Ethio-Fact
የህብረ ብሄራዊነታችን መገለጫ የሰላማችን ማስታወሻ
🇪🇹🇪🇹ኢትዮጵያ🇪🇹🇪🇹
16/10/2023
በሰንደቅ ዓላማችን ሥር ተሰባስበን የኢትዮጵያን ሕብረብሔራዊ አንድነት እናፀናለን!
*******************************
መላው ኢትዮጵያዊያን እንኳን ለ16ኛ ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን አደረሳችሁ!
የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ የሉዓላዊነታችን ምልክት፣ የነፃነታችን አርማና የክብራችን መገለጫ ነው፡፡ ሰነደቅ ዓላማችን ከትውልድ ትውልድ የተሸጋገረ፣ የጀግኖች አባቶቻችን የደማቸው ፍሳሽ፤ የአጥንታቸው ክሰካሽ እንዲሁም የመስዋዕትነት ውጤት የሆነ የድል ሰንደቅ ነው፡፡
የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለመጠበቅ፣ የሕዝቦቾን ነፃነትና ክብር ለማጽናት ጀግኖች ኢትዮጵያዊን ለሰንደቅ ዓማችን ፍቅርና ክብር በአንድነት መስዋትነት ከፍሏል፡፡ በመሆኑም የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ በትውልድ ቅብብሎሽ ለሉዓላዊነታችን የተከፈለ መስዋዕትነት እና ሕብረብሔራዊ አንድነታችንን የሚያንፀባርቅ ነው፡፡ የሀገራችን ሉዓላዊነት ምልክት የሆነው የሰንደቅ ዓላማችን ፀንቶ የቀጠለው ኢትዮጵያዊያን በአንደነት በከፈሉት መስዋእትነት ነው፡፡
ዛሬ ጥቅምት 5 ቀን 2016 ዓ.ም በሀገርአቀፍ ደረጃ 16ኛው የብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀን “የሰንደቅ ዓላማችን ከፍታ ለሕብረብሔራዊ አንድነታችንና ሉዓላዊነታችን ዋስትና ነው!” በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ይገኛል፡፡
የዘንድሮውን የሰንደቅ ዓላማ ቀን ስናከብር ሕብረብሔራዊ አንድነታችን ሉዓላዊነታችን እና የህልውናችን ዋስትና መኾናቸውን ታሳቢ ልናደርግ ይገባል፡፡ ኢትዮጵያ መልከ ብዙ ሕብረብሔራዊ ሀገር ናት፡፡ እጅግ ብዙ ባህሎች፣ ቋንቋዎች፣ ሃይማኖቶች፣ መልከአምድርና የአየር ጠባዮች፣ ፍላጎቶች፣ አስተሳሰቦች፣ እምቅ ሀብቶች ያላት ብዝኃነት መገለጫዋ የኾነች ዕፁብ ድንቅ ሀገር ናት፡፡ ኢትዮጵያችን ብዙ ኾና አንድ፤ አንድ ኾና ደግሞ ብዙ ነች፡፡
በዛሬው ዕለት የሰንደቅ ዓላማ ቀንን ስናከበር እነዚህን ኹለት የሀገራችንን ምሶሶ የኾኑ መገለጫዎች መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡
ሕብረብሔራዊ አንድነታችን ሲጠናከር የኢትዮጵያ ሉዓላዊነትም በፅኑ መሠረት ላይ ይቆማል፡፡ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓለማ ክብር ከፍ ይላል፡፡ የሰንደቅዓላማችን ከፍታ በዘላቂነት የሚቀጥለው ሕብረብሔራዊ አንድነታችንን ለማጠናከር በሚከናወነው ጠንካራ ሥራ መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡
ከትላንት እስከ ዛሬ ጀግኖች ኢትዮጵያዊያን የኢትዮጵያን ሉዓላዊነትና ነፃነት በደማቸው ጠብቆ አቆይቷል፣ ሰንደቅዓላማችንን ከፍ አድርጓል፡፡ የዛሬ ትውልድ በአባቶቹ የህይወት መስዋእትነት ሉዓላዊነቷ ተጠብቆ የቆየችውን ሀገር በላቡ ማፅናት ይጠበቅበታል፡፡ ዛሬ ላይ ሉዓላዊነታችን በዘላቂነት ሊረጋገጥ የሚችለው ሀገራችንን ከልመና ነፃ ስናወጣት ነው፡፡
ይህ የሚረጋገጠው ትውልዱ ያለበትን እዳ ተገንዝበው በተሰማራበት ዘርፍ ሁሉ በላቡ የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልፅግና ሲያረጋግጥ ነው፡፡ የሀገራችን ሁለንተናዊ ብልፅግና እውን ሲኾን የማንነታችን መገለጫ፣ ሰንደቅዓላማችንም ልዕልናው ይጨምራል፡፡ መላው ኢትዮጵያዊያን ለሀገራችን ሰንደቅ ዓላማ ያለንን ክብርና ፍቅር ሕብረብሔራዊ አንድነታችንን እና ሉዓላዊነታችንን ሊያስጠብቁ በሚችሉ ክንውኖች ላይ በመሳተፍ በተግባር ማሳየት ይገባናል፡፡ የሀገራቸውን ሰላምና ልማት ለማረጋገጥ መስዋዕትነት የሚከፍሉትን አካላት እንደ ወትሮው ኹሉ በማክበር ለሰንደቅ ዓላማችን ዘብ መቆማችንን በተጨባጭ ማስመስከር ይጠበቅብናል፡፡
ሕብረብሔራዊ አንድነታችንንና ሉዓላዊነታችንን አፅንተን የኢትዮጵያን ሰንደቅዓላማ በከፍታ እናውለበልባለን!
*************
ከመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ተጨማሪ ሃገራዊ መረጃዎችን ለማግኘት ተከታዮቹን ገፆቻችንን ይጎብኙ
Follow Government Communication Service pages for more information
*****
Facebook
https://www.facebook.com/FDRECommunicationService?mibextid=ZbWKwL
***********
Twitter/X
https://twitter.com/FdreService?t=4sPyRrDlsbdHQwP2xHcXdg...
**********
Telegram
https://t.me/gcsfdregovernment
*********
YouTube
https://youtube.com/-yj2pd?si=-Mq6LeLyru3UEp4F
*********
Tik Tok
https://www.tiktok.com/.ethiopia?_t=8fvgeUSiJwE&_r=1
16/08/2023
ከአማራ ክልል አመጽ በስተጀርባ በግንባር ቀደምነት ያሉት ሰው አቶ ገዱ አንዳርጋቸው መሆናቸው አሁን ግልፅ ሆኗል።
👉አቶ ገዱ እንዳሉት ከሦስት ወር በፊት መከላከያ በክልሉ ሕዝብ ዘንድ መልካም እይታ ነበረው፤ እውነታው ግን ይህ ጃውሳ ሃይል በመከላከያ ላይ ቃታ መሳብ ከጀመረ ድፍን ሁለት አመት መሆኑ ነው።
አቶ ገዱ መከላከያ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ወደ ካንፑ ይመለስ ብለዋል። ለመሆኑ ጃውሳው ሃይል በሁሉም የአማራ ክልል ከተሞች
👉የመከላከያን ካምፖች ከቦ ጥቃት ሲፈጽም፣
👉ወይን ቤቶችን ሰብሮ እስረኞችን ሲያስፈታ፣
👉የመሳሪያ ግምጃ ቤቶችን ሲዘርፍ
👉የፖሊስ ማሰልጠኛ ኮሌጆችን ሲያወድም
👉የመንግስት መዋቅሮችን ሲያፈርስ
👉የግል እና የመንግስት ተቋማትን ሲዘርፍ
👉አድባራት እና ገዳማትን የጦር መሳሪያ ዴፖ ሲያደርግ
አንድ ቃል ያልተነፈሱት፣ እንደውም እንደህዝባዊ አመፅ እና ትክክለኛ እርምጃ ቆጥረው በተቃራኒው መንግስትን እንደጥፋተኛ ሲቆጥሩ መስማት ክልሉን ሲያስተዳድሩ ከነበሩ ሰው የማይጠበቅ ብቻ ሳይሆን አሳዛኝም ጭምር ነው።
እኝህ ሰው በተደጋጋሚ የሚኮንኑት ብልጽግና ፓርቲ የአባልነት መልቀቂያ አስገብተዋል? ብልጽግናን ወክለው አይደለምን የተወዳደሩት? አቶ ገዱ በብልጽግና ማሊያ ለጃውሳው ሲጫወቱ እንደማየት ትልቅ ቅሌት የለም።
#ጃውሳ
15/08/2023
🚨ዱግማኑ የስልጣን ጥመናዉ ወንበዴ🚨
ከላይ የምትመለከቱት ግለሰብ የአማራ የብሄር ፖለቲካ ጠንሳሽ እና ነብስ አባት እና የአማራ ህዝብ የመከራ መፍለቂያ የሆኑትን የዘር ፖለቲካ ፓርቲዎች እና አደረጃጀቶችን ባርኮ ያስመሰረት ግለሰብ ነዉ፡፡
የአማራ ህዝብ ፖለቲካ በአዝማሪዎች እና በተወዛዋዦች እንዲመራ ካደረጉ ደካማ ግለሰቦች መካከል ግንባር ቀደሙ ነዉ፡፡ በአቅም ማነስ ያጣቸዉን ስልጣኖች በሀይል ለማግኘት የጃዉሳዉ የፖለቲካ ክንፍ በመሆን በህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ዉስጥ እየታገለ ይገኛል፡፡
#ጃውሳ
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Addis Ababa