Henok Tibebu

Henok Tibebu

Share

no more

29/04/2026

የሀሳብ ፖለቲካ!

28/04/2026

አዲስ አበባ ውብ አበባ!

27/04/2026

ለከተማነትት የማይመጥኑ የነበሩ አካባቢዎችን ወደ ዘመናዊነት ያሸጋገረች ከተማ

ቀደም ሲል በአሳፋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩት እንደ ፒያሳ፣ ካዛንችስ፣ አዋሬ እና እሪ በከንቱ ያሉ ሰፈሮች ዛሬ ታሪካቸውን አድሰው ለነዋሪዎቻቸው ምቹና ለዓይን ማራኪ ወደሆኑ የሥልጣኔ ማዕከላትነት ተቀይረዋል።

አሁን ደግሞ ይህ ታላቅ የለውጥ ማዕበል ወደ ቅጠል ተራ ደርሷል፤ በዚያም በሦስት ወራት አጭር ጊዜ ውስጥ ብቻ 500 ቤቶች ተገንብተው ለነዋሪዎች ሊተላለፉ መሆኑን ስንሰማ ተግባሩ እጅግ የሚያስደንቅና የከተማዋን ብሩህ ተስፋ የሚያበስር ሆኖ እናገኘዋለን።

ይህ ተነሳሽነት ቅጠል ተራንም ከድሮው የተራ አኗኗር ታሪክ አውጥቶ የዘመናዊነት አካል እንደሚያደርገውና በታቀደለት ጊዜም ስኬታማ እንደሚሆን ሙሉ እምነት አለን።

26/04/2026

ፕሮጄክቱ ሲጠናቀቅ ከ20ሺ በላይ ወገኖቻችን የዘመናዊ መኖርያ ቤት ባለቤት ይሆናሉ።

25/04/2026

የጅብ ችኩል ቀንድ ይነክሳል!

16/04/2026

የ5 ቢሊዮን ብር አስገራሚ ውሳኔ፤ ምርጫው በ100 ሚሊዮን፣ ቀሪው ለኑሮ ውድነት መረጋጊያ!"

30/03/2026

ጉድ በል ጎንደር

26/03/2026

ኪነ-ጥበብ ከመድረክ ድምቀት ወደ ሀገር ግንባታ ቁንጮ፤ የብልፅግና አዲስ ምዕራፍ!
= = = = = =
ለረጅም ዘመናት በሀገራችን ፖለቲካ ውስጥ ኪነ-ጥበብ እንደ "ሁለተኛ ረድፍ" ተግባር፣ አርቲስቱም እንደ "አዝናኝ" ብቻ ሲታይ ቆይቷል። ዛሬ ግን ብልፅግና ፓርቲ ይህን የታሪክ ስህተት በማረም፣ እንደ አርቲስት ካሙዙ ካሳ ያሉ የጥበብ ባለውለታዎችን ወደ ፖለቲካው ማዕከልና ወደ ህግ መወሰኛ ምክር ቤት እጩ አድርጎ ሲያቀርብ፣ ጥበብ የሀገር ግንባታ ዋነኛ ምሰሶ መሆኗን በተግባር እያረጋገጠ ነው። ይህ እርምጃ ግን "ከእኛ በቀር ለፖለቲካው የሚመጥን የለም" በሚል አባዜ ለተለከፉ፣ ፖለቲካን የጥቂት "ልሂቃን" የግል ንብረት አድርገው ለሚያስቡ ወገኖች ትልቅ የእግር እሳት ሆኖባቸዋል።

እነዚህ ወገኖች ካሙዙ ካሳ ላይ የሚከፍቱት ዘመቻ የግለሰቡን ብቃት ሳይሆን፣ የእነሱን ጠባብ አስተሳሰብ ነው የሚያሳየው። "የካሙዙ ቦታ ስቱዲዮ ውስጥ ነው" የሚሉን ወገኖች፣ ፖለቲካ ማለት ህዝብን ማድመጥ፣ የማህበረሰብን ስሜት መረዳትና ለለውጥ መስራት መሆኑን የዘነጉ ናቸው።

ካሙዙ በዜማዎቹና በቅንብሮቹ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን ልብ ማገናኘት የቻለ፣ ብሄርና ቋንቋ ሳይገድበው በኪነ-ጥበብ አንድነትን የሰበከ ወጣት ነው። እንዲህ ያለ ተፅዕኖ ፈጣሪና በስራው የተመሰከረለት ሰው ለህዝብ ውክልና ሲቀርብ "አይመጥንም" ማለት፣ አርቱንና ወጣቱን ትውልድ ከመናቅ በላይ ምን ሊሆን ይችላል?

ብልፅግና ፓርቲ ለኪነ-ጥበብ የሰጠው ትኩረት ድንገታዊ ሳይሆን፣ በግልፅ ራዕይ የሚመራ ነው። ፓርቲው እንደ ዓድዋ መታሰቢያ ያሉ ታላላቅ የኪነ-ጥበብና የታሪክ ማዕከላትን በመገንባት፣ ለአርቲስቶች ክብርና የሙያ ዋስትና በመስጠትና አሁን ደግሞ የዘርፉን ወኪል ወደ ምክር ቤት በማምጣት አዲሷን ኢትዮጵያ በሁሉም ዘርፍ ተሳታፊነት እየገነባ ነው። ፖለቲካው እንደ ትላንቱ በአንድ አይነት መስፈርት ብቻ የሚሞላ ሳይሆን፣ እንደ ካሙዙ ያሉ የፈጠራ ሰዎች፣ የጥበብ ባለቤቶችና ተፅዕኖ ፈጣሪ ወጣቶች የሚሳተፉበት ሰፊ አደባባይ ሆኗል።

"እኛ ካልሆንን" የሚሉ ወገኖች ሆይ! ፖለቲካ የናንተ የግል ድርጅት አይደለም። የኪነ-ጥበብ ሰዎች ህሊናቸው ለህዝብ፣ ስራቸው ለሀገር የሆነ ታላላቅ ዜጎች ናቸው። ካሙዙ ካሳን በእጩነት ማቅረብ ማለት፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወጣቶች ራሳቸውን በፖለቲካው ውስጥ እንዲያዩ መንገድ መክፈት ማለት ነው። ብልፅግና ፓርቲ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል — ከገበሬው እስከ አርቲስቱ — እኩል ወክሎ ወደፊት ለመጓዝ የያዘው ቁርጠኝነት የሚደነቅ ነው። ካሙዙ በፓርላማ የሚኖረው ድምፅ፣ የጥበብ ሰዎች ድምፅ፣ የፈጠራ ባለቤቶች ድምፅና የናንተን "አግላይ ፖለቲካ" የሚሰብር አዲስ ትውልድ ድምፅ ነው።

Via: ሰላማዊት ነኝ ከኪነጥበብ

25/03/2026

Abichu

Photos from የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ Addis Ababa City Communication's post 24/03/2026
Want your business to be the top-listed Media Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Website

Address


Addis Ababa