥር የለውም፡፡
ደንበኞቻችንን ለማገልገል ባሳየነው ቁርጠኝነት የተገኘ የላቀ አፈጻጸም ስለመሆኑም አምናለሁ፡፡ ደንበኞቻችንን በማስቀደም እና ፍላጎታቸውን በመረዳት፤ ተገቢውን አገልግሎት ለማቅረብ ያደረግነው ትጋት ማሳያ ነው፡፡
ለባንካችን ይህ ስኬት ትርጉሙ ከፍ ያለ ነው፡፡ ይህም፡-
የባንካችን ሰራተኞች ታታሪነትና ጠንካራነት ማሳያ
በትብብር የመስራት እና ለአንድ ዓላማ የመቆም ምልክት
ለባንካችን ያለንን ፍቅርና የባለቤትነት ስሜት ምስክር
ለደንበኞቻችን የምንሰጠውን አክብሮትና ዋጋ የገለጽንበት እና
የባንካችንን ራዕይ ለማሳካት ያለንን ቁርጠኝነት ያመላከትንበት ነው ማለትም ይቻላል፡፡
በሌላ መልኩም ባንካችን ፈተናዎችን እና ተግዳሮቶችን በመቋቋም፣ በጥንካሬ እና በከፍታ መዝለቅ የቻለ መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው፡፡
የተከበራችሁ የባንካችን ሰራተኞች!፤
ለዚህ ስኬት አስተዋጽኦ ለነበራችሁ ትጋት ሁሉ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ። ያሳየነው ስኬት ድንቅ እና ሁላችንንም የሚያስደምም ነው፡፡ ሁላችንም ልንኮራ ይገባናል። ለመጪው በጀት ዓመት ታላቅ ስንቅ ሆኖን በላቀ ከፍታ ለመጓዝ ጠንክረን እንቀጥል፡፡
ለተሻለ ስኬት እንትጋ!
አመሰግናለሁ፡፡
አቤ ሳኖ
ፕሬዝዳንት
" የውጭ ባንኮች እና ኢንቨስተሮች ማመልከቻቸውን ለብሔራዊ ባንክ ማቅረብ ይችላሉ " - ብሔራዊ ባንክ
ኢትዮጵያ የባንክ ዘርፉን ለውጪ ባንኮች ክፍት ማድረጓን በይፋ አስታወቀች።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያን የፋይናንስ ዘርፉን ለውጭ ባንኮች ለመክፈት የሚያስችለውን መመሪያ አጽድቋል።
ባንኩ፥ መመሪያ ቁጥር SBB/94/2025 ወይም "የባንክ ሥራ ፈቃድ፤ የእድሳት መስፈርቶች እና የውክልና ቢሮ መመሪያ " መጽደቁን ነው ያስታወቀው።
በዚህ መመሪያ መሰረትም ለመጀመሪያ ጊዜ የውጭ ባንኮችን ጨምሮ ሌሎች ስትራቴጂክ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ የባንክ ሥርዓት ውስጥ እንዲሳተፉ ይፈቅዳል።
ብሔራዊ ባንክ ትላንት ባወጣው መግለጫ ፥ " የኢትዮጵያ የባንክ መስክ ለውጭ ኢንቨስተሮች ተከፍቷል፤ የውጭ ባንኮች እና ኢንቨስተሮች ማመልከቻቸውን ለብሔራዊ ባንክ ማቅረብ ይችላሉ " ሲል አስታውቋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
ከስራ ድካም በኋላ ፈታ በሉ👇👇👇😁
ሰውዬው በድመቱ ይበሳጭና አውጥቶ ይጥላታል። ምሽት ላይ ድመቷ ወደ ቤት ትመለሳለች።በማግስቱ እንደገና ራቅ ወዳለ ስፍራ ወስዶ ይጥላታል። ይሁንና እሱ እቤቱ ሳይደርስ ድመቷ ቀድማው ደርሳ አገኛት። ንዴቱ የባሰ ጨመረ፣ ደሙ ፈላ። ከዚያ በጆኒያ አድርጎ እርሱ ራሱ ወደማያውቀው ሌላ ከተማ ወስዶ በጣም ውስብስብ ባለ ሰፈር ውስጥ አዙሮ፣ አሽከርክሮ ጣላት። ይሁንና ይህን እርምጃ ከወሰደ በኋላ እሱ ራሱ እንዴት ወደ ቤቱ ይመለስ? ቢዞር፣ ቢሽከረከር መንገዱ ጠፍቶት ወደ ቤቱ መመለስ አቃተው። የመጨረሻ ሲጨንቀው ወደ ቤቱ ስልክ ደወለና ባለቤቱ ስልኩን አነሳች ....
ባል: ሄሎ ሃኒ
ሚስት: ሄሎ የት ጠፋህ የኔ ማር?
ባል: ትንሽ ለጉዳይ ወጣ ብዬ ነው። ድመቷ አለች?
ሚስት: አዎ ምነው?
ባል: አንዴ አቅርቢልኝ 😅
26/06/2025
ደጉ ዘመን!!
ከለውጡ በፊት😉
09/11/2020
Condemnation of President Trump’s reckless remark on the Grand Ethiopian Renaissance Dam- pls sign the petition and also share to others
Condemnation of President Trump’s reckless remark on the Grand Ethiopian Renaissance Dam | We the People: Your Voice in Our Government We the people of Ethiopia, Ethiopian origin & friends of Ethiopia are deeply concerned & offended by the statement recently made by the POTUS evoking that Egypt should blow up the GERD. Despite the long-standing relationship our two nations enjoyed, President Trump’s remarks are wrong, reckless an...
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Addis Ababa