Biblically with Robi
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Biblically with Robi, Digital creator, Addis Ababa.
13/08/2023
የመፅሐፍ ቅዱስ ጥናት ክፍል 4/ How to study the bible part 4 መፅሐፍ ቅዱስን ስናጠና ይሄኛውን(በዚህ ቪድዮ ላይ የተዳሰሰውን) መንገድ ከረሳን የምናጠናበትን አላማ ስተናል ማለት ነው።ወደ ህይወት መተርጎም(Application) የመጨረሻው የመፅሐፍ ቅዱስ ጥና.....
13/08/2023
የመፅሐፍ ቅዱስ ጥናት ክፍል 3/How to study the bible part 3 @Biblicallywithrobi ሁሉም የክርስትና እምነት ተከታዮች(ኦርቶዶክሳውያን፣ ካቶሊካውያን፣ ፕሮቴስታንቶች...) ይህን ቪድዮ እንዲመለከቱ አበረታታለሁ።Subscribe በማድረግና የደወል ምልክቱን በመንካት በየጊዜው ....
13/08/2023
የመፅሐፍ ቅዱስ ጥናት ክፍል 2/How to study the Bible part 2 ሁሉም የክርስትና እምነት ተከታዮች(ኦርቶዶክሳውያን፣ ካቶሊካውያን፣ ፕሮቴስታንቶች...) ይህን ቪድዮ እንዲመለከቱ አበረታታለሁ።Subscribe በማድረግና የደወል ምልክቱን በመንካት በየጊዜው ....
09/08/2023
ግብረሰዶማዊያን ዛሬም የመዳን ተስፋ አላቸው!
እግዚአብሔር አለምን ሲወድ መልካም ስነምግባር ያላቸውን ብቻ መርጦ አልወደደም። እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ አለምን ሁሉ እንዲሁ(መስፈርቱን ሳናሟላ) ወዶናል። “በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።”
— ዮሐንስ 3፥16
ምንም ያህል ሀጢኘተኛ እንደሆናችሁ ቢሰማችሁ እግዚአብሔር ግን ከሀጢአታችሁ ሊያነፃችሁ ፈቃደኛ ነው። አንዳንዶቻችሁ ሳታውቁት በግብረሰዶማውያን የመደፈር ጥቃት ደርሶባችሁ ወደዚህ አፀያፊ ነገር እንድትገቡ ሆናችኋል። አንዳንዶቻችሁ ደግሞ ምክንያቱ ምን እንደሆነ በማታውቁት ሁኔታ ወደ ተመሳሳይ ፆታ የመሳብ ዝንባሌን በራሳችሁ ላይ አይታችሁም ሊሆን ይችላል ወደዚህ ህይወት የገባችሁት። እግዚአብሔር ግን ከዚህ ሁሉ እስራት ነፃ ሊያወጣችሁ ፈቃደኛ ነው።
እኔ በግሌ ሰው በራሱ ይህንን አፀያፊ ተግባር መፈፀም ይችላል ብዬ አላምንም። አጋንንት በሰዎች ውስጥ ሲገቡ ግን ሰው በጤናው የማይያደርገውን ነገር ሁሉ ማድረግ ይጀምራል። ከዚህ እስራት ነፃ ለመውጣት ብቸኛው መንገድ በኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት ማመንና ወደ ቤተክርስቲያን መምጣት ነው። ያን ጊዜ እግዚአብሔር ይረዳችኋል።
ኢየሱስ ወደ አለም የመጣው በሀጢአተኞች ፋንታ የሀጢአት መስዋዕት ለመሆን ነው። በከፈለው መስዋዕትነት(የመስቀል ሞት) በእሱ የሚያምኑትን ሁሉ ከሀጢአታቸው አንፅቶ በእግዚአብሔር ፊት ተቀባይነት እንዲያገኙ ምህረትን ያስገኝላቸዋል። የኢየሱስ ደም ከሀጢአት ሁሉ ያነፃል።
"የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል።
ኃጢአት የለብንም ብንል ራሳችንን እናስታለን፥ እውነትም በእኛ ውስጥ የለም።
በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው።
ኃጢአትን አላደረግንም ብንል ሐሰተኛ እናደርገዋለን ቃሉም በእኛ ውስጥ የለም።" 1ኛ ዮሐንስ 1፥7-10
ኑ ወደ ኢየሱስ! እግዚአብሔር እናንተን ይቅር ለማለት ዛሬም ዝግጁ ሆኖ ይጠብቃችኋል። እግዚአብሔር ይርዳችሁ! እወዳችኋለሁ!
ፈቃደኛ የሆንን ሁሉ ይህንን ምስል የማህበራዊ ሚዲያዎቻችን አካውንቶች ላይ profile picture በማድረግ ለግብረሰዶማውያን ወንጌልን እናድርስ! መልእክቶችን እና ምስሎችን ስንለጥፍ የሚከተለውን ሀሽታግ ተጠቅመን በመልቀቅ መልእክቱ ብዙዎች ጋር እንዲደርስ እናድርግ።
Photo edited by Pheven Nigatu
08/08/2023
08/08/2023
Watch and subscribe if you are interested!
የመፅሐፍ ቅዱስ ጥናት ክፍል 1/ How to study the bible part 1 in Amharic ይህ ቪድዮ እንዴት መፅሐፍ ቅዱስን መፍታት/ማጥናት እንደሚቻል ጠቅለል ባለ መልኩ ያስገነዝባል።ሁሉም ክርስቲያን ይህንን የመፅሐፍ ቅዱስ አጠናን ዘዴ መጠቀም ይኖርበታል።በቀጣዮቹ ክፍ....
06/08/2023
ፈቃደኛ የሆንን ሁሉ ይህንን ምስል የማህበራዊ ሚዲያዎቻችን አካውንቶች ላይ profile picture በማድረግ ለግብረሰዶማውያን ወንጌልን እናድርስ! መልእክቶችን እና ምስሎችን ስንለጥፍ የሚከተለውን ሀሽታግ ተጠቅመን በመልቀቅ መልእክቱ ብዙዎች ጋር እንዲደርስ እናድርግ።
05/08/2023
ግብረሰዶማዊያን ዛሬም የመዳን ተስፋ አላቸው!
እግዚአብሔር አለምን ሲወድ መልካም ስነምግባር ያላቸውን ብቻ መርጦ አልወደደም። እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ አለምን ሁሉ እንዲሁ(መስፈርቱን ሳናሟላ) ወዶናል። “በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።”
— ዮሐንስ 3፥16
ምንም ያህል ሀጢኘተኛ እንደሆናችሁ ቢሰማችሁ እግዚአብሔር ግን ከሀጢአታችሁ ሊያነፃችሁ ፈቃደኛ ነው። አንዳንዶቻችሁ ሳታውቁት በግብረሰዶማውያን የመደፈር ጥቃት ደርሶባችሁ ወደዚህ አፀያፊ ነገር እንድትገቡ ሆናችኋል። አንዳንዶቻችሁ ደግሞ ምክንያቱ ምን እንደሆነ በማታውቁት ሁኔታ ወደ ተመሳሳይ ፆታ የመሳብ ዝንባሌን በራሳችሁ ላይ አይታችሁም ሊሆን ይችላል ወደዚህ ህይወት የገባችሁት። እግዚአብሔር ግን ከዚህ ሁሉ እስራት ነፃ ሊያወጣችሁ ፈቃደኛ ነው።
እኔ በግሌ ሰው በራሱ ይህንን አፀያፊ ተግባር መፈፀም ይችላል ብዬ አላምንም። አጋንንት በሰዎች ውስጥ ሲገቡ ግን ሰው በጤናው የማይያደርገውን ነገር ሁሉ ማድረግ ይጀምራል። ከዚህ እስራት ነፃ ለመውጣት ብቸኛው መንገድ በኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት ማመንና ወደ ቤተክርስቲያን መምጣት ነው። ያን ጊዜ እግዚአብሔር ይረዳችኋል።
ኢየሱስ ወደ አለም የመጣው በሀጢአተኞች ፋንታ የሀጢአት መስዋዕት ለመሆን ነው። በከፈለው መስዋዕትነት(የመስቀል ሞት) በእሱ የሚያምኑትን ሁሉ ከሀጢአታቸው አንፅቶ በእግዚአብሔር ፊት ተቀባይነት እንዲያገኙ ምህረትን ያስገኝላቸዋል። የኢየሱስ ደም ከሀጢአት ሁሉ ያነፃል።
"የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል።
ኃጢአት የለብንም ብንል ራሳችንን እናስታለን፥ እውነትም በእኛ ውስጥ የለም።
በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው።
ኃጢአትን አላደረግንም ብንል ሐሰተኛ እናደርገዋለን ቃሉም በእኛ ውስጥ የለም።" 1ኛ ዮሐንስ 1፥7-10
ኑ ወደ ኢየሱስ! እግዚአብሔር እናንተን ይቅር ለማለት ዛሬም ዝግጁ ሆኖ ይጠብቃችኋል። እግዚአብሔር ይርዳችሁ! እወዳችኋለሁ!
17/07/2023
ሁላችንም የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት በህይወታችን ብዙ ጊዜ ጥሰናል። ማንም ንፁህ የለም።ስሜን በከንቱ አትጥሩ ብሎን ሳለ እኛ ግን በየስበብ አስባቡ በማይረባ ነገር፣ በውሸት በመማል ሳይቀር ስሙን እናዋርዳለን። በሀሰትም እንመሰክራለን።
መፅሐፍ ቅዱስ እንደሚናገረው ሰው አንዲትን ሴት/ወንድ ለወሲብ ከተመኘ አመንዝሯል። እኛ የሰው ልጆች ግን ከመመኘትም አልፈን በተግባር ጭምር እንዘሙታለን። የሰውን ሚስትም/ባል የራሳችን ለማድረግ እንመኛለን።
በዚህ ክፉ ዘመን ከጋብቻ በፊት ወሲብ መፈፀም እንደ ሀጢአት አይቆጠርም። ሀጢአትን ሀጢአት ያሰኘው ነገር ከእግዚአብሔር ባህርይ ጋር አለመስማማቱ ነውና ይህንን ድርጊት እግዚአብሔር ስለሚፀየፈው ሀጢአት ነው። ብዙ ወጣቶች ግን ይህንን ብዙ ጊዜ አድርገውታል።(ምናልባትም ከተለያዩ ሰዎች ጋር)
በተጨማሪም መፅሐፍ ቅዱስ እንደሚያስተምረን ጥላቻ የግድያን ያህል ሀጢአት ነው። ይህንንም ቢሆን በህይወታችን ብዙ ጊዜ አድርገነዋል። አንዳንዶቻችን እንደውም ከዚህ አልፈን ነፍስ አጥፍተንም እናውቅ ይሆናል።
ብቻ ምን አለፋችሁ በተለያዩ መንገዶች አምላክን የሚያስቆጡ ነገሮችን አድርገናል። አምላክም ፍትሀዊ በመሆኑ ሀጢአትን ሳይቀጣ አያልፍም። ስለዚህ እኛን የመቅጣት ሙሉ መብትም ሆነ ስልጣን አለው።
ነገር ግን እግዚአብሔር አለምን ሁሉ ስለወደደ(ዮሐንስ ወንጌል 3፥16) ሁላችንንም ከገዛ ፍርዱ ለማዳን ሲል በእኛ ላይ ሊያመጣ የነበረውን ቁጣውን/ፍርዱን በንፁህ ልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ አደረገው። በዚህም ትእዛዛቱን ባለመጠበቃችን ምክንያት ከሚመጣብን እርግማንና ቅጣት ሊያድነን ቻለ።(ገላትያ 3፥10-13)
“በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።”
— ዮሐንስ 3፥16
ዛሬም በየትኛውም ሀይማኖት ውስጥ ያላችሁ በኢየሱስ አዳኝነት ካመናችሁ ከእግዚአብሔር ፍርድ መዳን ትችላላችሁ። ከእግዚአብሔር ጋር መታረቅ ትችላላችሁ። ፈቃደኛ ከሆናችሁ የክርስትና ትምህርት እንድትማሩ ልረዳችሁ እችላለሁ፤ በውስጥ መስመር አናግሩኝ። እወዳችኋለሁ! Everyone
17/07/2023
ሁላችንም የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት በህይወታችን ብዙ ጊዜ ጥሰናል። ማንም ንፁህ የለም።ስሜን በከንቱ አትጥሩ ብሎን ሳለ እኛ ግን በየስበብ አስባቡ በማይረባ ነገር፣ በውሸት በመማል ሳይቀር ስሙን እናዋርዳለን። በሀሰትም እንመሰክራለን።
መፅሐፍ ቅዱስ እንደሚናገረው ሰው አንዲትን ሴት/ወንድ ለወሲብ ከተመኘ አመንዝሯል። እኛ የሰው ልጆች ግን ከመመኘትም አልፈን በተግባር ጭምር እንዘሙታለን። የሰውን ሚስትም/ባል የራሳችን ለማድረግ እንመኛለን።
በዚህ ክፉ ዘመን ከጋብቻ በፊት ወሲብ መፈፀም እንደ ሀጢአት አይቆጠርም። ሀጢአትን ሀጢአት ያሰኘው ነገር ከእግዚአብሔር ባህርይ ጋር አለመስማማቱ ነውና ይህንን ድርጊት እግዚአብሔር ስለሚፀየፈው ሀጢአት ነው። ብዙ ወጣቶች ግን ይህንን ብዙ ጊዜ አድርገውታል።(ምናልባትም ከተለያዩ ሰዎች ጋር)
በተጨማሪም መፅሐፍ ቅዱስ እንደሚያስተምረን ጥላቻ የግድያን ያህል ሀጢአት ነው። ይህንንም ቢሆን በህይወታችን ብዙ ጊዜ አድርገነዋል። አንዳንዶቻችን እንደውም ከዚህ አልፈን ነፍስ አጥፍተንም እናውቅ ይሆናል።
ብቻ ምን አለፋችሁ በተለያዩ መንገዶች አምላክን የሚያስቆጡ ነገሮችን አድርገናል። አምላክም ፍትሀዊ በመሆኑ ሀጢአትን ሳይቀጣ አያልፍም። ስለዚህ እኛን የመቅጣት ሙሉ መብትም ሆነ ስልጣን አለው።
ነገር ግን እግዚአብሔር አለምን ሁሉ ስለወደደ(ዮሐንስ ወንጌል 3፥16) ሁላችንንም ከገዛ ፍርዱ ለማዳን ሲል በእኛ ላይ ሊያመጣ የነበረውን ቁጣውን/ፍርዱን በንፁህ ልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ አደረገው። በዚህም ትእዛዛቱን ባለመጠበቃችን ምክንያት ከሚመጣብን እርግማንና ቅጣት ሊያድነን ቻለ።(ገላትያ 3፥10-13)
“በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።”
— ዮሐንስ 3፥16
ዛሬም በየትኛውም ሀይማኖት ውስጥ ያላችሁ በኢየሱስ አዳኝነት ካመናችሁ ከእግዚአብሔር ፍርድ መዳን ትችላላችሁ። ከእግዚአብሔር ጋር መታረቅ ትችላላችሁ። ፈቃደኛ ከሆናችሁ የክርስትና ትምህርት እንድትማሩ ልረዳችሁ እችላለሁ፤ በውስጥ መስመር አናግሩኝ። እወዳችኋለሁ!
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Addis Ababa
13/08/2023