SSA

SSA

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from SSA, Digital creator, bole road, .

12/06/2026

😊✨🇬🇲

08/06/2026

P1

Photos from SSA's post 04/06/2026

የሲዳማን ሕዝብና ሲዳማ ቡናን በገለልተኛና ውብ አንደበት ላደነቀው ጋዜጠኛ ሰለሞን አባቡ የላቀ ምስጋና እና አክብሮት ይግባው!⭐💥✨

Photos from SSA's post 02/06/2026

የአርሰናል የፕሪሚየር ሊግ ድል በአዲስ አበባ "WE CHAMPIONS 2026" ታሪካዊ ፌስቲቫል ሊካሄድ ነው

​ አርሰናል ከ22 ዓመታት በኋላ ያነሳውን የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ ለማክበር ግንቦት 29/2018 በአዲስ አበባ ስታዲየም ታሪካዊ የእግር ኳስና የመዝናኛ ፌስቲቫል ይካሄዳል። በቫርደስ ኢንተርቴይመንት የተዘጋጀውና በአዋሽ ባንክ (አዋሽብር ፕሮ) ዋና ስፖንሰርነት የሚከናወነው ይህ ዝግጅት፣ ከ30 ሺህ በላይ ታዳሚዎችን እና ዓለም አቀፍ እንግዶችን በአንድ ላይ ያሰባስባል።

​ዝግጅቱ የክለቡን ድል ከመዘከር ባለፈ፣ ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ዝግጅቶችን የማስተናገድ አቅሟን ለዓለም የምታሳይበት መድረክ እንደሚሆን ይጠበቃል። በስፍራውም ታዋቂ ድምፃውያን እና የስፖርት ቤተሰቦች ይታደማሉ።

በክስተቱ ላይ የቀድሞው የአርሰናል እና የኮትዲቯር ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች ኢማኑኤል ኢቡዌ በልዩ እንግድነት ይገኛል። ከእርሱ በተጨማሪ በዓለም ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ካላቸው የእግር ኳስ ሚዲያዎች አንዱ የሆነው AFTV ልዑካን ቡድን ወደ ኢትዮጵያ ይመጣል። በቡድኑ ውስጥ፡

​ሊ ዳጅስ (Lee Judges) – አቅራቢ (ዩናይትድ ኪንግደም)

​ሴሲል ጂ ቶማስ (Cecil Jee Thomas) – አቅራቢ (ዩናይትድ ኪንግደም)

​ጀረሚ (Jeremy) – ዲጂታል ይዘት ፈጣሪ (ደቡብ አፍሪካ) ይገኙበታል።
በዚህ ዝግጀት ላይ ከ 10 በላይ የሆኑ እውቅ እና ወጣት ኢትዮጵያዊ ድምፃዊያን የሙዚቃ ስራቸው እንደሚያቀረቡ ተገልጾ ከነዚህም መካከል ታደለ ሮባ ፣ ልጅ ሚካኤል (ፋፍ) ፣ ሳሚ ዳን ፣ አስጌ ዴንዳሾ ፣ ራሄል ጌቱ ፣ ሮቤል ሚዲቅሳ ፣ ዮ ማሪዮስ ፣ ሚክ ዋን ፣ አማኑኤል የማነ ፣ አዲስ ሙላት እንዲሁም እውቁ የዳስሆል/የአፍሮቢትስ ሙዚቃ ተጫዋቹ ፍራንኪዬ ዲ እና ሌሎችም ድምፃዊያን የሙዚቃ ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ::
የዝግጅቱ ብቸኛ የትኬት መሸጫ መድረክ "አዋሽብር ፕሮ" ነው። ደጋፊዎች ትኬታቸውን በሚከተሉት መንገዶች ማግኘት ይችላሉ፦

​በአዋሽብር ፕሮ አፕሊኬሽን
​በአዋሽ ባንክ ቅርንጫፎች (ከ1,000 በላይ ቅርንጫፎች)
​በአዋሽ ብር ፕሮ ኤጀንቶች
​በአዲስ አበባ ስታዲየም በተዘጋጁ ጊዜያዊ መሸጫ ጣቢያዎች (ከግንቦት 25 እስከ ግንቦት 29)

​ከግዢው ጋር በተያያዘ፣ ትኬታቸውን በቅድሚያ ለሚገዙ ደጋፊዎች የ"WE CHAMPIONS 2026" ይፋዊ ማሊያ የማግኘት ዕድል ተመቻችቷል።

02/06/2026

እንደዚሁ ነው የሚቀጥለው?
That's how it is next?

02/06/2026

ሃገራዊ ምርጫ ዉጤት በ አንድ prophet አማካይነት ይፋ ተደርጋል👇👇

01/06/2026

ይህንን ታላቅ ሕዝብ ማገልገል በእርግጥም መታደል ነው። ነገር ግን ይህ መታደል በትልቅ ተጠያቂነት (Accountability) የታጀበ መሆን አለበት። ሕዝቡ በየምርጫው ተስፋ ሰንቆ ድምጹን ይሰጣል፤ አመራሩ ግን ያንን ተስፋ ምን ያህል እየመለሰው ነው? አሁን ካለንበት ነባራዊ ሁኔታ አንጻር፣ ከምስጋና በላይ የሚቀድመው የሕዝብን ደህንነት ማስጠበቅ እና የኢኮኖሚ ጫናውን መቀነስ ነው። ስልጣን የሕዝብ አገልጋይነት እንጂ የክብር ወንበር አይደለም።

የኢትዮጵያ ሕዝብ አስደናቂም ተአምረኛም ሕዝብ ነው። ከፈጣሪ በቀር ሕዝባችንን አሟልቶ ሊያውቅና ሊገመግም የሚችል ማን ነው? የዳበረ ባህል፣ ሀገር ወዳድና የወል መሻቱን መጠበቅ የሚችል ሕዝብ መሆኑን በዘንድሮው ምርጫ ዳግም ለዓለም አሳይቷል። በዛሬው ታሪካዊ ዕለት፡-

• የሌሊቱ ብርድና ጨለማ ያላስፈራቸው፣
• የቀትሩ ፀሐይና ድንገተኛ ዝናብ ያልበገራቸው
• ሠርግ፣ ኀዘን፣ ወሊድና ሌሎች ማኅበራዊ ሁነቶች ያላገዳቸው፣
• ረጃጅም ሰልፎች ያላታከታቸው፣
• የአካል ጉዳት ድምጽ ለመስጠት ያልገደባቸው፣
• ሕመም እና እርጅና የሀገር ተስፋን ከማየት ያላገዳቸው፣
• የነገ ሀገር ተረካቢ ጨቅላ ልጃቸውን ማዘል ያላደከማቸው፣
• ከምንም በላይ የጠላት ጩኸትና ማስፈራሪያ ያላስቆማቸው ዜጎች፤

በብዙ ውጣ ውረዶች መካከል (against all odds) ያሳያችሁት ጽናት ለዴሞክራሲና ለሀገር ሕልውና የተከፈለ ነውና ከልብ የመነጨ ምስጋና ይገባቸዋል፡፡

ይሄንን ሕዝብ ማገልገል መታደል ነውና ተመራጮች ያከበራችሁን አክብራችሁ ለዴሞክራሲ ሥርዓት ዋጋ የከፈለውን ይሄንን ሕዝብ በንጽሕና ለማገልገል ያብቃችሁ።

Uummanni Itoophiyaa dinqisiisaafi ajaa'ibsiisaadha! Uumaa malee uummata keenya guutummaan beekuufi gamaaggamuu kan danda'u eenyu? Aadaa gabbataa, uummata biyya jaallatuufi fedhiisaa waloo eeguu danda'u ta'uusaa filannoo baranaatiin irradeebiidhaan addunyaatti agarsiiseera. Guyyaa seena-qabeessa har'aatiin:
- Qorriifi dukkanni halkani kan isaani hin sodaachifne,
- Aduun saafaafi bokkaan tasaa kan isaan jilbeenfachiifne,
- Cidhi, gaddi, da'umsiifi taateewwan hawaasummaa kanbiroon kan isaan dhorkine,
- Hiriironni dhedheeroon kan isaan hin nuffisiifne,
- Qaama miidhamtummaan sagalee kennuuf kan isaan hin daangessine,
- Dhukkubniifi dullumni abdii biyyaa arguuf kan isaan hin dhowwine,
- Daa'imasaanii kichuu bor biyya dhaalu baatanii filuun kan isaan hin dadhabsiifne
- Hundumaa caalaa lammiilee iyyiifi sodaachiifni diinaa isaan hin dhaabsifne,
Ciminni bu'aa bayii hedduu keessatti agarsiiftan gatii diimokraasiifi jiraachuu biyyatiif kanfalame waan ta'eef galata guddaatu malaafi.

Uummata kana tajaajiluun carroomuu waan ta'eef filatamtoonni warra isin kabajan kabajjanii uummata sirna diimookraasiif gatii baase kana qulqullummadhaan tajaajiluuf isin haa gahu.

The people of Ethiopia are an extraordinary and remarkable people. Other than the Creator, who can truly know and assess our people in their entirety? Through this year’s election, Ethiopians have once again shown the world that they are a people with a rich culture, deep patriotism, and the ability to safeguard the common good.

On this historic day:

* Citizens who were not intimidated by the cold and darkness of the night,
* Who were not deterred by the midday sun or sudden rain,
* Whom weddings, funerals, childbirth, and other social obligations did not prevent from participating,
* Who were not wearied by long lines,
* Whose physical disabilities did not stop them from casting their vote,
* Those whose illness and old age did not prevent from witnessing the hope of their country,
* Who were not exhausted by carrying their infant children; the future inheritors of the nation,
* And above all, whom the shouting and threats of enemies could not intimidate or stop;

The perseverance you demonstrated amid many challenges and hardships, against all odds, was a contribution made for democracy and for the very survival of the nation. For this, you deserve heartfelt gratitude.

It is a privilege to serve such a people. Therefore, may those who have been elected honor the trust placed in them and serve this people, with integrity and sincerity! A people who have paid a great price for the democratic system. May you be worthy of that responsibility.

Photos from SSA's post 30/05/2026

የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ (አሊቶዎቹ) አዳማ ከተማን 1ለ0 በማሸነፍ መሪነቱን አጠናክሯል። ከተከታዩ መቻል በ8 ነጥብ በመራቅ ለዋንጫው እጅግ ተቃርቧል። ሊጉ ለመጠናቀቅ 4 ጨዋታዎች ብቻ ስለቀሩ፣ ክለቡ የዘንድሮውን የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ ለማንሳት ትልቅ ዕድል አለው። ደጋፊዎችም በታላቅ ተስፋና ደስታ ዋንጫውን እየተጠባበቁ ይገኛሉ።
ROORI SIDAAMA ROORI SIDAAMA ROORI SIDAAMA. 💪💪💥💥

Photos from SSA's post 30/05/2026

የዘንድሮው የ2018 ዓ.ም(2025/26) የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ ማን የሚበላ ይመስላችኋል? አስተያየታችሁን ኮሜንት ላይ ጻፉ!::

24/07/2025

Good night!💊

Website