Infix Computer Technology

Infix Computer Technology

Share

ልታውቋቸው የሚገቡ የኮምፒውተር ትምህርቶችን ያገኛሉ

24/08/2022

ደክመው ያፈሩትን የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ እንደራሱ ሆኖ የሚቆጣጠርሎት ሰው አጥተዋል?
እንግዲያውስ ኢንፊክስ ቴክኖሎጂ ለድርጅቶች ጠቅላላ የቴክኖሎጂ ድጋፍ (it support) በመስጠት ላይ ይገኛል።
ማንኛውንም አይነት የድርጅቶን ኮምፒውተር ፣ ስካነር ፣ ፕሪንተር፣ፎቶኮፒ፣ዩፒኤስ እና ኔትዎርክ እንዲሁም ደግሞ የደህንነት ካሜራዎትን በቋሚነት ያሉበት ድረስ በመምጣት #እንከታተልሎታለን ከተበላሸም ነፃ በሚባል ዋጋ እንጠግንልዎታለን
ለበለጠ መረጃ
በ +251954834439

Infix Computer Technology ልታውቋቸው የሚገቡ የኮምፒውተር ትምህርቶችን ያገኛሉ

25/06/2022
29/04/2022

ከ Facebook ላይ እንዴት ቪድዮ ዳውንሎድ ማድረግ ይቻላል?

🚩 ፌስቡክ ላይ የምንፈልገው ዓይነት ቪድዮ እናገኝና ቪድዮውን ዳውንሎድ ማድረግ እንቸገራለን።
ቀጥሎ ፌስቡክ ላይ ማንኛውም ቪድዮ ወደ ሞባይል ስልካችሁ ወይም ኮምፒዩተራችሁ ላይ እንዴት ዳውንሎድ ማድረግ እንደምትችሉ እናያለን።

1ኛ፦ ፌስቡካችሁን ትከፍቱና ዳውንሎድ ማድረግ የፈለጋችሁትን ቪድዮ ያለበት ፖስት ከላይ በቀኝ በኩል (...) ምልክትን ክሊክ ማድረግ....

2ኛ፦ ስትነኩት "Copy Link" የሚል ይመጣል እሱን ክሊክ ማድረግ

3ኛ፦ አሁን ከፌስቡክ ትወጡና Opera Mini ብራውዘር ትገባላቹ

4ኛ፦ ብራውዘሩን ከከፈታችሁ በኋላ አድራሻ መፃፍያው ላይ ከላይ ኮፒ ያደረጋችሁትን Paste አድርጉት። Paste ስታደርጉት የፈለጋችሁት ቪድዮ ይመጣል።

5ኛ፦ ዳውንሎድ ልታረጉ የፈለጋቹት Video ይመጣል ቪዲዮውን ስትነኩት "Download Video" የሚል ይመጣል በቃ ማዘዠ ብቻ ነው።

6ኛ፦ ዳውንሎድ ያደረግነውን ቪድዮ ለማግኘት 👉Phone Storage 👉 Downloads ውስጥ ደቅ ብሎ ታገኙታላቹ!

27/04/2022

Get Online ICT Help any where in the world.
*Download and install by Google anydesk.
*Sms me code on anydesk withCall.
*Also text the problem you face.
*After fixing you can Pay with any method.
*For more information callCall.
*24/7 Available call any time.
*N.B:- First connect you device with internet. Inorder to get online help.
For more information
call us +251954834439

25/04/2022

ላፕቶፕ ስንገዛ ማወቅ እና ማየት ያለብን ወሳኝ ነጥቦች
1 የመሳሪያ ስርዓት (Operating system)
2 የስክሪን መጠን (Screen Size)
3 ሲፒዩ(CPU)
4 ራም(RAM)
5 የሃርድ ድራይቭ አይነት (Hard Drive Type)
6 የምስል ጥራት (Image Quality)
7 የባትሪ ቆይታ (Battery Life)
8 ብራንድ (Brand)
ኮርi3 ኮርi5 ኮርi7 ምንድናቸው?
በሃገራችን ገበያ አሁን አሁን በርከት ያሉ የላፕቶፕ እና
የኮምፒውተር ሱቆች እየታዩ ይገኛሉ፡፡ለገቢያም የተለያዩ
የላፕቶፕ አይነቶች.በተለያየ ይዘት ይገኛሉ፡፡ እንዚህን
የተለያየ ይዘት ያላቸውን የላፕቶፕ አይነቶች ለመግዛት በዋናነት መታየት ያለበትን ከዚህ በታች በዝርዝር ተቀምጠዋል፡፡
1. የመሳሪያ ስርዓት (platform) Windows, Mac
and Linux ለአጠቃቀም ምቹ እንደሆነ የሚነገርለት Windows የብዙ ሰዎች ምርጫ ነው፡፡ቀላል፣ ምቹ እና ተለዋዋጭ ነው፤ በዋጋም ደረጃ ጥሩ የሚባል ነው፡፡
ማክ( Mac) የአፕል ድርጅት ምርት ሲሆን ለዲዛይን ተመራጭ የሆነ ፕላትፎረም ነው፡፡ለደህንነትም ከWindows እንደሚሻል ይነገርለታል፡፡
2. የስክሪን መጠን ወደ ግዢ ከመግባታችን በፊት የምንገዛው ላፕቶፕ ከቦታ ወደ ቦታ ይዘን ለመንቀሳቀስ (portable) ምቹ መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡ ላፕቶፖች እንደየስክሪን መጠናቸው የተከፋፈሉ
ናቸው፡፡
• 11 to 12 inches(27.94cm-30.48cm) ፡በጣም
ቀጭን እና ቀላሉ የስክሪን ሳይዝ ነው፡፡ ከ1.1ኪሎ እስከ1.5ኪሎ ይመዝናል፡፡
• 13 to 14 inches (33.02cm- 35.56cm) ፡ይህ
የስክርን ሳይዝ ያለቸው ላፕቶፖች በጣም ተመጣጣኝ portability ያላቸው እና በላፕቶፕ ተጠቃሚዎች ተመራጭ ናቸው፡፡
• 15 inches(38.1cm): እውቁ የላፕቶፕ የስክሪን
ሳይዝ ሲሆን፤ተለቅ ያለ የስክሪን ሳይዝ ከፈለጉ ይህንን እንዲገዙ እንመክራለን ፡፡
• 17 to 18 inches (43.18cm- 45.72cm)፡
ላፕቶፖን ይዘው የማይንቀሳቀሱ ከሆነ እና ትልቅ የስክሪን ሳይዝ ከፈለጉ ይህንን ይግዙ፡፡ ለጌመሮች እና ትልልቅ የሶፈተዌር ዲዛይን ለሚያደርጉ ሰዎች ተመራጭ የሆነ የላፕቶፕ አይነት ነው፡፡
3. ሲፒዩ(CPU)
የኮምፒዉተር አይምሮ በመባል የሚታወቀው ሲፒዩ
(CPU), ላፕቶፕ ለመግዛት ሁላችንም ማየት ያለብን ዝርዝር ነው፡፡
• AMD A series or Intel Core i3 / i5: በየቀኑ
ለምንጠቀማቸው ስራዎች የሚሆኑ የሲፒዩ አይነቶች
ሲሆኑ Core i5 ለሶፈትዌር ዴቨሎፕመንት እና አነስተኛ የዲዛይን ስራዎችን ለምሳሌ እንደ Photoshop, Archicad, AutoCadን የመሳሰሉ በጥሩ ሁኔታ እንድንሰራ ይጠቅሙናል፡፡ በተጨማሪም
ግራፊክስ ካርድ ያለውና የሌለው በማለትም ይለያያሉ፡፡ግራፊክስ ካርድ ያለቸው የተሻለ የዲዛይን እና አኒሜሽን ስራዎችን ያከናውኑልናል፡፡ በዋጋውም ተመጣጣኝ ነው፡፡
• Intel Core i7፡ በጣም አስደማሚ የጌም እና
የዲዛይን እንዲሁም ልዩ የሆኑ የኮምፒውተር ስራችን ለምሳሌ አንደ ሜትሮሎጂ፤ውስብስብ ስሌቶችን እንድንሰራ የሚረዳን የላፐቶፕ አይነት ነው፡፡
4 .ራም(RAM): ለፍጥነት 4ጂቢ እና ከዛ በላይ የሆነ
RAM እንዲጠቀሙ እንመክሮታለን፡፡ ዋጋቸው አነስ ያሉ
ላፕቶፖች በ2ጂቢ ይመጣሉ፡፡ የዲዛይን ስራዎችን እና የሶፈትዌር ዴቨሎፕመንት ስራዎችን ለመስራት 6ጂቢ ራም እና ከዚያ በላይ ያለው ላፕቶፕ ቢገዙ ይመረጣል፡፡
5.የሃርድ ድራይቭ አይነት፡ ሁለት አይነት የሃርድ ድራይቭ
አይነቶች ያሉ( HDDrive እና SSDrive) ሲሆን
በሃገራችን ያልተለመደው SSDrive ከHDDrive የተሻለ የፍጥነት አቅም እና ድራይቩ ላይ ያለውን ዳታ በፍጥነት መድረስ እና መገልበጥ (copy)ያስችለናል፡፡
6 .የምስል ጥራት፡ የተሻለ ጥራት የተሻለ ምስል
እንድናገኝ ይረዳናል፡፡ 1366 x 768 ጥሩ የሚባል የምስል ጥራት ያለው ሲሆን ከዚህ የተሻለ ወጪ በማውጣት 1920 x 1080 የተሻለ ምስል ማግኘት እንችላለን፡፡Full HD 1080P በመባልም ይታወቃል፡፡
7 .የባትሪ ቆይታ፡ አብዛኛው ሃገር ውስጥ የሚገቡት
የላፕቶፕ አይነቶች 4 ሰዓታት የሚቆዩ ሲሆን ከ6-8 ሰዓታትም የሚቆዩ ኦርጅናል ላፕቶፖች አሉ፡፡
8 . ብራንድ፡ የተላያዩ የላፕቶፕ ብራንዶጭ ባሉበት ገቢያ
የተኛውን መግዛት እንዳለብን አስቀድመን ማወቅ አለብን፡፡
• ከጥራት አኳያ ደግሞ APPLEን የሚደርስ የለም፡፡ Toshiba, HP, DELL, lenovo የተሻሉ ብራንዶች ናቸው
እንዲሁም ከዚህ በፊት የለቀቅኳቸውን ቪዲዮዎችን ብትከታተሉ ምርጥ እውቀትን ልታገኙ ትችላላችሁ
አሁንም የቴሌግራምና የYouTube ቻናሌን Subscribe በማድረግ ድጋፋችሁን አሳዩኝ።
✅✅✅ #ያወቁትን ማሳወቅ ብልህነት ነው!✅✅✅

16/03/2022

ደክመው ያፈሩትን የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ እንደራሱ ሆኖ የሚቆጣጠርሎት ሰው አጥተዋል?
እንግዲያውስ ኢንፊክስ ቴክኖሎጂ ለድርጅቶች ጠቅላላ የቴክኖሎጂ ድጋፍ (it support) በመስጠት ላይ ይገኛል።😊
ማንኛውንም አይነት የድርጅቶን ኮምፒውተር ፣ ስካነር ፣ ፕሪንተር እና ኔትዎርክ እንዲሁም ደግሞ የደህንነት ካሜራዎትን በቋሚነት ያሉበት ድረስ በመምጣት #እንከታተልሎታለን ከተበላሸም እንጠግናለን።

በ0954834439አሊያም 0994637327

ኮምፒዩተር ምንድነው?

ኮምፒዩተር የኤሌትሮኒክስ መሳርያ ሲሆን ዲጂታል የሆኑ መረጃዎችን በተቀበለው ትእዛዝ መሰረት የሚያስቀምጥና የሚያቀነባበር እንዲሁም ሌሎችህ ስራዎችን በፍጥነት የሚያከናውን መሳሪያ ነው

ታዲያ ኮምፒዩተርዎ ማንኛውም አይነት ችግር ካጋጠመው ወደ ኢንፊክስ ቴክኖሎጂ ይደውሉ📞

+251954834439
+251994637327

Photos from Infix Computer Technology's post 07/03/2022

የኮምፒውተር የላፕቶፕ እና የፕሪንተርጸ ችግሮቾን ባሉበት መጥተን በተመጣጣኝ ዋጋ እናስተካክልዎ
7 አመት በላይ ልምድ
ያገለገለ ኮምፒውተር እንገዛለን እንሸጣለን
0954834439
0994637327
አስተማማኝ ጥገና
ታማኝነት መለያችን ነው
Infix Computer

28/02/2022

ኮምፒውተር ላይ ልታውቋቸው ግድ ነው ያልናቸውን አቋራጭ የኪቦርድ መንገዶችን (Shortcuts) እናሳውቃችሁ።

Ctrl+C እና Ctrl+X

Ctrl+C የመርጥነውን ጽሁፍ ወይንም ፎልደር ይሁን ፋይል ኮፒ ለማድረግ ይረዳናል። አይ ድግግሞሽ አልፈልግም ቆርጬ (Cut) ነው መውሰድ የምፈልገው ካልን ደሞ Ctrl+Xን መንካት ነው። ከት ካደረግንበት ቦታ ፋይሉን ወይም ጽሁፉን ያጠፋዋል።
ለአፕል ኮምፑተር ተጠቃሚዎች Ctrlን በcommand(cmd) በመተካት መጠቀም ይችላሉ።

Ctrl+V

ይህ አቋራጭ የሚጠቅመን ከላይ ኮፒ ወይም ከት ያደርግነውን በምፈልገው ቦታ ላይ ለማቀመጥ ነው። የንምፈልገው ቦታ ላይ ሄደን Ctrl+V ስንነካ ፋይሉን ያስቀምጥልናል።
ለአፕል ተጥቃሚዎች Cmd+Vን መጠቀም ይችላሉ

Ctrl+F

Ctrl+F በመካት የመፈለጊያ ሳጥን (Search) መክፈት እንችላለን። የህም የፈለግነዉን ጽሁፍ(text) እና ፋይል ለማግኘት ይረዳናል።
ለአፕል ተጠቃዎች Cmd+F በመንካት መጠቀም ይችላሉ።

Alt+Tab

Alt+Tab መጫን በተከፈቱ ፕሮግራሞች መሃል እንደፈለግን እንድቀያይር ያደርገናል። ለምሳሌ በብራውዘር ኢንተርኔት እየተጠቀምን ከነበር እና ወደ መፈትነው ወርድ ፋይል መሄድ ብንፈልግ Alt+Tab በመንካት መለወጥ እንችላለን።
ለአፕል ተጠቃሚዎች cmd+Tab ተጥቀሙ።

Ctrl+Backspace እና Ctrl+Left ወይም Right arrow

Backspace የጽሁፍ ፋይል ላይ አንድ ፊደልን ወይም ምልክትን ለማጥፋት ይጠቅምናል። ነገር ግን Ctrl+Backspace ሁሉንም ነገር አንድ ሳያስቀር ያጠፋልናል።
Ctrlን ተጭነን የግራ(left) እና ቀኝ(Right) ቀስቶችን ስንነካ እንደ ከርሰር ተጥቅመን የምንፈሊገዉን ተከታታይ ፋይል ወይም ጽሁፍ በጅምላ እንድንመርጥ ይረዳናል።

Ctrl+S

ዶክመንቶች ላይ እየሰራን የሰራበውን ቶሎ ሴቭ ማድረግ ቢያስፈልህልገን የምንጠቀመው Ctrl+S ነው። በተለይ እንደኛ አገር ላሉ የመብራት ችግር ላለባቨው አገሮች ዶችመታቭን ሴቭ ሳናደርግ እንዳይጠፋ ፍቱን መፍትሄ ነው።
ለአፕል ተጠቃሚዎች cmd+S ተጠቀሙ።

Ctrl+Home እና Ctrl+End

Ctrl+Home ከርሳችንን ወደ ዶክመንታችም መጅውመሪያ ይመልሰዋል። በተቃራኒው Ctrl+End ደሞ ከርሰራችንን ወደ. ዶክመንታችን መጨረሻ ይወስዋል።

Ctrl+P

ፒሪንት ማድረግ የምንፈልገው ፋይል ወንም ዶቹመንት ካለ Ctrl+P ስንነካ የፕሪንትን መስኮት በመክፈት የፕሪንት አማራጮችን ያሳየናል።
ለአፕል ተጠቃሚዎች cmd+Pን ተጠቀሙ።

PageUp ፣ Spacebar እና Pagedown

ከስሙ መገመት እንደሚቻለው PageUp እና Pagedown ዶክመንታችን ላይ ወደ ቀጣይ ገጽ ወንም ወደ ቀድሞ ገጽ ለመሄድ ይጠቅመናል። የኢንተርኔት ብራውዘር በመጠቀምበት ሰአት ደሞ Spacebar ወይም Shift+Spacebar አንድ ገጽ ለመዝለል ያስችለናል።
ፔጁን ላይክ ሼር እና ኮሜንት በመስጠት ያበረታቱኝ

26/02/2022

አንድ አፕሊኬሽን ዳውንሎድ ከማድረጋችን በፊት አፕሊኬሽኑ #ጎጂ ወይም #ጠቃሚ መሆኑን እንዴት ማረጋገጥ እንችላለን?

ከGoogle Play Store ላይ የምናወርዳቸው አፕሊኬሽኖች ጠቃሚ መሆናቸው የተረጋገጠላቸው እና ጎጂ እንዳልሆኑ የተመሰከረላቸው ናቸው፡፡

ነገር ግን አንድ አንድ ግዜ ጠቃሚ መስለው ጎጂ አፕሊኬሽኖችን Play Store ላይ ልታገኙ ትችላላችሁ፡፡

ታድያ Play Store ላይ አፕሊኬሽን ዳውንሎድ ስናደርግ አፕሊኬሽኑ ጠቃሚ ወይም ጎጂ መሆኑን እንዴት መለየት እንችላለን?

1. አፕሊኬሽኑ ምን ያህል ግዜ ዳውንሎድ እንደተደረገ መመልከት

ዳውንሎድ ማድረግ የፈለግንው አፕሊኬሽን ዳውንሎድ ከማድረጋችን በፊት አፕሊኬሽኑ ምን ያህል ግዜ ዳውንሎድ (Download Count) እንደተደረገ በደንብ መመልከት

ለምሳሌ ዳውንሎድ የምታደርጉት አፕሊኬሽን አንድ ሚሊዮን ግዜ ወይም ከዚያ በላይ ዳውንሎድ እንደተደረገ ካያችሁ ወድያው አፕሊኬሽኑ የተለቀቀበት ቀን በደንብ መመልከት፡፡

ምክንያቱም አብዛኛው አፕሊኬሽን ከተለቀቀበት ግዜ ጀምሮ አንድ ዓመት ወይም ከዚያ በላይ የቆየ ሲሆን ነወ ከሚሊዮን በላይ ዳውንሎድ ሊኖረው የሚችለው፡፡ ስለዚህ እናንተ ማውረድ የፈለጋችሁት አፕሊኬሽን ከተለቀቀ አንድ ዓመት ካልሞላው እና ዳውንሎድ የተደረገው ከሚሊዮን በላይ ከሆነ አፕሊኬሽኑን ከማውረድ ብትቆጠቡ ይሻላል፡፡

2. ስለ አፕሊኬሽኑ የተሰጡ የተወሰኑ አስተያየቶችን ማንበብ

ዳውንሎድ ማድረግ የምትፈልጉት አፕሊኬሽን ከማውረዳችሁ በፊት ከዚህ በፊት አፕሊኬሽኑን ዳውንሎድ ያደረጉ ሰዎች ስለ አፕሊኬሽኑ አስተያየት (Reviews)ያስቀምጣሉ፡፡ እነዚህን አስተያቶች በጥንቃቄ ማንበብ፡፡

ስለ አፕሊኬሽኑ በጣም የሚያማርሩ አስተያየቶች ካነበባችሁ አፕሊኬሽኑ ከማውረድ እንደጥቆጠቡ እመክራለሁ፡፡

3. የአፕሊኬሽኑ ስምምነት በጥንቃቄ ማንበብ

አፕሊኬሽኑ ከላይ የተጠቀሱትን ፍተሸዎች ካለፈ ዳውንሎድ ታደርጉታላችሁ፡፡ ከዚያ ኢንስቶል ስታደርጉት የአፕሊኬሽኑን ስምምነት በጥንቃቄ ማንበብ ያስፈልጋል፡፡

ሁላችንም ማለት ይቻላል አፕሊኬሽን ኢንስቶል ስናደርግ ስምምነቱን ሳናነብ "Accept" እንላለን፡፡ ልክ አይደለም፡፡
ምክንያቱም የሳይበር ወንጀለኞች ይህንን ባህሪያችን ስለሚያውቁ እኛን ሊጎዱ የሚችሉ ነገሮችን ስምምነቱ ላይ በማስገባት ጥቃት ሊፈፁሙብን ይችላሉ፡፡

ስለዚህ ስምምነቱን ስታነቡ ለምሳሌ data mining, data sharing, pop-ups ወዘተ የሚሉ ቃላት ከተመለከታችሁ የአፕሊኬሽኑን ኢንስቶሊንግ ሂደት እንድታቋርጡ እመክራለሁ፡፡፡


ስለዚህ ዳውንሎድ ማድረግ የፈለጋችሁት አፕሊኬሽን ቢያንስ እነዚህን 3 ፍተሸዎችን ካለፈ ጎጂ አይደለም ማለት ነው፡፡

24/02/2022

ውድ የቻናላችን ተከታታዮች ዛሬ ይዘን የቀረብነው ቴሌግራምን እንዴት አድርገን እንደምንቆልፈው ነው። app lock ሳንጠቀም በራሱ በቴሌግራም መቆለፍ ይቻላል።
የሚክተሉትን መንገዶችን መጠቅም ፦
1 setting የሚለው ውስጥ እንገባለን።
2.privacy and security የሚለውን
3.passcode lock የሚለውን ነክተን እንገባለን።
4.ከዛም በመቀጠልም passcode lock እናበራዋለን።
5.pin(ባለ 4 ይለፍቃል) ይጠይቀናል የምንፈልገውን ቁጥር እንስጠዋለን።
6. ሞልተን ከጨረስን በኋላ Auto lock የሚለው ውስጥ ገብተን የምንፍልገውን እንመርጣል።
7.በመቀጠልም ከመረጥን በኋላ ወደ ዋናው እንመለሳለን።
8.ከዛም ቴሌግራም ከሚለው አጠገብ Unlock የነበረውን ወደ Lock እንቀይረዋለን።
9.በመጨረሻም ይሄ ሁሉ ካደረግን በኋላ ከቴሌግራም እንውጣለለን ከዛም ተመልሰን ስንገባ የሞላነውን pin (ባለ 4 ይለፍቃል) ይጠይቀናል። ቁጥሩን መርሳት የለባችሁም።
ያልገባችሁ ነገር ካለ በውስጥ መስመር ጠይቁኝ

24/02/2022

5 ምርጥ አለምአቀፍ ነፃ የትምህርት ዕድል ማግኛ ድህረ ገፆች(Websites)

1 - StudentScholarships.org
2 - collegeboard.org
3 - StudentScholarships.org
4 - ScholarshipExperts.com
5 - SuperCollege.com
መልካም እድል
ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ ያለዎትን እውቀት ያሳድጉ በተጨማሪም በቴሌግራሜ ቻናል ምርጥ ምርጥ ስለኮምፒውተር የምለቃቸውን መረጃዎችን ለመከታተል እንዲያመችዎ ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ በፍጥነት መረጃ እንዲደርሳችሁ

Want your business to be the top-listed Computer & Electronics Service in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Address


Addis Ababa
1000