Koki mela
This page will help you to make your day beautiful!
08/05/2023
#ኢንዶሚ ላይ ምርመራ እየተደረገ ነው ❗️
ወደ ኢትዮጵያ በህጋዊ መንገድ ከውጪ አገር የሚገባ የኢንዶሚን ምርት የለም ተብሏል::
#በካንሰር የመያዝ እድልን የሚያስከትል ንጥረ ነገርን ይዟል በተባለው ኢንዶሚን ኑድልስ ላይ የተለያዩ አገራት ምርመራ ማድረግ ጀምረዋል፡፡ ማሌዥያና ታይዋን በኢንዶሚን ላይ “ኢቲሊን ኦክሳይድ” የተባለውን ካንሰር አምጪ ንጥረ ነገር በማግኘታቸው ምርቶቹን ከገበያ ላይ እንዲሰበሰቡ ማድረጋቸው ተዘግቧል፡፡የኢትዮጵያ ምግብና መድሃኒት ባለስልጣን፣ በህጋዊ መንገድ ተመዝግቦ ከውጪ አገር የሚገባ የኢንዶሚን ኑድልስ ምርት አለመኖሩን አመልክቷል፡፡ የባለስልጣኑ ምግብ ተቋማት ቁጥጥር ሃላፊ አቶ በትረ ጌታሁን ለአዲስ አድማስ እንደገለፁት፤ በባለስልጣኑ ተመዝግቦ በህጋዊ መንገድ ከውጪ አገር የሚገባ ኢንዶሚን የተባለ ምርት አለመኖሩን ጠቁመው፤ በአገር ውስጥ የሚመረትና በባለስልጣኑ ቁጥጥር የሚደረግበት ምርት አለ ብለዋል። ጉዳዩ እንደተሰማ በዚሁ የአገር ውስጥ ምርት ላይ ምርመራ መደረጉን የገለፁት ሃላፊው በምርቱም ላይ የተባለውን ዓይነት ለጤና ጎጂ የሆነ ንጥረ ነገር አለመገኘቱን አመልክተዋል፡፡በካንሰር የመያዝ እድልን ያስከትላል የተባለውን ንጥረ ነገር ይዟል በተባለው የኢንዶሚን ምርት ላይ ምርመራ ማድረግ ከጀመሩ የአፍሪካ አገራት መካከል አንዷ ናይጄሪያ ስትሆን፤ ከኢንዶሚን ኑድልስ ምርት የተለያዩ ናሙናዎችንና ቅመማ ቅመሞችን በመውሰድ ኢቲሊን አክሳይድ የተባለው ንጥረ ነገር መኖር አለመኖሩን ለማወቅ ምርመራ እያደረገች መሆኑን አስታውቃለች፡፡በማሌዥያና ታይዋን ልዩ የዶሮ ጣዕም ባለው የኢንዶሚን ምርት ላይ ካንሰር አምጪው አደገኛው ንጥረ ነገር በመገኘቱ ምርቶቹ ከገበያ እንዲሰበሰቡ ተደርገዋል፡፡
ኢንዶሚን የተባለውን ኑድልስ የሚያመርተው የኢንዶኔዥያው ግዙፍ የምግብ አምራች ተቋም “ኢንዶፍድስ” የምግብ ምርቱ ጤናማ መሆኑን በመግለፅ እየተከራከረ ነው፡፡
Adiss Admas
29/08/2022
08/08/2022
15/07/2022
13/06/2022
"አባዲናዎች ሶስት፣ አራት ቀን የቻሉትን ያህል ፈልገዋል፣ አሁን ግን የሉም። ህዝቡ ግን ፍለጋውን ቀጥሏል"--- የማርኮን አባት አቶ ይገረም ማምሻውን በስልክ ከነገሩኝ
ከአራት ወር በፊት ራያን የተባለ የ5 አመት ህፃን ሞሮኮ ውስጥ ሲጫወት በድንገት ጥልቅ ጉድጓድ ውስጥ ገብቶ ነበር፣ ፍፃሜው አሳዛኝ ቢሆንም አካሉን ማግኘት ተችሎ ነበር። ይህንን ጉዳይ አለም አቀፍ ሚድያዎች በቀጥታ ጭምር ሲዘግቡት ነበር፣ የሀገራችን ሚድያዎችም እንዲሁ።
ከስድስት ቀን በፊት በውሀ ስለተወሰደው የአራት አመት ህፃን ማርኮን ግን ከአንዳንድ የማህበራዊ ሚድያ መረጃዎች ውጪ ብዘዎቹ ሚድያዎች ችላ ብለዋል። ራስ ያቀለለውን...!
ማምሻውን አባት የሆኑትን አቶ ይገረምን በስልክ አውርቼ ነበር። እንዲህ ነበር ያሉት: "አባዲናዎች ሶስት፣ አራት ቀን የቻሉትን ያህል ፈልገዋል፣ አሁን ግን የሉም። ህዝቡ ግን ፍለጋውን ቀጥሏል። ተስፋችንን በእግዚአብሄር ላይ ጥለን ቁጭ ብለናል።"
ፍለጋው እስከ መጨረሻው በአባዲናዎች እንዲከናወን፣ እንዲሁም ህዝቡ ተደራጅቶ ፍለጋው ላይ እንዲሳተፍ ድምፅ እናሰማ። የሚዘንበው ሀይለኛ ዝናብ ጭራሽ ሳይገፋው ህዝቡ ከመንግስት አካላት ጋር በቅንጅት እንዲረባረብ እናድርግ።
"አይተውት ያልጠገቡትን፣ ስመውት ያልሰለቹትን ህፃን መሞቱን ተረድተው አስክሬኑን እየጠበቁ ውሎ ማደር የህመሙን ጥግ፣ ስቃይ እና ጭንቀቱን እንዴት ችለውት ይሆን?"
20/02/2022
✍ #ሙዝ #እና #አቮካዶ #ለህጻናት
🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
♥♥ #በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን♥♥
🔵 # #ሙዝ ለህፃናት ለመመገብ ቀላልና ጣፋጭ ከመሆኑም ባሻገር ከፍተኛ በሆነ ንጥረ ምግብ የበለፀገ ፍራፍሬ ነው፡፡ ሙዝ እንደ ቫይታሚን A ፣ ቫይታሚን B6 ፣ ቫይታሚን C ፣ ፖታሲየም ፣ዚንክ ፣ አይረን ፣ ካልሲየምና ማግኒዚየም ያሉ ንጥረ ምግቦች በውስጡ ይገኛሉ ፡፡ አንዲሁም በሰውነት ውስጥ ለመፈጨት ቀላል ነው ፤ ከሆድ ድርቀትና ከተመሳሳይ ችግሮች ይከላከላል፡፡
🔵 # #አዘገጃጀት
🔹 ሙዙን መላጥና መቆራረጥ
🔹 በጎድጓዳ ሰሃን ላይ ጨምሮ በሹካ ማላምና በተዘጋጀ የህፃናት ወተት ፤ የጡት ወተት ጨምሮ በደንብ እስኪለሰልስ ድረስ ማላም ከዚያ በማንከያ መመገብ
🔵 # አቮካዶው በውስጡ ከፍተኛ የሆነ ፍይበርና ሚኒራል ያለው ሲሆን በተጨማሪም በውስጡ ፖታሽየም ፣ ቫይታሚን B ፣ ቫይታሚን K ፣ ኮፐር ፣ ቫይታሚን ኢእና ቫይታሚን ሲ ይይዛል ፡፡
🔵 #አዘገጃጀት
ግብአቶች
• የበሰለ ሙዝ
• የበሰለ አቮካዶ
🔹 አቮካዶውን መላጥና በጎድጓዳ ሰሃን ላይ ፍቆ ማውጣት ሙዙንም ልጦ አንድ ላይ ማላም የተዘጋጀ የህፃናት ወተት፤በጡት ወተት በደንብ ማላምና መመገብ
👉👉 #ከህጻናት አመጋገብ ጋር በተያያዘ ማንኛውም ጥያቄ ካሎት ወደ 8809 ላይ በመደወል በቀጥታ ከጤና ባለሞያዎች ጋር ይመካከሩ፡፡ ከጧት 2 ሰዓት እስከ ማታ 2 ከሰኞ እስከ ሰኞ ቢደዉሉ የዶክተር አለ የጤና ባለሙያዎች ሊያማክሩዎ በመስመር ላይ ይገኛሉ!!!
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
✍ 9102 ok ብለዉ በእጅ ስልክዎ በመላክ አጭር መልእክቶቻችንን በቀላሉ መከታተል ይችላሉ።
♥♥ #በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን♥♥
🔺 በጤና፣ በግንኙነት፣ በስነ-ልቦና እና አመጋገብ ዙርያ ጠቃሚ መረጃ ለማግኘት 9102 Ok ብለዉ ይጠቀሙ።
🔺 ቅድመ-ጥንቃቄ ልናደርግላቸው የሚገቡ በሽታዎች የትኞቹ ናቸው? ብዙ ሰዎችን ከሚያጠቁ በሽታዎች እራሳችንን እንዴት መጠበቅ እንችላለን?
🔺 ክብደታችንን ለመቆጣጠር አመጋገባችን እንዴት መሆን አለበት?
🔺 ከፍቅረኛ፣ ከቤተሰብ እና ከባልደረባ ጋር በተደጋጋሚ የሚፈጠሩ የግንኙነት ችግሮችን እንዴት መፍታት እንችላለን?
በነዚህ ጉዳዮች ዙርያ የሚያውጠነጥኑ አጭር መልእክቶችን #በ9102 ማግኘት ይችላሉ።
♥9102 OK ♥♥
👇👇👇👇👇👇👇👇
👉 በሚከተሉት የማህበረሰብ ትስስር ድህረ ገጾች ይከታተሉን፡
✅የዶክተር አለ የአጭር መልእክት
👉👉👉 9102 OK
✅የዶክተር አለ የስልክ ምክክር
👉👉👉 8809
✅ የዶክተር አለ 8809 የፌስቡክ ገፅ፦
👉👉👉 http://tiny.cc/gf606y
✅ የዶክተር አለ 8809 የቴሌግራም ገፅ ፦
👉👉👉 T.ME/DOCTORALLE8809
✅ የዶክተር አለ 8809 የዩቱብ ቻነል፦ 👉
https://www.youtube.com/channel/UCg8YTjuR_i3pUeQ0Jexa5yQ
( #በጤና #ባለሙያ #ከድጃ)
19/02/2022
11/05/2021
አሁን ባለንበት ዓለም አብዛኛዎቹ ሰዎች እውነትን መናገር እየከበዳቸው ውሸትን መናገር ደግሞ እንደ ቀላልና የተለመደ አድርገው እየወሰዱ ነው። ታዋቂው የሬጌ ዘፋኝ ቦብ ማርሌይ በአንድ ወቅት "ችግሩ ሰዎች እውነተኛ ሲሆኑ መጠላታቸው፣ ሀሰተኛ ሲሆኑ ደግሞ መወደዳቸው ነው" ብሎ ነበር። ይህም የሚያሳየው በዓለም ላይ ሰዎች ከእውነተኝነት ይልቅ ውሸታምነትን እንዴት የጎላና በብዙ ሰዎች ዘንድ እየተተገበረ እንደሆነ ነው። በጥንት ጊዜም ፕሌቶ የተባለ ፈላስፋ እውነተኛ ሰው እንደማይወደድና ጓደኛ እንደሌለው ተናግሯል።
በሥነ-ልቦና ሳይንስ አንድን ባህርይ መማር ወይም አለመማር ይቻላል። እንደ ባህርያዊ የሥነ-ልቦና ጠበብቶች ሁሉም የሰው ልጅ ባህርይ በመማር የመጣ ነው። ለዚህም ማሳያ ሕጻናት ሲወለዱ "ባዶ ወረቀት" መሆናቸውንና አካባቢ [እኛ] እንደምንጽፋባቸው፣ በዚህም ልጆቻችንን እኛ እንደምንፈልገው አድርገን ማሳደግ እንደምንችል አስረግጠው ይነግሩናል።
ልጆቻችንን ለመቅረጽ ደግሞ የኛ የወላጆች ሚና እጅግ ከፍተኛ እንደሆነ ባለሙያዎቹ በጥናት አስደግፈው ይናገራሉ። እነርሱ እንደሚሉት ወላጆች የልጆች የመጀመሪያ የቅርብ ሰዎች በመሆናቸው ልጆች እነርሱን በማየት ወደፊት ምን አይነት ሰዎች እንደሚሆኑ ማወቅ ይቻላል። በመሆኑም ወላጆች መልካም የአስተዳደግ ዘይቤን መከተል እንዳለባቸው ይመከራል። ለምሳሌም ወግ አጥባቂና ጨቋኝ ወላጆች የልጆችን የወደፊት ባህርይ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳድራል። ፈሪ፣ በራሳቸው የማይተማመኑ፣ ኃላፊነትን የማይወስዱ፣ ጥገኛ እንዲሁም ነውጠኛ የመሆን እድላቸው የሰፋ ሲሆን ውሸታምና አጭበርባሪ ሊሆኑ ይችላሉ።
ቻናሎቻችንን ሰብስክራይብ በማድረግ ጠቃሚ ትምህርቶችን ያግኙ!
ዩቲዩብ: https://youtu.be/flghfRbyGVE
ቴሌግራም: https://t.me/psychforlife
Click here to claim your Sponsored Listing.
11/03/2022