Addis Truth

Addis Truth

Share

Addis Truth is a reliable and independent news channel dedicated to delivering accurate, timely, and fact-based reporting from Ethiopia and around the world.

17/04/2026

ኢትዮጵያውያን ከገቢያቸው 58.5 በመቶውን ለምግብ ፍጆታ ያውላሉ‼️

የዓለም ባንክ ይፋ ባደረገው አዲስ አህጉራዊ ሪፖርት፤ በኢትዮጵያ ያለውን የኑሮ ውድነት ጫና የሚያሳይ አሳሳቢ አኃዝ ይፋ አድርጓል።

ሪፖርቱ እንደሚጠቁመው፣ ኢትዮጵያውያን ከአጠቃላይ ወጪያቸው ውስጥ ከ58.5 በመቶ በላይ የሚሆነውን ለምግብ ፍጆታ ብቻ ለማዋል ተገደዋል።

የዋጋ ንረቱ የከተማ ነዋሪዎችን ብቻ ሳይሆን፣ በገጠር የሚገኙ ዜጎችንም በከፍተኛ ሁኔታ እየፈተነ ይገኛል።

የሸቀጦች ዋጋ መጨመር በገጠር ያለውን የኑሮ ሚዛን እያናጋው መሆኑ ተመልክቷል።

በመካከለኛው ምስራቅ እየተባባሰ የመጣው ቀውስ የነዳጅ ዋጋን በመጨመር፣ በሀገር ውስጥ ያለውን የትራንስፖርትና የምርት ዋጋ ይበልጥ ሊያናረው እንደሚችል ባንኩ አስጠንቅቋል።

ይህ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ከምግብ ዋስትና ጋር ተዳምሮ የዜጎችን የመግዛት አቅም ይበልጥ ሊያዳክም እንደሚችል ተጠቁሟል።


Addis Truth

17/04/2026

#በሊባኖስ እና #በእስራኤል መካከል ለ10 ቀናት የሚቆይ የተኩስ አቁም ስምምነት ከሐሙስ ምሽት ጀምሮ ተግባራዊ መሆኑን ፕሬዝዳንት ትራምፕ አስታወቁ

አዲስ አበባ — የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሊባኖስ እና በእስራኤል መካከል ለ10 ቀናት የሚቆይ የተኩስ አቁም ስምምነት ትላንት ሚያዝያ 08 ቀን 2018 ዓ.ም. ከምሽቱ 11:00 (በግሪንዊች መቁጠሪያ 21:00 GMT) ጀምሮ ተግባራዊ መሆኑን አስታወቁ።

ፕሬዝዳንቱ ይህንን ያስታወቁት ከሊባኖሱ ፕሬዝዳንት ጆሴፍ አውን እና ከእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጋር ውይይት ካደረጉ በኋላ መሆኑ ተገልጿል።

እስራኤል በሊባኖስ ለተከታታይ ሳምንታት ባካሄደችው አስከፊ ወታደራዊ ጥቃቶች ሳቢያ የሟቾች ቁጥር 2,196 መድረሱን እና 7,185 ሰዎች መቁሰላቸውን የሊባኖስ ብሔራዊ የዜና ወኪል ዘግቧል፤ ይህም የተኩስ አቁም ስምምነቱ ከመጀመሩ በፊት የደረሰውን ሰብዓዊ ቀውስ መጠን ያሳያል።


Addis Truth

16/04/2026

ዩኒቨርሲቲዎች ከ30 ዓመት በኋላ ይጠፋሉ - ጠ/ሚ አቢይ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ከሰሞኑ በሁለት ተከታታይ ክፍል በሰጧቸው ቃለ ምልልሶች አነጋጋሪ፣ አወዛጋቢ እና አስደንጋጭ አስተያየቶችን ሰንዝረዋል፡፡

ጠቅላዩ ትምህርትን እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮችን በተመለከተ የሰጧቸው አስተያየቶች ልብ ሊባሉ የሚገባቸው ናቸው፡፡

በተለይም ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ዩኒቨርሲቲዎች ይጠፋሉ ማለታቸው መነጋገሪያ ሆኗል፡፡

‹‹ዩኒቨርሲቲ ምንም ጥርጥር የለውም የዛሬ 30 እና 40 ዓመት ሟቾች ናቸው፤ የ30 እና 40 ዓመት ዩኒቨርስቲ የሚሰለፍ ሰው አይገኝም፤ ዩኒቨርሲቲ 4 እና 5 ዓመት የምትማረውን ትምህርት በ6 ወር በ3 ወር ከቤት መማር ትችላለህ፤ ምንም ጥርጥር የለውም፤ ትሬንዱ ነው እሱን የሚያሳየው። ያም ሆኖ ውስን በጣም ከፍተኛ ጥራት ያላቸው ዩኒቨርስቲዎች ያስፈልጋሉ›› በማለት ሀሰባቸውን አብራርተዋል፡፡

ቀጥለውም፣ ‹‹አሁን ዩኒቨርሲቲዎች ላይ ምርመራ ቢደረግ 1 ሺህ፣ 2 ሺህ ተማሪ መቀበል የሚችል ባዶ ኮንዶሚኒየም ይገኛል። ደሞ የተሰራበት ርካሽ ስለሆነ አይቀጥልም ፈራሽ ነው። እራሱ ዩኒቨርስቲ የእሳቤ ችግር አለበት›› ብለዋል፡፡

‹‹ዩኒቨርስቲ የገነባነው በቂ መዋለህጻናት ያለበት ሀገር ሆኖ ቢሆን ኖሮ ችግር አልነበረውም። በመንግስት የተገነባ 10 መዋለህጻናት አልነበረም ኢትዮጵያ ውስጥ። አንደኛው ዩኒቨርሲቲ ቢተው ኖሮ በኢትዮጵያ ደረጃ ከበቂ በላይ መዋለህጻናት መገንባት ይቻላል ምክንያቱም ቢሊዮኖች ነው የሚወጣባቸው ዩኒቨርሲቲዎች። እኛ ባለፉት 6-7 ዓመታት ከ34 ሺህ በላይ ገንበተናል። ለምን ዋናው ትምህርት የሚያስፈልገው Early Childhood Education ስለሆነ።


Addis Truth

16/04/2026

የነዳጅ አቅርቦት‼️
ባለፉት ጥቂት ቀናት በጅቡቲ ወደብ ተከስቶ የነበረው የቴክኒክ እና የሎጅስቲክስ መስተጓጎል በመፈታቱ፣ በርካታ የነዳጅ ጫኝ ቦቴዎች ወደ ሀገር ውስጥ መግባት መጀመራቸውን የደረሰን መረጃ ያመላክታል።
ይህንንም ተከትሎ በአሁኑ ሰዓት በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የሚገኙ ዴፖዎች ነዳጅ በማራገፍ ላይ የሚገኙ ሲሆን፣ ፈጣን የሆነ የስርጭት ስራ እየተከናወነ ይገኛል።

በአዋሽ፣ ሱሉልታ፣ አቃቂ፣ ኮምቦልቻ፣ ሻሸመኔ፣ ባህር ዳር እና ጎንደር የሚገኙ ዋና ዋና ዴፖዎች ከፍተኛ መጠን ያለው ነዳጅ ደርሷቸዋል።

መንግስት በዓለም አቀፍ ደረጃ (በተለይም በሆርሙዝ ወሽመጥ አካባቢ) በተከሰተው ቀውስ ምክንያት አጋጥሞ የነበረውን አቅርቦት ለማካካስ ተጨማሪ ግዢዎችን በመፈጸም እና ስርጭቱን በማፋጠን ላይ ይገኛል።

የነዳጅ ቦቴዎች ማደያዎች ላይ ደርሰው ማራገፍ በመጀመራቸው፣ በተለይም በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች የታየው ረጅም የሰልፍ ተርታ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደሚቀንስ ይጠበቃል።

ስርጭቱ ፍትሃዊ እንዲሆንና ህገ-ወጥ የነዳጅ ግብይትን ለመከላከል ጥብቅ የክትትል ስራ እየተሰራ መሆኑን የሚመለከታቸው አካላት ገልጸዋል።

ይህ እርምጃ በሀገሪቱ የትራንስፖርት እና የንግድ እንቅስቃሴ ላይ ተፈጥሮ የነበረውን ጫና በማቃለል ረገድ ትልቅ እፎይታ እንደሚሰጥ ይታመናል። ኢትዮጵያ በዋናነት ነዳጅ የምትገዛው ከኩዮት የነበረ ቢሆንም የሆርሙዝ ሰርጥ በመዘጋቱ ከህንድ እና ከሌሎች ሀገራት የተገዛ ነዳጅ በሶስት መርከቦች ተጭኖ በቅርቡ ጅቡቲ መግባቱን መዘገባችን ይታወሳል።


Addis Truth

15/04/2026

ኒዮርክ ታይምስ 'ትራምፕ ከኢራን ጋር እያደረጉት ያለው ጦርነት' 'አሜሪካን በአራት መንገድ እያዳከመ መሆኑን ዘግቧል።

👉ኢራን በአለም አቀፍ የነዳጅ ገበያ ላይ ያላትን ተጽእኖ እያስፋፋ መሆኑን፣

👉ውድ የተባሉ የአሜሪካ የጦር መሳሪያዎች ክምችት መሟጠጡ፣

👉ከአጋሮች ጋር ያለው ግንኙነት መሻከር፣
👉የአሜሪካ የሞራል ልዕልና መሸርሸር ናቸው" ብሏል።


Addis Truth

Photos from Addis Truth's post 15/04/2026

ኢራን በጦርነቱ ለደረሰባት ውድመት 270 ቢሊዮን ዶላር ካሳ ጠየቀች።

ኢራን በዩናይትድ ስቴትስ እና በእስራኤል ጥቃቶች ለደረሰባት ውድመት ካሳ እንዲከፈላት የጠየቀች ሲሆን፤ ሀገሪቱ አሁንም አቋሟን ሳታለሰልስ ቀጥላለች።

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢራን ልዩ መልዕክተኛ አሚር ሰዒድ ኢራቫኒ፥ ግዛታቸውን በኢራን ላይ ጥቃት ለመሰንዘር እንዲውል ፈቅደዋል ሲሉ የከሰሷቸው አምስት የቀጣናው ሀገራት ካሳ መክፈል አለባቸው ብለዋል።

በተጨማሪም ኢራን በሆርሙዝ ወሽመጥ ፕሮቶኮሏ መሠረት በወሽመጡ በሚያልፉ መርከቦች ላይ ቀረጥ በመጣል የደረሰባትን ጉዳት ለማካካስ ማሰቧን ገልጻለች።

የኢራን መንግሥት ቃል አቀባይ ፋጢሜህ ሞሃጄራኒ ለሩሲያው አርአይኤ ኖቮስቲ እንደገለጹት፥ ኢራን በጦርነቱ ምክንት በግምት የ270 ቢሊዮን ዶላር ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ያልሆነ ጉዳት ደርሶባታል።

ጉዳቱ ከደረሰባቸው መካከል መሠረተ ልማቶች፣ የትራንስፖርት አገልግሎት መስጫዎች እና ማህበራዊ ተቋማት ተጠቃሽ ናቸው።

‹‹አሜሪካ እና እስራኤል ወይ የኢራንን መብት የሆርሙዝ ስርጥ ቁጥጥርን ጨምሮ እውቅና መስጠት አለባቸው፥ ካልሆነ ግን ወደ ጦርነት እንመለሳለን" ሲሉም አስጠንቅቀዋል።


Addis Truth

15/04/2026

ሆርሙዝ ተከፈተ❓‼️
የሆርሙዝን ሰርጥ ሙሉ በሙሉ በመክፈታችን ቻይና በጣም ደስተኛ ሆናለች ሲሉ ትራምፕ ተናገሩ።

👉ቻይና 90% ነዳጅ እየገዛች ያለችው ከኢራን ነው።
ሆርሙዝ በቻይና ብቻ ሳይሆን ለአለም ክፍት ነው፣ይህ ሁኔታ ዳግመኛ አይከሰትም ብለዋል። ቻይናም ወደ ኢራን የጦር መሳሪያ ላለመላክ ተስማምታለች ብለዋል። የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ኢዚያ ስደርስ ወፍራም እቅፍ ያደርጉልኛል ብለዋል። በብልሃት አብረን ጥሩ ስራ እየሰራን ነው ብለዋል።

በተያያዘ ዜና ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 20 የንግድ መርከቦች በሆርሙዝ ማለፋቸውን የአሜሪካ ባልስጣናትን በምንጭነት ጠቅሶ ዎል ስትሪት ጆርናል ዘግቧል። ሆርሙዝ የተዘጋው ለኢራን መርከቦች ብቻ መሆኑን አሜሪካ አስታውቃለች።


Addis Truth

15/04/2026

👉በአሜሪካና ኢራን መካከል ድጋሜ ድርድር ሊካሄድ ነው

በአሜሪካና በኢራን መካከል የሚካሄደው ቀጣይ ዙር ድርድር ሐሙስ ዕለት በፓኪስታን ዋና ከተማ ኢስላማባድ እንደሚጀመር የአልጀዚራ ዘገባ ያመለክታል።

በፓኪስታን በኩል ያሉ ከፍተኛ ባለሥልጣናት በከፍተኛ ደረጃ” የሚካሄደው የአሜሪካና የኢራን ውይይት በጣም በቅርቡ እንደሚጀምር ማረጋገጣቸውን ዘገባው ጠቅሷል።

ይህ ድርድር ለበርካታ ዓመታት ሲንከባለሉ የቆዩትን በተለይም ከኢራን የኒውክሌር መርሐ ግብር ጋር የተያያዙ ውጥረቶችን ለመቀነስ የታለመ እንደሆነ ይታመናል። በአልጀዚራ የወጣው ዘገባ “ሰበር ዜና” በሚል የቀረበ ሲሆን፣ ድርድሩ ሊጀመር የሚችልበት ቀን ሐሙስ መሆኑን ጠቁሟል።

የፓኪስታን ባለሥልጣናትም በጣም በቅርቡ የሚለውን ቃል ተጠቅመው ድርድሩ ለመጀመር መቃረቡን አመልክተዋል። የሲኤንኤን ምንጭም “ጉዳዮች ወደዚያ አቅጣጫ ካመሩ” የሚለው አገላለጽ ድርድሩ የመካሄድ ዕድል እንዳለው ያሳያል።

ይህ ድርድር በሁለቱ አገራት መካከል ያሉትን ውጥረቶች ለመቀነስ እና ለቀጣናው ሰላምና መረጋጋት የበኩሉን አስተዋጽኦ ለማድረግ ያለመ እንደሆነ ተስፋ ይደረጋል። ድርድሩ በተሳካ ሁኔታ ከተጠናቀቀ፣ በበርካታ ዓመታት ሲንከባለሉ የቆዩትን በተለይም ከኢራን የኒውክሌር መርሐ ግብር ጋር የተያያዙ ውጥረቶችን ለመቀነስ ያስችላል ተብሎአል።


Addis Truth

15/04/2026

ይህ ቪዲዮ በሀገራችን በአምቦ የተከናወነ አሳዛኝ ድርጊት እንደሆነ እየተነገረ ነው። የሰው ልጅ በዚህ መልኩ መደብደቡ ቁጣን ቀስቅሷል። ድርጊቱ በአምቦ የተከናወነ እንደሆነ እየተገለጸ ይገኛል።

Addis Truth

15/04/2026

ጦርነት “ሊያበቃ ተቃርቧል”!

ትራምፕ የኢራን ጦርነት “ሊያበቃ ተቃርቧል” አሉ
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር የጀመሩት ጦርነት “ሊያበቃ ተቃርቧል” ሲሉ ለፎክስ ኒውስ ተናገሩ።

ትራምፕ ለፎክስ ኒውስ የሰጡት ቃለ ምልልስ የሚተላለፈው 7፡00 ላይ ቢሆንም በማስታወቂያው ላይ ግን ጦርነቱ “ሊያበቃ የተቃረበ ይመስለኛል” ሲሉ ተደምጠዋል።

ትራምፕ ይህንን ያሉት በቀጣዮቹ ሁለት ቀናት ከኢራን ጋር ኢዝላማባድ ተገናኝተው የተጀመረውን ውይይት እንደሚቀጥሉ ከተናገሩ በኋላ ነው።


Addis Truth

Category

Website

Address


Addis Ababa
0000