Hoha Multimedia and Promotion

Hoha Multimedia and Promotion

Share

የሚዲያና የማስታወቂያ ድርጅት

31/05/2026

ምርጫው ነገ ነው። እርስዎም ድምፅዎን ሊሰጡ ይሄዳሉ። ነገር ግን ለምርጫ ሲሄዱ ወደ ምርጫ ጣቢያ እንዳይገቡ የሚከለከሉ ነገሮች አሉ። ለጥንቃቄ እንዲረዳዎ እነዚህን ነገሮች እናስታውስዎ:-

1. በራሪ ወረቀት፣ ፖስተር እና በሌሎች አጭር ጽሑፍ መልክ የተዘጋጁ የምርጫ ቅስቀሳ ሰነዶችን ይዘው ወደ ምርጫ ጣቢያው መግባት አይችሉም፡፡

2. የጦር መሳሪያ ወይም እንደጩቤና ሴንጢ የመሳሰሉ ስለትነት ያላቸውን ወይም እንደየአካባቢው ሁኔታ ለሀይል መጠቀሚያነት የሚውሉ እንደዱላ፣ አለንጋ ፣ ቁራጭ እንጨት ወይም ብረት ወይም ሌላ ማንኛውንም ተቀጣጣይ ወይም የሚፈነዳ ጠጣር ወይም ፈሳሽ ነገር ይዘው ወደ ምርጫ
ጣቢያ መግባት የለብዎትም።

3. የተከለከሉ ነገሮችን ወደምርጫ ጣቢያ ይዘው ከመጡ የምርጫ ጣቢያው የሰልፍ አስከባሪ በሚሰጥዎት መመሪያ መሰረት በአደራ አስቀምጠው መግባት አለብዎት።

30/05/2026

የሊቀ ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ረድኤትና ምልጃ አይለየን🙏

ከአንገቱ የወጣው ደም እሳት ሆኖ አጥፍቷቸዋል

በ277 ዓ.ም ጥር 20 ፍልስጤም ልዩ ስሟ “ልዳ” የተወለደው ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ በዓለም አቀፍ ደረጃ በሁሉም ክርስቲያኖች ዘንድ ተቀባይነት ካላቸው ሰማዕታት ቀዳሚው ነው፡፡ የአባቱን ሞት ተከትሎ ከሌላ መኳንንት ጋር ያደገው ጊዮርጊስ የክርስትና ጠላት ከሆነው ዱዲያኖስና ከ70ው ነገስታት ጋር የተጋፈጠው የአባቱን ምስፍና እንዲሰጡት ሊጠይቅ በሔደበት ክርስቲያኖችና ክርስትና ሲገፉ በማየቱ ነው፡፡ ጊዮርጊስ ማለት “ብሩህ ኮከብ፣ ፀሐይ” ሲሆን ተጋድሎውን ሲጀምር የሃያ ዓመት ወጣት ነበር፡፡ በቤሩትም የሚመለክና ሴት ልጆቻቸውን የሚገብሩለትን ደራጎን ገድሎ ሕዝቡን ወደ ክርስትና አስገባቸው፡፡ በነገሥታቱ ፊትም የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክነት መሰከረ፡፡

ምንም እንኳን ንጉሡ ቅዱስ ጊዮርጊስ የመሣፍንት ወገን መሆኑን እንደ መግቢያ በመጠቀም ሊያባብለው ቢሞክርም “አምላኬ ኢየሱስ ክርስቶስን አልክድም” ብሎ በእምነቱ ጸና፡፡ ዱድያኖስም ብዙ አሠቃቂ መከራዎችን ያደርስበት ጀመር፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ግን ያጸናው ቍስሉንም ያድነው ነበር፡፡ ሦስት ጊዜ እንደሚሞት እርሱም እንደሚያስነሣው በአራተኛውም የሰማዕትነትን አክሊል እንደሚቀበል ነገረው፡፡ ቃል ኪዳንም ገባለት፤ ለሰባት ዓመትም በጽኑዕ መከራና በሥቃይም እንዲሁም በተጋድሎ እንደሚኖር በዚያም ስሙ በዓለሙ ሁሉ የተገለጠ እንደሚሆን መላእክትም እንደሚያገለግሉትም ነገረው፡፡ ንጉሥ ዱድያኖስም ቅዱስ ጊዮርጊስ ትእዛዙን ባለመቀበሉ ተቆጥቶ አትናስዮስ የሚባል ታላቅ መሠሪ አስጠርቶ በፍጥነት የሚገድል መርዝ ቀምሞ በጽዋ መልቶ አጠጣው፡፡

መርዙ ግን ምንም ጉዳት ሳይደርስበት ቀረ፡፡ ያ መሠርይም ይህን ድንቅ ሥራ ሲያይ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አምኖ በሰማዕትነት ሞተ፡፡ ቁጥራቸውም ሠላሳ ሺህ ሰባት መቶ የሚሆኑ ሌሎች ሰዎች ከእርሱ ጋር በሰማዕትነት ሞተው የሕይወትን አክሊል ተቀዳጁ፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስም ለሰባት ዓመታት በቅድስና ሲጋደል ቆይቶ፣ ታላቅ የምህረት ቃል ኪዳን ተቀብሎ ሚያዝያ 23 ቀን በሰይፍ አንገቱን ተመቶ ሲሞት ከአንገቱ የወጣው ደም እሳት ሆኖ ሰባውን ነገስታት አጥፍቷቸዋል፡፡ ስለክርሳቶስ ፍቅር ዓለምን የናቁ ገዳማውያን ይህን አብነት አድርገው የዓለም ደስታቸውን ስለክርስቶስ ፍቅር ትተዋልና በረከታቸው ብዙ ነው፡፡ ገዳማቸውን ስንደግፍ በዓታቸውን ስናጸና ከበረከታቸው እንሳተፋለን፡፡

ድጋፍ ለማድረግ፦ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

Photos from Hoha Multimedia and Promotion's post 29/05/2026

ቁሳቁስ በማጓጓዝ በኩል ያጋጠመ እክል የለም - ምርጫ ቦርድ
***************

በምርጫ ቁሳቁስ ስርጭት ሂደት እስካሁን እክል እንደገጠመው ሪፖርት ያደረገ የቦርዱ ቡድን አለመኖሩን ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል።

የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ፣ የመኪና ብልሽት እና የመንገድ አለመመቸትን ጨምሮ በተለያዩ ጥቃቅን ምክንያቶች የዘገየ ካልሆነ በስተቀር፣ በየትኛውም የምርጫ ክልል በፀጥታ ችግር ምክንያት የተስተጓጎለ የቁሳቁስ ማጓጓዝ እክል እንዳላጋጠመ ገልጸዋል።

ቦርዱ ከመራጮች ምዝገባ ጀምሮ የመጓጓዣ መዘግየቶችን ለመፍታት በቂ ዝግጅት አድርጎ እርምጃዎችን እየወሰደ መሆኑን እና አሁን ላይ ሁሉም ነገር በትክክል እየሄደ እንደሆነ ሰብሳቢዋ አረጋግጠዋል።

ኢቢሲ

27/05/2026

ቅዱስ ገብርኤል ከክፉ ነገር ሁሉ ይከልለን፤ የልባችንን መልካም መሻትም ይሙላልን🙏

የራማው ልዑል፣ መጋቤ ሐዲስ ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ገብርኤል በሉቃስ 1÷19 “እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ” ብሎ መገኛ ስፍራውንና እግዚአብሔር የሰጠውን ክብር በይፋ ያወጀ መልአክ ነው፡፡ ገብርኤል ማለት የእግዚአብሔር ኃይል ነው ማለት ነው። ቅዱስ ገብርኤል ድንቅ መልእክቶችን በማድረስና የተረበሹትን በማረጋጋት ይታወቃል፡፡ ነገደ መላክት በሰማይ አምላካቸው ተሰውሮባቸው ማን ፈጠረን ብለው በተጨነቁ ጊዜ ያረጋጋቸው እርሱ ነው፡፡ በክብሩ ከፍ ብሎ በመፈጠሩ መላዕክትን እኔ ነኝ የፈጠርኳችሁ ብሎ ሊያስት የሞከረውን የሀሰት አባት የያኔው (ሳጥናኤል) ጠላት ዲያብሎስ ተከራክሮ የረታው እርሱ ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡

ቅዱስ ገብርኤል ሆይ መረጋጋትን ስጠን አሜን 🙌

27/05/2026

😭😭😭
በጉጂ ዞን ኦዶ ሻኪሶ ወረዳ ሳዊና መንደር ተጥሎ ይተገኘው ህጻን...💔

የዚን ያህል ግን እናት በልጇ ትጨክናለች..? ምንም ችግር ቢደርስባት ምንስ ብትሆን ምናለ እንደው እርዱኝ ማሳደግ አቃተኝ ብትል?

ለአውሬ ሲሳይ እንዲሆን እኮ ነው ጫካ ውስጥ ት ታው የሄደችው።

ልብ ይሰብራል የዚ ዘመን ነገረስ !

Via Tezu Habeshawit

Photos from Hoha Multimedia and Promotion's post 27/05/2026

በአሶሳ ከተማ 1 ሺህ 447ኛው የኢድ አል አደሃ አረፋ በዓል በተለያዩ ኃይማኖታዊ ስርዓቶች ተከብሯል።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት ፕሬዚዳንት ሼህ ኢብራሂም ሲራጅ በ1 ሺህ 447ኛው የኢድ አል አደሃ አረፋ በዓል አከባበር ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ህዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከብር የቀደመ አብሮነቱን እና አንድነቱን በሚያጠናክር መልኩ መሆን እንዳለበት ገልጸዋል።

በዓሉንም ደጋፊ የሌላቸው ወገኖች በመጠየቅና ኃይማኖታዊ አስተምህሮቱ በሚያዘው መሰረት ማክበር እንደሚገባም ነው ሼህ ኢብራሂም ሲራጅ መልዕክታቸውን ያስተላለፉት።

የበዓሉ ታዳሚዎች በበኩላቸው፣ ህዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከብር አንድነቱን በማጠናከርና በመደጋገፍ ማክበር እንዳለበት ተናግረዋል ።

በዓሉንም ያለው ለሌለው በማካፈል እና እርስ በርስ በመጠያየቅ ማክበር እንደሚገባ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

1ሺህ 447ኛው የኢድ አል አደሃ አረፋ በዓል በሶላትና በተለያዩ ሀይማኖታዊ አስተምህሮ በድምቀት ተከብሯል፡፡

BGM

Photos from Hoha Multimedia and Promotion's post 24/05/2026

ጥብቅ ማሳሰቢያ
ለስፖርት ደጋፊዎችና የኳስ አፍቃሪያን ከአሶሳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የተላለፈ የጥንቃቄ መልዕክት ፥

ዛሬ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የመጨረሻ ጨዋታ የሚከናወን ሲሆን አሸናፊው የዋንጫ ርክክብ ሥነ-ሥርዓት የሚረከበው ክለብ ከአንድ ጨዋታ በፊት የታወቀ መሆኑ ይታወቃል ።

ስለሆነም ከቀናት በፊት የአንድ ክለብ ደጋፊዎች ከጨዋታው በፊት የደስታ ስሜት ለመግለጽ ሲባል የተለያዩ ዝግጅቶችን እያደረጉና ፕሮግራም በሆቴሎች ፤ በDSTV ቦታዎች ፤ በተሽከርካሪዎች እና በሌሎች ቦታዎች አካባቢዎች የአርሰናል ማለያ በመለጠፍ አላስፈላጊ ሁኔታዎች በከተማዋ ላይ እየተስተዋለ ይገኛል ብሏል ፖሊስ መምሪያው ።

በዚህም ዛሬ ከምሽቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ በሚደረጉ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የመዝጊያ ጨዋታ ይካሄዳሉ ።

የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ዛሬ በሚደረገው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መዝጊያ ጨዋታ በተመለከተ ሁሉም የስፖርት ጨዋነትን በተላበሰ መልኩ እንዲመለከት ጠይቋል ።

በዚህም መሠረት ፦
📢 ደጋፊዎች የአሸናፊነት ደስታቸውን በሚገልጹበት ወቅት አንዳንድ ስነ-ምግባር የጎደላቸው ግለሰቦች በሌሎች ደጋፊዎች ላይ ዛቻና ማስፈራሪያ እንዳያደርሱ ፤

📢 ደጋፊው ደስታውን ሲገልጽ የስፖርታዊ ጨዋነትን መርህ በተከተለ፣ በሰለጠነ እና በልክ መሆን እንዳለበት

📢 የሌላ ክለብ ደጋፊዎችን ስብዕና እና ክብር የሚነኩ ማናቸውም አይነት ትንኮሳዎች ፈጽሞ ተቀባይነት የሌላቸው መሆኑን

📢 ለደስታ መግለጫ ተብሎ በማንኛውም ተሽከርካሪ ሰልፍ መፍጠር ወይም መንገድ መዝጋት ፤ሪችት መተኮስ በጥብቅ የተከለከለ መሆኑ የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ አሳስቧል ።

በመጨረሻም ይህን መመሪያ ጥሰው በሚገኙ እና የከተማዋን ሰላምና ጸጥታ በሚያደፈርሱ አካላት ላይ ፖሊስ ህጋዊ እርምጃ በመውሰድ ህግ የማስከበር ስራውን በቁርጠኝነት የሚያከናውን መሆኑን እያሳሰበ፣ ህብረተሰቡና የስፖርት አፍቃሪያን ወንጀልን በጋራ በመከላከል ረገድ የተለመደውን ትብብር እንዲያደርግ ጥሪውን አቅርቧል።
የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ

23/05/2026
20/05/2026

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Tilahun Berhanu, Destaa Kateeloo Farda Bixalame, Zerfe Alemu, Kedir Husein Eleo, ፍቅር ከባዱ, Full Day

Photos from Hoha Multimedia and Promotion's post 19/05/2026

የምስራች የጠፉት ልጆች ተገኝተዋል!

ትንሽ ዘግየት ያልኩት ከኔት ወርክ ውጭ ስለነበርኩ ይቅርታ እየጠየኩ በማፈላለግ የየራሳችሁ አስተዋፆ ያደረጋችሁ ሁሉ በቤተሰቦቻቸው ስም አመሰግናለሁ።
ልጆቹ አምባ 5 አካባቢ መገኘታቸውን እወቁልን ከልብ እናመሰግናለን።
via getaneh

Want your public figure to be the top-listed Public Figure in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address


Addis Ababa