Erta'ale Media
Media company
የስሜት ብልህነት
በህይወታችን ስኬታማ ለመሆን ወሳኙ ጉዳይ የማሰብ ችሎታ intelligence (IQ) ሳይሆን የስሜት ብልህነት (Emotional intelligence (EQ) ነው፡፡
እ.አ.አ በ1995 ዳንኤል ጎልማን ለህዝብ ያስተዋቀው Emotional intelligence የተሰኘው መጸሐፍ በዓላም ላይ ከ አምስት ሚሊዮን በላይ ኮፒዎች ተቸብችቧል ከሰላሳ በላይ ቋንቋዎች ተተርጉሞ በተለያዩ ሀገራት ተሰራጭቷል፡፡
ለመሆኑ የስሜት ብልህነት ምንድነው ?
የራስ እና የሌሎች ሰዎችን ስሜት የመለየት፤የመረዳ የመቆጣጠር እና ተጽኖ የመፍጠር ብልሃት ማለት ነው፡፡
በእኛም ማህበረሰብ ውስጥ ይሄ ልጅ ብልህ ነው ፤ይቺ ልጅ በልህ ነች ይባልል ያ ማለት ነው የስሜት ብልህነት በቀላል አማርኛ፡፡
ዳንኤል ጎልማን ስለ የስሜት ብልህነት ሲያብራራ አምስት ገሮች በዋናነት ያነሳል
1.ራስን ማወቅ
2.ራስን መቆጣጠር
3.ተነሳሽነት
4.ርህራሄ ወይም አክብሮት
5.ከሰዎች ጋር ተግባብቶ የመኖር ብልሃት ናቸው፡፡
የስሜት ብልህነት የሰዎችን ባህሪ በአግባቡ እንድንረዳ ያሚያደርገን ሲሆን፤ከሰዎች ጋር ያለን ግንኙነት ምን መምሰል እንዳለበት እንድንወስን የሚረዳን ነው፡፡
የስሜት ብልህነት በየጊዜው እያደገ እየዳበረ የሚሄድ ነው የሚለው ጎልማን ፤ራን በቅጡ ማወቅ፤ሰዎችን በበጎ መልኩ መመልከት እና ከሰዎች ጋር ያለንን ተግባቦች በማሳደግ የስሜት ብልህነትን መደባር እንደሚቻል ይመክራል፡፡
06/12/2020
በማይካድራ ከተማ አቅራቢያ በሚገኝ የእርሻ ካምፕ ውስጥ የሕወሓት የጦር መሳሪያዎችና ማሰልጠኛ ተገኘ!
የተለያዩ ሃገራት ወታደራዊ ልብሶች፣ የአልሸባብ እና የኦነግ ሸኔ ወታደራዊ ልብሶችም መገኘታቸው ተገልጿል፡፡የሠው ማሠቃያ ሠንሰለቶች፣ መፅሐፎች፣ ካሴቶች እና ሲዲዎችም ተገኝተዋል ተብሏል፡፡
[Al-ain]
የብፁዕ አቡነ ገብርኤል (ዶ/ር) ሊቀ ጳጳስ ሥርዓተ ቀብር ተፈፀመ
**************
የብፁዕ አቡነ ገብርኤል (ዶ/ር) ሊቀ ጳጳስ ሥርዓተ ቀብር በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ፣ ብፁአን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ ካህናት እና ምእመናን በተገኙበት ዛሬ በቅድስት ስላሴ ቤተክርስቲያን ተፈጽማል።
ብፁዕ አቡነ ገብርኤል (ዶ/ር) ሊቀ ጳጳስ ታኅሣሥ 19 ቀን 1933 ዓ.ም ከአባታቸው ከመምህር ቀሲስ ገብረ ሕይወት ወልደ ሐዋርያት እና ከእናታቸው ወይዘሮ ብርነሽ ቸኮል በቀድሞ የወሎ ክፍለ ሀገር በዋግ ሕምራ አውራጃ ተወለዱ።
ብፁዕ አቡነ ገብርኤል (ዶ/ር) ሊቀ ጳጳስ እድሜአቸው ለትምህርት ሲደርስ መንፈሳዊ ትምህርታቸውን በትውልድ ስፍራቸው ወሎ ክፍለ ሀገርና በአዲስ አበባ ቅዱስ ፓውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ እንዲሁም እስከ 12ኛ ክፍል ተከታትለዋል።
ከዚህ በተጨማሪም የውጭ የትምህርት እድል በማግኘት በሞስኮ ቅዱስ ፒተርስበርክ መንፈሳዊ ኮሌጅ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን የተከታተሉ ሲሆን ሁለተኛ ዲግሪያቸውንም ከሞስኮ ቅዱስ ፒተርስበርክ መንፈሳዊ ኮሌጅና ከሰሜን አሜሪያ ፕሪስተን ዩኒቨርሲቲ መቀበላቸውን የህይወት ታሪካቸው አስረድቷል።
ብፁዕ አቡነ ገብርኤል በቤተክርስቲያኗ ልዩ ልዩ ሀገረ ስብከቶች እና በመንበረ ፓትርያሪክ ጽ/ቤትም ያገለገሉ ሲሆን ከመንፈሳዊ አገልግሎት በተጨማሪም በማህበራዊ ሁኔታ ምሳሌ የሚሆኑ አባት እንደነበሩ ተገልጿል።
ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው በተወለዱ በ80 ዓመታቸው ህዳር 26/2013 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
06/12/2020
የኦነግ ሸኔ አባላትን ዕድሜ ለማሳጠር የጂ ፒ ኤስ ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ እየዋለ ነው❗️
⚡️በኦሮሚያ በየጊዜው እያጋጠመ ለሚ ገኘው የህይወትና ንብረት ውድመት በህወሓት ጁንታ እና ተላላኪዎቹ የሚፈፀም መሆኑንና ይህንንም ለማስወገድ ብሎም የቡድንን ዕድሜውን ለማሳጠር በ‹ጂ ፒ ኤስ› ቴክኖሎጂ የታገዘ ሥራ እያከናወነ መሆኑን የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ፖሊስ ኢንዶክተሬሽን መምሪያ አስታወቀ።
⚡️እነዚህ አካላት ዜጎችን ለምን እንደሚገድሉ እን ደማያውቁ በመጠቆም በህግ ቁጥጥር ሥር ለማዋልም በቴክኖሎጂ የተደገፈ ሥራ መጀመሩን ጠቁመዋል። ቴክኖሎጂው እነዚህ አካላት ያሉበትን ቦታ ለመከታተል የሚያስችል እንደሆነም አመልክተዋል።
⚡️በዚህ ቴክኖሎጂ በመታገዝ የኦነግ ሸኔ አባላት በቁጥጥር ስር እየዋሉ መሆናቸውን የተናገሩት ኃላ ፊው፤ በሠላማዊ መንገድ እጅ ለማይሰጡና የኃይል አማራጭ ለመጠቀም የሚሞክሩት ላይ ደግሞ እርምጃ እየተወሰደባቸው እንደሆነ አስታውቀዋል ።
⚡️እነዚህ ጸረ ሠላም አካላት አባ ቶርቤ በሚል ስያሜ የሚንቀሳቀሱ መሆኑን አመልክተው ፣ ኦሮሚያ ክልልን የግጭትና ጦር አውድማ ለማድረግ ሲንቀሳቀሱ መቆየታቸውን ገልጸዋል። ሠላማዊ ዜጎችን መግደል ሥራቸው አድርገው መቆየታቸውንም አመልክተዋል።
©ኢፕድ
01/12/2020
ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም ለመንግስት እጅ ሰጡ❗️
⚡️ ከተፈላጊ የህወሓት ጁንታ አባላት አንዷ የሆኑት ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም ለመንግስት እጅ ሰጡ።
⚡️ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም የህውሓት ከፍተኛ አመራርና በመንግስት ከፍተኛ ሃላፊነት የነበራቸው እንዲሁም በፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤነት አገልግለዋል።
⚡️One of the 9 central committee leaders of the TPLF, Keria Ibrahim, has surrendered to Federal forces.
⚡️IKeria Ibrahim held one of the key federal government posts as Former Speaker of the House of Federation until her resignation to join the clique in Mekelle.
28/11/2020
❗️
የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል ብርሀኑ ጁላ ጀግናው ሠራዊታችን መቀሌን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩን አረጋገጡ ❗️
28/11/2020
የትግራይ ሕዝብ ከስግብግቡ ጁንታ ጋር እንዳልሆነ በተግባር አስመስክሯል።
የመከላከያ ሠራዊት በድል በገሠገሠባቸው የትግራይ አካባቢዎች ሁሉ የትግራይ ሕዝብ ለሀገሩ ያለውን ፍቅርና ለመከላከያ ሠራዊቱ ያለውን ክብር አሳይቷል። ጁንታው ካስታጠቃቸው ጥቂት የክፋት ኃይሎች ውጭ ያለው የትግራይ ሕዝብ መቀሌ እስኪገባ ድረስ ለመከላከያ ሠራዊቱ የሚጠበቅበትን ድጋፍ ሁሉ አድርጓል። ይህም የሠራዊቱን ድልና የጁንታውን ሽንፈት አፋጥኖታል።
ስግብግቡ ጁንታ በየትኛውም መመዘኛ ለትግራይ ሕዝብ አይመጥነውም። የትግራይ ሕዝብ ከእውነት ጋር በመቆምና የጁንታውን እኩይ ዓላማ በመፃረር ከቀበሌ ቀበሌ፣ ከዞን ዞን መቀሌ እስኪገባ ድረስ ተመሳሳይ ድጋፍ ለሠራዊቱ ሰጥቷል። ለዚህም ከፍ ያለ ምስጋናዬን አቀርባለሁ። ጁንታው በሸሸበት ከተማና አካባቢ ሁሉ የጤና ተቋማትን፣ ተ/ቤቶችን፣ ድልድዮችን፣ መንገዶችን፣ መሥሪያ ቤቶችን እያወደመ ሄዷል። በዚህም የገዛ ወገኑ ጠላት መሆኑን አሳይቷል። ጁንታው እኔ ከሞትኩ ብሎ ያፈረሳቸውን መሠረተ ልማቶች በፍጥነት በመገንባት የትግራይ ሕዝብ ወደ ሰላማዊ ኑሮው እንዲመለስ ለማድረግ የቻልነውን ሁሉ እንደምናደርግ ቃል እገባለሁ።
በዚህ ዘመቻችን ንጹሐን ዜጎች ዒላማ ሳይሆኑ፣ ከተሞቻችንና ቅርሶቻችን ሳይጎዱ መቀሌ ለመግባት ተችሏል።
28/11/2020
የህወሓት ቡድን ልዩ ሃይል አባላት በአዲ ምስኖ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ብዛት ያላቸው ጥይቶችን በማከማቸት የአካባቢውን ህብረተሰብ ያስቆጣ ተግባር ፈፅሟል ተባለ።
[አበበ ሰማኝ ( ከግዳጅ ቀጣና )]
አቶ በሀይሉ በርኸ "ቤተ ክርስቶያን ውስጥ የመድፍ ጥይት እና ቢ ኤም መሳሪያ አምጥተው አስቀመጡ፡፡ለምን ስንላቸው ቤተክርስትያኑ አይመታባችሁም ከተመታም የጥይት ሳጥን እንሰጣችሁና እሱን ሸጣችሁ ታስጠግኑታላችሁ አሉን" ብለዋል።
አቶ በሀይሉ፣ ቤተ ክርስትያኑ ፈርሷል ውስጡ ያለው ፅላትም ይኑር አይኑር የምናውቀው ነገር የለም ፥ ወያኔ ለሃይማኖት እኩልነት እቆማለሁ ሲል የነበረ ድርጅት ዛሬ ግን ስጋወደሙ የምንቀበልበትን የእምነት ቦታ አርክሶብናል ሲሉ በሃዘንና በቁጭት ስሜታቸውን አጋርተውናል።
በየትኛውም ፖለቲካዊ እይታ ህዝብን ያልያዘ ሃይል የድል ባለቤት ሊሆን አይችልም፡፡ከሞቱ መቃብር አፋፍ ላይ የሆነው ትህነግ፣ ግን በራሱ ልክ በተሰፋው የሴራ ፖለቲካ ተተብትቦ በሰው ህሊና ሊፈፀሙ አይደለም ሊታሰቡ የማይችሉ ተግባራትን ከመፈፀም አልቦዘነም።
ለሁሉም በመላው ህዝባችን ድጋፍ በጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን ጀግንነት ዘራፊውና ከሃዲው ቡድን ያለችው የተስፋ ጭላንጭል ተሟጣ የመኖር ጀንበሩ ልትጠልቅ አጭር እድሜ ብቻ ቀርተውታል።
[ፎቶግራፍ ብርሀኑ አባተ]
27/11/2020
በማይካድራ ተጨማሪ የጅምላ መቃብሮች ተገኙ፡ አብመድ
በማይካድራ ተጨማሪ ጅምላ መቃብሮች መገኘታቸውን የአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት(አብመድ) ዘግቧል፡፡
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ከሰሞኑ ባወጣው የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት ከ600 በላይ ንጹሃን መገደላቸውን ገልጾ ነበረ ቢሆንም አሁን ግን ተጨማሪ የጅምላ መቃብሮች በአካባቢው መገኘታቸው ተዘግቧል፡፡
የጅምላ መቃብሮቹ የተገኙት ከማይካድራ ከተማ ወጣ ባሉ የገጠር አካባቢዎች ሲሆን ግድያውም ዘርን መሠረት ያደረገና በአማራ ተወላጆች ላይ ያነጣጠረ ጅምላ ጭፍጨፋ እንደነበር ኢሰመኮ መገለጹ ይታወሳል፡፡ የሟቾች ቁጥር በትንሹ 600 ነው ተብሎ የተገለጸው በማይካድራ ከተማ በየቤቱ ህይወታቸው አልፎ የተገኙ እና በቤተክርስቲያን ውስጥ የተቀበሩትን ብቻ መሠረት ተደርጎ የተቆጠረ እንደሆነም በዘገባው ተጠቅሷል፡፡
በአንድ ቦታ 18 ሰው በጉድጓድ ውስጥ በጅምላ የተጣሉ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን በሌላ የገጠር አካባቢ ደግሞ 57 ሰዎች በጎርፍ ማፋሰሻ ቦይ ውስጥ በጅምላ ተገድለው እና ተጥለው መገኘታቸውን ተረጋግጧል ነው የተባለው፡፡
በዛሬው ዕለትም በማይካድራ ሌላ የገጠር ቀበሌ ውስጥ 17 ሰዎች በጅምላ ተገድለው በጉድጓድ ውስጥ ተጥለው ተገኝተዋል ብሏል አብመድ ፡፡ አሁንም ሴንትራል፣ ደሮ እርባታ፣ በረኸት በሚባሉ አካባቢዎች ላይ አሠሳ እየተደረገ እንደሚገኝ እና ቁጥሩ ሊጨምር እንደሚችል የማይካድራ ነዋሪዎች ገልጸዋል ተብሏል፡፡
27/11/2020
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአፍሪካ ህብረት ልዑክ ጋር መወያየታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ልዑኩን በጽህፈት ቤታቸው ነው ተቀብለው ያነጋገሩት፡፡ከልዑካኑ መካከል የቀድሞ የላይቤሪያ ፕሬዚዳን ኤለን ጆንሰን ሰርሊፍ፣ የቀድሞው የሞዛምቢክ ፕሬዚዳንት ጆኣኪም ቺሳኖ፣ የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ኪጋሌማ ሞትላንቴ ናቸው፡፡ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይና የአፍሪካ ህብረት ልዑካን በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ልዑኩ በአፍሪካዊ ወንድማማች መንፈስ የኢትዮጵያ ሁኔታ አሳስቦት መምጣቱን አድንቀዋል፡፡በውይይቱ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሁን በትግራይ ክልል እየተካሄደ ስላለው የህግ ማስከበር ዘመቻ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡እንዲሁም ለሁለት ዓመታት ያህል ህወሓት ሃገሪቷን ለማተራመስ የሄደበትን ርቀትና መንግስት ያሳየውን ያላሰለሰ ሆደ ሰፊነት ለልዑካኑ አስረድተዋል፡፡
Via PMOEthiopia
27/11/2020
⬆️
ትህነግ ለውሸት ድምሰሳ 21ኛ ክ/ጦርን ለምን መረጠ?
በአበበ ሰማኝ (ከአዲ-ቀይህ) ህዳር 17 ቀን 2013 ዓ.ም
ከምስረታው ጀምሮ ምንም አይነት ሰብዓዊነት ያልፈጠረበት ትህነግ ለበርካታ አመታ የውሸት ካህን ሆኖ በህዝቦች ዘንድ መጠራጠርን፥ ኢትዮጵያን መካድን ለትውልድ አውርሶ በመቃብሩ ጫፍ ላይ ዛሬም እንደትናንቱ በተሰፋበት የሃሳዊነት አኮፋዳ ቱሪናፋውን ይለቃል።
ሰሞኑን የትህነግ የውሸት ቱቦ ማፍሰሻ ጌታቸው ረዳ በበቀቀኑ ቴሌቪዥን ጣቢያ ቀርቦ ትርጉም በሌለውና ውጤት አልባ ሆኖ በትህነግ የፖለቲካ ሴራ በተሸረበው ነገር ግን ውስጡን ያላውቁት ቆራጥ የህዝብ ልጆች ለድንበራቸው መከበር ዋጋ በከፈሉበት የሻዕቢያ ጦርነት ታላቅ ገድል የፈፀመችው 21ኛ ክ/ጦር ሙሉ በሙሉ ደምስሰናታል ብሏል ።
ለመሆኑ ትህነግ ኢትዮጵያችን ካሏት ጀግና ክ/ጦሮች ውስጥ 21ኛን መርጦ ሙሉ በሙሉ ለምን ደመሰስኩ አለ?
21ኛ ጉና ክ/ጦር ከሃገራዊ ለውጡና ከሃገር ከሃዲዎች የመቀሌ መመሸግ ማግስት በኦሮሚያ ክልል የተፈጠረውን አለመረጋጋት ወደቀደመ ሰላሙ ለመመለስ ከጫካ ውጭ ሌላ የትግል አማራጭ የማያውቀውን የትህነግ ታናሽ ወንድም ኦነግ ሸኔን እግር በእግር ተከታትላ አፈር ድሜ ያበላችና ለአካባቢው ህዝብ እፎይታን የሰጠች ጀግና ክ/ጦር ናት ።
ዛሬም መንግስት ህግን ለማስከበርና የዘመናት የህዝቦችን ጥያቄ በዘለቄታዊነት ለመፍታት ተገዶ በገባበት ጦርነት ውስጥ ትውልድ የሚሻገር ገድል በራያ ግንባር ተሰልፋ በመስራት ላይ ትገኛለች፥ ከቆቦ እስከ አዲቀይህ ያለውን 160 ኪሎመትር የሚረዝም ፈታኝ የመሬት ገፅ በኢትዮጵያዊነት ፍቅር በተማረኩት ጅግና ልጆቿ ታጅባ የጠላትን መቃብር ያፋጠነች እውነተኛ ኢትዮጵያዊ ጀግና ክ/ጦር ነች።
27/11/2020
የግብጹ ፕሬዚዳንት ነገ ደቡብ ሱዳን ይገባሉ!
የግብጹ ፕሬዚዳንት አብዱል ፋታህ አልሲሲ ነገ ጁባ እንደሚገቡ የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡ፕሬዚዳንት ሳል ቫኪር ማያርዲት ነገ በጁባ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው ለግብጹ አቻቸው አቀባበል እንደሚያደርጉ የገለጸው ጽ/ቤቱ ሕዝቡም በቦታው ተገኝቶ አቀባበል እንዲያደርግ ጥሪ አቅርቧል፡፡ሁለቱ መሪዎች የምሳ ፕሮግራም እንደሚኖራቸው የተገለጸ ሲሆን በጁባና ካይሮ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ላይ እንደሚወያዩ ይጠበቃል፡፡ከዚህ ባለፈም በቀጣው የጸጥታ ጉዳዮች ላይ ውይይት እንደሚደርጉም የፕሬዚዳንቱ ጽ/ቤት ገልጿል፡፡
[Al-ain]
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Telephone
Website
Address
Addis Ababa