SNN

SNN

Share

SNN የአማርኛ ዜና ድረ-ገፅ ሲሆን አለም አቀፍ ዜና ፖለቲካዊ፡ኢኮኖሚያዊና ስፖርት የሚተላለፍበት ፔጅ ነው፡፡

15/06/2026

ግብፅ ከቤልጂየም አቻ ተለያዩ

AMN- ሰኔ 8/2018 ዓ.ም

በምድብ ሰባት የምትገኘው ግብፅ ከ ቤልጂየም ጋር ተጫውታ 1ለ1 ተለያይታለች።

ኢማም አሹር የግብፅን ግብ አስቆጥሮ ፈርኦኖቹን መሪ አድርጎ ነበር። ሞሐመድ ሃኒ በራሱ ላይ ያስቆጠረው ግብ ቤልጂየምን አቻ አድርጓል።

በዓለም ዋንጫው አራተኛ ተሳትፎዋን እያደረገች የምትገኘው ግብፅ አሁንም በውድድሩ ድል ማስመዝገብ አልቻለችም።

15/06/2026

የደካማ/ተንኮለኛ /መሪ መገለጫዎች:-

🔐ብቃት የሌለው እና ተንኮለኛ (ክፉ አሳቢ) መሪዎች የሚፈጽሟቸው ተግባራት የአንድን ተቋም፣ ቡድን ወይም ሀገር ህልውና አደጋ ላይ የሚጥሉ ናቸው። እነዚህ መሪዎች በአብዛኛው በግል ጥቅምና በስልጣን ጥም ስለሚመሩ የሚከተሉትን ዋና ዋና ጎጂ ተግባራትን ይፈጽማሉ፦

1.በሴራ እና በመከፋፈል ማስተዳደር (Divide and Rule)
• ሰዎችን ማጋጨት፦ ተንኮለኛ መሪ በበታቾቹ መካከል እርስ በእርስ ጥርጣሬና አለመተማመን እንዲፈጠር ያደርጋል። ሰዎች አንድ ላይ ከሆኑ እሱን ሊቃወሙት እንደሚችሉ ስለሚሰጋ፣ ወሬ በማውራት እና ወገንተኝነትን በመፍጠር አንድነታቸውን ያጠፋል።

• በቡድን መክፈል፦ ሰራተኞችን ወይም ተከታዮችን "የእኔ መስመር ተከታይ" እና "ተቃዋሚ" በማለት ፈርጆ በመካከላቸው የጥላቻ መንፈስ ይዘራል።

2.ብቃት ያላቸውን ሰዎች ማራቅና ማሳደድ
• የበታችነት ስሜት፦ ተንኮለኛ መሪ እውቀትና ክህሎት ያላቸውን ሰዎች እንደ ስጋት ያያቸዋል። የራሱን ድክመት እንዳያጋልጡበት በመፍራት የተማሩ እና ጠንካራ ሰራተኞችን ወደ ጎን ያገላል።

• አሽቃባጮችን መሰብሰብ፦ በዙሪያው የሚያሰባስበው እውነትን የሚናገሩ ሰዎችን ሳይሆን፣ ስህተቱንም ጭምር "ልክ ነህ" እያሉ የሚያጨበጭቡለትን ደካማና አድርባይ ሰዎችን ነው።

3.ተቋማዊ አሰራርንና ህግን ማፍረስ
• የግል ውሳኔ ማብሰል፦ ተንኮለኛ መሪ ህግና መመሪያን አይከተልም። ተቋማዊ አሰራርን በመጣስ ውሳኔዎችን በግል ፍላጎቱና በስሜቱ ላይ ተመስርቶ ያስተላልፋል።

• ድብቅ አጀንዳ መያዝ፦ ውሳኔዎቹ ግልጽነት የሌላቸው፣ ሚስጥራዊ እና ለግል ወይም ለተወሰኑ ቡድኖች ጥቅም ብቻ ያደሉ ይሆናሉ።

4.ስልጣንን ለበቀል እና ለማስፈራሪያነት መጠቀም፦
• ማስፈራራትና ጫና መፍጠር፦ ተከታዮቹ ወይም ሰራተኞቹ በሃሳብ ሲለዩት በስልጣኑ ተጠቅሞ ያስፈራራቸዋል፣ ጥቅማ ጥቅማቸውን ይከለክላል፣ ወይም ከስራ ያባርራል።

• በቀልኝነት፦ ትናንሽ ስህተቶችን እንኳን ይቅር ከመስራትና ከመማር ይልቅ፣ ሰዎችን ለመጉዳትና ለመበቀል እንደ ትልቅ አጋጣሚ ይጠቀምባቸዋል።

5.ሃላፊነት አለመውሰድ (ጥፋትን ወደ ሌላ ማዛወር)
• የአውራ ጣት ስልት (Scapegoating)፦ ተንኮለኛ መሪ ስራ ሲበላሽ ወይም ውድቀት ሲያጋጥም መሪነቱን ወስዶ አያስተካክልም። ይልቁንም ጥፋቱን በሙሉ ወደ በታችኞቹ በማላከክ ራሱን ንጹህ ለማድረግ ይሞክራል።

• የሌሎችን ስኬት መስረቅ፦ ቡድኑ ጥሩ ስራ ሲሰራ ግን ውጤቱን የራሱ ብቻ አድርጎ ያቀርባል።

6.አርቆ አሳቢነት ማጣትና በአጭር እይታ መመራት
• ጊዜያዊ ጥቅም ማሳደድ፦ ለረጅም ጊዜ የሚዘልቅ እቅድና ራዕይ የለውም። ዛሬን በሴራና በውሸት ማለፍ ላይ ብቻ ያተኩራል።

• ለልማትና ለለውጥ ዝግ መሆን፦ አዳዲስ ሃሳቦችን እና ተቋማዊ ለውጦችን አይቀበልም። ለውጥ ከመጣ ጥቅሜ ይነካል ብሎ ስለሚሰጋ የቆየውንና ያልሰራውን አሰራር ሙጥኝ ብሎ ይኖራል።

ባጭሩ ተንኮለኛ መሪ የቆመበትን ተቋም የሚያፈርስ፣ የሰዎችን ተነሳሽነት የሚገድል እና በሰላም አብሮ የመስራት ባህልን የሚያጠፋ "መርዛማ መሪ" (Toxic Leader) ነው።

📌እርስዎስ እንዲህ ዓይነት መሪ ገጥሞዎት ያውቃል ??

15/06/2026

ስፔን ከኬፕ ቨርዴ 0 ለ 0 ተለያዩ
***********

በዓለም ዋንጫ የምድብ 8 የመጀመሪያ ጨዋታ ስፔን ከ ኬፕ ቨርዴ የተገናኙበት ጨዋታ ግብ ሳይቆጠርበት ተጠናቋል።

በዓለም ዋንጫ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሳተፈችው ደሴቲቱ ሀገር ኬፕ ቨርዴ የመጀመሪያ አንድ ነጥቧን አግኝታለች።

ላሚን ያማልን ተቀያሪ ወንበር ላይ አድርጋ ጨዋታዋን የጀመረችው ስፔን በኳስ ቁጥጥሩ እና የግብ ዕድሎችን በመፍጠር የተሻለች ብትሆንም የመጀመሪያ ጨዋታዋን በአቻ ውጤት አጠናቃለች።

Photos from SNN's post 15/06/2026

የኢራን ብሔራዊ ቡድን የመጀመሪያ የምድብ ጨዋታውን ለማድረግ አሜሪካ ገብቷል
*********************

በ2026 ዓለም ዋንጫ ላይ የሚሳተፈው የኢራን ብሔራዊ ቡድን፤ የመጀመሪያ የምድብ ጨዋታውን ለማድረግ አሜሪካ ካሊፎርኒያ ደርሷል።

ብሔራዊ ቡድኑ በሎስ አንጀለስ ስታዲየም ከኒውዚላንድ ጋር የመክፈቻ ጨዋታውን ዛሬ ለሊት 10፡00 ሰዓት ላይ ያከናውናል ።

የኢራን ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ አሚር ቃሌኖይ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፣ ቡድናቸው ምንም ዓይነት ከሜዳ ውጪ ለሚነሱ ሀሳቦች ትኩረት ሳይሰጥ በጨዋታው ላይ ብቻ ትኩረት ማድረጉን ገልጸዋል።

አሰልጣኙ አክለውም ቡድኑ እጅግ ማራኪ እና ከፍተኛ ብቃት የተሞላበት ጨዋታ ለደጋፊዎቹ ለማሳየት መዘጋጀቱንና ዋናው ዓላማቸው እግር ኳስን በመጫወት በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ደጋፊዎቻቸውን ማስደሰት እንደሆነ አስታውቀዋል።

በዘረንቶስ ሰለሞን

15/06/2026

📆 ሰኞ ማክሰኞ ረቡዕ የሚደረጉ የዓለም ዋንጫ የምድብ ጨዋታዎች ።

15/06/2026

ትላንት በተደረጉ ጨዋታዎች የክለባችን ተጫዋቾች ቫንዳይክ እና ኢሳክ የጨዋታው ኮከብ ሆነው ተመርጠዋል!🇳🇱🇸🇪

15/06/2026

🎇የሁለቱ ተወዳጅ ኮከቦች ውህደት ✨

➤አሌክሳንደር ኢሳቅ በዛሬው እለት ለሀገሩ ስዊድን ጎል አስቆጠረ።

➤ቪክቶር ዮከሬሽ ለአሌክሳንደር ኢሳቅ ጎል አሲስት አደረገለት።

➤ቪክቶር ዮከሬሽ በዛሬው እለት ለሀገሩ ስዊድን ጎል አስቆጠረ።

➤አሌክሳንደር ኢሳቅ ለቪክቶር ዮከሬሽ ጎል አሲስት አደረገለት።

➤ሁለቱ አጥቂዎች በዛሬው እለት በአለም ዋንጫ የመጀመሪያ ጎላቸውን አስቆጥረዋል።

➤ሁለቱ አጥቂዎች በዛሬው እለት በአለም ዋንጫ የመጀመሪያ አሲስታቸውን አድርገዋል።

➤ሁለቱ አጥቂዎች ያለምንም ርህራሄ፣ ጭካኔ በተሞላበት መንገድ፣ ቱኒዚያን አፈራርሰው ጥለዋታል።

➤ሀገራቸው ስዊድን የአለም ዋንጫ የምድብ የመጀመሪያ ጨዋታዋን ቱኒዚያን 5️⃣ለ1️⃣ እንድታሸንፍ ቁልፍ ሚና ተጫውተዋል።

Photos from SNN's post 15/06/2026

በዓለም ዋንጫ ኮትዲቯር ስታሸንፍ ኔዘርላንድ አቻ ተለያየች
***************************

የ23ኛው ዓለም ዋንጫ የምድብ ጨዋታዎች ሌሊት ቀጥለው የተካሄዱ ሲሆን፤ በምድብ 5 የምትገኘው ኮትዲቯር ኢኳዶርን 1 ለ 0 በመርታት ሙሉ ሦስት ነጥብ አግኝታለች።

ለኮትዲቯር ብቸኛዋን የማሸነፊያ ግብ ያስቆጠረው የማንቸስተር ዩናይትዱ አማድ ዲያሎ በጨዋታው ፍፃሜ 90ኛው ደቂቃ ላይ ነው።

በተደጋጋሚ የዓለም ዋንጫ የፍፃሜ ተፋላሚ የሆነችው ኔዘርላንድ ከጃፓን ያደረጉት ጨዋታ 2 ለ 2 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቅቋል።

በዚህ የምድብ ስድስት ጨዋታ ሁሉም ግቦች በሁለተኛው አጋማሽ ነው የተቆጠሩት።

ቨርጂል ቫንዳይክና ክሪሴንሶ ሰመርቪል ለኔዘርላንድ ሲያስቆጥሩ፤ ኬይቶ ናካሙራ እና ዳይቺ ካማዳ የጃፓንን ግቦች ከመረብ አሳርፈዋል።

15/06/2026

🎇ብራዚልን ብቻውን ያፈራረሰው ወጣቱ አማካይ✨

➤ከ8️⃣ አመት በፊት የ2018ቱ የዓለም ዋንጫ ላይ የ🔟 አመት ልጅ ሳለ ሞሮኮን በስታድየም ተገኝቶ ደግፏታል።

➤በ2026 በትናትናው እለት ለሞሮኮ ብሄራዊ ቡድን በአለም ዋንጫ የመጀመሪያ ጨዋታውን አድርጓል።

➤አዮብ ቡአዲ ሀገሩ ሞሮኮ ከብራዚል ጋር አቻ በተለያየችበት ጨዋታ ላይ ያሳየው ድንቅ ብቃት ከብዙዎች አድናቆትን ተችሮታል።

➤የመሀል ሜዳው ሊቅ አዮብ ቡአዲ ካሰሚሮ፣ ብሩኖ ጊማሬሽ እና ሉካስ ፓኩየታን በእራሱ ቁጥጥር በማዋል የብራዚልን መሀል አፈራርሶ ጥሎታል።

➤የ1️⃣8️⃣ ዓመቱ ኮከብ በአጠቃላይ የኮከቦች መፍለቂያ የሆነውን የብራዚል ብሄራዊ ቡድንን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሮታል።

➤ፈረንሳይ ለአለም ዋንጫ እንዳልጠራችው ሲያውቅ በምትኩ የእናት እና አባቱ ሀገር ሞሮኮን መረጠ።

➤ፈረንሳይ ለወደፊት እንደምትፀፀትበት በትክክል አስመስክሯል።

➤በፈረንሣዩ ክለብ ሊል የሚጫወተው አዮብ ቡአዲ በአርሰናል፣ በፒኤስጂ እና በባየርን ሙኒክ በጥብቅ ይፈለጋል።

Want your public figure to be the top-listed Public Figure in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Address


Tor Hayloch
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 09:00 - 18:00
Tuesday 09:00 - 18:00
Wednesday 09:00 - 18:00
Thursday 09:00 - 18:00
Friday 09:00 - 18:00
Saturday 09:00 - 18:00