Ethio Inform
provide relevant information to society
04/10/2021
talented actress ruta mengsteab
02/10/2021
ለግለሰቧ መጠለያ እና ህክምና እንድታገኝ የሚመቻች ሲሆን
በተጨማሪም በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ማዕከል ውስጥ
ስራ የምትጀምር ይሆናል።" - ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ
የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ አንዲት በመንገድ ዳር
የተቀመጠችን እናት በልጅዋ ፊት ጭካኔ የተሞላበት ኢ-ሰብዓዊ
ድርጊት ሲፈፀምባት አይተው በመረጃ ያጋለጡ ግለሰቦችን
አመሰግነዋል።
የከተማዋ ፖሊሶች አብዛኛዎቹ በትህትናና ቅንነት ህዝቡን
እያገለገሉ ቢሆንም በጥቂት ስነ-ምግባር የጎደላቸው የፖሊስ
አባለት የሚፈፀም ተግባር ደግሞ በፍጥነት መታረም
እንዳለበትም ከንቲበዋ ተናግረዋል ።
በመሆኑም ድርጊቱ መፈፅሙ እንደታወቀ ፖሊሶቹ በቁጥጥር ስር
እንዲውሉ ተደርጓል። ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙም ክትትል
እናደርጋለን ብለዋል።
በቀጣይም ለግለሰቧ መጠለያ እና ህክምና እንድታገኝ
ይመቻቻል በተጨማሪም በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ማዕከል
ዉስጥ ስራ እንድትጀምር ይደረጋል ብለዋል ከንቲባ አዳነች ።
ከንቲባ አዳነች ከህብረተሰቡ ጋር ተባብረን ስንሰራ፤ እንደዚህ
አይነት ኢ-ሰብዓዊ ድርጊቶችን ማስቆም እንችላለን፤ አሁንም
በርቱ መሰል ድርጊቶችንንም አጋልጡ ብለዋል በማሕበራዊ
ትስስር ገፃቸው ጉዳዩን አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት።
ebc
01/10/2021
ሰሜን ኮሪያ ሐሙስ ዕለት አዲስ የፀረ-አውሮፕላን ሚሳኤል ሙከራ ማድረጓን ገለጸች .................................................
በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ አራተኛ የጦር መሣሪያ ሙከራዋ ሆኖ ተመዝግቧል።
ሰሜን ኮሪያ አዲሱን ሙከራዋን ያደረገችው የኒውክሌር አቅም
እንዳለው የሚታመነውን አዲስ የሃይፐርሶኒክ ሚሳኤል ሙከራ
ካደረገች ከጥቂት ቀናት በኋላ ነው።
የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ሙከራዎቹ
"አለመረጋጋትን እና አለመተማመንን የበለጠ ይፈጥራሉ"
ብለዋል።
ፒዮንግያንግ የጦር መሣሪያው ራስን ለመከላከል የሚያስፈልጉ
መሆናቸውን በመግለጽ አሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያን "ፍትሐዊ
ያልሆነ አቋም ይዘዋል" በማለት ወንጅላለች።
ሙከራዎቹ ምንም እንኳን ጥብቅ ማዕቀቦች ቢኖሩም
ፒዮንግያንግ የጦር መሣሪያ መሥራቷን ለማዘግየት ፍላጎት
እንደሌላት የሚያሳይ ግልፅ ምልክት ተደርገው ተወስደዋል።
በመንግሥታዊው የዜና ማሰራጫ ኬሲኤንኤ መሠረት አዲሱ
የፀረ-አውሮፕላን ሚሳኤል "አስደናቂ አፈፃፀም" ያሳየ ሲሆን
"አዳዲስ ቁልፍ ቴክኖሎጂዎችን" አካቷል ሲል ዘግቧል።
ሙከራው የተደረገው የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ-ኡን
ከደቡብ ኮሪያ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ወደነበረበት መመለስ
እንደሚፈልጉ መግለጻቸውን ተከትሎ ነው።
ኪም የአሜሪካን ዲፕሎማሲያዊ ተሳትፎን ከሰዋል። " አሜሪካ
ዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ በማታለል የጥላቻ ድርጊቱን
ለመደበቅ ሞክራለች" ብለዋል።
አንዳንድ ተንታኞች ፒዮንግያንግ ከደቡብ ኮሪያ ጋር ግንኙነቷን
በማስቀጠል አሜሪካን በማስወጣት ዋሽንግተን እና ሴኡልን
ለመለያየት እንደምትፈልግ አመላካች ነው ብለው ያምናሉ።
ሆኖም ሰሜን ኮሪያ የማዕቀብ እፎይታን እና ሌሎች ድጋፎችን
አሜሪካ እንድታደርግላት የደቡብ ኮሪያን ድጋፍ ትፈልጋለች።
ሰሜን ኮሪያ ከዓለም ተቆራርጣ ከአንድ ዓመት በላይ
አሳልፋለች።
ወረርሽኙ በተከሰተበት ወቅት ከቅርብ አጋሯ ከቻይና ጋር
አብዛኛውን ንግዶች አቋርጣለች። በዚህም ምክንያት
ኢኮኖሚው በአስከፊ ሁኔታ ውስጥ በመሆኑ የምግብ እጥረት
አሳሳቢ ነው ተብሎ ይታሰባል።
በመጋቢት ወር አገሪቱ ማዕቀቦችን ወደ ጎን በማለት የባልስቲክ
ሚሳኤሎችን ሞክራለች። ይህም ከአሜሪካ፣ ከጃፓን እና ከደቡብ
ኮሪያ ጠንካራ ወቀሳ አስነስቶባታል።
ባለፈው ወር የተባበሩት መንግሥታት የአቶሚክ ኤጀንሲ ሰሜን
ኮሪያ "በጣም አሳሳቢ" ያለውን ለኒዩክሌር መሣሪያዎች
የሚረዳ ፕሉቶኒየም ማምረት የሚችል ማብላያዋን እንደገና
እንደጀመረች ገልጿል።
01/10/2021
የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታ ምክር
ቤት በኢትዮጵያ ጉዳይ ዛሬ ይወያያል
ተባለ
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ዛሬ አርብ
በኢትዮጵያ የትግራይ ክልል ጉዳይ ላይ እንደሚወያይ ተገለጸ።
የምክር ቤቱ መርሃ ግብር እንዳመለከተው ቀደም ሲል ከተያዘ
ጉዳይ ውጪ በሆነ መድረክ የፀጥታው ምክር ቤት አባልት
በትግራይ ክልል ውስጥ ስላለው ሁኔታ ይወያያሉ ብሏል።
ይህ የምክር ቤቱ ስብሰባ የኢትዮጵያ መንግሥት ሰባት
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅቶች ውስጥ የሚሰሩ ከፍተኛ
ኃላፊዎች በአገሪቱ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ እንደገቡ በመግለጽ
ከግዛቱ እንዲወጡ ካዘዘ በኋላ የሚደረግ ስብሰባ ነው።
የኢትዮጵያ መንግሥት ውሳኔን ተከትሎ የተመድ ዋና ፀሐፊ
አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በእርምጃው መደንገጣቸውን አመልክተው፤
ውሳኔውን በተመለከተ ከኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣንት ጋር
እየተወያዩ መሆኑን ገልጸዋል።
የአሜሪካ፣ ዩናይትድ ኪንግደም እና ጀርመን መንግሥታት
በዓለም አቀፉ ድርጀት የሰብአዊ እርዳታ ሠራተኞች ላይ
የተወሰደው እርማጃ እንዳሳሰባቸው በመግለጽ የኢትዮጵያ
መንግሥት ውሳኔውን እንዲያጤን ጠይቀዋል።
ዛሬ ይካሄዳል የተባለውን ይህንን የፀጥታው ምክር ቤት ስብሰባ
እንዲካሄድ የጠየቁት የምክር ቤቱ አባል የሆኑት ኢስቶኒያ ፣
ፈረንሳይ፣ አየርላንድ፣ ኖርዌይ፣ ዩክሬንና አሜሪካ ናቸው።
አስራ አምስት አባላት ያሉት ከፍተኛው የተባበሩት መንግሥታት
ድርጅት የውሳኔ አካል የሆነውን የፀጥታው ጥበቃ ምክር ቤትን
የፕሬዝዳንትነት መንበር ዛሬ በሚጀምረው የፈረንጆቹ የጥቅምት
ወር የምትረከበው ኬንያ ናት።
ምክር ቤቱ ለዛሬ በያዘው ስብሰባው በጥቅሉ በኢትዮጵያ
የትግራይ ክልል ስላለው ሁኔታ እንደሚወያይ የተነገረ ሲሆን፤
ሐሙስ ዕለት የኢትዮጵያ መንግሥት የመንግሥታቱ ድርጅት
ሠራተኞችን ከአገሩ እንዲወጡ የሰጠው ውሳኔ ላይ
እንደሚነጋገር ይጠበቃል።
በተጨማሪም በሠሜን ኢትዮጵያ እየተካሄደ ባለው ጦርነት
ሳቢያ የትግራይ ክልል የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦትንና ያለውን
አሳሳቢ ሰብአዊ ቀውስ በተመለከተ ሊወያይ ይችላል ተብሏል።
የተባበሩት መንግሥታት የትግራይ ክልል ይፋዊ ባልሆነ የሰብአዊ
እርዳታ እገዳ ስር ነው ሲል የገለጸ ሲሆን፣ የድርጅቱ የሰብአዊ
እርዳታ ኃላፊ ማርቲን ግሪፊትስ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ
በክልሉ ረሃብ ሳይከሰት እንደማይቀርም ብለው እንደሚገምቱ
መግለጻቸው ይታዋሰል።
ኃላፊው የኢትዮጵያ መንግሥት የእርዳታ አቅርቦት የያዙ
ተሽከርካሪዎች ወደ ትግራይ እንዲገቡ እንዲያደርግ ጠይቀው
"ይህ ችግር ሰው ሰራሽ ነው፣ መንግሥት እርምጃ ከወሰደ
መፍትሄ ሊያገኝ ይችላል" ሲሊ ለሮይተርስ ዜና ወኪል
ተናግረዋል።
ኒው ዮርክ ሚገኘው በተባበሩት መንግሥታት የኢትዮጵያ ተልዕኮ
በበኩሉ ወደ ትግራይ እርዳታ እንዳይገባ "እገዳ ተጥሏል
የሚባለው ክስ መሰረተ ቢስ ነው" ሲል አጣጥሎታል።
ጨምሮም የረድኤት ድርጅቶች "እርዳታ ለማቅረብ የሚያስችሉ
የጭነት ተሽከርካሪዎች እጥረት የገጠማቸው ቀደም ሲል ወደ
ትግራይ እርዳታ ለማድረስ የተሰማሩ መኪኖች ሳይመለሱ
በመቅረታቸው ነው" ማለቱን ሮይተርስ ዘግቧል።
በትግራይ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች የእርዳታ ድጋፍ
እንደሚያስፈልጋቸውና በመቶሺዎች የሚቆጠሩ ደግሞ በረሃብ
ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ የመንግሥታቱ ድርጅት ሲገልጽ ቆይቷል።
ይፋዊ ያልሆነ የሰብዓዊ እርዳታ እቀባ ተደርጓል የሚሉት
የተባበሩት መንግሥታት የአስቸኳይ ጊዜ የሰብዓዊ እርዳታ
አቅርቦት ኃላፊ ማርቲን ግሪፊትስ፤ ወደ ትግራይ መድረስ
ከሚገባው እርዳታ 10 በመቶ ብቻ ለተረጂዎች መቅረቡን
በመግለጽ በክልሉ ረሃብ ጉዳት እያስከተለ ነው ብለው
01/10/2021
በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት የሚካሄደው ዓለም አቀፉ የቴሌኮም
ኮንፈረንስ ለስኬታማነቱ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የኢኖቬሽንና
ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ገለፀ
*******************
በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት የሚካሄደው ዓለም አቀፉ የቴሌኮም
ኮንፈረንስ ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን አፍሪካንም የሚወክል
በመሆኑ ለስኬታማነቱ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የኢኖቬሽንና
ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ አህመዲን መሐመድ(ዶ/ር)
አስታወቁ፡፡
የአለም አቀፉ የቴሌኮሙኒኬሽን ልማት ጉባኤ አዘጋጅ የኢትዮጵያ
ብሄራዊ ኮሜቴ ዝግጅቱን የተመለከተ ስብባውን አካሂዷል።
በአፍሪካ ለመጀሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ የሚካሄደው ይህ ጉባኤ
በስኬት እንዲጠናቀቅ አስፈላጊ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች
እየተሰሩ መሆናቸውን ኮሚቴው አንስቷል።
የብሄራዊ ኮሚቴው ሰብሳቢ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር
ዴኤታ አህመዲን መሐመድ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት
የሚካሄደው ዓለም አቀፍ የቴሌኮም ኮንፈረንስ ኢትዮጵያን ብቻ
ሳይሆን አፍሪካንም የሚወክል በመሆኑ ለስኬቱ በትኩረት
እየሰራን ነው ብለዋል።
ዓለም አቀፉ የቴሌኮም ኮንፈረንስ በኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን
ቴክኖሎጂ ዘርፍ ከዓለም ሀገራት ልምድ የምንለዋወጥበትና
የኢትዮጵያን ገፅታ የምንገነባበት ይሆናል ያሉት ሚኒስትር
ዴኤታው፣ ለዝግጅቱ በስኬት መጠናቀቅ የሚመለከታቸው ሁሉ
በትብብር እንዲሰሩ አሳስበዋል።
Ebc
01/10/2021
አሁን የሚካሄደው የመንግሥት ምሥረታ ኢትዮጵያ ካለችበት
ችግር ለመውጣት የሚያግዝ ነው፦ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ
*************
አሁን የሚካሄደው የመንግሥት ምሥረታ ኢትዮጵያ ካለችበት
ችግር ለመውጣት የሚያግዝ መሆኑን የኢትዮጵያ ዜጎች
ለማኅበራዊ ፍትሕ /ኢዜማ/ መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተናገሩ።
ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከኢቲቪ ጋር በነበራቸው ቆይታ አዲስ
በሚመሠረተው መንግሥት ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተሳትፎ
እንዲኖራቸው በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከብልጽግና ፓርቲ ጋር
ምክክር መጀመሩን ገልጸዋል።
የተወሰኑ የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች በፓርላማ ወንበር
ማግኘታቸውም የተለያዩ ሐሳቦች እንዲንሸራሸሩ ዕድል የሚፈጥር
መሆኑን ነው የተናገሩት።
በቀጣይ ሀገሪቷ አሁን ካለችበት ችግር እንድትወጣ መንግሥት
የሚመሠርተው ፓርቲ እና ተፎካካሪ ፓርቲዎች ሕዝብን ያስቀደመ
ኃላፊነት እንዳለባቸው የኢዜማ መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ
ገልጸዋል።
Ebc
30/09/2021
ዶ/ር ይልቃል ከፍአለ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ሆነው
ተሾሙ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)የአማራ ክልል
ትምህርት ቢሮ ሃላፊ የነበሩት ዶክተር ይልቃል ከፍአለ አስረስ
ለክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ሆነው ተሹመዋል፡፡
የቀድሞው የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኝው ተሻገር
አዲስ ለተመረጡት ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር ይልቃል ከፍአለ
የስራ ርክክብ አድርገዋል።
ክልሉን ለአምስት አመታት መምራት የሚችሉ ምክትል ርዕሰ
መስተዳድርን ጨምሮ የቢሮ ሃላፊዎች ሹመት ይሰጣል።
ሹመቱ የስራ ሃላፊዎቹን የትምህርት ዝግጅት የአመራር ብቃት
እንዲሁም አካባቢውን በሚገባ የተረዳ መሆኑን መሰረት ያደረገ
ነው ተብሏል።
ebc
29/09/2021
ኢትዮ ቴሌኮም የኮሙኒኬሽን ኢንጅነሪንግ ተማሪዎች ዘመኑ
የደረሰበትን የቴሌኮም ቴክኖሎጂ የተግባር ስልጠና እንዲያገኙ
የሚያስችል የቴክኖሎጂ መሳሪያዎች ድጋፍ ለዩኒቨርሲቲዎች
እንደሚያደርግ ገለጸ።
በዋና ሥራ አስፈፃሚ ወ/ት ፍሬሕይወት ታምሩ የተመሩ
የኩባንያችን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ
የቴክኖሎጂ ቤተ-ሙከራና ዳታ ሴንተርን የጎበኙ ሲሆን፣ በቀጣይ
ተማሪዎች ተግባራዊ የቴሌኮም ምርምር እና ሙከራ
የሚያደርጉባቸውን መሣሪያዎች ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልፀዋል።
በተጨማሪም ታሪካዊው የሼህ ሆጀሌ አልሃሰን ባህላዊ የዳኝነት
እና የዕርቅ ችሎት አዳራሽን በመጎብኘት ባህላዊና ዘመን ተሻጋሪ
እሴቶችን በማስቀጠል ችሎቱ በማህበረሰቡ ዘንድ የሚፈጠሩ
አለመግባባቶችና ቅሬታዎችን በአጠረ ጊዜ ለመፍታት ያለውን
ከፍተኛ አስተዋጽኦ በመግለጽ የተጀመረው የማዕከሉ ጥገናና
ግንባታ በአጭር ጊዜ ተጠናቆ አገልግሎት እንዲሰጥ ኩባንያችን
የበኩሉን አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ ገልፀዋል።
29/09/2021
ህጋዊ ፈቃድ ሳያገኙ ድሮኖችን ለቀረፃ መጠቀምና ማብረር
በህግ ያስጠይቃል - የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት
ህጋዊ እውቅና ሳያገኙ ድሮኖችን የሚጠቀሙና ሲያበሩ የሚገኙ አካላት
በህግ ተጠያቂ እንደሚሆኑ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት
አገልግሎት አሰታወቀ፡፡
አገልግሎቱ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ
አንዳንድ ግለሰቦችና ድርጅቶች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ
ከሚመለከተው አካል ህጋዊ ፈቃድ ሳያገኙ ድሮኖችን በሀገሪቱ
በሚካሄዱ ሃይማኖታዊ፣ ባህላዊ እና ህዝባዊ ሁነቶች ላይ ቀረፃ
የሚያካሂዱና ሲያበሩ የሚገኙ አካላት ከህገውጥ ከህገ ወጥ
ድርጊታቸው ሊታቀቡ እንደሚገባ አሳስቧል፡፡
የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የሀገሪቱን ደህንነትና
ብሔራዊ ጥቅም የመጠበቅ ተልዕኮ የተሰጠው ተቋም መሆኑ
አስታውሶ ÷ ከሚመለከተው አካል ፈቃድ ሳያገኝ ድሮኖችን
ለቀረፃ ሲጠቀም እና ሲያበር የተገኘ ማንኛውም አካል ወይም
ግለሰብ በህግ እንደሚጠየቅ አስጠንቅቋል፡፡
FBC
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Addis Ababa
18/03/2022