Meri Konjoo
I'm Focusing on Facts and Unity:
I speak for the real facts and unwavering spirit of my Ethiopian people.
We reject the narratives of division and stand firm in our unity. #EthiopiaFacts #UnitedForEthiopia🇪🇹ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር። 🇪🇹
🙏
13/06/2026
“ሁለት ዓመት ከመዋጋት 20 ዓመት መወያየት ይሻላል”
Abiy Ahmed Ali
በዲጂታሉ ዓለም በልኩ ለመዘጋጀት የጀመርነው ታሪካዊ ምዕራፍ፤ የጉዟችን ማብቂያ ሳይሆን፥ ብሔራዊ ርዕያችንን ይበልጥ የምናፋጥንበት መነሻ ነው
ጠ/ሚ/ር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ
በዲጂታሉ ዓለም በልኩ ለመዘጋጀት የጀመርነው ታሪካዊ ምዕራፍ፤ የጉዟችን ማብቂያ ሳይሆን፥ ብሔራዊ ርዕያችንን ይበልጥ የምናፋጥንበት መነሻ ነው። እስከ ነሐሴ 2018 ዓ.ም. ድረስ የሰልጣኞችን ቁጥር 7 ሚሊዮን ለማድረስ የተሰነቀውን ግብ ለማሳካት፥ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የዚህ ብሔራዊ ተልዕኮ አካል እንዲሆን ጥሪዬን አቀርባለሁ።
የምትገነቡት ነገ የሚጀምረው ዛሬ ነው!
ለመመዝገብ እዚህ ይጫኑ:
ethiocoders.et/
#ኢትዮኮደርስ
11/06/2026
ሰበር መረጃ
የፕሪቶሪያ ስምምነት አደራዳሪ ከነበሩት ኦሊሴንጎ ኦባሳንጆ የአውስትራሊያና የኢንግሊዝ ተወካዮች ያካተቱ የልኡካን ቡድን ከተማ መቐለ ገቡ። አደራዳሪዎች “ህወሓት በዓለም አቀፍ ማሕበረሰብ አሸባሪ ተብሎ ከመሰየሙ በፊት የነበረውን ጊዜያዊ አስተዳደር መልሱ” በማለት የህወሓት አመራሮችን አስጠቅቀዋል።
09/06/2026
የሀገር መከታ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት
ኢትዮጵያ—የጥቁር ሕዝቦች የነፃነት ተምሳሌት፣ የጀግኖች እና የኩሩ ሕዝቦች ምድር! ይህችን ታሪካዊ ሀገር ከትውልድ ወደ ትውልድ በክብር ያሸጋገራት የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ነው። የሀገራችን መከላከያ ሠራዊት የድንበር ጠባቂ ብቻ አይደለም፤ የኢትዮጵያ አንድነት ምሰሶ፣ የሉዓላዊነታችን ቀኝ እጅ እና የሕዝባችን የሰላም ዋስትና ነው።
09/06/2026
ከሕልውና እስከ ልዕልና የሠራዊታችን የለውጥ ጉዞ!
ኢትዮጵያ ዛሬ በኩራት የምትመለከተው መከላከያ ሠራዊት፣ በዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የመሪነት ዘመን የተገኘ ታላቅ የጋራ ድል ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በግል ትኩረት እና በጠንካራ አመራር የጀመሩት የተቋማዊ ሪፎርም ሥራ፣ ሠራዊቱን ከኋላ ቀር አደረጃጀት ወደ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ተሸጋሪ፣ የራሱን ትጥቅ በራሱ አቅም ማምረት ወደሚችልበት ደረጃ አድርሶታል። የሠራዊቱ ጥንካሬ የሚለካው በጦር መሣሪያ ብቻ ሳይሆን፣ ለሕዝቡ ባለው ጥልቅ ፍቅር፣ ለዜጎች ደኅንነት በሚከፍለው የሕይወት መሥዋዕትነት እና በአደራ ጠባቂነቱ ጭምር ነው።የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በፖለቲካ ጫና ውስጥ ሳይሆን፣ በሙያዊ ብቃት ብቻ የሚመራ ተቋም በመሆኑ የዜጎች የኩራት ምንጭ ሆኗል። የሰላም እና የፀጥታ ተቋማትን በማዘመን የዜጎችን ደኅንነት በዘላቂነት ማረጋገጥ የቻለው ይህ የለውጥ ጉዞ፣ ሀገራችንን በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍ አድርጓታል። የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ቁርጠኝነት፣ ሠራዊታችንን የሕዝብ ደኅንነት አስተማማኝ ዋስትና እና የሉዓላዊነታችን የማይበገር ምሽግ አድርጎታል፤ ለዚህም ነው ዛሬም ነገም "የቀጣናው ግርማ ሞገስ" ብለን በኩራት የምንጠራው። #ኢትዮጵያ #መከላከያ #የቀጣናውግርማሞገስ #ለውጥ #ዐቢይ አሕመድ
ሰበር መረጃ ‼
የህወሓት ታጣቂ አባል ሚስጥር አጋላጠ።
➖➖➖➖➖
“የድርግም ይሁን የሻዕቢያ እንዲሁም የ 2013 ዓ/ም ትግል የህወሓት ትግል ህወሓትን ማዳን የተደረገ ነው። በሶስቱ ጦርነቶች ወንድምህ ይሁን አባትህ ከተሰዋ ለህወሓት ነው የተሰዋ። አንተም አካልህ ከጎደለ ለህወሓት እንጂ ለትግራይ ህዝብ አይደለም። ለትግራይ ብዬ ለትግራይ ባንዴራ ከፍ ብሎ ብዬ እያላችሁ ራሳችሁን አሸውዱ። ውሸት ነው አዕምሮችሁን አትሸውዱ። ለማንም አልታገልክም ለህወሓት እንጂ። “የትግራይ እናት ተደፈረች ምናምን” ይባላል። በጣም የሚገርማችሁ ነገር ግን በ 2013ቱ ጦርነት መከላከያ እና ሻዕቢያ ከደፈራቸው እናቶች በላይ “TDF” የደፈራቸው በቁጥር ይበዛሉ። ስለዚህ እናቴ ተደፈረች ምናምን እያላችሁ አዕምሮችሁን አትሸውዱ።”
09/06/2026
ጨቅላ ህጻናትን በጦር ግንባር ማሰለፍ ወንጀል ነው!
ህወሓት ለራሱ የፖለቲካ ስልጣንና ጥቅም ሲል የነገ ሀገር ተረካቢ ህጻናትን ለጦርነት እየማገደ የሚገኝ ቡድን ሲሆን፣ እድሜያቸው ለጦርነት ያልደረሱ ህጻናትን ከትምህርት ገበታቸው ጭምር በግድ በመመልመልና በማፈን ለጥፋት ተልዕኮ እንዲሰማሩ በማድረግ የቡድኑን የጭካኔ ጥግ እና ለወጣቱ ትውልድ ያለውን ንቀት በግልፅ ያሳያል። ይህ የህጻናት ምልመላ ተግባሩ ህጻናት ከትምህርት ቤት ታፍሰው ወደ ጦር ግንባር በማሰለፍ ለጦርነት እንዲማገዱ መደረጉ ትውልድን የመግደል ያህል የሚቆጠር ነው።
09/06/2026
ፅኑ ሰላም በጋራ ክንዳችን ለዘላቂ ሀገራዊ መግባባት የተጣለው የማይናወጥ መሠረት!
የአንድ ሀገር ህልውና፣ ሉዓላዊነትና የሕዝቦች ሁለንተናዊ ብልጽግና ሊረጋገጥ የሚችለው በማይናወጥ ፅኑ ሰላም ላይ ሲመሰረት ብቻ እንደመሆኑ መጠን፣ ባለፉት ስምንት የለውጥ ዓመታት በታላቁና አርቆ አሳቢው መሪያችን በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ቆራጥ አመራርና ግንባር ቀደም ተዋናይነት የተከናወኑ የስልጣኔና የተቋማት ግንባታ ስኬቶች ለሀገራችን ዘላቂ መረጋጋት አስተማማኝ ዋስትና ሆነዋል! ለዘመናት የቆዩ ጽንፈኛ የታሪክ ትርክቶችንና ውስጣዊ ግጭቶችን በዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ስልታዊ መሪነትና ቀጥተኛ ሚና በመቀየር ረገድ የተመዘገቡት ስኬቶች የሀገራችንን ሉዓላዊነት አስተማማኝ አድርገውታል። በተለይም በዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ዘመን የተገነቡ ዘመናዊ እና አስተማማኝ የሰላምና ጸጥታ ተቋማት፣ የሕግ የበላይነትን በማስከበር፣ የዜጎችን ደህንነት በመጠበቅና የሀገር መረጋጋትን በማጠናከር ረገድ የወደፊት ትውልድ የሚኮራበት ታላቅ ቅርስ ሆነው ለታሪክ ተቀምጠዋል። ልዩነቶች የአብሮነታችን ሕብረ ቀለሞች ቢሆኑም፣ የኢትዮጵያዊነትን እሴት የሚሸረሽሩና የሀገርን ህልውና አደጋ ላይ የሚጥሉ ችግሮችን በጋራ ለመከላከል አሰባሳቢ ትርክቶችን ማስረፅ እና ማኅበራዊ ትስስርን ማጠናከር የነገ የማይባል ተግባራችን ሲሆን፣ ይህንን ታሪካዊ የለውጥ ጉዞ ለማሳካት ከመንግሥትና ከጸጥታ ኃይሎች ጎን ለጎን መላው ሰላም ወዳድ የኅብረተሰብ ክፍል ወጣቶች፣ ምሁራን፣ ተማሪዎች፣ መምህራንና የፖለቲካ ፓርቲዎች ሁሉ በአንድነት በመቆም ሰላማችንን ሌት ተቀን እንደ ዓይናችን ብሌን ልንጠብቀውና ለልጆቻችን የምትመች የተከበረች ሀገር ልናስረክብ ይገባል #ፅኑሰላም #ብሔራዊመግባባት #ጠቅላይሚኒስትርዐቢይ #የተቋማትግንባታ #የሕግየበላይነት #ኢትዮጵያ ትንሳኤ #አንድነት #ዘላቂሰላም
08/06/2026
የሕወሓት እብሪተኛ ቡድን በትግራይ ክልል አስገዳጅ ህግ አወጣ!
እምቢተኝነት እስከ 50ሺህ ብር ያስቀጣል
አሁን ላይ በትግራይ ክልል ሰፊ ወታደራዊ አፈሳና ምልመላ እየተካሄደ መሆኑ ሲዘገብ ቆይቷል።
ዕድሜና አካላዊ ብቃቱ እየፈቀደ ወደ "ትግራይ ሰራዊት" ለመቀላቀል ወይም ግንባር ለመሰለፍ እምቢተኛ ሆኖ የተገኘ ማንኛውም የትግራይ ተወላጅ፣ ከ10,000 እስከ 50,000 ብር በሚደርስ ከፍተኛ የገንዘብ መቀጮ እንደሚቀጣ ታውቋል።በቀይ የተሰመረበትን ይመልከቱት።
የትግራይ #ወጣት ከዚህ ሻዕቢያዊ አምባገነንነት ራሱን ማዳን አለበት!!!!
#ትግራይ
#ኢትዮጵያ
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Address
Addis Ababa