ECLG Church
“We preach the Gospel to bring all nations to the living God.”
31/07/2026
የእውነተኛ መንፈሳዊ ሕይወት መገለጫዎች፤ (በትንቢተ ዮናስ መፅሐፍ)
በአገልጋይ ሙላቱ በፀጋው
ሁላችሁም ተጋብዛቹሃል።
27/07/2026
የፊሊሞና መጽሐፍ || ወንጌል ይለውጣል || በአገልጋይ አበበ ውብነህ || ኤፍታህ ቤተክርስቲያን || ትምህርት || ECLG Church || #2026 ኤፍታህ የሕያው እግዚአብሔር ቤተክርስቲያንአድራሻ፦ አዲስ አበባ ፤ ቦሌ አራብሳEPHPHATHA CHU...
አድራሻችን መስቀሉ ስር ነው
ኤፍታህ የሕያው እግዚአብሔር ቤተክርስቲያን
አድራሻ፦ አዲስ አበባ ፤ ቦሌ አራብሳ
EPHPHATHA CHURCH OF THE LIVING GOD
Addis Ababa, Ethiopia.
Phone Number:- ☎️ +251952013404
☎️ +251952014464
facebook.com/profile.php?id=100069328791382
T.me/ECLGChurch
#አምልኮ #ኤፍታህቤተክርስቲያን ። #ፕሮቴስታንት #መዝሙር #ኢየሱስ
#ፕሮቴስታንት #ፕሮቴስታንትመዝሙር #መዝሙር #ጴንጤ #ኢየሱስ #አምልኮ #መዝሙር #ፋሲካ
16/07/2026
⏳ ታገሡ! ⏳
"በለሱን የጠበቀ ፍሬዋን ይበላል፥ ጌታውንም የሚጠብቅ ይከብራል።" (ምሳሌ 27:18)
በሕይወታችን ውስጥ ከባድ ፈተናዎችና የመከራ ጊዜያት ሲመጡ ትዕግሥት ማጣት ቀላሉ መንገድ ሊመስል ይችላል። ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል የሚነግረን ሌላ ነው። ያዕቆብ በትዕግሥት የጸኑትን እንጂ የወደቁትን ብፁዓን እንደማንላቸው ይነግረናል።
📖 የጌታን መምጣት በትዕግሥት እንጠብቅ
"እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ጌታ እስኪመጣ ድረስ ታገሡ። ... እናንተ ደግሞ ታገሡ፥ ... ኢዮብ እንደ ታገሠ ሰምታችኋል፥ ጌታም እንደ ፈጸመለት አይታችኋል፤ ጌታ እጅግ የሚምር የሚራራም ነውና።" (ያዕቆብ 5:7-11)
ሐዋርያው ጳውሎስም በሮሜ 12:12 ላይ "በመከራ ታገሡ" ይለናል። የመከራ ጊዜ ከባድ እንደመሆኑ መጠን፥ መታገሥ የግድ ያስፈልገናል።
⚠️ ያለመታገሥ ዋጋ ያስከፍላል!
በትዕግሥት ማጣት ምክንያት ሕይወታቸው የተናወጠ ታላላቅ የእግዚአብሔር ሰዎችን ታሪክ እናስታውስ፡
ሙሴ፡ የጸሎት ሰው፣ ታላቅ ነብይ፣ እግዚአብሔርን ፊት ለፊት ያነጋገረ መሪ ነበር። ነገር ግን ትዕግሥት በማጣቱ ጽላቱን ሰበረ፤ በኋላም ዓለቱን ተናገር ሲባል በበትር በመምታቱ ምክንያት ወደ ምድሪቱ ሳይገባ ቀረ (ዘዳ 32:51-52)።
ሣራ፡ የእግዚአብሔርን ጊዜ በትዕግሥት መጠበቅ ስላቃታት አብርሃምን ወደ አጋር እንዲገባ አደረገችው። ውጤቱ ግን መናቅ፣ ቅናትና እስከ ዛሬ ድረስ የቀጠለ ጦርነት ሆነ።
✨ ከሁሉ በላይ ደግሞ...
የእኛ አዳኝና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ባይታገሥ ኖሮ እኛ ዛሬ የት እንሆን ነበር?
"...እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና።" (ዕብ 12:2)
💪 ስለዚህ ወንድሜ/እህቴ ሆይ፡
🌅 በፊታችሁ ደስታ አለና ታገሡ!
🏆 በፊታችሁ ድል አለና ታገሡ!
👑 በፊታችሁ ክብር አለና ታገሡ!
🌧 መከራው ያልፋልና ታገሡ!
⏱️ ሁሉ ያልፋልና ታገሡ!
እግዚአብሔር በትዕግሥት የምንጠብቅበትን ጸጋ ያብዛልን! አሜን 🙏✨
አገልጋይ ጌትነት አለሙ
ኤፍታህ የሕያው እግዚአብሔር ቤተክርስቲያን
ለፀሎትና ለምክር አገልግሎት ለማግኘት
☎️+251920538314
#ትዕግሥት #እምነት #ክርስትና
29/06/2026
ድንቅ ጊዜ ...
የዕሁድ አምልኮ ፕሮግራም
25/06/2026
መማር ከፈለጋቹህ...
"የእግዚአብሔር ፍርድ ምሕረት ለማያደርግ ሰው ምሕረት አያደርግም፤ ሆኖም ምሕረት ፍርድን ያሸንፋል።"
ያዕቆብ 2:13 (ዓ.መ.ት)
የእግዚአብሔር ቃል በያዕቆብ 2:13 ላይ ምሕረት ስለማያደርግ ሰው ፍርድ ምን እንደሚሆን በግልጽ ይነግረናል። ሆኖም የእግዚአብሔር ምሕረት በፍርዱ ላይ አይሎ እኛን እንዳዳነን እናውቃለን። ስለዚህ፣ እኛም ያገኘነውንና የተማርነውን መለኮታዊ ምሕረት ለሌሎች ልናካፍል ይገባል፤ ይህ ለእኛ ምርጫ ሳይሆን ክርስቲያናዊ ግዴታችን ነው።
በማቴዎስ 18:21 ላይ ጴጥሮስ ማን እንዳማረረው ባናውቅም፣ ወደ ጌታ ቀርቦ "ጌታ ሆይ፥ ወንድሜ ቢበድለኝ ስንት ጊዜ ይቅር ልበለው? እስከ ሰባት ጊዜ ነውን?" ብሎ ጠየቀው። ከሰባት ጊዜ በኋላ እርምጃ መውሰድ የፈለገ ይመስላል።
የጌታ መልስ ግን የጴጥሮስን ግምት ሙሉ በሙሉ የሚቀይር ነበር፤ "እስከ ሰባ ጊዜ ሰባት (70 X 7) እንጂ እስከ ሰባት ጊዜ አልልህም" አለው።
ጴጥሮስ በልቡ "በቀንማ ይህን ያህል ጊዜ አይበደለኝም፤ በየሦስት ደቂቃው እንኳ ቢበድለኝ ከ480 አይበልጥም" ብሎ አስቦ ሊሆን ይችላል።
ነገር ግን ጌታ የጠቀሰው ቁጥር የይቅርታን ወሰን አልባነት የሚያመለክት እንጂ ቁጥራቸውን ለመቁጠር የተሰጠ አልነበረም።
ጌታ ኢየሱስ ይህንን እውነት ለማብራራት አንድ ምሳሌ ነገራቸው፡- ለጌታው መክሊት ዕዳ ያለበት አንድ ባሪያ ነበረ። መክፈል ስላልቻለ ሊሸጥ ሲል ጌታውን ለመነው፤ ጌታውም አዝኖለት ዕዳውን በሙሉ ተወለት። ይህ የተማረውና ዕዳው የተተወለት ባሪያ ግን ወጥቶ መቶ ዲናር ብቻ ያለበትን ሌላ ባልንጀራውን አገኘውና አነቀው።
ባለዕዳው ባልንጀራው ወድቆ "እባክህ ታገሰኝ፣ እከፍልሃለሁ" ብሎ ቢለምነውም፣ እሱ ግን የተደረገለትን ታላቅ ምሕረት በመርሳት ወስዶ ወኅኒ አወረደው። ይህንን ያዩ ጓደኞቹ እጅግ አዝነው ለጌታው ነገሩት። ጌታውም ጠርቶ፡ "አንተ ክፉ ባሪያ፥ ስለ ለመንኸኝ ያን ዕዳ ሁሉ ተውሁልህ፤ እኔ እንደ ማርሁህ ባልንጀራህን ልትምረው ለአንተስ አይገባህም ነበርን?" አለው።
የተዘጋውን ፋይል መልሶ ከፈተበትና ዕዳውን ከፍሎ እስኪጨርስ ድረስ ለሚያሰቃዩት አሳልፎ ሰጠው። ከዚያም ጌታ ኢየሱስ ቆም ብለን ልናስብበት የሚገባ አስደንጋጭ ማስጠንቀቂያ እንዲህ ሲል ተናገረ፡- "ከእናንተ እያንዳንዱ ወንድሙን ከልቡ ይቅር ካላለ፥ እንዲሁ ደግሞ የሰማዩ አባቴ ያደርግባችኋል።"
ይህ ቃል ኢየሱስ ለማለት ብቻ የተናገረው ተራ ንግግር አይደለም፤ ቆም ብለን ሕይወታችንን እንመርምር። "ለመሆኑ ሕይወቴ የታሰረው፣ መንገዴስ የተዘጋው ይቅር ባላልኩት ሰው ምክንያት ይሆን እንዴ?" ብለን ራሳችንን ብንጠይቅስ?
ውስጣችንን መርምረን ለበደሉን ሁሉ ይቅርታን ከልባችን ብንሰጥ፣ ሕይወታችን ትፈወሳለች፤ ነፍሳችንም ታርፋለች።
ያኔ ጌታ ያስተማረን ጸሎት በልማድ የምንደግመው "ብሔራዊ መዝሙር" መሆኑ ቀርቶ፣ "እኛም ደግሞ የበደሉንን ይቅር እንደምንል በደላችንን ይቅር በለን" የሚለው ቃል በሕይወታችን ውስጥ በተግባር የሚገለጥ እውነት ይሆናል።
በአገልጋይ ቀዲዳ ወርቁ
ኤፍታህ የሕያው እግዚአብሔር ቤተክርስቲያን
ለምክርና ለፀሎት አገልግሎት ለማግኘት
👉 +251920538314
ክርስትና ቴያትር አይደለም
ኤፍታህ የሕያው እግዚአብሔር ቤተክርስቲያን
አድራሻ፦ አዲስ አበባ ፤ ቦሌ አራብሳ
EPHPHATHA CHURCH OF THE LIVING GOD
Addis Ababa, Ethiopia.
Phone Number:- ☎️ +251952013404
☎️ +251952014464
#ፕሮቴስታንት #ፕሮቴስታንትመዝሙር #መዝሙር #ጴንጤ #ኢየሱስ #አምልኮ #መዝሙር #ፋሲካ
20/06/2026
የጌታ ራት ፕሮግራም
#ፕሮቴስታንትመዝሙር #ክርስቲያን #አምልኮ
17/06/2026
You all are invited!!!
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the place of worship
Telephone
Website
Address
Bole Ararsa
Addis Ababa