Yes mobile accessory

Yes mobile accessory

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Yes mobile accessory, Addis Ababa.

19/09/2019

አብልቸው ልሙት

“በሰው ልብ ውስጥ ራእይ ብቻ ሊሞላው የሚችል ባዶነት አለ”

በአንዲት ከተማ ውስጥ አንድ ከቤተሰቦቹ ኃብትን የወረሰ ባለጠጋ እንደነበረ ይነገራል፡፡ ይህ ሰው የፈለገውን ያህል ወጪ በፈለገው ጊዜ ለማውጣት የሚያስችለው በቂ ገንዘብ ነበረው፡፡ ጥሩ ቤት፣ ጥሩ መኪናና የተሟላ ሁኔታ ነበረው፡፡ በዚህ ምቹ ሕይወት ብዙ አመታትን ኖሯል፡፡ ሆኖም ኑሮ የሕይወት ድግግሞሽ አዙሪት ሆኖበታል፡፡ ይበላል፣ ይጠጣል፣ ከወዳጆቹ ጋር ይጫወታል፣ እቤቱ ይገባል፣ ይተኛል፣ እንደገና ደግሞ ጠዋት ይነሳል፡፡ የሚቀጥለውም ቀን ያንኑ ይደጋግመዋል፡፡ ከቁጥር በላይ ጓደኞች አሉት፡፡ ሰውየው ይህ የኑሮ ዑደት ሰለቸውና ወደ ግራ መጋባት መጣ፡፡ የስሜት ቀውሱ ሲበዛበት አንድ ቀን፣ “ራሴን አጠፋለሁ” ብሎ ተነሳ፡፡

ራሱን በምን መልክ ሊያጠፋ እንደሚችል ሲያስብ በአካባቢው ያለ አንድ ትልቅ ድልድይ እንዳለ ትዝ አለው፡፡ ወደዚያ ድልድይ ሄዶ ራሱን በመጣል ራሱን ሊያጠፋ መንገድ ጀመረ፡፡ የሚያስፈራ ከፍታ ባለው በዚያ ድልድይ ጫፍ ላይ ቆሞ ራሱን ሊጥል ሲዘጋጅ በድንገት አንድ ድምጽ ሃሳቡን ሰረቀው፡፡ የሚያሳዝን የሕጻን ልጅ ድምጽ ነው፡፡ ዘወር ብሎ ሲመለከት አንድ ህጻን ተመለከተ፡፡ ይህ ሕጻን እርቦት በጣም ከስቷል፡፡ እዚያ ድልድይ ጋር ማን ትቶት እንደሄደ አይታወቅም፡፡ ይህ ራሱን ሊያጠፋ የነበረ ሰው ይህንን ሕጻን ጠጋ ብሎ ሲያየው ከረሃብ የተነሳ መገርጣቱን ተመለከተና በጣም አዘነለት፡፡ በልቡም እንዲህ ሲል አሰበ፣ “ይህንን የከሳ ሕጻን አንድ ቀን እንኳን አብልቸው ልሙት”፡፡ ስለዚህም፣ ራሱን የማጥፋት ቀጠሮውን ለበኋላ አስተላለፈው፡፡

ሕጻኑን አቅፎ አነሳውና ወስዶ ካጠበው፣ በደንብ ካበላውና ካጠጣው በኋላ ራሱን ወደማጥፋት እቅዱ ለመመለስ መንገድ ቀጠለ፡፡ በመንገድ ላይ ሲሄድ ግን የዚህ ሕጻን ሁኔታ ከአይኑ አልለይ አለው፡፡ ደግሞ እንዲህ ሲል አሰበ፣ “እኔ ከሞትኩ በኋላ ይህንን ህጻን ማን ሊያበላው ነው? ገና በአንድ ቀን ምግብ ፊቱ መለስ ብሏል”፡፡ ይህንን ካሰበ በኋላ ስላላስቻለው ህጻኑን ትቶ ወደመጣበት አካባቢ በመመለስ እንደገና ሊያበላው ወሰደው፡፡ ሌላ ቀን ጨመረለት፡፡ እንደገናም ሌላ ቀን አበላው፡፡ እንዲህ እያለ ለጥቂት ቀናት ካበላው በኋላ ልጁን ሲያየው ነፍሱ ተመልሳለች፡፡ አሁን ይሄ ባለጠጋ ተመልሶ ራሱን ስለማጥፋት ማሰብ ሲጀምር የዚህ ልጅ የወደፊት ሕይወት ይታየው ጀመረ፡፡ ይህ ልጅ አድጎ ጥሩ ደረጃ ላይ ሲደርስ ለማየት መናፈቅ ጀመረ፡፡ ለመኖር ጓጓ፤ የሚኖርለት ትርጉም አግኝቷልና፡፡ ከዚያም በኋላ ዳግም ራስን ስለማጥፋት አስቦም አያውቅ፡፡

ሰው የሚከስረው ንግድ አልሳካ ሲለው አይደለም፣ ራእይ ሲያጣ ነው … ሰው ብቸኝነት የሚሰማ ብቻውን ሲሆን አይደለም፣ ራእይ ሲያጣ ነው … ሰው ዝቅተኝነት የሚሰማው ከሌሎች ስላነሰ አይደለም፣ ራእይ ሲያጣ ነው … ሰው ወዲ ወዲያ የሚንከራተተው መንገዱ ሲጠፋው አይደለም፣ ራእይ ሲያጣ ነው … ሰው በማይመለሱ ጥያቄዎች የሚሞላው መልስ ሲያጣ አይደለም፣ ራእይ ሲያጣ ነው … ሰው ስራ የሚያጣው ስራ ሲጠፋ አይደለም፣ ራእይ ሲያጣ ነው …

LIKE & SHARE !

16/09/2019

ሁሉንም ሰው የማስደሰት ሱስ

ከሰዎች ጋር ባለህ ግንኙነት ልትሰራቸው ከምትችላቸው ስህተቶች መካከል ሁሉንም ሰው ለማስደሰት የመሞከር ስህተት አንዱ ነው፡፡ ይህንን ሁኔታ ስህተት ነው ከምንልበት ምክንያት ዋነኛው፣ ምንም ያህል ሰዎችን ሁሉ ለማስደሰት ብንጣጣር እንኳ ሁኔታው የማይቻል በመሆኑ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ሰዎችን ሁሉ ለማስደሰት መሞከርና በማንኛውም ጊዜ በሁሉም ሰው ተቀባይነትን ለማግኘት መሯሯጥ እጅግ አድካሚና ለጉዳት የሚዳርግ በመሆኑ ነው፡፡

በአካባቢው የሚገኙትን ሰዎች ሁሉ ለማስደሰት የሚታገል ሰው የመነሻ ሃሳቡ የተቀባይነትና በሁሉ የመወደድ ፍላጎት ነው፡፡ ከዚህ ነጥብ በመነሳት ከሚያደርጋቸውና ከሚናገራቸው ነገሮች የተነሳ ለጊዜው ሰዎች ሊደሰቱበት ቢችሉም፣ ብዙም ሳይቆይ የመገፋትና የባዶነት ስሜት ይጫጫነዋል፡፡ ምክንያቱም ሁሉም ሰው እርሱን በመቀበልና በሁኔታው በመደሰት እንደማይዘልቅ ቀስ በቀስ ስለሚደርስበት ነው፡፡

ሁሉንም ሰው ለማስደሰት ትታገላለህ? ራስህን መዝነው …

1. ሌሎች ሰዎች ስለተሰማቸው ስሜት አንተ ሃላፊነት ይሰማሃል?

2. አንድ ሰው በአንተ ላይ እንደተበሳጨ ወይም እንዳዘነ ስታውቅ ከልክ ባለፈ ሁኔታ በስሜትህ ላይ ጫና ያስከትልብሃል?

3. ሰዎች እንደፈለጉ ወዲህና ወዲያ የሚያደርጉህ አይነት ሰው እንደሆንክ ይሰማሃል?

4. በአንድ ጉዳይ ላይ ከሌሎች ሰዎች ተቃራኒ ሃሳብ እያለህ እንኳን ተቀባይነት አጣለሁ በሚል ሰበብ ያንን ሃሳብህን ከመናገር ይልቅ መተባበር ይቀልሃል?

5. ብዙ ጊዜ ግልጽ የሆነ ጥፋት እንዳልሰራህ እያወከው እንኳን ይቅርታ የመጠየቅ ዝንባሌ አለህ?

6. አለመግባባት እንዳይፈጠር ለማድረግ ከአቅምህ በላይ ስትታገል ራስህን ታገኘዋለህ?

7. ሰዎች ስሜትህን ሲጎዱት ስለሁኔታው ለሰዎቹ በግልጽ ማውራት ይከብድሃል?

8. ሰዎች አንድን ነገር እንድታደርግላቸው ሲጠይቁህ ማድረግ ባትፈልግም እንኳን ካለብህ የመገደድ ስሜት የተነሳ እሺ የማለት ዝንባሌ አለህ?

9. ሌሎች ሰዎች የሚፈልጉትን ነገር ስታይ ከዚያ በመነሳት እነሱን ለማስደሰት ስትል ሁኔታህን፣ ተግባርህንና ባህሪህን ትለዋውጣለህ?

10. ሰዎች በአንተ ላይ ያላቸው አመለካከት ጥሩ እንዲሆን ብዙ ስትሯሯጥ ራስህን ታገኘዋለህ?

ከላይ ለተጠየቁት አስር ጥያቄዎች ከግማሽ በላይ ለሆኑት “አዎ” የሚል መልስ ከሰጠህ ምናልባት ከመስመር ያለፈ ሌሎች ሰዎች ለማስደሰት የመታገል ዝንባሌ ሊኖርህ ስለሚችል በሚገባ አስብበት፡፡

በነገራች ላይ፣ በእርግጥም ሰዎች ደስ እንዲላቸው ከራሳችን ምቾት ወጥተን ረጅም ርቀት ልንሄድ የሚገባን ጊዜ ሊኖር ይችላል፣ ሆኖም፣ ሰዎችን ለማስደሰት የማደርገው ጥረት የራሴን ሕልውና ወደሚነካ ክልል ውስጥ የሚያስገባኝ ከሆነ ሁኔታውን በሚገባ ላስብበት ይገባኛል፡፡

LIKE & SHARE !

15/09/2019

ኃይል (ስልጣን) እና ራስን መግዛት

“የመጨረሻው ሰው ለማግኘት ሊጣጣር የሚገባው ኃይል (ስልጣን) ራስን የመግዛት ኃይል (ስልጣን) ሊሆን ይገባዋል” - Elie Weisel

“ሌሎችን መግዛት ጥንካሬ ነው፣ ራስን መግዛት ግን እውነተኛ ኃይል ነው” ይላል የሰነበተ የሩቅ ምስራቆች አባባል፡፡ ሰው ሰፊ ቤተሰብ፣ ግዙፍ ድርጅት፣ ከዚያም አልፎ አገር እያስተዳደረ ራሱን በቅጡ ላያስተዳድር ይችላል፡፡ ቤተሰብ ለማስተዳደር ምናልባት በቂ ገንዘብን ማቅረብ ሊጠይቅ ይችላል (ሁኔታውን በዚያ ጎኑ ብቻ ለማየት ከወሰንን)፡፡ ድርጅትና ሃገርን ማስተዳደር ምናልባት እውቀትንና ሹመትን ይጠይቅ ይሆናል፡፡ ራስን ለማስተዳደር ግን ይህ ነው የማይባል ዲሲፕሊን ይጠይቃል፡፡

ባለህ ገንዘብ ሰዎችን ስታስተዳድር በአንተ ላይ የተደገፉትን ሰዎች ለተወሰነ ጊዜ ታኖራቸዋለህ፡፡ በጨዋነትህና በዲሲፕሊንህ ራስህን ስታስተዳድር ግን ለራስህም ሆነ ለእነሱ ለረጅም ጊዜ ትኖራለህ፡፡ ባካበትከው ገንዘብ፣ በቀሰምከው እውቀትም ሆነ በሌሎች ነገሮች አማካኝነት በእጅህ በገባው ኃይልና ስልጣን ተጠቅመህ ትክክለኛውን ነገር ማድረግ የምትችለው፣ በአካባቢህ የሚገኙትን ሰዎችን ባለህ ኃይለኛነት ተጠቅመህ አንቀጥቅጠህ ስለገዛሃቸው ሳይሆን ራስህን በመግዛት ለእውነት ስትኖር ነው፡፡

የአንድ ሕብረተሰብ ውድቀት የሚጀምረው ኃይልና ስልጣንን ከዚህ ከዚያ ብለው እጃቸው ካስገቡ በኋላ የራስን አጀንዳና ለማራመድና ሰውን ለመጨፍለቅ የሚጠቀሙ ሰዎች ሲበራከቱ ነው፡፡ እደ እውነቱ ከሆነ፣ “ኃይል የሚያስፈልግህ ሰዎችን የሚጎዳ ነገር ለማድረግ ስትፈልግ ብቻ ነው፡፡ አለዚያ፣ ማንኛውንም ነገር ለማከናወን ፍቅር በቂ ነው” – Charles Chaplin

LIKE & SHARE !

13/09/2019
10/09/2019

ሚዲያዎቻችን ከ DJ ነት መውጣታቸውን በተግባር ማየት እንፈልጋለን!!!

የሚዲያ ዋነኛ ተልእኮው ለማኅበረሰቡ medium ሆኖ የተረጋገጠ መረጃ የሚያስተላልፍ የሁሉ ሜዳ መሆን ነው:: አለመታደል ሆኖ የእኛ ሀገር ሚድያ እንደ ኮምፓስ ከመጣው ጋር ራሱን የሚያስተካክል መሥመሩን የሳተ ልማታዊ ጋዜጠኝነት (Developmental journalism aka DJ) ቁመና ያለው ነው:: በሌሎች ሀገራት በሕግ ደረጃ በመንግሥት የሚደገፉ የሚድያ ተቁዋማት ላይ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓቱን እንዳያደናቅፉ ጫና በሚደረግበት ዘመን እኛ ጋር ግን ገና ብዙ ይቀራል::
አሁን አሁን ደፈር ብለው የሚሞግቱ ሚዲያዎች ብቅ ብቅ ማለታቸው ተስፋ ሠጪ ነው::

ባሳለፍነው ዓመት በተከታታይ አብያተ ክርስቲያናት ሲቃጠሉ ሚድያዎቻችን ያሳዩት ዝምታ ግን ጮኾ የሚሰማ ዝምታ ነው:: ገበያ ሲቃጠል "እሳቱ በከፊል ቁጥጥር ሥር ውሎአል" እያሉ ተከታታይ ዜና የሚሥሩ እሳት የላሱ ጋዜጠኞች የኢትዮጵያ ሞግዚት ሆና የኖረች ቤተ ክርስቲያን ስትቃጠል ዝም ማለታቸው እና ጉዳዩ ሲነሣም "አንዳንድ የእምነት ተቋማት ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች" የሚሉት ነገር ግራ የሚያጋባ ነበር::

ይህንን የሚያደርጉት ምናልባት ሀገር ላለመበጥበጥና ግጭት ላለማባባስ ሓላፊነት ተሰምቷቸው ከሆነ ተገቢ ነው:: ሆኖም ሰሞኑን በቅድስት ቤተክርስቲያንዋ ፓትርያርክ የተነበበውን ፍጹም ሰላማዊ መግለጫም አልዘገቡም::

ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ሲቃጠልስ እሺ አይዘግቡ: : "አታቃጥሉብኝ" ስትልስ ቤተ ክርስቲያን የማይነገርላት ለምንድን ነው? የሸማቾች ማኅበርን መግለጫ በሰፊው የሚዘግቡ ሚድያዎቻችን የቅዱስ ሲኖዶስን መግለጫ ጨርሶ አለመዘገባቸው ሚድያዎቻችን ሃይማኖታቸው አይፈቅድ ይሆን? ያሰኛል::

ቤተ ክርስቲያን ከሌለች በዚህች ሀገር ብዙ ነገር የለም:: ይህን እውነታ በእምነት የማይመስሏትም በቅን ልብ ይመሰክራሉ:: በዓመት ውስጥ እንደ ወራጅ ወንዝ የሚፈስሰው የውጪ ሀገር ቱሪስት ወደዚህች ሀገር ለመምጣቱ ከዋነኛ ምክንያቶቹ አንድዋ ይህች ቤተ ክርስቲያን ስትሆን በሀገሪቱ tourist season (ሰሙነ ሐዋጽያን) ተብሎ የሚታወቀውም የቤተ ክርስቲያኒቱ ክብረ በዓላት ተከታትለው የሚከበሩበት ከመስቀል እስከ ጥምቀት ያለው ወቅት ነው:: የየትኛውም እምነት ተከታይ የሆኑ ፎቶግራፈሮች የኢትዮጵያን ፎቶ ለዓለም የሚሸጡትና ብዙ ገንዘብ የሚያተርፉት በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ውበት ነው:: ሚድያዎቻችን ይህች ቤተ ክርስቲያን ከሠራቻቸው ባለ ብዙ ቀለም ክስተቶች ውጪ የሚዘግቡት "አሉ ተባሉ" የሚል ወሬ ብቻ ነው:: ሌላው ቀርቶ ዘፋኙም ደራሲውም ተዋናዩም ያለ ቤተ ክርስቲያን መቼት የለውም:: እውን ሙሽራ ጌጥዋን ትረሳለችን? ኢትዮጵያ ግን ጌጥዋን ቤተ ክርስቲያንን ረስታለች::

እርግጥ ነው ሚድያዎቻችን የቤተ ክርስቲያንን በዓላት በዘገቡበት ጊዜም ቤተ ክርስቲያንዋ በራስዋ መንገድ እንድትታይ ፈቅደው ነበር ለማለት ያስቸግራል:: ከሰሞኑ በዓላት ከአሸንዳ ሻደይ ሶለልና ደብረ ታቦር እንጀምር:: አሸንዳ የድንግል ማርያምን ዕርገት የሚመለከት በዓል ነው:: በሚድያ ሰዎች ግን የመነሻዋ የድንግል ማርያም ዕርገት ጉዳይ ቦታ ተሠጥቶት አልተነሣም:: ቤተ ክርስቲያኒቱም እንድትናገር አልተደረገም:: አሸንዳ የሰሜን ኢትዮጵያ ክፍላተ ሀገራት ፋሽንና ጭፈራ ፌስቲቫል ሆኖ አለፈ:: "አሸንዳ ፍቅር ነው አሸንዳ ሰላም ነው" በሚሉ መፈክሮች ተጠናቀቀ:: ቤተ ክርስቲያን ለወለደቻቸው በዓላት ሚድያው ስም አውጥቶ አይዘለቅም::

መስቀል ሲመጣ ደግሞ እዩ:: ምንም መረጃ ሳይኖረው የመስቀል በዓል ዕለት ቴሌቪዥን ሲያይ የሚውል ሰው ንግሥት ዕሌኒ "የጉራጌ ንግሥት" መስቀሉም ተቆፍሮ የወጣው "ከክትፎ ውስጥ" ሊመስለው ይችላል:: የጉራጌ ውብ ባሕል ቢተዋወቅ የሚያኮራ ነው:: ሆኖም መስቀሉን የሚሸፍን ሌላ ተራራ እንዲሆን ግን በመስቀሉ የሚመኩ የጉራጌ ክርስቲያኖችም አይፈልጉም:: ችግሩ የሚበዙት ሚድያዎቻችን ከባለቤትዋ አንደበት እንዲሰማ ዕድል አልሰጡም:: ዕድል ሲሰጡም "የዘንድሮውን መስቀል ካለፈው ምን ይለየዋል" "የበዓሉ እሴቶች ምን ምን ናቸው?" በሚሉ ችኮና መንቻኮ ጥያቄዎች እየገደቡ ነው:: ጥቂት ወርቅ ጋዜጠኞቻችንን አይጨምርም::

ይኼን ሁሉ ያስነሣኝ መስከረም 4 ከደመራ በፊት ለሚለኮሰው ደመራ በአግባቡ ሽፋን ሠጥተው እንዲዘግቡ ለማስታወስ ነው:: ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በመንግሥት ፈቃድ የተሠጠው : በአደባባይ ድምፅዋን የምታሰማበት : በአደባባይ ምህላ የምታደርስበት : አንድነትዋን የምትሰብክበት : የአብያተ ክርስቲያናትን መቃጠል : የምእመናንን መገፋት የምታውጅበት ሰልፍ ነው:: ሰልፉ ከማንኛውም ፖለቲካዊ አላማ የጸዳ የሰማያዊት መንግሥት የቤተ ክርስቲያን ሰልፍ ነው::
ሚድያዎቻችን ሁሉ ይህንን ሀገር አቅፍ ክስተት በሚገባ እንድትዘግቡ እንጠብቃለን::

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ጳጉሜን 4 2011

28/08/2019

ስብሐት ስለ አማርኛ ቋንቋ እንድህ ብሎ ነበር
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
እንግሊዝኛ ምን በአለም ቢነገር ፣ ምን ቢሊዮኖች ቢመኙት
፣እዛው ከቻይና ብር ይበደሩበት እንጂ ፤ፊልም ይስሩበት
እንጂ ፤ እንደኔ ላለው መች እንደ አማርኛ የልብ ያደርሳል?
እስቲ አሁን " አይዞህ "ን በእንግሊዝኛ ልበልህ ብለው
እንዴት ይገለጻል ?
እንግሊዘኛ እንደ ቋንቋ መተሳሰብን መች ይደግፋል ? እስቲ
አሁን ፣ " እኔን " ብሎ ነገር የት አባቱ ያውቃል? እሱን
ተውት ፣ " የት አባቱ ! " ማለትንስ የት አባቱ አውቆት?
ሰው እንቅፋት ሲመታው " እኔን " በሚለው መተሳሰብ
ፋንታ ፣ " ዋች አውት ! አር ዩ ኦ ኬ? የት ያደርሳል ?
" ዋች አውት " አጠጋግተን ስንተረጉመው እንግዲህ ፣
"ምን አባሽ ያደናብርሻል ? " አይደለም?

28/08/2019

ሼር ሼር

"ባለ 5 ብር ኖት ላይ ያለው ሰውዬ ኪታ አጋ
ይባላል። የኢትዮጵያ መንግስትም ሆነ ቤሔራዊ ባንክ
አንድም ብር አልከፈሉለትም። ይህ ሰው አሁን
የምኖሩት ወለጋ ነቀምት ከተማ ውስጥ ስሆን የደሃ
ደሃ የኑሮ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።ምንም ዓይነት የገቢ
ምንጭ ያላቸውም። የዚህ ሰው ፎቶ ብያንስ
በሁላችንም ኪስ ውስጥ ይገኛል። የኢትዮጵያ
ብሄራዊ ባንክ ለዚህ ሰው ተገቢውን ክፍያ ሊፈፅምለት
ይገባል። መልእክቱን ሼር በማድረግ የዜግነት
ግዴታችንን እንወጣ መልእክት ነው።

Want your business to be the top-listed Furniture Store in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address


Addis Ababa
251911671339