EBS SPORT
We love football forever. It is recreation, entertainment, sport & every thing for us!
እግር ኳስን በፌስቡክ
Comedian Yasin
Rayan cherki Confidence over Arsenal
Arsenal Manchester City
Cherki
ReelShort TV
22/03/2026
ማንችስተር ሲቲ ሻምፒዮን 🏆 ሆኗል !
ማንችስተር ሲቲ ከአርሰናል ጋር ያደረገውን የካራባኦ ካፕ ፍፃሜ ጨዋታ 2ለ0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ሻምፒዮን ሆነዋል።
የማንችስተር ሲቲን የማሸነፊያ ግቦች ኦሬሊ 2x ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።
ማንችስተር ሲቲ 9️⃣ ኛ የእንግሊዝ ካራባኦ ካፕ ዋንጫቸውን አሸንፈዋል።
መድፈኞቹ ለመጨረሻ ጊዜ በ 1993 ድል ካደረጉ በኃላ የካራባኦ ካፕ ዋንጫ ማሸነፍ አልቻሉም።
ማንችስተር ሲቲ ካደረጋቸው 1️⃣0️⃣ የካራባኦ ካፕ ፍፃሜ ጨዋታዎች 9️⃣ አሸንፏል።
22/03/2026
አርሰናሎች የካራባኦ ካፕ ዋንጫን ከ 33ዓመታታ በኃላ ለማሸነፍ የሚያደርጉት ፍልምያ
መድፈኞቹ ለመጨረሻ ጊዜ በ 1993 ድል ካደረጉ በኃላ ዋንጫውን ለማሸነፍ አልቻሉም።
አርሰናሎች በሶስት አጋጣሚ ለፍፃሜ መድረስ ቢችሉም ባለፉት አመታት አንዱንም ማሸነፍ ሳይችሉ ቀርተዋል።
በዚህም ባለፉት ሶስት ፍፃሜዎች :-
እ.ኤ.አ 2007 ዓ.ም :- ቼልሲ 2-1 አርሰናል
እ.ኤ.አ 2011 ዓ.ም :- በርሚንግሀም ሲቲ 2-1 አርሰናል
እ.ኤ.አ 2017 ዓ.ም :- ማንችስተር ሲቲ 3-0 አርሰናል
19/03/2026
The quarter-finals are looking crazy!
I think Arsenal have chance.
17/03/2026
አርሰናል እና ፒኤስጂ ድል አድርገዋል !
በሻምፒየንስ ሊግ ጥሎ ማለፍ የመልስ ጨዋታ አርሰናል ባየር ሌቨርኩሰንን 2ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
መድፈኞቹን አሸናፊ ያደረጉ ግቦች ኢቤሬ ኢዜ እና ዴክላን ራይስ አስቆጥረዋል።
ውጤቱን ተከትሎ አርሰናል በድምሩ 3ለ1 በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር አልፏል።
በሌላ ጨዋታ ፒኤስጂ ከቼልሲ ያደረገውን ጨዋታ 3ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
የፒኤስጂን የማሸነፊያ ግቦች ቅቫራስኬሊያ ፤ ባርኮላ እና ማዩሉ አስቆጥረዋል።
ፒኤስጂ በድምር ውጤት 8ለ2 በማሸነፍ ሩብ ፍፃሜውን ተቀላቅሏል።
ሪያል ማድሪድ በበኩሉ ከማንችስተር ሲቲ ጋር ያደረገውን የመልስ ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
የሪያል ማድሪድን የማሸነፊያ ግብ ቪንሰስ ጁኒየር 2x ሲያስቆጥር ለማንችስተር ሲቲ ሀላንድ ከመረብ አሳርፏል።
ሎስ ብላንኮዎቹ በድምር ውጤት 5ለ1 በማሸነፍ ቀጣዩን ዙር ተቀላቅለዋል።
1st half what a amazing chances of arsenal
17/03/2026
እረፍት
አርሰናል 1 - 0 ባየር ሌቨርኩሰን
⚽ ኢዜ
ድምር ውጤት :- 2-1
31/01/2026
ቼልሲ ዌስትሃም ዩናይትድን 3 ለ 2 አሸነፈ
ምሽት 2፡30 ላይ በተደረገው ጨዋታ የቼልሲን የማሸነፊያ ግቦች ዣኦ ፔድሮ፣ ኩኩሬላ እና ኢንዞ ፈርናንዴዝ አስቆጥረዋል፡፡
የዌስትሃም ዩናይትድን ግቦች ደግሞ ቦውን እና ሳመርቪሌ ከመረብ አሳርፈዋል፡፡
07/01/2026
በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ስምንት ጨዋታዎች ይደረጋሉ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ21ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ዛሬ ምሽት ስምንት ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡
ከሰንደርላንድ እና ቼልሲ ጋር ያደረጋቸውን ያለፉት ሁለት ጨዋታዎች አቻ የተለያየው ማንቼስተር ሲቲ ወደ አሸናፊነት ለመመለስ ምሽት 4 ሰዓት ከ30 በኢትሃድ ብራይተንን ያስተናግዳል፡፡
አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካን በማሰናበት የ41 ዓመቱን እንግሊዛዊ ሊያም ሮዚኒየር የሾመው ቼልሲ በተመሳሳይ ምሽት 4 ሰዓት ከ30 በክራቨን ኮቴጅ ፉልሃምን ይገጥማል፡፡
ባሳለፍነው ሰኞ አሰልጣኝ ሩበን አሞሪምን ያሰናበተው ማንቼስተር ዩናይትድ ወደ ተርፍ ሙር አቅንቶ ምሽት 5 ሰዓት ከ15 በወራጅ ቀጣናው የሚገኘውን በርንሌይ ይገጥማል፡፡
በሊጉ ያለፉትን ሁለት ጨዋታዎች አቻ የተለያዩት ማንቼስተር ዩናይትዶች ወደ አሸናፊነት ለመመለስ በቀድሞ ተጫዋቻቸው ዳረን ፍሌቸር እየተመሩ ወደ ሜዳ ይገባሉ፡፡
👉ፉሊሃም ከቼልሲ
👉ማን ሲቲ ከብረይተን
👉አስቶን ቪላ ከክሪስታል ፓላስ
👉ቦርንማውዝ ከቶተንሃም ሆትስፐር፣
👉ብሬንትፎርድ ከሰንደርላንድ፣ ኤቨርተን ከወልቭስ ምሽት 4 ሰዓት ከ30 እንዲሁም
👉ኒውካስትል ዩናይትድ ከሊድስ ዩናይትድ ምሽት 5 ሰዓት ከ15 ይጫወታሉ፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!
19/10/2025
Mechester United አሸነፈ!!!!!!
ሊቨርፑል 1 - 2 ማንችስተር ዩናይትድ
⚽ ጋክፖ ⚽ ምቤሞ
⚽ ማጓየር
-
ባሎን ዶር አሸናፊ ይፋ ሆኗል !
በፍራንስ ፉትቦል አዘጋጅነት ለ 69ተኛ ጊዜ በተካሄደው የአመቱ የወንዶች ምርጥ እግር ኳስ ተጫዋች የሽልማት ስነ-ስርዓት አሸናፊው ታውቋል ።
የ 2025 የአመቱ ምርጥ የወንድ እግር ኳስ ተጫዋች በመባል ፈረንሳዊው የፒኤስጂ የፊት መስመር ተጫዋች ኡስማን ዴምቤሌ ማሸነፍ ችሏል።
ኡስማን ዴምቤሌ የመጀመሪያው የሆነውን የባሎን ዶር ሽልማት ከሮናልዲንሆ እጅ መቀበል ችሏል።
በሽልማቱ ላሚን ያማል #ሁለተኛ ፣
ቪቲንሀ #ሶስተኛ እንዲሁም
ሞሀመድ ሳላህ #አራተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል።
እንዲሁም
5ኛ - ራፊንሀ
6ኛ - አሽራፍ ሀኪማ
7ኛ - ኪሊያን ምባፔ
8ኛ - ኮል ፓልመር
9ኛ - ጂያንሉጂ ዶናሩማ
10ኛ - ኑኖ ሜንዴዝ በመሆን አጠናቀዋል።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Addis Ababa