Ethio plus

Ethio plus

Share

በኢትዮ-plus ገፃችን ሀገራዊ፣ ማህበረሰቧዊ፣ ፖለቲካዊ እንዲሁም አያሌ ሀሳቦችን እያነሳን እንነጋገራለን !!

26/05/2026

ማን ነበረ? የማዉቀዉ መሰለኝ 🤔?

Photos from Ethio plus's post 24/05/2026

#ቆርቤም ኳስ ማየቴን አልተዉም!!
ታማኝ የአርሰናል ደጋፊ "እማማ አርሰናል"
አርሰናል ሲሸነፍ እራትም አልበላም ሰዉም ማናገር አልወድም ።
ሲያሸንፍ ግን "ያኔ ነዉ እኛን ማየት"

ወኔያቸው ደስ ይላል ።

Photos from Ethio plus's post 24/05/2026

እናንተ አከባቢ ድባቡ እንዴት ነዉ?

Photos from Ethio plus's post 23/05/2026

#በውቀቱ ስዩምን አንድ ሰዉ አቀባበል አላደረገለትም።
በስፔን በተደረገው የዓለም የግጥም ፌስቲቫል ከተመረጡ ጥቂት የዓለማችን ገጣምያን አንዱ የሆነው የትውልዴ ጀግና-በውቀቱ ስዩም፤ አምስት ግጥሞችን አቅርቦና አድናቆትን ተችሮ ወደ ሀገሩ ሲገባ እንኳን ደህና መጣህ! "እንኳን ሀገርህን አስጠራህ!"ብሎ የተቀበለው አንድም ሰው የለም። የባህል፣ የስነ ጽሁፍ፣ የማስታወቂያ...ሹማምንት ተራ ቲክቶከር አጅበው እያበዱ ነው።

ጀግናችን በውቄ! እውቀት የሚከበርበት ስርዓት ሲመጣ ሐውልት እንተክልልሃለን።

23/05/2026

ለፈጣንና ለታማኝ መረጃዎች ቤተሰብ ይሁኑ
Ethioplus (ኢትዮ-plus) 👇👇👇👇👇

🌐 ⓨ YouTube
https://youtube.com/?si=ZtvIXxD10Y6-x_bs

📍ⓣ Telegram https://t.me/ethioplus2

📲 ⓕ Facebook https://www.facebook.com/profile.php?id=100064007739218

💥ⓣ TikTok https://vm.tiktok.com/ZMSnRUehY/

Photos from Ethio plus's post 23/05/2026

በአዲስ አበባ ከተማ በከፍተኛ ሁኔታ የአርሰናል ማልያ እጥረት ተከሰተ። 3500 እስከ 15,000 ብር ድረስ እየተሸጠ ነዉ ። የነገው ድባብ ገና ከአሁኑ ጀምሯል

እናንተ ጋር የአርሰናል ማልያ ስንት እየተሸጠ ነዉ?

22/05/2026

ይህ ዉብ ቦታ የት ነው!?

22/05/2026

ሀገር ቤት እያለ በከፍተኛ ትምህርት ተመርቆ ወጣቶችን በደስታና በታማኝነት ሲያስተምር የነበረው ጎበዝ መምህር ቀፀላ፣ የተሻለ ኑሮን ፍለጋ እና ቤተሰቦቹን ለመደገፍ በዲቪ ሎተሪ አማካኝነት ወደ አሜሪካ ያቀናል። ይሁን እንጂ ብዙዎች እንደሚያልሙት የአሜሪካ ህይወት ቀላልና አልጋ በአልጋ አልሆነለትም፤ ይልቁንም ያልታሰቡ ፈተናዎች ቀስ በቀስ ህይወቱን ሙሉ በሙሉ ወደ ሌላ አቅጣጫ ቀየሩት። የቋንቋ አለመስማማት፣ በድንገት የገጠመው የቆዳ ጤና እክል እና ተደራራቢ የኑሮ ውጣ ውረዶች ስራ መስራት እንዳይችል ክፉኛ አዳከሙት።
ይህንን ተከትሎ የቤት ኪራይ መክፈል ያቃተውና የነበረችውን መኪና በዕዳ የተነጠቀው ወጣቱ ቀፀላ፣ ላለፉት ሁለት ዓመታት መኖሪያውን ለማድረግ የተገደደው በቨርጂኒያ ግዛት ውስጥ በሚገኝ አንድ ጥቅጥቅ ያለ አስፈሪ ጫካ ውስጥ ነበር። በዚያ በሚያስፈራ ምድረ በዳ፣ በሚቆራርጥ የክረምት ብርድ፣ በበረዶና በከባድ ዝናብ ውስጥ በፌስታልና በሳር በተሰሩ መጠለያዎች ብቻ ተጠልሎ ሁለት ሙሉ ዓመታትን ማሳለፉን መስማት በእጅጉ አንጀት ይበላል። ችግርና ብቸኝነት ሲበዛበት የሰው ፊት መጋፈጥ ከብዶት፣ ወደ ኋላ መመለሻ መንገዱም ጠፍቶበት በዚህ መራራ ህይወት ውስጥ ለመቆየት ተገዷል።
ሆኖም ግን እኛ ኢትዮጵያውያን በችግርና በመከራ ጊዜ ወገናችንን ጥለን የማንወጣ፣ ሁልጊዜም በመተሳሰብና ለሰው በመድረስ የምንታወቅ ኩሩ ህዝቦች ነን። ዛሬ ቀፀላ ከዚህ ከገባበት የጨለማና የብርድ ህይወት ወጥቶ እንደገና የሰው ፊት እንዲያይ፣ ሙቀት ባለው መጠለያ ውስጥ እንዲያድርና ህክምና አግኝቶ ህይወቱን በአዲስ ተስፋ እንዲጀምር የሁላችንንም የድረሱልኝ ጥሪ እየጠየቀ ይገኛል። እሱ የሚፈልገው ትልቅ ነገር ሳይሆን ህክምና አግኝቶ፣ አነስተኛ መኪና ገዝቶ በዴሊቨሪ ስራ ራሱን መቻል ብቻ ነው። ስለዚህ የሰው ልጅ ክቡር ነውና ይህንን ወንድማችንን ከዚህ የጫካ ስቃይ ለመታደግ አቅማችን በፈቀደው መጠን የሞራልና የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ከጎኑ እንድንቆም ጥሪው ቀርቧል፤ ብዙዎችም ለዚህ በጎ ተግባር እየተረባረቡ ይገኛሉ።

Photos from Ethio plus's post 22/05/2026

የአርቲስት ሰለሞን ቦጋለ ልጅ ቀለበት አሰረች።

21/05/2026

#960 ጊዜ የመንጃ ፍቃድ ፈተና የወደቀችዉ ሴት
“እጅ አትስጥ… ምናልባት ቀጣዩ ሙከራህ ሕይወትህን ሊቀይር ይችላል።”

የ69 ዓመቷ የደቡብ ኮሪያዊቷ ቻ ሳ-ሱን የመኪና ፈተናዋን ለማለፍ 960 ጊዜ ሞክራለች።
አዎ… 960 ጊዜ!

ብዙ ሰዎች ከ2 ወይም 3 ጊዜ ውድቀት በኋላ “አልችልም” ብለው ይቆማሉ።
እሷ ግን አልተቆመችም።
ይሉኝታ፣ ድካም፣ ሰዎች የሚሰጡት አስተያየት… ምንም አላቆማትም።

በየቀኑ እየተመለሰች ሞከረች።
ደጋግማ ወደቀች።
ነገር ግን ዳግም ተነሳች።

በመጨረሻም… አለፈች። ❤️

ዓለም ሁሉ ታሪኳን ተናገረ።
ምክንያቱም ሰዎችን ያስደነቀው ፈተናዋን ማለፏ ብቻ አልነበረም፤
960 ጊዜ ከወደቀች በኋላም እንኳን ተስፋ አለመቁረጧ ነበር።

ይህ ታሪክ አንድ ትልቅ መልእክት አለው፦

ስኬት ፈጣን መሆን አይደለም።
ብልህ መሆንም ብቻ አይደለም።
እውነተኛው ስኬት ምንም ያህል ብትወድቅ ዳግም መነሳት ነው።

ዛሬ ሕይወት እያስቸገረህ ከሆነ…
ሰዎች እየሳቁብህ ከሆነ…
ወይም ሕልምህ ሩቅ እየመሰለህ ከሆነ…

ተስፋ አትቁረጥ ።

ምናልባት ቀጣዩ ሙከራህ
የሕይወትህን ትልቅ ስኬት ሊያመጣ ይችላል። ✨

Photos from Ethio plus's post 20/05/2026

ታዋቂው የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪ ዲላን አዲስ አበባ ገባ

በማህበራዊ ሚዲያ ይዘቶቹ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ተሰሚነትን ያተረፈው ዲላን (ዲላን ፔጅ ) አዲስ አበባ ገብቷል።

ዲላን በቲክቶክ ብቻ ከ19 ነጥብ 3 ሚሊዮን በላይ ተከታዮች ያሉት ሲሆን፣ አዲስ አበባ መግባቱን አስመልክቶ ባስተላለፈዉ መልእክት በርካታ ቀናትን የሚወስደውን ታላቁን ጉዞዬን፣ በቅኝ ግዛት ባልተገዛችዉ ሀገር ኢትዮጵያ ጀምሬያለሁ ብሏል።

ግርማ ሞገስ ያለው መልክዓ ምድር፣ በርካታ የታሪክ እና የሃይማኖት እሴቶች ያሏት ኢትዮጵያ የሰው ልጅ እና የቡና መገኛ መሆኗን ተናግሯል፡፡

ተፅዕኖ ፈጣሪዉ ዲላን ለተከታዮቹ፤ “ከምነግራችሁ ይልቅ ባሳያችሁ ይሻላል” በማለት ቀጠሮ ይዟል።

Want your business to be the top-listed Business in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address


4 Kilo
Addis Ababa