Doch HD
ጥላቻን ለጠላ! Doch HD ገና በጅምር ላይ ያለ የመረጃና የመዝናኛ ሚዲያ ነው። በዚህም መረጃ ሰጪ ቪዲዮ እና ምስል እንዲሁም ፅሁፍ በየቀኑ በየሰዓቱ ከእኛ ይመልከቱ። ዶች
13/08/2026
በክልላዊ የ8ተኛ ክፍል ፈተና ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች፣ ወጤታቸውና ት/ቤታቸው
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በዛሬው እለት ይፋ በተደረገው ክልላዊ የ8ተኛ ክፍል ፈተና 96.9 ከፍተኛ ውጤት ሆኖ ሲመዘገብ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የሚከተሉት ሲሆኑ ውጤታቸውና ትምህርት ቤታቸው ተመላክቷል።
1ኛ). Mintesnot Desta Damota (ወንድ/ Male)
•ደረጃ (Rank): 1
•ትምህርት ቤት (School): Karawo
•ወረዳ (Woreda): Zaba Gazo | ዞን (Zone): Dawuro
•ውጤት (Average / Percentile / Total): 96.9 / 100 / 678
2ተኛ). Yetnayet Tamrat Feleke (ሴት/ Female)
•ደረጃ (Rank): 1
•ትምህርት ቤት (School): Adis Fana Primary and Medium Level
•ወረዳ (Woreda): Tarcha | ዞን (Zone): Dawuro
•ውጤት (Average / Percentile / Total): 96.9 / 100 / 678
3ተኛ). Dilachew Getachew Faris (ወንድ / Male)
•ደረጃ (Rank): 2
•ትምህርት ቤት (School): Tarcha 7th Day Adventist Primary and Medium Level
•ወረዳ (Woreda): Tarcha | ዞን (Zone): Dawuro
•ውጤት (Average / Percentile / Total): 96.43 / 99.99 / 675
4ተኛ). Minase Ayele Ayida (ወንድ / Male)
•ደረጃ (Rank): 3
•ትምህርት ቤት (School): Gessa Mulu
•ወረዳ (Woreda): Gessa | ዞን (Zone): Dawuro
•ውጤት (Average / Percentile / Total): 95.71 / 99.99 / 669
5ተኛ). Eyob Teshale Mamo (ወንድ/ Male)
•ደረጃ (Rank): 4
•ትምህርት ቤት (School): Berhan
•ወረዳ (Woreda): Bonga | ዞን (Zone): Kafa
•ውጤት (Average / Percentile / Total): 95.14 / 99.98 / 570
6ተኛ). Sumeya Nesru M***a (ሴት/ Female)
•ደረጃ (Rank): 5
•ትምህርት ቤት (School): Mizan-Misgena
•ወረዳ (Woreda): Mizan Aman | ዞን (Zone): Bench Sheko
•ውጤት (Average / Percentile / Total): 94.86 / 99.98 / 569
7ተኛ). Tinsae Ageno Alanche (ሴት/ Female)
•ደረጃ (Rank): 6
•ትምህርት ቤት (School): MT Pre Primary, Primary and Midium Level
•ወረዳ (Woreda): Tarcha | ዞን (Zone): Dawuro
•ውጤት (Average / Percentile / Total): 94.64 / 99.98 / 662
8ተኛ). Makbel Eshetu Haile (ተባዕት / Male)
•ደረጃ (Rank): 7
•ትምህርት ቤት (School): Mizan-Misgena
•ወረዳ (Woreda): Mizan Aman | ዞን (Zone): Bench Sheko
•ውጤት (Average / Percentile / Total): 94.31 / 99.97 / 565
9ኛ). Yabsira Amsalu Kesito (ወንድ/ Male)
•ደረጃ (Rank): 7
•ትምህርት ቤት (School): Beko 1st and Middle Level School
•ወረዳ (Woreda): Tepi | ዞን (Zone): Sheka
•ውጤት (Average / Percentile / Total): 94.31 / 99.97 / 565
ዶች ኤችዲ
13/08/2026
ክልላዊ የከታ-ገጠም የሩዝ እርሻን በተመለከተ ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ያስተላለፉት መልእክት
የኩታ-ገጠም እርሻ ልማት ከእርሻ ጀምሮ የምርት ማሳደጊያ ግብዓቶችን አጠቃቀም በማሳደግ፣ የሰብል እንክብካቤና ተባይ በሽታ መከላከልን በማጠናከር፣ የምርት አሰባሰብን መሰል ተግባራትን በተቀናጀ ሁኔታ በመምራት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግና እርሻዎችን ወደ ካምፓኒ ደረጃ በማድረስ የግብርናና ገጠር ትራንስፎርሜሽንን እውን ለማድረግ ሁነኛ መንገድ ነው፡፡
በዚህም መነሻ በክልላችን በአርሶ አደሮች በኩታ-ገጠም የሚለሙ ሰፋፊ እርሻዎች በክልላችን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደጉ መጥተዋል፡፡
በባለፈው በልግ አጠቃላይ በኩታ-ገጠም ከለማው 119ሺህ በላይ መሬት 18ሺህ 724 በ493 ክላስተር በሩዝ የለማ ሲሆን አሁናዊ የሰብሉ ቁመና በጥሩ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ ለዚህም በቤንች ሸኮ ዞን ጉራፈርዳ ወረዳ ኩጃ ቀበሌ በኩታ-ገጠም እየለማ ያለው በምሳሌነት የሚወሰድ ነው፡፡
አርሶ አደረሩና ሁሉም መዋቅሮቻችን ምርቱ እስኪሰበሰብ ተገቢውን እንክብካቤና የምርት አሰባሰብ ሂደቱ ከብክነት የጸዳ በማድረግ ረገድ አስፈላጊውን ሁሉ እንዲያከናውኑ እያልኩ መንግሥትና አጋር አካላት የዘርፉን ውጤታማነት ለማጎልበት የሚያደርጉት ያልተቋረጠ ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ለማሳወቅ እወዳለሁ፡፡
ክቡር አቶ ማስረሻ በላቸው
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ሃላፊ፤
ዶች ኤችዲ
13/08/2026
የአዲስ ብርሃን ቀበሌው አጫ ፏፏቴ -ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ🔥
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ሸካ ዞን የኪ ወረዳ አዲስ ብርሃን ቀበሌ አጫ ፏፏቴ፤
📷ሳሙኤል መኳንንት
13/08/2026
የክልሉ የክልላዊ ፈተና ከፍተኛ ውጤት (96.9) በዳውሮ ዞን ተማሪዎች የተመዘገበ ነው
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዘቦች ክልል ትምህርት ቢሮ በዛሬው እለት በሰጠው መግለጫ የክልሉ የ8ተኛ ክፍል ውጤት ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ ይፋ ይደረጋል። በዚህም ቀደም ብለው በወጡ መረጃዎች ቢሮው በመግለጫው 96.9 አማካይ ውጤት ከፍተኛው ክልላዊ ውጤት ነው ባለው መሠረት ተማሪዎቹ ተለይተዋል።
በዚህም የዳውሮ ዞን ተፈታኞቹ የትናየት ታምራትና ምንተስኖት ደስታ እኩል 678 ድምር ውጤት፤ 96.9 አማካሪ ነጥብ በማስመዝገብ የዘንድሮውን ቀዳሚነት ተቆናጠዋል። ቀሪዎቹን ከፍተኛ ወጤቶች ስንመለከትም በተመሳሳይ 3ተኛና 4ተኛዎቹ ከዳውሮ ሲሆኑ የካፋና ቤንች ሸኮ ተፈታኞች ይከተላሉ።
ዶች ኤችዲ
13/08/2026
ዶክተር ዬርቾ ብርሃኑ በቢሮው ለፎለር ፕሮጀክት አስተባባሪነት መደብ አለፉ
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የአካባቢ ጥበቃና አየር ንብረት ለውጥ ቢሮ በፎለር ፕሮጀክት አስተባባሪ መደብ ላይ ተወዳዳሪዎችን ተቀብሎ በውድድር ለመደደብ ብቁ የሆነዉን በቅጥር ለማወዳደር በቁጥር 225/1-8/2026 በቀን 21/05/2026 ቃወጣዉ ማስታወቂያ አውጥቶ ነበር።
በዚህም መሠረት ከተመዘገቡ ተወዳዳሪዎች መካከል ተለይተው/ተመልመለው ለፈተና እንዲቀርቡ በቁጥር 6499/1-8 በቀን 05/10/2018 ዓ/ም በተገለጸው መሠረት የብቃት መመዘኛ ፈተና በቀን 06/08/2026 ዓ/ም እንዲሰጥ ተደርጎ በፅሁፍፈተና 75%! ቃል ፈተና 25% (በድምሩ ከ100%) ተይዟል።
በውጤቱም መሠረት ከተለዩ 4 ሰዎች መካከል ዶክተር ዬርቾ ብርሃኑ ለመደቡ ከፍተኛ ወጤት (81) በማስመዝገብ አልፈዋል።
የቢሮው የውጤት መግለጫ በአስተያየት መስጫው ተያይዟል
ዶች ኤችዲ
13/08/2026
በ8ተኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከፍተኛው ውጤት 96.9 ሲሆን በሁለቱም ፆታ ተመዝግቧል🔥
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የ2018 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት ዛሬ ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ጀምሮ ይፋ ይደረጋል።
በክልሉ ትምህርት ቢሮ መረጃ የሚከተሉት ቁጥራዊ መረጃዎች ተመላክተዋል፦
•በአጠቃላይ 31 ሺህ 159 ተማሪዎች የወሰዱ ሲሆን፣ ከእነዚህም ውስጥ 16 ሺህ 061 ወንዶች እና 15 ሺህ 098 ሴቶች ናቸው፤
•ፈተናውን ከወሰዱ መካከል 20 ሺህ 618 ተማሪዎች 50% እና ከዚያ በላይ አማካይ የማለፊያ ውጤት ሲያስመዘግቡ ከእነዚህም 10 ሺህ 737 ወንዶች እና 9 ሺህ 879 ሴቶች ናቸው፤
•በዚህም በአጠቃላይ 50% እና ከዚያ በላይ መመዝገቡን ተከትሎም የማለፍ ምጣኔው 66.21 በመቶ ደርሷል፤
•ይህ ውጤት ከባለፈው የትምህርት ዘመን ጋር ሲነጻጸር የ9.62 በመቶ ብልጫ ያለውና በክልሉ በትምህርት ጥራት ላይ እየታየ የመጣውን መሻሻል የሚያመላክት ነው ተብሏል፤
•የማለፊያ ነጥብ ለአርብቶ አደርና ልዩ ድጋፍ ለሚሹ አካባቢዎች ተማሪዎች 47 እና ከዚያ በላይ፤
•ከላይ ከተጠቁት ውጭ ለሌሎች አካባቢዎች መደበኛ ተማሪዎች ደግሞ 50 እና ከዚያ በላይ እንዲሆን ተወስኗል፤
•በክልል ደረጃ የተመዘገበው ከፍተኛ የፈተና ውጤት 96.9 አማካይ ውጤት ሲሆን በሁለቱም ፆታዎች የተመዘገበ ነው፤
ተማሪዎች ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ በ sw.ministry.et ማስፈንጠሪያ በመግባት ሥምና መለያ ቁጥራቸውን በማስገባት ውጤታቸውን መመልከት ይችላሉ ተብሏል፤
መልካም ዕድል!
ዶች ኤችዲ
13/08/2026
የ8ተኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት ዛሬ ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ ይፋ ይደረጋል
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ትምህርት ቢሮ የ2018 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት ዛሬ ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ጀምሮ ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል።
የክልሉ ትምህት ቢሮው እንዳስታወቀው በትምህርት ዘመኑ የ8ኛ ክፍል ፈተናን በክልሉ በአጠቃላይ 31 ሺህ 159 ተማሪዎች የወሰዱ ሲሆን፣ ከእነዚህም ውስጥ 16 ሺህ 061 ወንዶች እና 15 ሺህ 098 ሴቶች መሆናቸው ተገልጿል።
ፈተናውን ከወሰዱ መካከል 20 ሺህ 618 ተማሪዎች 50% እና በላይ አማካይ የማለፊያ ውጤት አስመዝግበዋል።ከእነዚህም 10 ሺህ 737 ወንዶች እና 9 ሺህ 879 ሴቶች ሲሆኑ፣ ይህም አጠቃላይ 50% እና በላይ በማስመዝገብ የማለፍ ምጣኔውን 66.21 በመቶ አድርሶታል።
ይህ ውጤት ከባለፈው የትምህርት ዘመን ጋር ሲነጻጸር የ9.62 በመቶ ብልጫ ያለውና በክልሉ በትምህርት ጥራት ላይ እየታየ የመጣውን መሻሻል የሚያመላክት ነው ተብሏል።
በዘመኑ የተያዘው የማለፊያ ነጥብ ለአርብቶ አደርና ልዩ ድጋፍ ለሚሹ አካባቢዎች ተማሪዎች 47 እና ከዚያ በላይ ሲሆን፣ ለሌሎች አካባቢዎች መደበኛ ተማሪዎች ደግሞ 50 እና ከዚያ በላይ እንዲሆን ተወስኗል።
በክልል ደረጃ የተመዘገበው ከፍተኛ የፈተና ውጤት 96.9 አማካይ ውጤት መሆኑ ተጠቅሶ ይህም በሁለቱም ፆታዎች የተመዘገበ እንደሆነም ተገልጿል።
በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አልማው ዘውዴ እንደገለጹት፤ የዘንድሮው የ8ኛ ክፍል ፈተና ውጤት በክልሉ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ እየተደረገ ባለው ጥረት ውስጥ ሂደታዊ ለውጥ የታየበት ነው ብለዋል።
አቶ አልማው አክለውም፣ በቀጣይ የትምህርት ዘመን የተሻለ ስኬት ለማስመዝገብ ከወዲሁ ከትምህርት ዘመኑ ጅማሬ አንስቶ ልዩ ድጋፍ የሚሹ ተማሪዎችን በመለየት የማጠናከሪያ ትምህርት መስጠትና ተገቢውን ክትትል ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።
በሁሉም አካባቢ የሚገኙ ተማሪዎች እና የተማሪ ቤተሰቦች ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምረው sw.ministry.et በተሰኘ ማስፈንጠሪያ ገብተው ስምና መለያ ቁጥራቸውን በማስገባት ውጤቱን ማየት እንደሚችሉም አስተውቀዋል።
ዶች ኤችዲ
13/08/2026
"ዛራ እበላሻለሁ" ተብላ "ኬጅ ይዳኘናል" ያለችበት የሴቶች የመጀመሪያ ፍልሚያ ይጠበቃል
የዐድዋ ድል መታሰቢያ የፍልሚያ ምሽት (02) ለመጀመሪያ ጊዜ ሴቶችን ያፋልማል። አለምአቀፍ የውድድር ልምድ ባለቤቷ ዘሃራ ከያቡ ተጠባቂ ውድድር ነው። ያቡ "ፈተና መጥቶብሻል፤ እበላሻለሁ" ስትል ዘሃራ በአንጻሯ "ሪንግ ይዳኘናል እናያለን" ስትል ዝታለች። ማን የመጀመሪያው የሴቶች ሻምፒዮን ይሆናል። ልምድ፣ ድልና አለምአቀፍ የውድድር ዕድል ባለቤቷ ዘሃራ ወይንስ የሀገር ውስጥ ውድድሮች ባለድሏ ያቡ?
ዶች ኤችዲ
13/08/2026
ተጠባቂው ውድድና የበቀል ዛቻ የተቀላቀለበት ፍልሚያ አጓጊ ሆኗል፤ ማን ያሸንፋል?
"ሮቤል ጭብጥ አይሞላም፤ ከአንድ ቡጢ አያልፍም" -ንቃተ ህሊና
"በስሌት እንጂ በስሜት አይደለም" ሮቤል
ድሉ የማን ይሆን ይሁን?
ዶች ኤችዲ
12/08/2026
በክረምቱ ለድላው ልጅ አንድ እሽግ ደብተር በመግዛት በጎነት እናድርግ 🔥
“በትምህርት ቁሳቁስ ምክንያት አንድም ልጅ ከትምህርት ቤት መቅረት የለበትም!” በማለት ባለፉት 4 ዓመታት የብዙ ህጻናትን ህልም የደገፈውና ትምህርት ቤት መላክ የቻለው ኒው-ዳውሮ ፋውንዴሽን ዘንድሮም ያንኑ በጎ ተግባር ጀምሯል።
በዚህም 5ተኛ የኒው-ዳውሮ ፋውንዴሽን አንድ እሽግ ለአንድ ልጅ ዘመቻ (One Pack for One Child Challenge) የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፉን ከደጋጎች ማሰባሰብ ጀምሯል።
ዓላማውም አቅም የሌላቸውን ህፃናትን በመደገፍ በአዲሱ የትምህርት ዘመን ወደ ትምህርት ገበታ እንዲመለሱ ማገዝ ሲሆን ለድሃው ልጅ ትልቅ እረፍት የሰጠ ተምሳሌታዊ የበጎነት ተግባር ነውና የበኩላችንን እንወጣ እንላለን።
🎒 አንድ እሽግ፦ 12 ደብተር፣ 2 እስክሪብቶ፣ 2 እርሳስ፣ 2 መቅረጫ እና 2 ላጲስ
💰 ዋጋ፦ 1,000 ብር
እርስዎም አቅምዎ የቻለውን በመለገስ አንድ ልጅን ወደ ትምህርት ገበታ ይመልሱ!
🏦 CBE Account: 1000563357798
📞 0917 411 711 — በቴሌግራም የባንክ ደረሰኝ ይላኩ።
አንድ እሽግ፣ ለአንድ ልጅ፣ የወደፊት ተስፋ!
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Telephone
Website
Address
Addis Ababa
1000