Oromia Monitor
Personal
07/08/2025
የአዲስ አበባ ልማት ማንም የማይሽረው ታሪካዊ ስኬት ነው
ያኔ ቅርስ ፈረሰ ሀገር ተናደ ብለው እንዲጮሁ የተመቻቹና በደቦ እዬዬውን ያስነኩት የዳያስፖራ የኪቦርድ ታጋዮች ዛሬ የከተማዋ ገጽታ ከዝንብ መራቢያነትና ከመንገድ ሽንት ቤትነት ተላቆ እንዲህ ተለውጣ፣ አምራና ተውባ ሲያዩዋት ተሳስተን ነበር ይሉ ይሆን? ወይስ ካፈርኩ አይመልሰኝ ብለው በምን ዋጋ አለው ድባቴ ውስጥ ይቀጥላሉ?
ለማንኛውም እንዲህ ከመሰሉ ለሰው ልጅ ከማይመቹ የሰፈር ሁኔታዎች ውስጥ የከተማችን አስተዳደርና የመንግስት ጠንካራ ፖሊሲ አዲስ አበባን ነፃ እያወጣ ነው! ልማት አስቀድሞ የሚለውጠው ሰውንና አከባቢን ነው የሚለው አዲስ አበባ ላይ በማይፋቅ ዘላለማዊ ማህተም ተመቶ ተረጋግጧል። ሊያሻር የማይችል ታሪካዊ ስኬት ተመዝግቧል!
ዛፍን የሚተክል ተስፋን ይተክላል ! እናንተ የሀሳብ ሰዎች ናችሁ ! ተስፋን እና በጎ ሀሳብን በትውልዱ መካከል ዝሩ ! ትከሉ !
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
16/07/2025
የህዳሴው ግድብ ለኢትዮጵያ ህዝብ የብልጽግና እና የኢኮኖሚ ብርሃን ነው። ግድቡ የሃይል አቅርቦትን በማሳደግ የኢንዱስትሪ ልማትን ያፋጥናል፣ የግብርና ምርታማነትን ያሳድጋል፣ ለዜጎችም የተሻለ ኑሮን ይፈጥራል። ይህ ሁሉ የሚሆነው ደግሞ በራሳችን ገንዘብና ጥረት የተገነባ በመሆኑ ነው።
16/07/2025
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በህዝብ ሙሉ ተሳትፎና ድጋፍ የተከናወነ ትልቅ ፕሮጀክት ነው። የዲያስፖራው ማህበረሰብም ሆነ በሃገር ውስጥ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ሁሉ ከትንሽ እስከ ትልቅ በመዋጮውም ሆነ በጉልበቱ ሳይታክት ተባብሮ ለዚህ ታላቅ የልማት ምሰሶ እውን መሆን የበኩሉን አስተዋጽኦ አበርክቷል። ይህም ግድቡ የህዝብ ብቻ እንደሆነ ያረጋግጣል።
09/07/2025
"ለውጥና እድገት በራስ አቅም ሲሆን መሰረቱ ሰፊ፤ ምሰሶውም ጠንካራ ይሆናል።"
ክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ከጎበኘኋቸው የአውሮፓ ሀገራት ከተሞች በበለጠ አዲስ አበባ የተሻለች ውብ ከተማ ሆና አግኝቻታለሁ”
በኢትዮጵያ ያለውን ዕድገት ሳልገልፅ ማለፍ አልፈልግም አዲስ አበባን በጎበኘሁበት ጊዜ አስደናቂ ከተማ እየሆነች መምጣቷን ለማየት ችያለሁ፡፡
ይህ የጥሩ መሪ የአመራር ጥበብ መገለጫ ነው፡፡
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሀሙድ አሊ ዩሱፍ
14/06/2025
"በምሳሌነት የምንገልጻችሁ የከተማችን ባለሀብቶች፣ ወጣቶች፣ ሴቶች እና ተቋማት በሙሉ በተለመደው መልኩ በገንዘባችሁ፣ በጉልበታችሁ እና በእውቀታችሁ አብራችሁን እንድትሰሩ ጥሪዬን እያቀረብኩ፤ እስካሁን ላበረከታችሁት ታሪካዊ አስተዋጽኦ አመሰግናለሁ።" ክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ
13/06/2025
አዲስ አበባ ላይ የተሰራው ስራ ከሩቅ እያዩ አይናቸው መቅላቱ ራሱ ሌላ ስኬት ነው
ተሽሎ መገኘት ካላስደሰተ ሌላ ምንም አያስደስትም። ስራው ተሰርቷል። ድጋፍ አያስለምንም.... እንቅፋትም ችለው አይሆኑም፣ እዚያው ከሩቅ እያዩ አይናቸው መቅላቱ ራሱ ሌላ ስኬት ነዉ። አዲስ አበባ ግን ተሽላ ተገኝታለች። አዲስ አበባ ላይ የተሰራው ስራ ድምፁን ከፍ አድርጎ እየተናገረ ነው። አዲስ አበባ ተሽላ በመገኘቷ ያልተደሰተ እንግዲህ ሌላም ነገር ስለማያስደስተው ለማስደሰት ድካም አያስፈልግም፣ ለመስራት የማይታክቱ እጆች ግን አሉ።
3ሶስት ቀን ቀረው
👇👇👇👇👇
በከተማ አስተዳደሩ የተለያዩ ስፍራዎች ተገንብተው ለአገልግሎት ዝግጁ የተደረጉ ፕላዛዎችና ፓርኪንጎች ውስጥ የሚገኙ የንግድ ሱቆችንና መጋዘኖችን በጨረታ አወዳድሮ ለማከራየት የወጣ ማስታወቂያ።
የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ እና የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ
13/06/2025
13/06/2025
እብድ ይሻለዋል እንጂ አይድንም ማለት👇🏻👇🏻👇🏻ነው
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the public figure
Telephone
Website
Address
Addis Ababa