Addis Ababa Corridor and Riverside Development Management Authority

Addis Ababa Corridor and Riverside Development  Management Authority

Share

Addis Ababa; Ethiopia

14/08/2026
13/08/2026

የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ምክትል ስራአስኪያጅ እና የቀድሞ የልደታ ክፍለከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ በነበሩት ወ/ሮ አበባ እሸቴ ህልፈት ጥልቅ ሀዘን ተሰምቶኛል ።

ለመላው ቤተሰቦቻቸው ፣ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እና የስራ ባልደረቦቻቸዉ መፅናናትን እመኛለሁ።
ፈጣሪ ነብሳቸውን በአፀደ ገነት ያኑር

Lubbuun darbuu Aadde Ababaa Ishatee, Itti Gaafatamtuu Itti Aantuu Seera Kabachiisaa Magaalaa Finfinnee fi Hoji Raawwachiistuu Olaanaa Kutaa Magaalaa Lidataa kan turanitti gaddi guddaan natti dhaga'ameera.

Maatii isaanii, firoottan isaanii fi waahillan hojii isaanii hundaaf jajjabinan hawwa.

Waaqni lubbuu isaanii Jeennata haa jiraachisu

Photos from Addis Ababa Corridor and Riverside Development  Management Authority's post 12/08/2026

ቀበና !
የአዲስ አበባ ሌላኛዉ ውብ ገጽታ መገለጫ!

Qabbannaa!
Ibsituu fuula miidhagina Finfinnee kan biraa!

:- ከንቲባ Adanech Abiebie- አዳነች አቤቤ

Photos from Addis Ababa Corridor and Riverside Development  Management Authority's post 09/08/2026

የከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት...!

ተመራቂዎች እንኳን ደስ አላችሁ!

በተለያየ ማህበራዊ ችግር ውስጥ የነበሩ በየለነገዋ የሴቶች ተሃድሶና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል በ5ኛ ዙር የክህሎት እና የስብዕና ግንባታ የሰለጠኑ 858 እህቶቻችንን አስመርቀን ወደ ስራ አሰማርተናል።

በከተማችን ከምንሰራቸው ሰው ተኮር ስራዎች አንዱ ትላንት በጎዳና፣ በችግር እና በተለያዩ ማህበራዊ ቀውሶች ውስጥ የነበሩ ሴቶችን በሙያ ክህሎትና ስብዕና ገንብተን ከነበሩበት አስከፊ ህይወት በማውጣት ወደ ተሻለ ህይወት የምናሰማራበት ቀዳሚው ተግባር ነው።

አዲስ አበባችን ማህበራዊ ፍትህ የሰፈነባት እንዲሁም ለዘመናት የከረሙ ስብራቶቿ የሚጠገኑባት ከተማ የማድረግ የተግባር ውጤት ፍሬ ማሳያዎች ከለነገዋ ተመርቀው አዲስ ህይወት እየመሩ ያሉት ሴቶች እህቶቻችን ናቸው።

የዛሬዎቹ ተመራቂዎችን ጨምሮ በማዕከሉ በድምሩ 3259 ሰልጣኞችን አስመርቀን ወደ ስራው ዓለም እንዲቀላቀሉ በማድረግ ህይወታቸውን በተሻለ መንገድ እንዲመሩና ለሌሎችም አርዓያ እንዲሆኑ አድርገናል።

ውድ ተመራቂዎች፤ አስከፊውን ትላንታችሁን አልፋችሁ፤ በማዕከሉ በነበራችሁ ቆይታ በቀሰማችሁት ክህሎት እና ባገኛችሁት የተሀድሶ ስልጠና ዛሬ ማሸነፍ ችላችኋል፤ ነገም በስራው ዓለም ስኬታማ ለመሆን የሚገጥማችሁን ማንኛውንም ፈተና አሸንፉችሁ ህይወታችሁን ይበልጥ ብሩህ እንደምታደርጉ እናምናለን።

በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ!

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ!

09/08/2026

የአዲስ አበባ ወንዞች የውበት መነሻዎች!!

Photos from Addis Ababa Corridor and Riverside Development  Management Authority's post 07/08/2026

የከንቲባ አዳነች አቤቤ መልእክት...!

ዛሬ በቤኒን ሪፐብሊክ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽንና ኢኖቬሽን እና ፈጠራ ሚኒስትር ማሁና አክፕሎጋን የተመራውን የልዑክ ቡድን ተቀብለን በከተማችን እየተገበርነው ያለውን Smart City (ስሉጥ ከተማ) ግንባታ ልምድ አካፍለናል።

ቤኒን የጀመረችውን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ለማሳካት በከተማችን ተግብረነው ውጤታማ እየሆነ ያለውን Smart City (ስሉጥ ከተማ) ግንባታ በተለይ በዋና ዋና ግቦች ( Smart Economy, Smart Environment, Smart Governance, Smart Living, Smart Mobility, Smart People) እና ለስኬቶቻችን መሰረት የሆኑት የተቋማት ቅንጅት፣ የህጎችና ደንቦች ትግበራ፣ የህዝብ ተሳትፎ፣ የመንግስትና የግል ዘርፍ ቅንጅታዊ ስራዎችን ለልዑክ ቡድኑ አካፍለናል።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!

Photos from Addis Ababa Corridor and Riverside Development  Management Authority's post 03/08/2026

ዛሬም በጋራ ሆነን ሌላ ታላቅ ታሪክ ፅፋናል !!
ተስፋችንንም ተክለናል!

በከተማችን አዲስ አበባ “ተስፋን እንትከል!” በሚል መሪ ቃል በአንድ ጀንበር ሲከናወን የዋለውን የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር እጅግ ደማቅ በሆነ ነዋሪዎቻችን በነቂስ በመውጣት ፣በሚያስደንቅ ርብርብ ከዕቅዳችን በላይ 1.5 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል ሌላ አዲስ ታሪክ ፅፈናል፣ ሌላ አዲስ ድል አሳክተናል።

በእርግጥም ስንተባበር እንችላለን! ሁላችንም በአንድነት ተግተን ስንሰራ ለዛሬ ብቻ ሳይሆን ለትውልድ የሚሻገር አሻራ እናኖራለን፤ የማይነጥፍ ምንዳም እናኖራለን።

ይህ ታላቅ ስኬት እውን ይሆን ዘንድ ከማለዳው ጀምሮ ላደረጋችሁት የማይታክት ጥረት፣ ላሳያችሁት አስደናቂ አብሮነት እና የባለቤትነት ስሜት አሻራችሁን ላኖራችሁ የከተማችን ነዋሪዎች እና ላስተባበራችሁ አመራሮቻችን በከተማዋ አስተዳደር ስም ልባዊ ምስጋናዬን አቀርባለሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ!

:-ከንቲባ Adanech Abiebie- አዳነች አቤቤ

#805.3Milion

Photos from Addis Ababa Corridor and Riverside Development  Management Authority's post 03/08/2026

"እንኳን ለ8ኛ ዙር የአረንጋዴ አሻራ የአንድ ጀንበር ችግኝ ተከላ ቀን አደረሰን !

ዛሬ በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል አገራዊ ንቅናቄ አዲስ አበባችንም በሰፊ ንቅናቄ የተተከለ ነዉ።

ለአንድ ጀምበር አረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብሩ 176 የሚሆኑ ቦታዎች ተለይተዋል። የሚተከሉ ችግኞችን የጽድቀት መጠን በሚጨምር መልኩ በባለሙያ እየተገዘ በመከናወን ላይ ይገኛል።
የምንተክላው ተስፋን ፤ የኢትዮጵያ ብልፅግና፥ ለነገ ትውልድ የምናስተላልፈው ለምለሟ ኢትዮጵያን በምናባችን አይተን፥ በሃሳብ አንድ ሆነን፥ በተግባራችን በእጆቻችን ተክለን ውዷ ሃገራችን አረንጓዴ እያለበስናት ነው ።

የምንተክለው ምግባችን፥ ጥላ፥ ውበት ነው። እየተከልን ያለነው ነገ በአየር መዘባት ምክንያት የሚወጣውን የብክለት፥ የጤና ችግር፥ የጎርፍ አደጋን አስቀድመን ለመከላከል ነው ።
የአረንጓዴ አሻራ ህጻናት፥ ወጣቶች፥ ሴቶች አዋቂዎች ፥ አዛውንቶች በጋራ የምናሳካው ነው ። የተከልነውን በጋራ እንክባከብ፥ እንጠብቅ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ!"

- ከንቲባ Adanech Abiebie- አዳነች አቤቤ

Photos from Addis Ababa Corridor and Riverside Development  Management Authority's post 03/08/2026

!

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮሪደር እና ወንዝ ዳርቻ ልማት አስተዳደር ባለስልጣን አመራሮች እና ሰራተኞች የ8ኛው የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሀግብር በፎቶ!

Photos from Addis Ababa Corridor and Riverside Development  Management Authority's post 02/08/2026

የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ፤ ለትውልድ የሚሻገር የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ!

የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም፣ የደን ሽፋንን ለመጨመር እና አካባቢን ለመጠበቅ በኢትዮጵያ በሀገር ደረጃ የሚከናወነው የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃግብር ለትውልድ የሚሻገር የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ ፕሮግራም ነው፡፡

በመርሃ ግብሩ ሚሊዮኖችን በማሳተፍ ቢሊዮኖች ዛፎችን መትከል ተችሏል፡፡ በፕሮግራሙ አካባቢን መጠበቅ፥ የአፈር መሸርሸርን መቀነስ ፥ የተራቆቱ መሬቶችን ማልማት፡ የውሃ ምንጮች እንዲጎለብቱ እና የአረንጓዴ ሽፋን በማሳደግ ተስማሚ ምህዳር እንዲፈጠር ማድረግ ተችሏል።

በከተማችንም ከ2011 ዓ.ም እስከ 2018 ዓ.ም ድረስ ነዋሪው በየዓመቱ በነቂስ በመውጣት ከ90 ሚሊዮን በላይ የጥላ ዛፎች፤ የውበትና የፍራፍሬ እፅዋት ተተክለዋል፡፡ በከተማችን በተሰራው የአረንጓዴ ልማት ስራዎች የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከመጀመሩ በፊት የነበረውን የከተማችን የአረንጓዴ ሽፋን ከ 2.8% ወደ 24% ማሳደግ ተችሏል።

በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በከተማችን በየዓመቱ በሚሊዮኖች ችግኞች ተተክለዋል፡፡
በ2011 ዓ.ም 6,084,371
በ2012 ዓ.ም 8,511,531
በ2013 ዓ.ም 11,445,961
በ2014 ዓ.ም 14,795,585
በ2015 ዓ.ም 17,445,385
በ2016 ዓ.ም 26,720,918
በ2017 ዓ.ም 5,644,620 ችግኞች ተተክለዋል።
በአንድ ጀንበር ችግኝ ተከላ ዘመቻም እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ችግኞች ተተክለዋል።

በከተማችን አዲስ አበባ በአንድ ጀንበር መርሃ ግብሮች ከ2011 እስከ 2018 ዓ.ም ብቻ በድምሩ 17.6 ሚሊዮን ችግኞች ተተክለዋል።
በከተማችን በአንድ ጀንበር መርሃ ግብር፡
በ2011 ዓ.ም 1 ሚሊዮን
በ2012 ዓ.ም 2 ሚሊዮን
በ2013 ዓ.ም 1 ሚሊዮን
በ2014 ዓ.ም 4 ሚሊዮን
2015 ዓ.ም 3 ሚሊዮን
2016 ዓ.ም 4.5 ሚሊዮን
2017 ዓ.ም 1.1 ሚሊዮን ችግኞች ተተክለዋል፡፡

ነገ ሃምሌ 27/2018 ዓ.ም በአንድ ጀንበር ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በከተማችን ከ1 ሚሊዮን በላይ ችግኝ ለመትከል ሙሉ ዝግጅት ተደርጓል፡፡

በእነዚህ ዓመታት ውስጥ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ችግኝ መትከል ብቻ ሳይሆን ትኩረቱ ከብዛት ባልተናነሰ በጥራት፣ በአገር በቀል ዛፎች፣ በከተማ ውበትና በኮሪደር ልማት ለተዘጋጁ ቦታዎች ተስማሚ የሆኑ ችግኞችን መትከል ላይ በማተኮር የአረንጓዴ ልማት ስራው ተጠናክሮ ቀጥሏል።

በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ህብረተሰቡ በባለቤትነት ስሜት በየዓመቱ በስፋት እየተሳተፈ በሚሊዮኖች ችግኞችን ይተክላል፣ የተተከሉ ችግኞች እንዲፀድቁም የእንክብካቤ ስራዎችን ያከናውናል፡፡

Address


Addis Ababa