Abe Sam
ስለኢትዮጵያና ስለጀግናው መከላከያ ሰራዊት ውሎ ክግንባር የ? This page is about sharing the adventures of the Defense Forces
22/03/2022
ውዱ ልጄ ፈጣሪ በጤና ያሳድግህ ፨፨፨ ካንተ ርቆ መኖር ምንኛ ከባድ ነው?
እኔ ሃገሬ መቄትን የማውቀው በጀግንነት ነው ለዚህም ሩቅ ሳልሄድ የ "አንችም" ድልን ማንሳት በቂ ነው። ትህነግ የዘመናት ጥላታችን ነው። በሴራ የተካነ፣ በዕብሪት ልቡ ያበጠ፣ በውክልና ጦርነት ያበደ፣ ጨቅላ ህፃናትን ለስልጣኑ ማደለቢያ ሲጠቀም እንደሰው ህሊናው የማይሸነቁጥ አሳፋሪ ስብስብ ነው።
በዚያ ላይ በሃሰት ወሬ ጥርሱን የነቀለ ወሮበላ ቡድን ነው። ታዲያ እንዴት ለዚህ ከንቱ መንገድ መክፈት ቀለለን። ከሃዲው ትህነግ እስታይሽ ያዝኩኝ ሲል ቀድመን ከተማችን ለወራሪ ሰጥተን ከወጣን ጀግንነታችን ምኑ ላይ ነው? የሸሸንበት ቦታስ ላለመምጣቱ ማነው ማረጋገጫ የስጠን?
ይልቅ የሚበጀን እንደተፈጠርንበት ጀግንነት ጀግነን፣ መውጫ ጠፍቶት የሚደናበረውን ሽብርተኛ ዋጋውን መክፈል ነው። እናም መቄት ሆይ ስሚኝ የተፈጠርሽበትን የጀግንነት መቀነት ጠበቅ አድርጊና ደካማና ህፃናት ልጆችሽን ከባዶ ጭንቀት ገላግያቸው።
ምንም ባልተፈጠረ ነገር አላስፈላጊ መንገላታት አያስፈልግም።
ውድ የሃገሬ ወጣቶች ዘመኑ የሚጠይቀውን አሰተዋይነት በጥልቀት ተረድታችሁ ራሳችሁንና ምስኪን ወገናችሁን ከረብ የለሽ ጭንቀት ታደጉት።
እንደገባኝ አሁን የከበደን ከጦርነቱ በላይ እዚህም እዛም የሚነዛው የሃሰት ወሬ ነው። ለዚህ መፍትሄ ቀዳዳ የሌለው አንድነት መገንባት ነው።
መልካም ነገር ሁሉ ወደኛ በቀረበ ቁጥር አስፈሪ ነገሮች ቀኑን ያጨልማሉ። ጨለማውን የተጋፈጠና በብልጠት የተጓዘ ብርሃኑን የማየት እድል አለው።
ለሁሉም ሳናውቀው የጁንታውን መንገድ እያቀናነው ነውና ራሳችን መመልከቱ አይከፋም። ጠንክረን ሃገራችን እናጠንክር።
31/07/2021
ከኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የተሰጠ ማሳስቢያ
| የህዝባችን አንድነትና ፅናት ለመሸርሸር ጠላት እየፈበረከ የሚረጫቸውን አሉባልታዎች መከላከል ያስፈልጋል ሲል የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት አሳስቧል።
በመላው ኢትዮጵያ ህዝብ የታየው ህብረትና በአንድነት መቆም ጠላቶቻችንን አስደንግጧል ያለው መከላከያ የአሸባሪው ጁንታ ጎራ በፍርሃት እንዲርድ አድርጓል፡፡
ሆኖም የህዝባችን አንድነትና ፅናት ለመሸርሸር ጠላት እየፈበረከ የሚረጨው አሉባልታዎችን መከላከል ፣ ሳያውቁ ጠላት ሆን ብሎ የሚለቀውን አሉባልታ በመቀባበል የጠላት ወኪል የሚሆኑ ወገኖችን መምከር ፣ መገሰፅ ያስፈልጋል፡፡
በአሸባሪው ህወሓት እየተፈበረኩ በማህበራዊ ሚዲያ የሚረጩ የውሸት መረጃዎችን ፣ በየአገልግሎት መስጫዎች የሚነዙ አሉባለታዎች ፣ ስለ ሠራዊታችን የግዳጅ ውሎ ሰው የሚቀባበለው ወሬ ለጠላት ግብዓት የሚሆኑና የወገንን እንቅስቃሴን የሚጎዱ ናቸው ነው ያለው፡፡
ስለዚህ ወገኖች ሁሉ ቀጥሎ የተዘረዘሩ ጉዳዮችን በማህበራዊ ሚዲያና እርስ በርስ እንዳንቀባበል እና ሼር እንዳናደርግ እናሳስባለን፡፡
1.የመረጃ ምንጩ ያለታወቁ ቀልብ የሚስቡ መረጃዎችን ሼር ከመድረግ እንቆጠብ፤
2.የሠራዊታችን ከቦታ ቦታ እንቅስቃሴ ፣ የሚጓጓዙ የጦር መሳርያዎች አይነትና ብዛት ፣ የሎጂስቲክስ ድጋፍ እንቅስቃሴዎችን ፎቶ በማንሳት በማህበራዊ ሚዲያ አንለጥፍ ፡፡ የህን የሚፈፅም ከተመለከቱም ያስቆሙ፤ ፍቃደኛ ካልሆነ ለፀጥታ ሃይሎች ወዲያው ይጠቁሙ፡፡
3.የጠላትን ትንኮሳን የመከላከል ሥራ በማህበራዊ ሚዲያ አንለጥፍ፤
4.አንዳንድ ዩ-ቲዩበሮች ለሽርፍራፊ ሳንቲም ብላችሁ ሰበር ! ሰበር ! እያላችሁ ምንጩ ያለታወቀና ያለተረጋገጠ አሉባልታ በመንዛት የወገናችሁንና የሀገራችሁን ጥቅም አሳልፋችሁ ለጠላቶቻችን አትስጡ፤
5.ወቅታዊ ወታደራዊ እንቅስቃሴን በሚመለከት በታወቀ መንግስታዊ ወይም በሚመለከተው የመከላከያ ሃላፊ ወይም አዛዥ ያልተሰጠ መረጃ ከሆነ አንመን ፣ ሼርም አናድርግ፤
6.ሁሉም ሀገር ወዳድ ዜጋ በሰራዊታችን ግዳጅ አፈፃፀምና በህዝባችን ሞራልና ስነ-ልቦና የበላይነት ላይ ተፅዕኖ የሚፈጥሩና ጠላት ሆን ብሎ የሚለቃቸውን መረጃዎች ባለማሰራጨት እንተባበር ብሏል የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት በፌስ ቡክ ገጹ፡፡
28/07/2021
ʺከእንግዲህ አይኖርም ነገር ማለሳለስ፣
እነርሱም አያርፉም እኛም አንመለስ "
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 17/2013 ዓ.ም (አሚኮ) አንተ ዓለም ቆሞ ያጨበጨበለት፣ በጀግንነቱ የተደነቀበት፣ ጠላት ከባሕር ማዶ ሆኖ የተሸበረለት፣ ኃያላን ነን ያሉት እጅ የነሱለት፤ ጠላት እንደ ቆሎ በእጁ የሚጨብጥ፣ እንደ ቋንጣ ከፍም ላይ የሚያርመጠምጥ፣ የጠላትን ጉሮሮ ለማነቅ የሚቋምጥ፣ በግራው እያረሰ፣ በቀኙ እየተኮሰ፣ በሰፊ አውድማ ነጭና ጥቁር እያፈሰ፣ ገፍቶ የመጣ ጠላትን ከድንበር ማዶ እየመለሰ፣ ለእናት ሀገር ደም እያፈሰሰ፣ አጥንት እየከሰከሰ የኖረ ሕዝብ ልጅ ነህ፡፡
ውሽንፈር ከማይገፋው፣ ጠላት ገፍቶ ከማያልፈው፣ ትዕግስቱ እንደ ውቅያኖስ ከሰፋው፣ ልቡ ከደነደነው፣ በግርማው ከሚጥል፣ በአፈሙዙ ከሚነጥል ጀግና ሕዝብ የወጣህ የጀግና ልጅ ጀግና ነሕ፡፡ የአንተን ልብ የሚበልጥ አይደለም፣ በእኩል የሚቀመጥ ጠላት አይገጥምህም፣ ጠላትን በልብህ ኩራት፣ በአሞትህ ሙላት፣ ከአባት በወረስከው የጦር ብልሃት፣ የአተኳኮስ ሥርዓት ኹሉ ትበልጠዋለህ፡፡ ችሎ የሚገጥምህ፣ ገፍቶ የሚያሸንፍህ ማንም የለም፡፡ ጀግንነትህ ከተራራ የገዘፈ ነውና፡፡
በአንተ ጀግንነት በጨለማ ውስጥ ሲርመሰመሱ የነበሩት ኹሉ ብርሃን አይተዋል፣ በአንተ ጀብዱ ግርማችን ኃያል ነው ያሉት ሁሉ ተንኮታኩተዋል፣ በአንተ ገድል መነሻነት ጠላት ኹሉ ከነበረበት ሸሽቷል፡፡ ለዘላለም የጨለመች የመሰለችውን ጀንበር ለዘላለም እንዳትጠፋ አድርገህ ያበራህ፣ ለተጨቆኑት ዋስ ጠበቃ ሆነህ የተጠራህ፣ አንገታቸውን ለደፉት ደርሰህ ያኮራህ፣ አንገታቸውንም ያቃናህ፣ የጥቁርን መገኛ ምድር በኩራት ያስጠራህ፣ በዝናህ ዓለማትን ያስፈራህ፣ በጉብዝናህ ጠላትን ያፈራረስክ፣ ለአሸናፊነት ብቻ የተፈጠርክ ነህ፡፡
ብዙ ሀገራት እንደ ሀገር ሳይፈጠሩ፣ ሥርዓት ሳይሠሩ፣ በሀገር መንፈስ ሳይዘምሩ አስቀድሞ ገና መንግሥት መስርቶ፣ ግዛት አስፍቶ፣ ሥርዓት ሠርቶ፣ እውቀት አስፍቶ፣ ታሪኩን አግዝፎ በክብርና በዝና ይኖር ነበር አንተ የወጣህበት ሕዝብ፡፡ ሀገር በመመስረት፣ ሥርዓት በመዘርጋት፣ የተጨነቀን በማረጋጋት፣ የጠገበን በመውጋት፣ የተጠማን በማጠጣት፣ የተራበን በማብላት የተመሰከረለት ሕዝብ የፈለቅህ ነህና በታሪክህ ኩራ፣ የወረስከውን ታሪክ የሚመጥንም ሥራ፡፡
እሳት የጨበጠውን፣ ዙፋን ላይ የተቀመጠውን፣ ኃይል ሁሉ በእጁ የነበረውን ጨቋኝ ገዢ በባዶ እጅህ ወጥተህ፣ በወኔ ተሞልተህ፣ ሲተኩስ እየቀረብክ፣ ሲመጣ እየፎከርክ፣ ከዙፋን አውርደኃል፣ የተጫነውን የጭቆና አገዛዝ አውልቀህ ጥለሃል፣ ከቤተ መንግሥት አውጥተህ፣ እንደ ዝንጀሮ ገደል ለገደል እንዲሄድ አድርገሃል፡፡ ዛሬ ላይ አፈር ልሶ፣ ዳግም ሊመጣ ቢል እንዴት ይችልሃል?
ጠላትህ በክንድህ አይደለም በስምህ ይሸበራል፡፡ አማራ ሲባል በግርማህ ይደነግጣል፣ ፋኖ ሲባል እግር አውጪኝ ይፈረጥጣል፣ ታዲያ በክንድህ ከዙፋኑ የወረደው፣ በኃይልህ በእሳት የነደደው አሸባሪው ትህነግ ዳግም መጣሁ እያለ ነው፡፡ አማራውም ክብሩን ላለማስነካት፣ ልኩን ለማሳዬት መጣሁ ወደ አለበት ሥፍራ እየሄደ ነው፡፡ አሸባሪው ትህነግ በጦርነት ያልቻለውን ሕዝብና ሠራዊት በውሸት ያሸንፍ ዘንድ ተስፋ ሰንቋል፣ ዳሩ በግንባር የሚያመጣው ያልሰለጠነ ታጣቂ እየተለቀመ ያልቃል፣
ʺከእንግዲህ አይኖርም ነገር ማለሳለስ፣
እነርሱም አያርፉም እኛም አንመለስ" ተው ሲባሉ አልተውም፣ አትደረሱብን ሲባሉ ደርሰዋል፣ የተቀመጠላቸውን ሕግ ጥሰዋል፣ ክብር ነክተዋል፣ የትዕግስትን ወሰን አልፈዋል፡፡ አዎን አሁን ነገር ማለሳለስ አያስፍልግም፡፡ አደብ አሰይዞ መቀመጥ ይሻላል እንጂ፤ አሁን ላይ በጋራ የመመለስና የማሸነፊያ ጊዜ ነው፣ ሌላው ከድል በኋላ የሚደርስ ጉዳይ ነው፡፡ ስለ ፍቅርና ስለ ሀገር ተው ሲባሉ አላረፉምና፤ እንደ አመጣጣቸው ማስተናገድ ግድ ኾኗል፡፡
ʺለኹሉ ዘመን አለው ከሰማይ በታችም ለኾነ ነገር ኹሉ ጊዜ አለው።
ለመወለድ ጊዜ አለው፣ ለመሞትም ጊዜ አለው፣ ለመትከል ጊዜ አለው፣ የተተከለውንም ለመንቀል ጊዜ አለው፤ ለመግደል ጊዜ አለው፣ ለመፈወስም ጊዜ አለው፤ ለማፍረስ ጊዜ አለው፣ ለመሥራትም ጊዜ አለው፤ ለማልቀስ ጊዜ አለው፣ ለመሳቅም ጊዜ አለው፤ ለመዝፈንም ጊዜ አለው፤ ድንጋይን ለመጣል ጊዜ አለው፣ ድንጋይንም ለመሰብሰብ ጊዜ አለው፤ ለመተቃቀፍ ጊዜ አለው፣ ከመተቃቀፍም ለመራቅ ጊዜ አለው፤ ለመፈለግ ጊዜ አለው፣ ለማጥፋትም ጊዜ አለው፤ ለመጠበቅ ጊዜ አለው፣ ለመጣልም ጊዜ አለው፤ ለመቅደድ ጊዜ አለው፣ ለመስፋትም ጊዜ አለው፤ ዝም ለማለት ጊዜ አለው፥ ለመናገርም ጊዜ አለው፤ ለመውደድ ጊዜ አለው፥ ለመጥላትም ጊዜ አለው፤ ለጦርነት ጊዜ አለው፣ ለሰላምም ጊዜ አለው" እንዳለ ጠቢቡ የጊዜውን በጊዜው ማድረግ ተገቢ ነው፡፡
ʺቢመክሩት አልሰማም ቢነግሩት እምቢ አለ፣
ፋኖ እየመታው ነው ተመልከት እያለ" ፋኖ፣ ልዩ ኃይልና ሚሊሻው የሚመጣውን ኹሉ ተመልከት እያለ እየመታው ነው፡፡ ፋኖን አልፎ የሚመጣ፣ ፋኖ ከሚተፋው እሳት የሚወጣ ኃይል አይገኝም፣ ኹሉም በፋኖ፣ በልዩ ኃይሉና በሚሊሻው እሳት ይለበለባል፣ እንዳልነበር ይሆናል እንጂ፤ አማራ የአባቶቹን ታሪክ የማስቀጠል፣ ክብሩን የመጠበቅና ሀገሩን የማስከበር ታላቅ ኃላፊነት ተጥሎበታል፡፡ ኹሉም ኢትዮጵያዊያንም ከአማራው ጎን መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡ አማራ በታሪኩ የሀገርን ክብር ከፍ ማድረግና ወገንን ማኩራት ነውና ይህንም ለማድረግ ተዘጋጅቷል፡፡
ጀግናው በጦር ሜዳ ጠላቱን ሲቆላ፣ ሕዝቡ ደግሞ ስንቅና ትጥቅ እያቀበለ ከኋላ ደጀን ኾኖ ይከተላል፡፡ የጋራን ጠላት በጋራ ማጥፋት ግድ ነውና፡፡
ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ የኦሮሞና የአማራ እውነተኛ የዘር ምንጭ በሚለው መጽሐፋቸው ስለ አማራ ሕዝብ ሲገልጹ ʺመላዋ ኢትዮጵያ የእኛ ናት ብለው ነው አማሮች የሚያስቡት፡፡ ምክንያቱም ባለፉት በሺህዎች በሚቆጠሩ ዓመታት ውስጥ በውትድርና ሙያቸው መንግሥታትን ሲጠብቁ እና የሀገሪቱን ዳር ድንበርና የግዛት አንድነት ሲያስከብሩ ጠንካራ የኢትዮጵያዊነትና ብሔራዊ ስሜት ገንብተዋል፡፡ ለኢትዮጵያ ሀገርነት መኖር ሌሎቹ ኢትዮጵያዊያን የፈፀሙት ታላቅ ጀብዱ እንደ ተጠበቀ ኾኖ ስለ እውነት ብለን እውነት ብንናገር በኢትዮጵያ ነጻነት ላይ አማሮች የመሪነት ሚና ባይጫወቱ ኖሮ ቅኝ ገዢዋ ጣልያን ኢትዮጵያን በቀላሉ ድል አድርጋ ለመያዝ በቻለች ነበር፡፡ የዚህም ምስክሩ ጣልያን ናት፡፡ የአማራን ወሳኝ ሚና በመረዳትዋ ጣልያን ከኹሉም በፊት አማራን ነበር ለማጥፋት የተነሳችው፡፡ አማሮች ከተበታተኑ ኢትዮጵያም እንደምትበታተን ጣልያኖች በሚገባ ያውቁ ነበር፡፡ ኢትዮጵያን አዳክመው ለመቆጣጠር የሚሹ ከባሕር ማዶ የመጡም ኾኑ የውስጥ ኃይሎች ኹሉ ይህንኑ አድርገዋል፡፡ የአማራ ጠላት የበዛውም ለዚሁ ነው" ብለዋል፡፡
አሸባሪው ትህነግ አቅም አልባ ሀገር ለመፍጠር አማራውን ቢቻለው ማጥፋት፣ ካለበለዚያ ማዳከም ዋና ዓላማው ነው፡፡ ታዲያ አማራ የውጭ ጠላት ያላንበረከከውን፣ በየዘመኑ የመጣው ጠላት ከክበሩ ያላጎደለውንና ያልደፈረውን አሸባሪው ትህነግ እንደምን ችላ ትደፍረዋለች? አሸባሪው ትህነግ በጦርነት ብላው ብላው አልሆን ያላትን አማራን በውሸትና በዛቻ ታሸንፈው ይመስል ውሸቷንና ዛቻዋን ታቀላጥፈው ጀምራለች፡፡ ዋሽቶ ማሸነፍና ጉድብ ማለፍ እንደማይቻል አሳዬው፡፡
አማራ በውሸት አይደለም በጦርነት እጥፍ የሚል ግንባር የለውም፡፡ በጦር የመጣን በጦር፣ በፍቅር የመጣን በፍቅር ይቀበላል እንጂ፡፡ አሁን ላይ የአማራ ወጣት እውነቱ ጦርነቱ መሆኑን አውቆ፣ ከኋላው ስንቅና ትጥቅ ማቀበል፣ ማበረታታት፣ አካባቢውን በንቃት መጠበቅ ነው፡፡ ድሉ እውነትን የያዘው ሕዝብ መሆኑ አይቀርምና፡፡
በታርቆ ክንዴ
25/07/2021
አፋር ላይ ለሞት የተጣደፉትን እንኳን ደህና መጣችሁ ብለን በህይወት ይዘናቸዋል
አፋር ክልል በርከት ያሉ የጁንታው ታጣቂዎች ከነመጡበት መኪና ከበባ ተድርጎ ሃይል ሳባክን ገቢ ሆነዋል:: ገና ምን አይተሽ አለ አቤ ሾፌሩ ይቀጥላል
21/07/2021
እንደሚመስለኝ ወቅቱ የሚያስገነዝበን ግዳይ
አሜሪካና አውሮፓ በዚህም በዚያም ብለው አዲስ አበባ ላይ የመዋጮ መንግስት እንዲቋቋም ውስጥ ለውስጥ እየሰሩ ነው የሚለውን ወሬ መናቅ አያስፈልግም። የሟሸሸውን የህወሀት ቡድን በጄሶና በቅስት ጠግነውና ቀና አድርገውት ለአቅመ ትንኮሳ ከማብቃት አልፈው ሌሎች ሃይሎችን በማደራጀት የሽግግር ዓይነት በመዋጮ የሚመሰረት ጊዜያዊ መንግስት እያሰቡ እንዳለ ከጭምጭምታ ያለፈ ነገር እየሰማን ነው። ክብራቸውን ያጎደፉ፡ ሰውነታቸውን ያረከሱ፡ ህሊናቸውን ያጡ ቆሞ ቀር 'ፖለቲከኞችን' በጀርባ ተደራጅተው ለአራት ኪሎ ቤተመንግስት የሚሆን መንግስት የሚመስል ነገር እንዲያዘጋጁ የቤት ሰራ እንደሰጧቸው በስፊው ይወራል። ይህን መረጃ በግሌ ትክክለኛነቱን ለማረጋገጥ ያልቻልኩ ቢሆንም ፈጽሞ ውሸት ነው ብዬ ላጣጥለውም ወኔ አጥሮኛል። ነጠብጣቦችን ገጣጥሞ አንድ ምስል ማየት ከተቻለ እነአሜሪካን ሀገር ለማፍረስ ያሰፈሰፉ ሃይሎችን በማደራጀት የጠሚ/ር አብይን መንግስት ስልጣን እንዲያጋራ አልያም እንዲወገድ የሚያደርግ እንቅስቃሴ ጀምረዋል።
እንግዲህ የኢትዮጵያ ጉዳይ ጎንበስ ቀና እያደረገን ቀጥሏል። በአባይ ግድብ ሙሌት ጮቤ የረገጠችዋን ልባችንን የሚያስከፉ ክስተቶች መምጣታቸው የማይቀር ነው። በእርግጥ ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነው ከተነሱና ለእነአሜሪካን ወጥመድ ጀርባቸውን ከሰጡ ኢትዮጵያችን አዲሱን ዓመት በአዲስ ተስፋ ልትቀበለው እንደምትችል አምናለሁ። ከአንድ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዥ ባለፈው የሰማሁት መረጃ እነአሜሪካን ሊደርሱ ያሰቡትን ፌርማታ በግልጽ አመላክቶኛል። እንደመረጃው ከሆነ ኮረምና አላማጣ የተለቀቁበት ምክንያት ዳግማዊ ሀውዜን እንዲፈጠር የተቀናጀ መረብ መዘርጋቱን መንግስት በመድረሱ ነው። እቅዱ ህጻናት ወታደሮችንና እናቶች ያሉበት ሲቪል ሃይል ከፊት ተሰልፎ የኢትዮጵያን ጦር እንዲገጥም፡ በውጤቱም ህጻናቱና እናቶቹ በጦርነቱ በብዛት እንዲሞቱ፡ ይህንንም በእርዳታ ሰራተኛነት ስም ወደሀገር ቤት የገቡ ጋዜጠኞች ከህወሀት ሰዎች ጋር በመሆን በዘመናዊ ዲጂታል ካሜራ እንዲቀርጹትና ለዓለም እንዲያሰራጩት ነው። በውጤቱም የኢትዮጵያ መንግስት ህጻናትንና እናቶችን ጨፈጨፈ በሚል በዓለም ዓቀፍ የጦር ወንጀሎች ፍርድ ቤት ለመክሰስ ትልቅ ማስረጃ እንዲሆን ታቅዷል። የኢትዮጵያ የደህንነት መስሪያ ቤት እቅዱን አነፍንፎ በመድረስ የኢትዮጵያ ሰራዊት አከባቢውን በመልቀቅ ታላቁን እልቂት አስቀርቶታል። አሁንም መንግስት ሁኔትውን በጥንቃቄ ማየትና እርምጃውንም በሃላፊነት ለማከናወን እየሰራ ነው። ወጥመድ ውስጥ ላለመግባት የሚያደርገውን ጥንቃቄ እንደሚቀጥልበት ይታመናል። የህጻናት ወታደሮችን ጉዳይ እነአሜሪካን ዝምታን የመረጡት ያለምክንያት እንዳልሆነ ግልጽ ነው።
እንግዲህ ለህወሀቶች የድል ፌሽታ የሆነውና የኢትዮጵያ መንግስት በከፍተኛ ሀገራዊ ሃላፊነት የወሰደው እርምጃ ሌላ ታሪክ የለውም። ህወሀቶች በአደባባይ ይጨፍሩ እንጂ ህጻናቱና እናቶቹ ባለመጨፍጨፋቸው ብስጭት ውስጥ መከረማቸውንም ሰምተናል። አሁንም ይህን እቅድ እነአሜሪካ አልተዉትም። በሁሉም ግንባሮች ህጻናትና እናቶች እንዲሰለፉ ተደርጓል። ዓላማዉ ሁለት መንታ ግቦችን አስቀምጧል። የኢትዮጵያ ጦር ቦታዎችን ከለቀቀ፡ የድል ነጋሪት እየጎሰሙ በሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የስነልቦና ሽንፈት እንዲደርስበትና መንግስቱ ላይ ተቃውሞ እንዲያነሳበት ነው። ሁለተኛ መንታ ግብ የኢትዮጵያ ጦር ወጊያውን ገጥሞ ህጻናቱንና እናቶቹን ከገደለ እነአሜሪካን ላዘጋጁት የጦር ወንጀል ፍርድ ቤት የክስ ዶሴ ማቅረብ ነው። በአጭሩ በተዘዋዋሪ እየተፋለምን ያለነው ከአሜሪካንና አውሮፓ ጋር መሆኑን በሚገባ መረዳት ያስፈልጋል።
አሜሪካን ሀገር ቢፈርስ ጉዳይዋ እንዳልሆነ በእኛ እድሜ ያፈረሰቻቸው አምስት ሀገራት ምስክር ናቸው። ከ20ዓመት በላይ አፍጋኒስታን ቆይታ፡ ሀገሪቱን አወላልቃና ብትንትኗን ካወጣች በኋላ ህዝቡን ለአውሬዎች ትታ እብስ ያለችበት የቅርብ ጊዜው እርምጃዋ የአሜሪካን ፍላጎት እስከየት ጥግ ሊደርስ እንደሚችል እንገነዘባለን። ኢትዮጵያ ተሸንሽና ቁርጥራጭ ሀገራት ምስራቅ አፍሪካ ላይ ቢፈጠሩ ምርጫዋ ላይሆን ይችላል። ብሄራዊ ጥቅሟን እስካስጠበቀ ድረስ ግን አይኗን ሳታሽ እንዲፈጸም ልታደርገው ትችላለች። አውሮፓዎች አፍቃሪ ህወሀት የሆኑትንና አዲስ አበባ የገቡትን የምስራቅ አፍሪካ ተወካይቸውን ወይዘሮ ሲመድቡ ኢትዮጵያ ላይ ምን እንዲመጣ እንደፈለጉ በግልጽ የሚያሳይ ውሳኔ ነው። ወይዘሮዋ ዓመታትን የዘለቀ፡ በፍጹም ታማኝነት የቆየ የህወሀት ወዳጅነት ያላቸው፡ ስለኢትዮጵያ መንግስት የሚጻፉ አሉታዊ ነገሮችን እየለቀሙ በግል የማህበራዊ ሚዲያ ገጻቸው የሚያጋሩ ዓይን ቀቅለው የበሉ አፍቃሪ ህወሀት ናቸው። እኚህን ወይዘሮ ለምስራቅ አፍሪካ ተወካይ የመደመበው የአውሮፓ ህብረት ዙሩን ለማክረር እንደወሰነ የሚያመላክት ነው።
ከእንግዲህ ተስፋችን ማን ነው? የኢትዮጵያ ህዝብ አይደለምን? እነአሜሪካ ሀገር ለማፍረስ ሲዶልቱ፡ ህወሀትን እንደትሮይ ፈረስ ተጠቅመው የኢትዮጵያን አንድነት ሲያወላልቁ በዝምታ የማይመለከተው የኢትዮጵያ ህዝብ ከድብታና ውዥንብር ውስጥ በመውጣት ሀገር ለማዳን ጉዞ ላይ ያለውን ባቡር መሳፈር ግድ ይላል። በአፋር የአፋር ህዝብ ክተት ብሏል። በምዕራብ የአማራ አርሶ አደር ነፍጥ አንስቷል። በራያም የኢትዮጵያ ውድ ልጆች ደማቸውን ሊያፈሱ፡ አጥንታቸውን ሊከሰክሱ በቀበሮ ጉድጓድ ገብተዋል። ከአራቱም የኢትዮጵያ አቅጣጫዎች የኢትዮጵያን አድን ሃይል በአንድ ልብ ግንባር ዘምቷል። ይህ ታሪካዊ ሀገር የማዳንን ትንቅንቅ ሁለት ምርጫዎችን ከፊታችን አስቀምጧል። እንደልማዳችን እንደታሪካችን ጠላትን አደባይተን፡ ትምህርት ሰጥተን፡ ኢትዮጵያን ዳግም እንዳይነኩ አድርገን ፋይሉን እንዘጋለን፡ አልያም በከፋፋይ አጀንዳዎች ተሸንፈን፡ በሀሰተኛ ፕሮፖጋንዳ ተወናብደን፡ ሀገራችንን ለአውሬዎች ሲሳይ በማድረግ ሀገር አልባ ዜጎች ሆነን እንቀራለን። ምርጫው የእኛው ነው።
13/01/2021
የመጨረሻው መጀመሪያ ‼️
አቶ ስዩም መስፍንን ጨምሮ ሌሎች የህወሓት አመራሮች የሚገባቸውን ተሰጥተዋል።
የተደመሰሱት አመራሮች ፦
1. አቶ ስዩም መስፍን፣ የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩ እንዲሁም ውጊያውን የመሩና ሰራዊቱ ከቦታ ቦታ እንዳይንቀሳቀስ ያዘዙ፣ በመጨረሻም በሰራዊቱ ላይ ውጊያ እንዲከፈት ትዕዛዝ የሰጡ፣
2. አቶ አስመላሽ ወልደስላሴ፣ የህወሓት ከፍተኛ የፖለቲካ አመራር የነበሩ
3. አቶ አባይ ፀሃዬ፣ የህወሓት ከፍተኛ የፖለቲካ አመራር የነበሩ
4. ኮሎኔል ኪሮስ ሀጎስ ከመከላከያ የከዱ ከነጥበቃዎቻቸው ተደምስሰዋል።
በሌላ በኩል በቁጥጥር ስር የዋሉ ወታደራዊና የክልል አመራሮች ፦
1. ኮሎኔል ገብረመስቀል ገብረ ኪዳን፣ ከመከላከያ የከዱ
2. ኮሎኔል ፍስሃ ብርሃኔ፣ ከመከላከያ የከዳ፣
3. ኮሎኔል ዘረአብሩክ ታደሰ፣ ከመከላከያ የከዳ፣
4. ኮማንደር ገብረኪዳን አስገዶም የልዩ ሀይል ክፍለ ጦር አዛዥ የነበረ
5. አቶ መብራህቶም ክንዴ ሀይሉ፣ የክልሉ ውሃ ስራዎች ድርጅት ፋይናንስ ሀላፊ የነበረ በቁጥጥር ስር ውለዋል።
የሀገር መከላከያ ሰራዊት ኃይል ስምሪት መምሪያ ሀላፊ ብ/ጀነራል ተስፋዬ አያሌው፣ አሁንም የተደበቁ የህወሓት ቡድን አባላት በሰላማዊ መንገድ እጅ እንዲሰጡ ጥሪ አቅርበዋል። ~ ኢዜአ
12/01/2021
ጊዜ ሲያዘምብህ ምርኩዝህ ሲከዳህ
ከረገጥከው ክብር ከከዳሀው መሬት ይጥልሃል እዳህ
02/01/2021
ደቡብ ዕዝ ከራያ አላማጣ ወረዳ መረዋ ቀበሌ እስከ ራያ ቆቦ ወረዳ ማህጎ ቀበሌ ድረስ 20 ኪሎሜትር የሚሸፍን የጠጠር መንገድ መገንባቱን አስታወቀ፣ የመንገዱ መገንባት ለአካባቢው ማህበረሰብ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንደሚኖረው ነዋሪዎቹ ተናግረዋል ።
የግንባታውን ሂደት ተዘዋውረው በመመልከት ከህብረተሰብ ተወካዮች ጋር ውይይት ያደረጉት የዕዙ ዋና አዛዥ ተወካይ ሜጀር ጀነራል ሰለሞን ኢተፋ እንዳሉት ሰራዊቱ ዋነኛ ተልዕኮው ህግን ማስከበር ቢሆንም ከህዝብ የወጣና ራሱን ለህዝብ የሰጠ ሃይል በመሆኑ በህዝባዊ የልማት ስራዎች ላይ ቀጥተኛ ተሳታፊ ነው ብለዋል ።
ህብረተሰቡ አንድነቱን በማጠናከር የአካባቢውን ሰላም ነቅቶ መጠበቅ ይኖርበታል ያሉት ዋና አዛዡ ከዚህ ጎን ለጎንም የሚገነቡ መሰረተ ልማቶች የሚጠበቅባቸውን አግልግሎት እንዲሰጡ ደህንነታቸውን መጠበቅና ተገቢውን እንክብካቤ ማድረግ ይገባል ብለዋል ።
የማህጎ ቀበሌ ሊቀመንበር አቶ አለሙ ሞላ በበኩላቸው የቀበሌው ነዋሪ የህክምና አገልግሎት ለማግኘት ምንም አይነት አማራጭ የሌለው በመሆኑ በርካታ ወገኖቻችን በሞት አጥተናል፣ ብዙ እናቶች በወሊድ ምክንያት ህይወታቸውን አጥተዋል፣ ይህም የሆነበት ምክንያት ቀበሌው ከራያ አለማጣ ወረዳ ጋር የሚዋሰን በመሆኑ መንገዱ እንዲገንባ ተደጋጋሚ ጥያቄ ብናቀርብም በወቅቱ በነበረው የህውሃት አመራር ዘንድ ከፈለጋችሁ እርሻችሁ ውስጥ መሞት ትችላላችሁ የሚል ምላሽ እንደተሰጣቸው ተናግረዋል ።
ለ30 አመታት ተደጋጋሚ ጥያቄያቸውን ቢያቀርቡም ምንም አይነት ምላሽ ያላገኙት ነዋሪዎቹ አካባቢውን የተርሳ ቀበሌ ነው በማለት ይገልፁታል።
መከላከያ ሰራዊት ህዝባዊ ግዳጅ ተቀብሎ የዘመናት ጠላትችን ለመቅበር በሚጣደፍበት ሰዓት የእኛን ጥያቄ በማዳመጥ ለገነባልን መንገድ ደስታችን ወደር የለውም ያሉት ነዋሪዎቹ በግንባትው ምክንያትም በወሊድ ምክንያት የምትሞት እናት፣ በትራንስፖርት እጥረት ምክንያት የሚያልፍ ህመምተኛ አይኖርም ለዚህም ክልብ እናመሰግናችኋለን ብለዋል ።
የደቡብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ በራያ ግንባር ተሰልፎ ጁንታው ከቀበረበት የህግ ማስከበር ማግስት ከዚህ ቀደም ያልታዩና በርካታ የመሰረተ ልማት ችግር ያለባቸውን ቀበሌዎች በመለየት ህዝባዊ የልማት ስራዎችን በማከናውን ላይ ይገኛል ።
አበበ ሰማኝ
ፎቶ በአበበ ሰማኝ
01/01/2021
በጀግናው መከላከያ ሰራዊት እርምጃ እንደተወሰደባቸው የተገለፁት አካላት እጅ ስጡ ተብለው ተጠይቀው እጃቸውን ለመስጠት ፈቃደኛ ያልሆኑትን ነው ።
አንዳዶቹ እጅ አንሰጥም ብለው ለማምለጥ ሲሞክሩ እርምጃ ተወስዶባቸዋል ።
በተለይም ከእኛው ጓዳ ወጥተው ሰፈር ውስጥ የተወሸቁና ከታላቋ ኢትዮጵያችን ይልቅ ጎጣቸው በልጦባቸው እኛኑ የወጉ ከሃዲዎች የሚገባቸውን በሚገባቸው ቋንቋ ተሰጥተዋል ።
በሌላ በኩል ፦
አሁን ላይ የተደበቁ የህወሓት አመራሮች ከማንም ጋር የሚገናኙበት ምንም አይነት እንጥፍጣፊ ዕድል እንደሌለ ሊሰመርበት ይገባል ።
አባላቱ በየቤተክርስቲያን እና በየዋሻው ራሳቸውን ቀይረው ሲንቀሳቀሱ እየተያዙ መሆኑን ተቋማችን በመግለጫው ገልጿል።
የሀገር መከላከያ ሠራዊት የቀሩ የህወሓት አመራሮችን ይዞ በቅርቡ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ይፋ እንደሚያደርግ አሳውቋል። ~ ENA
እውነት ድሮ ሁለነገራችን ያምራል
29/12/2020
ታሪክን ለትውልድ ለማሻገር ራያ ግንባር የዶለተው ፨፨፨፨
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the practice
Telephone
Website
Address
Addis Ababa