DemxComputer

DemxComputer

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from DemxComputer, Education, Addis Ababa.

Excel - መሰረታዊ ጽሑፍ ማስተካከያ መንገዶች | Basic Text Formatting in Excel - Part 5 (Zizu Demx) 14/02/2024

✅ Part 5 ✅

Excel - መሰረታዊ ጽሑፍ ማስተካከያ መንገዶች | Basic Text Formatting in Excel - Part 5 (Zizu Demx) Timestamps:00፡00 - Introduction to the video | በቪድዮው ስለተካተቱ ርዕሶች ገለጻ01፡05 - Intro | መግቢያ01፡15 - How do you solve a project problem? | ፕሮጀክቱን ለመስራት የምንከተለው ሒደ...

07/02/2024

Microsoft Excel for Beginner (ኤክሴል ለጀማሪዎች)

✅ ወርክቡክ (Workbook) ማዘጋጀት
---------------------------------
🔵 ኤክሴል ወርክቡክን እንደ አንድ መረጃ መያዣ ቋት ወይም እንደ መጽሃፍ ማየት እንችላለን፡፡ ይህ መጽሀፍ በውስጡ ብዙ ገጾች ይኖሩታል፡፡ ገጾቹን በወርክ ሽት ልንመስላቸው እንችላለን፡፡ እያንዳንዱ ወርክ ሽት የተለያየ መረጃን ይይዛል፡፡ ባጠቃላይ የወርክ ሽት ጥቅም በአንድ ቦታ ግን በተለያየ ገጽ የተለያየ መረጃ የምናስቀምጥበት ክፍል ነው፡፡ እነዚህን ሁሉ ገጾች (መረጃዎች) በአንድ ላይ እንደ መጸሀፍ የሚይዝልን ደግሞ ወርክቡክ እንለዋለን፡፡

🟤 ማይክሮሶፍት ኤክሴልን ለመጀመሪያ ግዜ ስንከፍት የተለያዩ እይታዎችን የያዘ አንድ መስኮት ይከፈትልናል። ሁልግዜም አዲስ የኤክሴል ወርክቡክ ለመክፈት Blank Workbook የሚለውን እንጫናለን። ለመጀመሪያ ግዜ በምንፈጥረው ወርክቡክ ውስጥ አንድ ወርክሽት ብቻ ይኖረናል። ይህም ማለት አንድ ገጽ ብቻ ያለው መጽሃፍ ይኖረናል እንደማለት ነው። አንድ ግዜ ወርክቡክ ከከፈትን በኋላ የፈለግነውን ያህል ወርክሽቶችን መጨመር እንችላለን።

✅ሴል (Cell)
========
ሴል ማለት በአንድ ወርክሽት ውስጥ የሚገኝ መረጃ የምናስቀምጥበት አራት መዓዘን ቦታ ነው፡፡ በውስጡም ጽሁፍ ቁጥር ወይም ፎርሙላ ሊቀመጥበት ይችላል፡፡ ይህ ቦታ በቁጥር (Number) እና በፊደል (Letter) ጥምረት የተገኘ ነው፡፡ ቁጥሩ ከተርታ (Row) የሚነሳ ሲሆን ፊደሉ ደግሞ ከቋሚ ረድፍ (Columns) ይነሳል፡፡ እነዚህ ሁለት መስመሮች ሲገናኙ አንድ ሴል ይፈጥራሉ፡፡

ለምሳሌ ፡- የመጀመሪያው ሴል ከላይ በ A ትክክል የተቀመጠ ሲሆን ከጎን ደግሞ በ 1 ትክክል ተቀምቷል፡፡ ስለዚህም ይህ ሴል ስሙ A1 ይሆናል፡፡ በተመሳሳይ በኤክሴል መጨረሻ ላይ የሚገኘው ሴል ስም XFD1048576 ይሆናል፡፡
✅ ወርክሽት (Worksheet)
===============
ኤክሴል ወርክሽት ማለት በአንድ ስፕሪድሽት ላይ የሚገኙ የብዙ አራት መአዘን ሴሎች ስብስብ ነው፡፡ ይህ ስብስብ በአግድም አምድ (Columns) እና በቋሚ ረድፍ (Row) ድርድር ውጤት ነው፡፡ በዚህ ድርድር ላይ 1,048,576 አምድ (Columns) እና 16,384 ረድፍ (Row) ይገኛል፡፡ በጠቅላለውም 17,179,869,184 ሴሎች በአንድ ገጽ ላይ ይገኛሉ፡፡ ስፕሪድ ሽት (ወርክሽት) ላይ የሚገኙ ረድፍ (Row) ከአንድ ጀምሮ ወደ ታች እስከ 1,048,576 የሚቆጥር ሲሆን አምድ (Columns) ደግሞ ከ A ጀምሮ ወደ ጎን እስከ XFD ይሄዳል፡፡
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
ሙሉ ትምህርቱን በሚከተሉት አማራጮች መከታተል እና ቤተሰብ መሆን ትችላላችሁ!

📌 Facebook = DemxComputer
📌 Instagram = Instagram.com/DemxComputer
📌 Tiktok = Tiktok.com/
📌 Telegram = t.me/DemxComputer
📌 Youtube = Youtube.com/

Most Important Excel Tips & Tricks | በእነዚህ እውቀቶች የኤክሴል መረጃችሁን ትቆጣጠራላችሁ - Part 4 (Zizu Demx) 07/02/2024

https://youtu.be/3riRLJovEAs

Most Important Excel Tips & Tricks | በእነዚህ እውቀቶች የኤክሴል መረጃችሁን ትቆጣጠራላችሁ - Part 4 (Zizu Demx) Timestamps:00:00 – Intro | መግቢያ01:03 - 3 Ways to Change the Column Width in Excel | የኮሎመንን ስፋት መቆጣጠሪያ 3 መንገዶች01:52 - How do I change multiple column widths a...

How to Enter Data Into Excel | ለመጀመሪያ ግዜ መረጃን ኤክሴል ላይ ማስገባት - Part 3 (Zizu Demx) 07/02/2024

https://youtu.be/plDmM9hzhpI

How to Enter Data Into Excel | ለመጀመሪያ ግዜ መረጃን ኤክሴል ላይ ማስገባት - Part 3 (Zizu Demx) Timestamps:00:00 – Intro | መግቢያ00:10 – Previous video preview | ከዚህ በፊት የነበረው ክፍል ዋና ዋና ሀሳቦች00:39 – How to Open an existing workbook? | የተሰራን ፕሮጀክት መክፈት00:53...

What is Workbook, worksheet and Cell in Excel | ኤክሴልን ከመክፈት መጀመር - Part 2 (Zizu Demx) 06/02/2024

https://youtu.be/cqh1_NWzLWE

What is Workbook, worksheet and Cell in Excel | ኤክሴልን ከመክፈት መጀመር - Part 2 (Zizu Demx) Timestamps:00:00 - Intro | መግቢያ00:10 - How to Get Microsoft Excel Software? | ኤክሴል ሶፍትዌርን የት ማግኘት እችላለሁ? 00:42 - Where can i find excel software shortcut ico...

6 Excel ከመማራችሁ በፊት ማወቅ ያለባችሁ | Introduction to the Course Ms Excel - Part 1 (Zizu Demx) 06/02/2024

https://youtu.be/E-YL7Oabt8E

6 Excel ከመማራችሁ በፊት ማወቅ ያለባችሁ | Introduction to the Course Ms Excel - Part 1 (Zizu Demx) :00:00 - ድሜክስ ኮምፒውተር መግቢያ00:11 - ቪዲዮውን ውስጥ የማገኛቸው ጠቃሚ ዕውቀቶች ምን ምን ናቸው?00:43 - ጥያቄ 1 - ትምህርቱን ለመማር ከኔ ምን ይጠበቃል?02:...

30/09/2023

Excel ከጀማሪ ወደ አስተማሪ በቅርብ ቀን . . .

Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address


Addis Ababa