Ethiopian Informer

Ethiopian Informer

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ethiopian Informer, News Personality, Addis Ababa.

Photos from Ethiopian Informer's post 04/01/2023

በአሁን ሰዓት የኢትዮጵያ ህልውና አደጋዎች
1. ብቃት አልባው ጠ/ሚ
2. የበሰበሰው በሙስና የዘቀጠው እና የመከነው ብልጽግና ፓርቲ የመንግሰትን የማስፈጸም አቅም ማሳጣቱ
3. በበቀል ስሜት ጠላቴ ያለውን የአማራን ህዝብ ሊፈጅ ከእነትጥቁ ገብቶ ዘር ማጥፋት በመንግሰት መዋቅራዊ ድጋፍ እየፈጸመ ያለው ኦነግ
4. በኦህዴድ ከሀዲነት እና ተረኝነት ምሬት ከፓርቲው የሚወጡ አንጃዎች እና ብሔሮች
5. በከፍተኛው ዘር ማጥፋት በእልህ እና ቁጭት እየጋመ ያለው የአማራ ብሔርተኝነት
6. በበቀል ስሜት የልቡን በልቡ ይዞ ወደ መንግሰት አስተዳደር እየመጣ ያለው ብርቱው ህወሓት
7. መለስ ዜናዊ ሊፈታው ያልቻለው እና ቀስ በቀስ ስር ወደ ሰደደ ጥላቻ እየተቀየረ ያለው የአዲስ አበባ ህዝብ ሊቀሰቅስ የሚችለው ከፍተኛ ህዝባዊ እምቢተኝነት እና አመጽ
8. በማድበስበስ በአሻጥር እና አለፍ ሲልም አፍ አውጥተው የኦሮሞን ጥቅም እስካልነካ ድረስ ወልቃይትም ራያም ወደ ትግራይ መመለስ ይችላሉ የሚለው የደካማው ጠ/ሚ አቋም አማራ እና ትግራይ ወደ ማይቀር ጦርነት ቢገቡ ይዳከሙልኛል የሚለው የተሳሳተ ስሌት
9. በሁለቱ አመት ጦርነት ውጤት ቀያሪ የነበረችው ኤርትራ ህልውናዋን ለማስጠበቅ በአማራ ኃይሎች በአፋሮች እና እንደአዲስ በአዳራጀችው የደካማዋ ሶማሊያ ጦር ልትፈጥር የምትችለው ጫና
10. የደቡብ አፍሪካው ስምምነት የሰብዓዊ መብት ጥሰት የፈጸሙ ዘር ማጥፋትን ሴቶች እና ህጻናትን በበቀል ሲደፍሩ በነበሩ በሁለቱም ተፋላሚዎች ውስጥ ያሉ ወንጀለኞችን ለፍርድ እንዲቀርቡ ጉዳዩም በገለልተኛ ወገን እንዲጣራ አለማድረጉ ወደ ዳግም ጦርነት ላለመመለስ ዋስትና አለመስጠቱ
11. የውጭ ኃይሎች የሚፈጥሩት እና እየፈጠሩ ያሉት ከፍተኛ ጫና
12. በብቃት አልባው በሙስና በዘቀጠው እና በዘር እየታመሰ ባለው ብልጽግና ችግር እየደረሱ ያሉት የኢኮኖሚ ቀውሶች አሁን ባለው ሁኔታ ሊሻሻሉ የማይችሉ በመሆናቸው…
የኢትዮጵያ ጉዳይ የጋራ የህልውና ጉዳይ በመሆኑ ምሁራን ወጣቶች የፖለቲካ ፓርቲዎች እና መላው ህዝብ በሀገሪቱ ዘላቂ ሰላም ዲሞክራሲያዊ አስተዳደር እና ፍትሕ እንዲሰፍን ከጎሰኝነት እና ጠባብ ብሔረተኝነት ወጥተው ለሰብዓዊነት እና እኩል ተጠቃሚነት በሁሉም መድረክ ሰላማዊ ትግል ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡
PLEASE SHARE THIS MESSAGE FOR ALL ETHIOPIANS

15/08/2022

ሰ በ ር ዜ ና ! !
ሕወሓት ጥቃት ጀመረ !!
የቀረበውን የሰላም አማራጭ ወደ ጎን በመተው የአሸባሪው ሕወሓት ታጣቂዎች በአፋር ግንባር ዛሬ ምሽት ጦርነቱን ጀምረዋል!! Like/Follow Ethiopian Examiner
https://www.facebook.com/groups/609902437160785/?ref=share

Photos from Ethiopian Examiner's post 26/06/2022
25/06/2022

ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የተሰጠ መግለጫ፤
___________

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ኦሮሚያ ክልል ምእራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ወረዳ በቶሌ ቀበሌ እና አጎራባች ቀበሌዎች በአማራ ተወላጆች ላይ የተፈጸመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል አስመልክቶ የወሰደው አቋም የተጣለበትን ኃላፊነት የማይመጥን እና ሊታረም የሚገባው ነው፡፡

1. ሰኔ 11 ቀን 2014 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ እና አጎራባች ቀበሌዎች ነዋሪ የሆኑ የአማራ ተወላጆች ላይ የተፈጸመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል ተከትሎ የፓርቲያችን አመራር እና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት የተከበሩ ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ምክር ቤቱ የተፈጸመውን የዘር ማጥፋት አስመልክቶ በአስቸኳይ አጀንዳነት ይዞ ውይይት እንዲያደረግ ጥያቄ ቢያቀርቡም የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ የሆኑት የተከበሩ አቶ ታገሰ ጫፎ ጥያቄውን ውድቅ ማድረጋቸው ይታወቃል፡፡ ምክር ቤቱ በአጀንዳነት ከተያዙ ጉዳዮች ውጭ ያሉ አሰቸኳይ ጉዳዮችን ለማስተናገድ የሚያስችል አሰራር በሕግ የተፈቀደለት ሲሆን ፣ አስቸኳይ ጉዳዮችን በተመለከተ በሕግ ያልተገደበ እና ሙሉ ሥልጣን የተሰጠው የምክር ቤቱ አፈጉባኤ ሲፈቅድ ጥያቄውን ማስተናገድ እንደሚቻል በግልጽ ተደንግጓል፡፡ በክቡር ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ እና በክቡር አቶ ታገሰ ጫፎ መካከል ከተከናወነው ምልልስ ቪዲዮ ላይ በግልጽ እንደሚታየው የተከበሩ አቶ ታገሰ ጫፎ የምክር ቤቱን መተዳደሪያ ደንብ ጥሰው “በአጀንዳ ባልተያዘ ጉዳይ ላይ አንወያየም” በማለት በአስቸኳይ ጉዳይነት እንዲያዝ የተጠየቀውን የዘር ማጥፋት ወንጀል ጉዳይ ውድቅ አድርገዋል፡፡

በፓርቲያችን አመራር እና የምክር ቤቱ አባል በሆኑት የተከበሩ ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ የቀረበው ጥያቄ ምክር ቤቱ የሚመራበትን ደንብ እና ሥርአት መሰረት አድርጎ የቀረበ አስቸኳይ ጉዳይ ሲሆን ፣ ምክር ቤቱ በይፋዊ ማኅበራዊ ድረገጾች ባወጣው አጭር መግለጫ በአጀንዳነት ከተያዙ ጉዳዮች ውጭ ያሉ አስቸኳይ ጉዳዮችን ለማስተናገድ የሚያስችል አሰራር በሕግ የተፈቀደለት ለመሆኑ የሚያረጋግጠውን የሕጉን ክፍል የለጠፈ ቢሆንም ፣ “ምክር ቤቱ የውይይት እና የምክክር እንጅ የፖለቲካ ነጥብ ማስቆጠሪያ መሆን የለበትም” በማለት የዘር ማጥፋት ወንጀልን በሚመለከት የቀረበን አጀንዳ ተራ የፖለቲካ ነጥብ ማስቆጠሪያ ነው ሲል ተሳልቋል፡፡

የምክር ቤቱ አፈጉባኤ ክቡር አቶ ታገሰ ጫፎ በአጀንዳነት ያልተያዘ አስቸኳይ ጉዳይን የማስተናገድ በሕግ የተፈቀደ እና ያልተገደበ ሙሉ ሥልጣን እያላቸው ፣ ጥያቄውን ውድቅ ማድረጋቸው ፣ ምክር ቤቱ ባወጣው አጭር መግለጫ የብሔራዊ ደኅንነት ከፍተኛ ስጋት የሆነውን እና ሀገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ወደ ለየለት ቀውስ ውስጥ የሚከትን የዘር ማጥፋት ወንጀልን የሚመለከት ጉዳይ “ተራ የፖለቲካ ነጥብ ማስቆጠሪያ” ሲል መሳለቁ ፣ ፓርቲያችን የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)ን ፣ የአማራን ሕዝብ እና መላው ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውንን ያሳዘነ፣ ምክር ቤቱ የተጣለበትን አደራ ያጎደለ ተግባር ሆኖ አግኝተንዋል፡፡

2. ክቡር አቶ ታገሰ ጫፎ ሰኔ 16 ቀን 2014 ዓ.ም በጻፉት ደብዳቤ እጅግ አንገብጋቢ እና ጊዜ የማይሰጠውን የዘር ማጥፋት ወንጀል ጉዳይ መንግስት እየወስድኩት ነው ከሚለው የሕግ ማስከበር ዘመቻ ጋር ተያይዞ እየቀረቡ ካሉ ቅሬታዎች ጋር ተዳብሎ እንዲጣራ የጤና ፣ ማኅበራዊ ፣ ባህል እና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አጣርቶ እንዲቀርብ የሰጡት ቀን ያልተቆረጠለት ትዕዛዝ ለተፈጸመው የዘር ማጥፋት ወንጀል የማይመጥን እና እጅግ የዘገየ ከመሆኑም በላይ ፤ ሰኔ 11 ቀን 2014 ዓ.ም በቶሌ ቀበሌ እና አጎራባች ቀበሌዎች ነዋሪ በሆኑ የአማራ ተወላጆች ላይ የደረሰውን እልቂት አስመልክቶ የኦሮሚያ ክልል መንግስትም ሆነ የፌዴራሉ መንግስት ባለስልጣናት ባልካዱበት ሁኔታ በሕግ ማስከበር ዘመቻው ከሚነሱ ቅሬታዎች እኩል ተጣርቶ እንዲቀርብ ማዘዛቸው ክቡር አፈጉባኤው እና የተከበረው ምክር ቤት ጉዳዩን የያዘበትን አግባብ ጥያቄ ላይ የሚጥል ነው፡፡

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ በቶሌ ቀበሌ እና አጎራባች ቀበሌዎች የደረሰው የዘር ማጥፋት ወንጀል አስመልክቶ የተከበሩ አቶ ታገሰ ጫፎ የሰጡት የይጣራ ትዕዛዝ ቀን ያልተቆረጠለት እና ብዙ ውስንነት እያለበትም ቢሆን ጥረቱን የሚያበረታታ ሲሆን ፣ ክቡር አፈጉባኤው እና የተከበረው ምክርቤት እስካሁን ሀገር ባወቀው ጉዳት ልክ የሚመጥን ተገቢውን እርምጃ ለመውሰድ ዳተኛ መሆናቸው ፓርቲያችንን አሳስቦታል፡፡ በበርካታ የሀገር ውስጥና ዓለም ዓቀፍ ሚዲያዎች ዘገባ መሰረት እና ከታመኑ ምንጮች በተገኝ መረጃ እስካሁን ድረስ ቢያንስ 600 መቶ የቶሌ ቀበሌ እና አጎራባች ቀበሌዎች ነዋሪ የሆኑ የአማራ ተወላጆች ተገድለው በጅምላ ቀብራቸው የተፈጸመ ፣ ሌሎች በርካቶች ተጠቂዎች ቀብራቸው ተፈጽሞ ያላለቀ ስለመሆኑ እና በአስር ሽህዎች የሚቆጠሩ ተፈናቃዮች ተገቢውን እርዳታ እና ድጋፍ አጥተው እየተንገላቱ ስለመሆናቸው የተረጋገጠ በመሆኑ ፣ ምክርቤቱ እስካሁን በታወቀው ጉዳት ልክ ተመጣጣኝ እርምጃ ሊወስድ በተገባው ነበር፡፡ ስለሆነም አብን ለክቡር አፈጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ እና ለተከበረው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚከተለውን ጥሪ ያስተላልፋል፦

1. የተከበሩ አፈ ጉባኤ ክቡር አቶ ታገሰ ጫፎ በምክር ቤቱ አባል ክቡር ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ የቀረበላቸውን አስቸኳይ ጉዳይ በአጀንዳነት እንዲቀበሉ እና ምክር ቤቱ በቶሌ ቀበሌ እና አጎራባች ቀበሌዎች በተፈጸመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል አስመልክቶ ውይይት እንዲያደረግ እና በጉዳዩ ላይ ተገቢውን አቋም እንዲያዝ እንዲደርግ፤

2. ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ እና የሚመሩት መንግስታቸው የሀገራችን እና ሕዝቦቿን ደኅንነት ለማረጋገጥ የሚያስችል አቅም እና በቂ የጸጥታ ኃይል የገነቡ ለመሆኑ በተደጋጋሚ ማረጋገጫ እየሰጡ ባለበት ወቅት ፣ በአማራ ሕዝብ ላይ ሳያቋርጥ እያሰለሰ የቀጠለውን የዘር ፍጅት ወንጀል ለማስቆም ያልቻሉበትን እና የጥቃቱ ሰለባ ለሆኑ ተፈናቃዮች ተገቢውን ድጋፍ ለማድረስ ያልቻሉበተን ምክንያት በተከበረው ምክር ቤት ፊት ቀርበው እንዲያስረዱ እንዲታዘዙልን፤

3. በሀገራችን ኢትዮጵያ በተለይም በአማራ ሕዝብ ላይ በተከታታይ እና በመደበኛ ሁኔታ እየተፈጸመ ያለው የዘር ፍጅት እና የዘር ማጥፋት ወንጀል ተጨባጭ ፣ ግልጽ እና ተገማች አደጋ /Clear and Present Danger/ በመሆኑ ፣ የችግሩ ምንጭ የሆኑ የሕግ ፣ የመዋቅር እና የሥርአት-አቀፍ ችግሮች እስኪፈቱ ድረስ እና ችግሩ ወደለየለት እና አጠቃላይ የዘር ፍጅት /Full-Scale Genocide/ ከመድረሱ በፊት አደጋውን መከላከል የሚቻለው የዘር ማጥፋት እና በሰብዓዊነት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን መከላከል የሚያስችል ብሔራዊ ፖሊሲ ፣ ስትራቴጅ ፣ ሕግ እና አሰራር /National Mechanism for the Prevention of Genocide and other Atrocious Crimes/ ሥራ ላይ በማዋል በመሆኑ ፣ የተከበረው ምክር ቤት ፖሊሲውን እና አሰራሩን ሥራ ላይ በማዋል ታሪካዊ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪያችንን እያስተላለፍን ፣ በማያበራ የዘር ፍጅት እልቂት ውስጥ ለሚገኝው የአማራ ሕዝብ እና ለመላው ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን መጽናናትን እንመኛለን፡፡

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)
አዲስ አበባ ፣ ሸዋ
ሰኔ 18 ቀን 2014 ዓ.ም

Photos from Ethiopian Informer's post 04/06/2022

በዋሽንግተን ዲሲ የኢትዮጵያን መንግስት የሚያወግዝ ሰልፍ መካሄድ ጀመረ ።

04/06/2022

የነዳጅ ጭማሪው አሻጥር በዋናነት እንዲያንበረክክ የተቀነባበረው ለአዲስ አበባ ሕዝብ ነዉ ! ከ580 ሺ በላይ የግል እና የንግድ መኪኖች ሸገር ላይ ሲታመሱ የዋጋ ግሽበቱ የዚምባቡዌን ያስንቃል !! የሕዝብ ስቃይ ይብቃ !!

11/01/2022

የኢትዮጵያ ጸለምት እጣ ፈንታ : Now it is CHECK MET !!

የኢትዮጵያ ሰራዊት መቀሌን ለቆ የወጣው በሽንፈት ነው፡፡ ኮረምንም ግራ ካሱንም ዞብልንም እየተወ ትጥቁን እየጣለ የወጣውም በሽንፈት ነው፡፡ የህወሃት ወራሪ ኃይል አማራ ክልልን እና የአፋርን ዞኖች የጥቃት ሰለባ አድርጎ ያንን ሁሉ አሰቃቂ ውድመት እና ግፍ ሲፈጽም ሰራዊቱ እንዲያፈገፍግ እየታዘዘ በሽንፈት ታጅቦ ደብረ ሲና መድረሱ ልንቀበለው የሚገባ መራር እውነት ነው፡፡ ወረራውን ቀልብሶ ወደ ድል ሊመለስ የቻለባቸውም ዋና ዋና ምክንያቶች

1. ሚሳይል እና ተተኳሽ የገጠማ ስራቸው ዘግይቶ የነበሩት ድሮኖች ለግዳጅ መሰማራታቸው
2. የጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ጦር ግንባር ለመዝመት መወሰናቸው
3. ታዋቂ ግለሰቦች አትሌት ኃይሌ ገ/ስላሴ አትሌት ሌሊሳ ፈይሳ፡ ታማኝ በየነ ነዓምን ዘለቀ እና ሌሎችም የጠቅላዩን ፈለግ በመከተል ወደ ግንባር መዝመታቸው ከፍተኛ የህዝብ መነቃቃት በመፈጠሩ ሰራዊቱ ሞራሉ በከፍተኛ ደረጃ መነሳሳቱ
4. ዲያስፖራው ያለማቋረጥ በመላው አለም ከፍተኛ ሰልፎችን በማካሄድ የህዋሓትን የጄኖሳይድ እና ልንጠፋ ነው ትርክት ማደብዘዝ በመቻሉ
5. ቻይና ቱርክ አርብ ኤምሬት ኢራን እና ሩሲያ በዲፕሎማሲ እና በወታደራዊ ዘርፍ ከኢትዮጵያ መንግስት ጎን መቆማቸውን ማሳየታቸው የአፍሪካ ህብረትም አቋሙን እንዲያጸና በማድረጋቸው ሲሆን

የኢትዮጵያ ጦር አላማጣ ድረስ ደርሶ ትግራይን እንደ ሉዓላዊ ግዛት በሚቆጥር መልኩ አልፌ አልገባም የሚለው የተሳሳተ ፓለቲካው ውሳኔ ግን ግብጽ ሲና በርሃ ደርሳ የተሸነፈችበትን የዮም ኪፑር ጦርነት ያስታውሰናል፡፡ የአራተኛው የአረብ እስራኤል ጦርነት የዮም-ኪፑር ጦርነት ወይም የረመዳን ጦርነት በመባል ይታወቃል፡፡ በዚህ ጦርነት ግብጽ እና ሶሪያ በተመሳሳይ በጎላን እና በሲና በረሃ ተመሳሳይ ጥቃት በመፈጸም ወረራ የጀመሩበት ዘመቻ ሲሆን ብዙ የጦር ጠበብት ለአረቦች ሽንፈት ግብጽን ተጠያቂ ያደርጋሉ፡፡ በወቅቱ በከፍተኛ ማጥቃት ሲና በረሃን ያቋረጠው የግብጽ ጦር የእስራኤል ጦር ከሸሸ በኋላ ወደ ፊት ማጥቃቱን በማቆም ለቀናት በረሃ ላይ ሆኖ የጎላንን ጦርነት ውጤት በመጠባበቅ እስራኤላውያን ሙሉ ኃይላቸውን ሶሪያን በማጥቃት የጎላንን ኮረብታ ጭምር ከሶሪያ በመንጠቅ ድል አድርገው እስኪመለሱ ቁጭ ብሎ በመጠበቅ ሽንፈት የተከናነበበትን አሳፋሪ ውጊያ አካሂዷል፡፡ በመሆኑም በአላማጣ ደርሶ የመቆምን ውሳኔና ከዚያን በኋላ የተፈጠሩ እና ወደፊት የሚፈጠሩ ኩነቶችን እንደሚከተለው ይቀርባሉ፡፡

1. የኢትዮጵያ ጦር የሚሸሸውን ወራሪ ተከታትሎ ማጥፋት የሚችልበትን ወርቃማ እድል አጥቷል፡፡
2. መንግስት ከምዕራባውያን ጦርነቱን ትግራይ ድንበር በማቆም ሊያገኝ የፈለገውን የዲፕሎማሲ ድጋፍ ሊያገኝ አልቻለም፡፡ እንደውም አሜሪካ የጀመረቸውን ማዕቀብ በማጠናከር ኢትዮጵያን ከአጎዋ አስወጥታታለች፡፡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንም ሶስት አጣሪዎች የሰየመበትን በአውሮፓ ህብረት የተጠነሰሰውን ጉባኤ ውሳኔ ከመወሰን አላገደውም፡፡
3. ህዋሓት የደረሰበትን መራር ሽንፈት ስልታዊ ማፈግፈግ በሚል በምዕራባውያን ሚዲያ ጭምር ዘመቻ በማካሄድ ለዳግም ወረራ ወታደራዊ ዝግጅት እንዲያደርግ እና በኋላም ወደ ዋጃ እና አባላ ወልቃይት እና ማይጠብሪ ላይ አዲስ ጥቃት እንዲሰነዘር እድል አግኝቷል፡፡
4. በወታደራዊ መስክ መንግስት ሊያገኘው ከጫፍ ደርሶ የነበረውን ሙሉ ድል ሳያረጋግጥ ሲና በረኃ ቆሞ ለቀናት የእስራኤልን የሶሪያ ድል እንደጠበቀው የግብጽ ጦር ለዳግም ጥቃት ራሱን አጋልጧል፡፡
5. በወታደራዊው መስክ ሙሉ ድል ባለመረጋገጡ ከዚህ በኋላ ህወኃት ሊጠፋ የማይችል እንዲሆን በግድ በመቀበል ወደ ምዕራባውያን የድርድር መንገድ እንዲገባ መንግስት ራሱ አንገቱ ላይ ገመድ አስገብቷል፡፡
6. እነስብሃት ነጋ እና ሌሎች የሕዋሓት ቁንጮ መስራቾች ከእስር እንዲለቀቁ የተደረገበትን ኢትዮጵያውያንን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን ያስቆጣ ውሳኔ በመወሰን የፍትሕ ስርዓቱን በመናድ የፓለቲካ ሊጠገን የማይችል ኪሳራ በራሱ ላይ አምጥቷል፡፡
7. ከዚህም በኋላ ቅርቃር ውስጥ በመግባቱ ያልተጠኑ እና ያልታሰበባቸው ውሳኔዎችን በመወሰን የህወኃትን ከአሸባሪ ሊስት በማስፋቅ ሰላም ይሻለናል የሚል ድርድር ይጀምራል፡፡ ወይም የህዝብ ይሁንታ ለማግኘት ከረፈደ ውጊያውን በመጀመር ከፍተኛ ኪሳራ ውስጥ ይገባል፡ አገሪቱን አደጋ ላይ ይጥላል ወይም ተሸንፎ አገር ያፈርሳል፡፡
8. ራያ እና ወልቃይትን ለድርድር ለማቅረብ ሰራዊቱን የማስወጣት አሳፋሪ ድርድር ውስጥ በአሚሪካ አሸማጋይነት (ከመድረክ ጀርባ) ስለሚገባ የአማራ ክልል የከፋ የጦርነት ቀጠና እና የሰብዓዊ ቀውስ ማዕከል በማድረግ የኦሮሞ ጽንፈኛ ፖለቲከኞች ድብቅ አጀንዳን በፌደራል መንግስት ስም ለማድረግ በሚደረግ አሻጥር ሀገር ያፈርሳል፡፡

CHECK MET !!

28/12/2021

ሰ በ ር ዜ ና ! !

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት፡ የአማራ ልዩ ኃይል እና ሚሊሻ ጦር የሽብርተኛው ህወሓት ጉጀሌ ታጣቂን በመደምሰስ አድርቃይን በአንፀባራቂ ድል በመቆጣጠር ወደፊት እየገሰገሰ ይገኛል:: የጥምር ጦሩ ህዝባዊ ሀይል ከአድርቃይ ቀጥሎ ፊት ለፊቱ እንደ አባ ጉና እንዲሁም ሽረ የትግራይ ከተሞችን እንዲጠብቁ አደራ የተጣለባቸውን አርሚ 1 እና 2 ሙሉ በሙሉ የደመሰሰ መሆኑን የተገነዘቡት የአሸባሪው አመራሮች በሱዳን በኩል የአልቡርሀን ኃይሎች ኢትዮጵያን እንዲያጠቁ ቢያስደርጉም የሱዳን ኃይሎች በአልፋሽቃ ትሪያንግል ከፍተኛ ውድመት ደርሶባቸው ትጥቅ እና ቁስለኛ እየጣሉ ሸሽተዋል! በዛሬው የአድርቃይ አውደ ውጊያ ከ500 በላይ የህወሓት ጉጀሌ ታጣዊዎች ከነ መሳሪያቸው ተማርከዋል::

Want your public figure to be the top-listed Public Figure in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Culinary Team

Attire

Website

Address


Addis Ababa