HaqCheck
A multilingual fact-checking initiative, dedicated to verifying false claims in Ethiopia and Africa.
05/10/2025
✅ ሀቅቼክ የዓለም አቀፉ የእውነታ አጣሪዎች ትስስር International Fact-Checkers Network(IFCN) ዕውቅና ያለው ፈራሚ ሆነ!
በኢንፎርም አፍሪካ ስር የተቋቋመው የሀቅቼክ ሀቅን የሚያጣራ ተቋም የዓለም አቀፉን የሐቅ አጣሪዎች መረብ (IFCN) የስነ ምግባር መርሆዎች የተረጋገጠ ትስስር በይፋ መቀላቀሉን ስናበስር በታላቅ ደስታ ነው። ይህም ሐቅቼክን ከኢትዮጵያ የመጀመሪያውና ብቸኛው ሐቅን የሚያጣራ አገልግሎት ያደርገዋል።
ይህ እውቅና በኢትዮጵያና ከዚያም በላይ የሀሰተኛ መረጃን በመታገልና የመረጃ ምሉዕነትን በማስፋፋት ረገድ ለገለልተኝነት፣ ለግልጸኝነት እና ለተጠያቂነት ያለንን ቁርጠኝነት የሚያረጋግጥ ነው።
ይህ እውን እንዲሆን ላደረጉት ለአጋሮቻችን እንዲሁም ለቀድሞ ባልደረቦቻችን እና የሀቅቼክ የቡድን አባላት በሙሉ ከልብ የመነጨ ምስጋናችንን እናቀርባለን።
Read more: https://ifcncodeofprinciples.poynter.org/profile/haqcheck-inform-africa
09/01/2025
የባንክ ቁጥሩ የአቶ ክርስትያን ታደለ ንግድ ባንክ አካውንት ኣይደለም!
ከሰሞኑ ከ15ሺህ በላይ ተከታይ ያለው የX ወይም በቀድሞ ስሙ ትዊተር አካውንት የቀድሞ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የህዝብ ግንኙነት ሀላፊና የኢፌዲሪ ህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባል የሆኑትን እና በአሁን ሰዓት በእስር ላይ የሚገኙት አቶ ክርስትያን ታደለ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ላይ ባለው አካውንታቸው ወደ 74 ሚልዮን የሚጠጋ ብር እንዳላቸው በመግለፅ የአንድ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥርን ከኮምፕዩተር ላይ በማንሳት አጋርቶ ነበር።
ከዚህም ባለፈ ይህ አካውንት አንድ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል እንዴት ይህን ያህል ገንዘብ ሊኖረው እንደቻለ ሲጠይቅ እና ከህዝብ ትወካዮች ምክር ቤት አባላት ደሞዝ ጋር ሲያወዳድረው ተመልክተናል።
ይህ በX ላይ የተጋራው ከ46ሺህ በላይ እይታዎች ሲኖሩት ከ139 በላይ ግብረ መልሶች አሉት። በX ላይ በተጋራው ፖስቱ ላይ ያለው ምስል የተለወጠ መሆኑን ከሚያሳዩ ነገሮች አንዱ Currency በሚለው የመግለጫ ቦታ ላይ “ETB Kristian Tadele” የሚል ፅሁፍ ይታያል።
የአቶ ክርስትያን ታደለ ነው ተብሎ የተቀመጠው የንግድ ባንክ ቁጥር “1000335830378” ሲሆን ሀቅቼክ በቀላል መንገድ የአካውንት ቁጥሩን ለማጣራት ባደረገው ጥረት አካውንቱ “The Memory of Artist Hachalu Hundesa” በሚል ስም የተከፈተ እንደሆነ ማረጋገጥ ተችሏል።
ሀቅቼክ ከዚህ በፊት ይህን መረጃ በተለያዩ ጊዜያት ሲጋራ አግኝቶት የነበረ ሲሆን በወቅቱም ከ136 ሺህ በላይ ተከታዮች ባሉት የፌስቡክ ገፅ በመጋቢት 22 ቀን 2015 ዓ.ም ላይ አገኝቶት ነበር።
ይህ መረጃ በድጋሚ ከአንድ አመት እና ጥቂት ወራቶች በኋላ በድጋሚ እየተጋራ እንደሆነ ማስተዋል ችለናል። ሀሰተኛ መረጃዎች ጊዜና ሁኔታዎችን እየጠበቁ በድጋሚ ሊጋሩ ይችላሉ። ሁልጊዜም ቢሆን መረጃዎችን ከማጋራታችን በፊት እናጣራ።
03/01/2025
የበዓል ወቅቶች በቀረቡ ቁጥር በኦንላይንም ከኦንላይን ውጪም የተለያዩ ሰዎችን የማጭበርበሪያ እና የማጥመጃ መንገዶች ጥቅም ላይ ይውላሉ። በአሁኑ ጊዜ እነዚህ አጭበርባሪዎች ከሚጠቀሟቸው መንገዶች አንዱ የሰዉን ደካማ ጎን እና ስሜቱን ሊይዝ የሚችሉ ነገሮችን በመጠቀም ሲሆን ሰዎች ሽልማቶችን እና ገንዘቦችን ማግኘት ከፈለጉ በፍጥነት እንዲያደርጉ በመገፋፋት ሰዎች ውሳኔን እንዲወስኑ ሲያደርጉ እንመለከታለን።
ይህንንም ሲያደርጉ የተለያዩ ታዋቂ ፤ ሀብታም እና ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦችን ስም እና ማንነት ከዚህም ባለፈ የታዋቂ ድርጅቶች ምልክቶችን እና ድረ-ገፆችን አስመስሎ በመስራት ታማኝ ለመምሰል ሲሞክሩ ይስተዋላል።
ከሰሞኑ በተለያዩ የፌስቡክ ገፆች ላይ ሼክ መሀመድ ሁሴን አሊ አል አሙዲን ለመጪው የገና በዓል ለኢትዮጵያውያን የ75ሺ ብር ስጦታ እየሰጡ እንደሆነ እና ሽልማቱንም ለማግኘት የተቀመጠውን ሊንክ በመጫን በድረ-ገፁ ውስጥ ያለውን ፎርም እንዲሞሉ ያስገድዳል።
ሀቅቼክ ከነዚህ መረጃዎች በመነሳት በእነዚህ የፌስቡክ ገፆች የተጋራውን ሊንክ ትክክለኛነት ያጣራ ሲሆን ኦንላይን የሚገኙ የማጣሪያ መሳርያዎችን ተጠቅመን ስንመለከት ሊንኩ የሚወስደን ድረ-ገፅ አደገኛ እና ሰዎችን ለማጥመድ የተዘጋጀ እንደሆነ ማረጋገጥ ችለናል። ከዚህ በተጨማሪም የማስፈንጠርያ ሊንኩን ሳንጫን ሊንኩ ሊወስደን የሚችለውን ድረ-ገፅ መመልከት ችለናል።
ሼክ መሀመድ ሁሴን አሊ አል አሙዲን እና ቤተሰቦቻቸው በተለያዩ ጊዜያቶች በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች እና በበዓላት ጌዜያቶች አቅም ለሌላቸው ወገኖች እርዳታን እንደሚሰጡ ይታወቃል።
ይሁን እንጂ ሀቅቼክ በፌስቡክ ገፆቹ የተጋራውን ፖስት እና የተያያዘውን ሊንክ በማጣራት ሰዎችን የማጥመጃ እና የማጭበርበር ይዘት እንዳለው ማረጋገጥ ችሏል።
ሙሉውን ያንብቡ https://bitl.to/3Yrn
26/12/2024
Dhiheenya kana akkaawuntii miidiyaa hawaasaa Abdurahman Buno jedhamun beekamu maxxansa falmii bal'aa kaase maxxanse ture. Barreeffamni kun suuraa iskiriinii fuula Feesbuukii Ministirri Muummee Abiy Ahmad irra fudhame jedhame kan kitaaba mata duree 'HIN GAABBU' jedhu kan Jawaar Mohaammad barreesse qabatanii agarsiisan kan of keessatti hammate yoo ta'u, akkasumas barreeffama "Reefu maxxansa addaa kitaaba “HIN GAABBU” argadheera. Kitaaba guddaadha, garuu natti hin tolle. hunduu akka dubbisu nan gorsa.Hafuura ispoortiitiin dubbisuuf qophaa'aa."
Seenaan siyaasaa walxaxaa Jawaar Mahaammad fi Muummicha Ministeeraa Abiy Ahmad gidduu jiru fedhii ummataa yaada maxxansa kana irratti cimsee kan ture yoo ta’u, himannaan kunnis fuula Feesbuukii adda addaa irratti qoodamaa ture. yeroo maxxanfamuttiis deebii 10,000 ol fi sheerii 300tti dhiyaatu argate jirra.
Haa ta'u malee HaqCheck maxxansa sana sakatta'ee soba ta’u isaa mirkanesera.
https://bit.ly/3Dv2WkR
13/12/2024
ከሰሞኑን በተለያዩ ማህበራዊ ሚድያዎች በዋናነት በዩትዩብ እና ቲክቶክ ላይ በተለያዩ የሃገራችን አርቲስቶች ስም በርከት ያሉ ሙዚቃዎች በመሰራጨት ላይ ይገኛሉ። እነዚህ ሙዚቃዎች በዋናነት ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸው ሲሆን በአጭር ጊዜ ውስጥ በርካታ ተመልካቾችን እንዲሁም ግብረ መልሶችን ማግኘት ችለዋል። ይሁንና እነዚህ ሙዚቃዎችን ጠለቅ ብለን ስንመለከታቸው በArtificial Intelligence (ሰው ሰራሽ አስተውህሎት) የተዘጋጁ ሆነው እናገኛቸዋለን። በአሁኑ ሰዓት ከቴክኖሎጂ መዘመን ጋር ተያይዞ በሰውሰራሽ አስተውልሆት የሚሰሩ ነገሮችን መለየት አስቸጋሪ እየሆነ ቢመጣም በኦንላይን የሚገኙ እና በሰውሰራሽ አስተውህሎት የተሰሩ ድምፆችን እና ቪድዮዎችን የመለያ መሳሪያዎችን ተጠቅመን ስናጣራ እነዚህ ከሰሞኑ እየተለቀቁ ያሉት ሙዚቃዎች አብዛኛዎቹ በአርቲስቶቹ የተዘፈኑ እንዳልሆኑ እና በሰውሰራሽ አስተውልሆት የተሰሩ እንደሆኑ ማረጋገጥ ችለናል።
ይህ ድርጊት ምናልባትም ገንዘብ ለማግኘት አልያም ደግሞ ፖለቲካዊ ጥቅም ለማግኘት ታዋቂ ሙዚቀኞችን ስም በመጥቀስ እና የነሱ ስራ በማስመሰል ተከታዮቻቸውን ለማንቀሳቀስ የተከናወነ ሊሆን ይችላል።
ነገርግን እንዲህ አይነቱ ሃሰተኛ ስያሜዎች በአርቲስቶቹ ስም ፣ ስራ እና ፖለቲካዊ አቋም ላይ ከሚያመጣው ተጽዕኖ ባለፈ በተከታዮቻቸው ዘንድ እምነት ማጣትን፣ የሚወዷቸውን ሙዚቀኞች ያላስተላለፉትን አቋም መያዝ እና ማንጸባረቅን ያስከትላል።
11/12/2024
በቅርቡ በፌስቡክ በሰፊው የተጋራ አንድ ፅሁፍ በጎጃም ክፍለጦር ውስጥ የፋኖ የፖለቲካ መምሪያ ሀላፊ የነበሩት አቶ አስረስ ማረ ለቢቢሲ የሰጠው ቃለምልልስ በሚል ተሰራጭቷል።
በመግለጫው “ከጠላት ጋር እያደረግነው ባለው ውጊያ ብልጫ ተወስዶብናል ነገር ግን ለሽንፈት የሚያበቃ አይደለም” የሚለው ጥቅስ አብሮ ተያይዞ ተሰራጭቷል። ይህ የፌስቡክ ልጥፍ አቶ አስረስ ማረ በፋኖ እና በመከላከያ መካከል እየተካሄደ ባለው ጦርነት መንግስት(መከላከያ ሰራዊት) የበላይነቱን እየወሰደ መሆኑን ለቢቢሲ ዜና አማርኛ እንደገለጹ ይናገራል።
ነገር ግን በቢቢሲ ዜና የአማርኛው ድረ-ገጽ ላይ እንዲህ ያለ ጽሁፍ አለመኖሩን ሀቅቼክ ማረጋገጥ
“ፋኖ” የሚለው ስያሜ “የነጻነት ታጋይ” የሚለውን ትርጓሜ የሚገልጽ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት የአማራን ህዝብ እንወክላለን ብለው የሚንቀሳቀሱ ታጣቂ ሃይሎች ይጠቀሙበታል።
ሀቅቼክ የቢቢሲ አማርኛ ባለፉት 3ወራት የሰራቸውን ዘገባዎች ላይ ማጣራት ያደረገ ሲሆን ቢቢሲ አማርኛ ከፋኖ አስረስ ማረ ጋር የተደረገን ውይይት የሚያሳይ የዜና ዘገባ አላገኘም። እንዲሁም በፌስቡክ የተሰራጨው ልጥፍ ላይ ቢቢሲ ዘግቦበታል የተባለበትን ቀን አላስቀመጠም።
በተጨማሪም ሀቅቼክ በኦንላይን የምርመራ ቴክኒኮች በጥልቀት ሲመረመር ፣ የተያያዘው ምስል የተቀናበረ ስለመሆኑ ፍንጭ አግኝቷል።
ሀቅቼክ በማህበራዊ ሚድያ ላይ ስለተሰራጨው ልጥፍ ሀቅቼክ የቢቢሲ አማርኛ BBC News Amharic አርታኢ የሆኑትን አቶ አሻግሬ ሀይሉን አነጋግሯል። እሳቸውም ቢቢሲ አማርኛው ይህን ዘገባ እንዳልሰራው እና መረጃውም የሀሰት ፈጠራ መሆኑን አሳውቀውናል።
አያይዘውም አንባቢዊች ዜናዎችን በቢቢሲ ስም ሲሰራጩ መረጃው ትክክለኛ መሆኑን ለማወለማወቅ ወደ ይፋዊ የቢቢሲ አማርኛ ድረ-ገጽ (https://www.bbc.com/amharic) የሚወስድ አገናኝ(link) እንዲጠቀሙ መክረዋል።
ከላይ በተዘረዘሩት ምክንያቶች ሀቅቼክ ልጥፉን ሀሰት መሆኑን አረጋግጧል።
ሙሉውን ያንብቡ 👇🏽
https://bitl.to/3MTd
04/12/2024
በቅርቡ በDiversity Visa (ዲቪ) ላይ የሚጣሉ ገደቦችን በተመለከተ የተመራጩ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ንግግርን የሚያሳይ ቪዲዮ በቲክቶክ ላይ በመሰራጨት ላይ ይገኛል። ይህ ቪድዮ በቅርብ ከተካሄደው የ(ዲቪ) 2026 ፕሮግራም ጋር በማያያዝ የቀረበ ነው።
ነገር ግን ሀቅቼክ ይህን ቪዲዮ በፈረንጆቹ 2017 ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የዲቪ ፕሮግራምን ለማቋረጥ ያላቸውን ፍላጎት የገለፁበት ንግግር ሆኖ አግኝተነዋል።
https://bitl.to/3IFN
16/11/2024
በወታደራዊ ጥንካሬ ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ሁለተኛ እንደሆነች ተደርጎ የሚገለፀው መረጃ ሀሰት መሆኑን ሀቅቼክ አረጋግጧል።
ከሰሞኑ በፌስቡክ ላይ ብዙ እይታዎችን ማግኘት የቻለ እና በብዙዎች ዘንድ እየተጋራ የሚገኝ አንድ መረጃ በስፋት ሲዘዋወር ቆይቷል። ይህ በፌስቡክ ላይ በስፋት ሲጋራ የቆየው መረጃ በያዝነው የፈረንጆቹ 2024 የአፍሪካ ሀገራቶችን የወታደራዊ ጥንካሬን እና ደረጃን ያሳያል በማለት የተጋራ ነው።
በተለያዩ የፌስቡክ ገፆች እና አካውንቶች በህዳር 3 ቀን 2017 ዓ.ም የተጋራው ይህ መረጃ በወታደራዊ ጥንካሬ ኢትዮጵያ በደቡብ አፍሪካ ተቀድማ ፤ አልጄርያ ፤ ግብፅ እና ናይጄርያን አስከትላ ሁለተኛ ደረጃ መያዟን ይገልፃል።
ሙሉ ፅሁፉን ያንብቡ https://bityl.co/SmOH
15/10/2024
ከሰሞኑ በአንድ የx ወይም በቀድሞ ስሙ ትዊተር ላይ የተጋራ ፖስት በያዝነው ዓመት በፈረንጆቹ 2024 ግማሽ የሚሆነው የአፍሪካ የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) የሚመጣው ከአምስት ሀገሮች እንደሆነ ገልጿል። እነዚህም ሀገራቶች አልጄርያ ፤ ግብፅ ፤ ኢትዮጵያ ፤ ናይጄርያ እና ደቡብ አፍሪካ እንደሆኑ ያስቀምጣል።
ሀቅቼክ የተለያዩ መረጃ እና ምንጮችን አመሳክሮ ይህ መረጃ ትክክል እንደሆነ ማረጋገጥ ችሏል።
አምስቱ የአፍሪካ ሀገሮች ግማሽ ያህል የሚሆነውን የአፍሪካ የሀገር ውስጥ ምርት ይሸፍናሉ? - HaqCheck ከሰሞኑ በአንድ የx ወይም በቀድሞ ስሙ ትዊተር ላይ የተጋራ ፖስት በያዝነው ዓመት በፈረንጆቹ 2024 ግማሽ የሚሆነውን የአፍሪካ የሀገር ውስጥ ምርትን (GDP) የሚመጣው ከአምስት ሀገሮች እንደሆ.....
14/10/2024
A recent post on X claims that half of Africa’s GDP in 2024 comes from the collective GDP of only five countries: Algeria, Egypt, Ethiopia, Nigeria, and South Africa.
As HaqCheck investigates the stated claim it has been found True!
Do the five African countries constitute half of the African total GDP? - HaqCheck A recent post on X claims that half of Africa’s GDP in 2024 comes from the collective GDP of only five countries: Algeria, Egypt, Ethiopia, Nigeria, and South Africa. As HaqCheck investigates the stated claim it has been found True! Link A recent report from the International Monetary Fund (IMF) h...
Click here to claim your Sponsored Listing.
Contact the organization
Telephone
Website
Address
Jambo Office Apartment, 8th Floor Gabon Street, Kirkos Sub-City, Woreda 03 Addis Ababa
Addis Ababa