She is this
This page is created to motivate women.
#ዲቦራ
ሴትነት! ዳኝነት! መሪነት!
የሴቶች የዳኝነት እና የመሪነት ብቃት መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት አለው፡፡
#ዲቦራ የዲቦራ ዘንባባ ተብሎ በሚጠራው ዛፍ ስር ትቀመጥ ነበር! የእሥራኤል ልጆችም ወደ እርስዋ ለፍርድ ይመጡ ነበር!
በመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፈ መሳፍንት ምዕራፍ 4 እና 5 ላይ ይህ እውነታ ተቀምጧል!!!
ዲቦራ የዳኝነት እና የግልግል ዳኝነት የላቀ ብቃት ነበራት፤ የታመነች ባለሥልጣን ነበረች፤ አለመግባባቶችን በእርቅ መፍታት፤ ባሕላዊ ሕጎችን በጥልቀት መረዳት፤ አድልዎ የሌለበት ፍርድ መስጠት፤ ባሕላዊ ሕጎችን በጥልቀት መረዳት ትችላለች፤ ችሎትዋ ሰዎች መፍትሔ ፍለጋ የሚመጡበት፤ የእሷን ጥበብ በፈቃደኝነት የሚሹበት የግልግል ዳኝነት ስፍራ ነበረ፣ ይህም በሕዝብ ዘንድ ታላቅ አመኔታን እንድታገኝ አድርጓታል።
በታላቅ መሪ የሚመራውን የታጠቀ እና የተፈራ የከነዓናውያንን ጦር ለመጋፈጥ ጊዜው በደረሰ ጊዜ፣ ዲቦራ እንደ የበላይ የጦር ዕቅድ አውጪ ሆና አገልግላለች። የክዋኔ ዕቅድዋን የጦር አዛዡን አስጠርታ ሰጥታለች፤ የጦርነት ቦታና ውጤት በትክክል ተንብያለች፤ የጦር አዛዡ ባርቅ አንቺ ከእኔ ጋር ካልሄድሽ አልሄድም ባላት ጊዜ ያለምንም ማንገራገር ተስማምታ ተነስታ ሄዳለች፡፡ እውነትን የመለየት፣ የጊዜ አጠባበቅንና የሞራል ግልጽነትን የመረዳት ችሎታ ነበራት፤ የመሪነት ብቃትዋ በአካላዊ ማስገደድ ላይ የተመሠረተ ሳይሆን በሞራል ልዕልናዋ እና በንግግር ብቃትዋ ላይ የተመሰረተ ነበር፡፡
ድል ከተቀዳጀች በኋላም የዲቦራ መዝሙር የሚባለውን “መጽሐፈ መሳፍንት ምዕራፍ 5” በመባል የሚታወቀውን የድል አድራጊነት ታላቅ ግጥም በጋራ ደርሳለች፤ ዘምራለችም በመዝሙርዋም ታሪክን ጠብቃ አቆይታለች፡፡
#እትመትአሰፋ
የቅጣት ገደብ ከፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የቅጣት አወሳሰን መመሪያ አንጻር ሲታይ፡-
የወንጀል ቅጣት እና አፈጻጸማቸውን በሚመለከት በኢ.ፌ.ዴ.ሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 87 ላይ የተቀመጠው መርህ በሕጉ የተመለከቱት ቅጣቶች እና የጥንቃቄ እርምጃዎች ሕጉ ሊደርስበት የሚችለውን ዓላማ ለማረጋገጥ በሚቻልበት ሁኔታ በሕጉ መሠረት መፈጸም አለባቸው፡፡ ቅጣቶቹ እና የጥንቃቄ እርምጃዎቹ ምን ጊዜም ሰብአዊ ክብርን በሚጠብቅ መንገድ መፈጸም ይኖርባቸዋል በማለት ይደነግጋል፡፡ የዚሁ ሕግ አንቀጽ 88(2) ቅጣቱ ሊወሰን የሚገባው የወንጀል አድራጊውን ግላዊ የአደገኝነት መጠን፤ ያለፈ የሕይወት ታሪኩን፤ ወንጀል ለማድረግ ያነሳሱትን ምክንያቶች እና የአሳቡን ዓላማ፤ የግል ኑሮውን ሁኔታ፤ የትምህርት ደረጃ እንዲሁም የወንጀሉን ከባድነት እና የአፈጻጸሙን ሁኔታዎች በማመዛዘን ነው በማለት ይደነግጋል፡፡ በንዑስ ቁጥር (4) ላይ ደግሞ የቅጣት አወሳሰንን ትክክለኛነት እና አንድ ወጥነት ለማረጋገጥ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የቅጣት አወሳሰን መምሪያ ሊያወጣ ይችላል በሚል ተመልክቷል፡፡
የወንጀል ሕጉ ዓላማ ወንጀል እንዳይፈጸም ማድረግ ሲሆን ይህንንም የሚያደርገው ስለወንጀሎች እና ስለቅጣታቸው በቅድሚያ ማስጠንቀቂያ በመስጠት፤ ማስጠንቀቂያነቱ በቂ ባልሆነ ጊዜ ደግሞ ወንጀል ፈጻሚዎች ተቀጥተው ሌላ ወንጀል ከመፈጸም እንዲቆጠቡ እና ለሌሎች ማስተማሪያ እንዲሆኑ ወይም እንዲታረሙ ማድረግ ነው፡፡
ወንጀል ፈጻሚዎች ሆነ ብለው ወንጀል ለመፈጸም በማሰብ ወይም በቸልተኝነት ከቀላል እስከ ከባድ ቅጣት የሚያስከትሉ ወንጀሎችን ይፈጽማሉ፡፡ ዳኞች ወንጀል ፈጻሚዎች ለፈጸሙት ጥፋት የወንጀል ሕጉን ዓላማ እና ግብ በሚያሳካ ሁኔታ ሚዛኑን ጠብቀው ቅጣት መጣል ይጠበቅባቸዋል፡፡ ይህን የሚያደርጉትም በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 88(2) ላይ በተቀመጠው ሁኔታ እንደ ሰው ሚዛን በመመዘን ነው? ወይስ ቅጣትን ለመገደብ የሚያስችሉ የቁጥር ስሌቶችን በማስላት?
ቅጣት ሲገደብ የፍርዱ ውሳኔ በወንጀለኞች መዝገብ ላይ ተመዝግቦ ከሌላው ውጤት ጋር ነዋሪ የሚሆን በመሆኑ ቅጣትን መገደብ በወንጀለኛው ላይ ቅጣት እንዳይፈጸም የማድረግ ውጤት ብቻ ያለው ሳይሆን ወንጀለኛው ዳግም ጥፋት ከመፈጸም እንዲታቀብ የማድረግ ውጤት ያለው በመሆኑ ቅጣትን መገደብ የወንጀል ሕጉ ዓላማ እና ግብ ከሚሳካባቸው መንገዶች አንዱ ነው፡፡
ቅጣት ሊገደብ የሚችለውም ጥፋተኛ የተባለን ሰው ለጥፋቱ መነሻ የሆኑትን ምክንያቶችን በጠቅላላው በመመልከት በጥፋተኛው ላይ የተወሰነውን ቅጣት ለጊዜው በገደብ እንዲታገድ በማድረግ የወንጀለኛውን ጠባይ ለማረምና ለማሻሻል እንዲሁም ወደ መደበኛ ማህበራዊ ኑሮው ለመመለስ ጠቃሚ መሆኑ በታመነ ጊዜ ስለመሆኑ የቅጣት ገደብን አስመልክቶ ከተደነገጉት የወንጀል ሕጉ ድንጋጌዎች መገንዘብ ይቻላል፡፡
ፍ/ቤቶች ቅጣትን ለመገደብ የሚያስችሉ የተለያዩ ሁኔታዎች ከግምት ውስጥ ማስባት እንዳለባቸው፤ እነዚህም ሁኔታዎች ወንጀለኛው ቀድሞ ያልተቀጣ ሆኖ ጠባዩም አደገኛነት እንደሌለው የሚታመንበት እንደሆነ፤ጥፋቱ በመቀጮ፤ በግዴታ ስራ ወይም ከሶስት አመት የማይበልጥ ቀላል እስራት የሚያስቀጣ እንደሆነ ፍርድ ቤቱ ጥፋተኝነቱን ካረጋገጠ በኋላ ለወደፊት ጠባዩን ለማረም እንደሚችል እምነት ሊጣልበት የሚችል መሆኑና በዚህ ውሳኔ ብቻ እስከ መጨረሻው ሊሻሻል የሚችል መሆኑን ሊያምንበት ይገባል፤ እንዲሁም ጥፋተኛው አስቀድሞ የተፈረደበት ቢሆንም ባይሆንም የተፈረደበትን ቅጣት ከመፈፀሙ በፊት ለተወሰነ ጊዜ ቅጣቱ ታግዶለት አመሉ ቢፈተን ሁለተኛ ጥፋት ከማድረግም የሚታገድ መሆኑና ስለጠባዩም መሻሻል አንድ ፅኑ ማስጠንቀቂያ ብቻ የሚበቃ መሆኑ ፍርድ ቤቱ ያመነበት እንደሆነ ቅጣቱ ከአፈፃፀም ታግዶ እንዲቆይ ሊያዝ የሚችል ስለመሆኑ ከወንጀል ሕግ አንቀጽ 192 እና ተከታይ ድንጋጌዎች ያስገነዝባሉ፡፡
ጥፋተኛው ከዚህ በፊት የጽኑ እሥራት ቅጣት ወይም ከሦስት ዓመት የሚበልጥ ቀላል እሥራት ቅጣት ተፈርዶበት እንደሆነ እና እንደገናም በተከሰሰበት ወንጀል ከእነዚህ ቅጣቶች አንዱ የሚወሰንበት እንደሆነ ወይም ጥፋተኛው ከዚህ ቀደም ያልተቀጣ ሆኖ በተከሰሰበት ወንጀል ከአምስት አመት የበለጠ የጽኑ እሥራት ቅጣት የሚፈረድበት እንደሆነ በጥፋተኛው ላይ የተወሰነው ቅጣት እንዳይገደብ የሚያደርጉ ሁኔታዎች መሆናቸውን በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 194 ድንጋጌ ላይ በዝርዝር ተመልክቷል፡፡
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 88(4) በተሰጠው ስልጣን መሠረት የቅጣት አወሳሰን ትክክለኛነት እና ወጥነትን ለማረጋገጥ የቅጣት አወሳሰን መመሪያ 1 እና 2 አውጥቶ ተግባራዊ ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ አሁን ደግሞ የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 3/2017 ወጥቶ በስራ ላይ ውሏል፡፡
አዲሱ የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ከያዛቸው አዲስ ሐሳቦች ውስጥ በአባሪ ሶስት ላይ የተቀመጠው የእስራት ቅጣትን በገደብ የማቆየት ውሳኔ አሰጣጥ ሰንጠረዥ ነው፡፡ ይህ ሰንጠረዥ ቅጣት ለመገደብ ታሳቢ የሚሆነውን ምክንያት፤ ለምክንያቱ የሚያዘውን ነጥብ እና ጥፋተኛ የተባለው ሰው ያገኘው ነጥብ የሚሞላበትን ሰንጠረዥ የያዘ ነው፡፡ ሰንጠረዡ እንደሚያመለክተው ለእያንዳንዱ የቅጣት መገደቢያ ምክንያት ዳኞች ከ - እስከ በማለት ፍቅድ ስልጣን አስቀምጦ የሚሰጡትን መነሻ እና መድረሻ ነጥብ አስቀምጧል፡፡ በዚሁ አግባብ ተሰልቶ ጥፋተኛ የተባለው ሰው የሚያገኘው ነጥብ ከመቶ እንደሚሰላ ያሳያል፡፡ በዚህ ስሌት መሰረት የሚመጣው ነጥብ ቅጣቱን ለመገደብ ጥቅም ላይ የሚውል መሆኑን መመሪያው ያሳያል፡፡
የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ባወጣው የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 3/2017 በአባሪ ሶስት ላይ ያስቀመጠው የእስራት ቅጣትን በገደብ የማቆየት ውሳኔ አሰጣጥ ሰንጠረዥ ዳኞች ወንጀል ፈጻሚዎች ለፈጸሙት ጥፋት የወንጀል ሕጉን ዓላማ እና ግብ በሚያሳካ ሁኔታ በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 88(2) ላይ በተቀመጠው ሁኔታ እንደ ሰው ሚዛናቸውን ሳይስቱ መዝነው የቅጣት ገደብን ለፍቀድ ወይም ለመንፈግ የሚያስችል ነው ? ወይስ ቅጣትን ለመገደብ የሚያስችሉ የቁጥር ስሌቶችን በማስላት ብቻ ውሳኔ እንዲወስኑ የሚያስገድድ ? የሚለው ትኩረት የሚያሻው ጉዳይ ነው፡፡
#እትመትአሰፋ
ሊታረም የሚገባው አሰራር፡-
በዚህ ወር ውስጥ በአንድ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የቤተሰብ ችሎት ተገኝቼ ነበር፡፡ እኔ ከያዝኩት ጉዳይ በፊት ሌሎች ባለጉዳዮችን እየጠሩ ያስተናግዳሉ፡፡ በመቀጠልም አንድ መዝገብ ተጠራ፡፡ መዝገቡ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 241 መሠረት ተከራካሪ ወገኖችን ለመመርመር የተያዘ ቀጠሮ ነው፡፡ ምርመራው ቀጠለ፡፡ የባል ወገን ጠበቃ ፍቺው የቀረበው ሚስት ከሌላ ሰው ጋር ግንኙነት ስለጀመረች ነው አሉ፡፡ ዳኛው ጥያቄ ማቅረባቸውን ቀጠሉ “ከሌላ ሰው ጋር ግንኙነት አለሽ? መማገጥ አለ? ብለው ጠየቁ” ይህ ሁሉ የሚሆነው በግልጽ ችሎት ብዙ የችሎት ታዳሚ ባለበት ነው፡፡ ሊታረም የሚገባው አሰራር እንግዲህ እዚህ ላይ ነው፡፡
በኢ.ፌ.ድ.ሪ ሕገመንግስት አንቀጽ 20(1) ድንጋጌ ላይ ዜጎች አጭር በሆነ ተገቢ ጊዜ ውስጥ ለሕዝብ ግልጽ በሆነ ችሎት የመሰማት መብት እንዳላቸው፤ ሆኖም የተከራካሪ ወገኖችን የሕዝብን ሞራል ሁኔታ እና የሐገሪቱን ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል ክርክሩ በዝግ ችሎት ሊሰማ ይችላል በሚል ተደንግጓል፡፡ ቤተሰብ የሕብረተሰብ መሠረት ነው፡፡ ሁሉም ለፍቺ የቀረቡ ጉዳዮ የፍቺ ውሳኔ ይሰጥባቸዋል ማለት አይደለም፡፡ ለፍቺ የቀረቡት ባለጉዳዮች ሊስማሙ ይችላሉ ሊፋቱም ይችላሉ፡፡ በሒደቱ ግን ሚስጥራቸው ሊጠበቅ ይገባል፡፡ ቤተሰብ የሕብረተሰብ መሠረት ስለሆነ የቤተሰቡን፤ በዚህ ቤተሰብ ውስጥ የተወለዱ ሕጻናትንም ጥቅም እና ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል እንደዚህ ዓይነት ጉዳዮች ዳኞች በዝግ ችሎት ቢያስተናግዱ ተመራጭ ነው፡፡
እትመት አሰፋ
Alimony (ከፍቺ በኃላ ለሚስት ወይም ለባል የሚከፈል ቀለብ)
የፍትሐ ብሔር ሥነ ሥርዓት ሕጋችን Alimony (ከፍቺ በኃላ ለሚስት ወይም ለባል የሚከፈል ቀለብ) እውቅና ይሰጣል ??? ድንጋጌው ባል ወይም ሚስት ከፍቺ በኃላ አንዳቸው ለሌላቸው ቀለብ የመክፈል ግዴታ ሊኖርባቸው እንደሚችል አመላካች ቀዳሚ ሕግ? ወይስ በመደበኛው ሕግ ለዜጎች ያልተጠበቀን መብት የሚፈቅድ የሥነ ሥርዓት ሕግ?
ከፍቺ በኋላ ለሚስት ወይም ለባል የሚከፈል ቀለብ ከፍቺ በኋላ አንደኛው ወገን ለሌላኛው ወገን የገንዘብ ድጋፍ እንዲያደርግ የሚጣልበት ሕጋዊ ግዴታ ነው። ጋብቻ በተጋቢዎች መካከል ከሚያስከትላቸው ውጤቶች ውስጥ አንዱ ኢኮኖሚያዊ አጋርነት ነው፤ ይህ አጋርነት ሲፈርስ የፍቺው ቀውስ በአንደኛውን ወገን ላይ ምንም ጉዳት ሳያደርስ በሌላኛው ወገን ላይ ግን ከፍተኛ የኢኮኖሚ ቀውስ የሚፈጥርበት አጋጣሚ አለ፡፡
የ Alimony (ከፍቺ በኃላ ለሚስት ወይም ለባል የሚከፈል ቀለብ) ዋነኛ ዓላማዎች ምንም ገቢ የሌለው ወይም በጣም አነስተኛ ገቢ ያለው የትዳር አጋር፤ ባልና ሚስቱ በትዳር ውስጥ በነበሩ ጊዜ ሌላኛው ወገን የተሻለ የትምሕርት እና የሥራ እድሎችን እንዲያገኝ እና በተሻለ ደረጃ ላይ እንዲደርስ ሲያደርግ የነበረው ወገን ከፍቺ በኋላ ወዲያውኑ ለችግር እንዳይጋለጥ ማድረግ፤ በፍቺው ምክንያት ለበለጠ የኢኮኖሚ ችግር የሚጋለጠው የትዳር አጋር ራሱን እንዲችል ማድረግ ነው፡፡
ተጋቢዎች በትዳር ውስጥ እያሉ አንዳቸው ለሌላቸው ከፍተኛ የጊዜ፤ የጉልበት እና የገንዘብ መስዋዕትነትን በመክፈል ሌላኛው ተጋቢ ትልቅ ደረጃ ላይ እንዲደርስ የሚያደርጉበት እና ዋጋ የሚከፍሉበት ጊዜ አለ፡፡ ይህን በማድረግ ሒደትም ራሳቸውን የሚገነቡበት የሚማሩበት የሚሰሩበት እና የተለያዩ ዕድሎችን የሚጠቀሙበትን አጋጣሚዎች ሁሉ ሳይጠቀሙባቸው ይቀራሉ፡፡ ይህ መስዋእትነት አብሮነትን በማሰብ የሚከፈል መስዋእትነት ነው፡፡ ታዲያ ትዳር በድንገት በፈረሰ ጊዜ ይህን መስዋእትነት ሲከፈል የነበረው የትዳር አጋር ከፍተኛ ችግር ውስጥ ይገባል፡፡
Alimony (ከፍቺ በኃላ ለሚስት ወይም ለባል የሚከፈል ቀለብ) ይህን ክፍተት ለመሙላት በሌላኛው ወገን ላይ የተቀመጠ የሕግ ግዴታ ነው፡፡
የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 404 ስለማይከበሩ እና በፍርድ አፈጻጸም ምክንያት ስለማይወሰዱ ሀብቶች በዝርዝር ያመለክታል፡፡ ድንጋጌው በንዑስ ቁጥር ፊደል (ሠ) ላይ ለጡረታው የሚከፈለው ገንዘብ እና ባል ሚስቱን ከፈታ በኋላ ለወር ቀለብዋ የሚከፍላት ገንዘብ የማይከበር እና በፍርድ አፈጻጸም ምክንያትም ከማይወሰዱ ሀብቶች ውስጥ አንዱ እንደሆነ ያመለክታል፡፡ በእንግሊዘኛው የሥነ ሥርዓት ሕጉ ላይ፡-
and Alimonies. በሚል ተቀምጧል፡፡
በፌዴራል የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 213/1992 ባልና ሚስት ከተፋቱ በኋላ አንዳቸው ለሌላቸው ቀለብ ለመክፈል የሚገደደቡበት ሁኔታ እንዳለ የሚያመለክት ድንጋጌ የለም፡፡ Alimony (ከፍቺ በኃላ ለሚስት ወይም ለባል የሚከፈል ቀለብ) በሕጋችን እንዲፈቀድ ብዙ ጥናቶች ተደርገዋል፡፡ አሁንም እየተደረጉ ነው፡፡
በ 1958 ዓ.ም ከ ዛሬ 60 ዓመት በፊት የወጣው የፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ሕጋችን ግን ባል ሚስቱን ከፈታ በኋላ ለወር ቀለብዋ የሚከፍላት ገንዘብ /Alimony/ የማይከበር እና በፍርድ አፈጻጸም ምክንያትም ከማይወሰዱ ሀብቶች ውስጥ አንዱ እንደሆነ ያመለክታል፡፡
እትመት አሰፋ
15/05/2026
በፊቴ ገበታን አዘጋጀልኝ!
ራሴንም በዘይት ቀባው!!!
How much is Your worth Mama?
The last person to sleep
The first to wake up
at count less nights!
Be confident
And let them miss You!
19/04/2026
Women should know their place... is wherever they want it to be!
19/03/2024
The ironies of Ethiopia in whole African game
1, 2 , 3
15/03/2024
"LENEGEWA"
Womens Rehablitation and Skill Development Centre ETHIOPIA
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Addis Ababa