New Line College
Maytsebri New Line College
13/05/2026
ማስታወቂያ ለ2018 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኞች በሙሉ
መጪ ሰኔ 24/2018 ዓ/ም ጀምሮ የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለሚወስዱ ተፈታኞች የተዘጋጀ የመፈተኛ ክፍል መግቢያ ካርድ (Admission Card) በፈተና አስተዳደር ሲስተም (https://exam.eaes.et/) ከ03/09/2018 ዓ/ም ጀምሮ ለክልል ትምህርት ቢሮ፣ ለዞን ትምህርት መምሪያዎች እና ለትምህርት ቤት ተወካዮች ተለቋል።
ስለሆነም፡-
1.እያንዳንዱ ተፈታኝ ተማሪ በአድሚሽን ካርዱ ጀርባ ላይ የተፈታኝ ተማሪው ትምህርት ቤት ወይም የወረዳው አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት ማህተም የተደረገበትን አድሚሽን ካርድ ከትምህርት ቤቱ ወስዶ በእጁ መያዝ ይጠበቅበታል።
2.በምዝገባ ወቅት በተፈታኙ ወይም በመዝጋቢው የተከሰተ የትምህርት መስክ፣ የጾታ፣ የፎቶ እና መሰል ማስተካከያዎች ካሉ ከግንቦት 30/2018 ዓ.ም በፊት ለትምህርት ቤቱ ማሳወቅና ሂደቱን ጠብቆ መስተካከሉንም ከትምህርት ቤቱ ማረጋገጥ ይጠበቅበታል።
3.እያንዳንዱ ተፈታኝ አድሚሽን ካርዱን ወደ መፈተኛ ማዕከልም ሆነ መፈተኛ ክፍል ለመግባት የሚጠቀምበት በመሆኑ በአግባቡና በጥንቃቄ መያስ ይገበዋል።
4.ተፈታኞች በፈተና ወቅት ከአድሚሽን ካርድ በተጨማሪ የፋይዳ መታወቂያ መያዝ ይጠበቅባቸዋል።
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት
13/05/2026
እንኳን ለዓለም አቀፉ የሠራተኞች ቀን አደረሰን!/አደረሳችሁ!
የሥራ ባለቤት እርስዎ ነዎት!
24/04/2026
18/04/2026
13/04/2026
#በሃሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ተቀጥረው ሲያስተምሩ የነበሩ የመምህራን ቅጥር ተቋረጠ።
ደባርቅ:- ሚያዝያ 05/2018 ዓ/ም (ሰሜን ጎንደር ኮሙዩኒኬሽን )
በሰሜን ጎንደር ዞን ጠለምት ወረዳ በሃሰተኛ የትምህርት ማስረጃ በመምህርነት ተቀጥረው ሲያስተምሩ የነበሩ የ19 መምህራን ቅጥር ማቋረጡን የጠለምት ወረዳ ትምህርት ፅህፈት ቤት አስታወቀ።
የጠለምት ወረዳ ትምህርት ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ቸርነት መኳንንት እንዳስታወቁት በተለያዩ ወቅቶች የተቀጠሩ መምህራን መረጃ ከተማሩበት ኮሌጅ ድረስ በመላክ የ19 መምህራን መረጃ ሃሰተኛ መሆኑ ስለተረጋገጠ ቅጥራቸው ተሰርዟል ብለዋል።
አቶ ቸርነት አያይዘውም ሃሰተኛ ዲግሪ በማያያዝ ከመምህር ወደ ርእሰ መምህር ያደጉ የ3 ርእሳነ መምህራን መረጃ ሃሰተኛ መሆኑን በማረጋገጥ ከርእሰ መምህርነት ታግደዋል ብለዋል።
ጠለምት ወረዳ ኮሙዩኒኬሽን
12/04/2026
የትንሳኤ በዓል ታሪክ መሠረቱ ተስፋ፣ ጽናት እና አዲስ ጅማሬ ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ካሳለፈው መከራ በኋላ በድል በመነሣት ለሰው ልጆች ድኅነትና አዲስ ሕይወት አምጥቷል።
❤️❤️❤️
በሥራችንም ሆነ በግል ሕይወታችን የሚያጋጥሙን ተግዳሮቶች ሁሉ ወደ ላቀ ስኬት መሸጋገሪያ መንገዶች መሆናቸውን ይህ ታላቅ በዓል ያሳስበናል።
❤️❤️❤️
በዓሉ ለእያንዳንዳችን አዲስ ነገር፣ አዲስ ሰላም እና አዲስ ስኬት ይዞ እንዲመጣ መልካም ምኞታችን ነው።
ኒው ላይን ኮሌጅ ማይፀብሪ ዋና ካምፖስ ማስተባበርያ ቢሮ
መልካም ፋሲካ!
10/04/2026
☦️ መልካም የስቅለት በዓል! ☦️
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታይ በሙሉ፦
"እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!"
ይህ በዓል፦
የሰላም🕊️
የፍቅር ❤️ እና
የበረከት ✨
እንዲሆንላችሁ ከልብ እንመኛለን!
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Telephone
Website
Address
Addis Ababa