Kufa Multimedia
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Kufa Multimedia, News & Media Website, Addis Ababa.
ወቅታዊ ሁኔታን በተመለከተ
ከሁለት ወራት ቀደም ብሎ ሸገር ሲቲ ተብሎ በተሰየመው የኦሮሚያ ክልል ውስጥ የሚገኙ በርካታ መስጊዶች ተገቢ ባልሆነ እና በህገወጥ መንገድ መፍረስ መጀመራቸውን ተከትሎ ይህ ህገወጥ የመስጊድ ፈረሳ እስከ አሁንም ድረስ በመቀጠሉ ህዝበ ሙስሊሙን በማስቆጣቱ ዕለተ አርብ ግንቦት 18/2015 በታላቁ አንዋር መስጊድ ህዝበ ሙስሊሙ ተቃውሞ ማሰማቱ ይታወቃል። በዕለቱ በነበረው ተቃውሞ ፖሊስ በሰላማዊ ሰዎች ላይ በወሰደው የኃይል እርምጃ 2 ሙስሊሞች መስዋእትነት ሲከፍሉ በርካታ ሙስሊሞች ለአካል ጉዳት እና ለእስር ተዳርገዋል። በህዝባችን ላይ በደረሰው ጉዳት ነጃሺ ኢስላማዊ ማህበር የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ይገልፃል። መስዋእትነት የከፈሉ ወንድሞቻችን በጀነተል ፊርደውስ ከነብዩ ሙሐመድ ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ጉረቤት እንዲያደርጋቸው አላህን እንማፀናለን።
ማህበረሰባችን ለዚህ የከፋ ጉዳት የተጋለጠው ሀቀኛ፣ ብቁ እና ህዝባዊ ተቀባይነት ያለው መሪ ተቋም የሌለው በመሆኑ እንደሆነ ይታወቃል። በታሪካችን ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ሙስሊሞች በብዙ መስዋእትነት የሰሯቸው መስጊዶች ከአንድ ተራ መኖሪያ ቤት እኩል ህገወጥ ናቸው ተብለው በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት እንዲፈርሱ ሲደረግ አሁን ላይ በህገወጥ መንገድ በመፈንቅለ መጅሊስ የሙስሊሙን መሪ ተቋም የተቆጣጠረው ቡድን መስጊዶቹ አንድ ብለው መፍረስ ሲጀምሩ ከማስቆም ይልቅ ዝምታን እና ማድበስበስን በመምረጡ ጉዳዩ ተባብሶ ቁጥራቸው በርካታ የሆኑ መስጊዶች እንዲፈርሱ ትልቁን በር ከፍቷል። ለመስጊዶቹ ጥብቅና በመቆም ህዝብን በማስተባበር ከመፍረስ ሊታደጋቸው ያልቻለው ህገወጡ መጅሊስ ለመስጊዶቹ መፍረስ እና ህዝበ ሙስሊሙ መሪ አልባ እንዲሆን በማድረጉ ረገድ ቅድሚያ ተጠያቂው ነው።
መንግስት የህዝብን ደህንነት የመጠበቅ ኃላፊነት አለበት። ሙስሊሙ ማህበረሰብ የእምነት ተቋማቱ ያለ ምክንያት ሲፈርሱበት ተቆጥቶ በሰላማዊ መንገድ ቅሬታውን ሲገልፅ የፀጥታ አካል ያልተገባ የኃይል እርምጃ በመውሰድ የዜጎችን ህይወት መቅጠፍ እና ለአካል ጉዳት መዳረጋቸው በፍፁም ተገቢ ያልሆነ አካሄድ ከመሆኑ ባሻገር መንግስት የዜጎቹን ደህንነት የመጠበቅ ኃላፊነቱን ያለመወጣት ተግባር ነው። በመሆኑም መንግስት የዜጎችን ህይወትና አካል ከሚቀጥፍ የኃይል ተግባር በመቆጠብ የሙስሊሙን ማህበረሰብ ደህንነት የመጠበቅ ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል።
በእለቱ አድማ በታኞች ወደ አንዋር መስጊድ ቅጥር ጊቢ ለመግባት ያደረጉት ሙከራ ፍፁም የተሳሳተ እና ሙስሊሙን ማህበረሰብ ከፀጥታ ኃይላት ጋር ወደ ግጭት እንዲገባ ያደረገ ትንኮሳ ነበር። አስለቃሽ ጭስ ወደ መስጊድ ቅጥር ጊቢ መተኮሳቸው እጅግ የተወገዘ ተግባር ነው። የእምነት ተቋማት ሊከበሩ እና ሊታፈሩ፣ በውስጡ የተቀመጡ ምእመናን በሰላም በመስጊዱ ቅጥር ጊቢ ውስጥ የመቆየት እና የአምልኮ ተግባር የመፈፀም ሰብአዊ መብታቸው ሊከበር ይገባል።
መስጊዶቻችን የህልውናችን መሰረት አላህን በብቸኝነት ለማምለክ የምንጠቀምባቸው ተቋሞቻችን እንደመሆናቸው ያለ ምክንያት ሲፈርሱ መመልከት እጅግ ስሜታዊ ያደርጋል። ሆኖም ግን በማህበረሰባችን ላይ የመጣውን ፈተና እንዴት መሻገር አለብን? ምን ብናደርግ ምን እናገኛለን ምን እናጣለን? በምን አይነት አቅጣጫ ነው መጓዝ ያለብን? ፈተናውን ለመጋፈጥ ያለን አቅም ምን ያህል ነው? … ለሚሉ በርካታ ጥያቄዎች መልስ እየሰጠን መጓዝ ከስሜት እና ከተናጠል አካሄዶች በመቆጠብ እንደ ሙስሊም ማህበረሰብ ነገን አሻግረን እያየን ፈተናውን መሻገር ግድ ይሆናል። እንደ አለመታደል ሆኖ መሪ ዑለማኦቻችን ከመሰረቱት ተቋም በታጣቂ ኃይል ተገፍተው በመውጣታቸው እና መጅሊሱን የሚሾፍሩት የአንድ ቡድን ስሜት ብቻ የሚያንፀባርቁ ፅንፈኛ እና ህገወጥ ሰዎች በመሆናቸው ከህወገጡ መጅሊስ ለሙስሊሙ ማህበረሰብ የሚበጅ አቅጣጫ ይኖራል ተብሎ አይታመንም። በኦሮሚያ ክልል መስጊዶች ዛሬም ድረስ እየፈረሱ ቢሆንም ህገወጡ መጅሊስ አፉን ዘግቶ ተለጉሞ ቁጭ በማለቱ ዘላቂ መፍትሄ ከህገወጥ አካል አንጠብቅም።
በመሆኑም በአቅራቢያችን በአካባቢያችን የሚገኙ ዑለማኦቻችን ጋር ምን ይበጀናል? ብሎ በመመካከር
ካልተቀናጀ ከተናጠል እና ከስሜታዊ አካሄድ በመቆጠብ ሙስሊሙ ማህበረሰብ የነፍስ፣ የደም፣ የአካል እና የንብረት መስዋእትነት ተገቢ ባልሆነ መንገድ እንዳይገብር እጅግ የበረታ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርብናል። በአስተውሎት መራመድ ዛሬ የተፈፀመብን ግፍና መድሎ ነገ በተሻለ ህብረት እና ጥንካሬ እንድንቋቋመው ያስችለናል።
ባለፉት ጊዜያት "ድምፃችን ይሰማ" የተባለው ቡድን በዲን ሽፋን ሙስሊሙን ማህበረሰብ ለድብቅ የፖለቲካ አጀንዳ ሲያታግል እና ተገቢ ያልሆነ መስዋእትነት ሙስሊሙን ማህበረሰብ ሲያስከፍል እንደነበር የብልፅግና መንግስት መምጣትን ተከትሎ "የለውጡ ሃዋሪያ እኛ ነን፣ ዛሬ ለተገኘው ለውጥ ፈር ቀዳጆቹ ነን" እያሉ በወቅቱ የነበረው እንቅስቃሴ የፖለቲካ አጀንዳ ይዞ እንደተንቀሳቀሰ እማኝነታቸውን ሰጥተዋል ዛሬም ድረስ በራሳቸው ላይ እየመሰከሩ ይገኛል። በመሆኑም ካለፈው ስህተት በመማር የሙስሊሙን ወቅታዊ ቁስሎች መነሻ በማድረግ ወደማናውቀው አቅጣጫ ይዘውን ለመጓዝ ለሚፈልጉ ለሚታወቁ እና ለማይታወቁ አካላት ተገዢ ባለመሆን ተደራራቢ ጉዳቶችን ማህበረሰባችን እንዳያስተናግድ ጥንቃቄ ማድረግ የሁላችንም ኃላፊነት ነው። ማንነታቸው የማይታወቁ እና ኃላፊነት የማይወስዱ አካላት በሚያስጀምሩት ተቃውሞዎች ተሳታፊ ባለመሆን ማህበረሰባችንን ከጉዳት እንጠብቅ።
ዕለተ አርብ ግንቦት 18/2015 በአንዋር መስጊድ እና በመርካቶ ዙሪያ ለተገደሉ፣ ቆስለው የአካል ጉዳት ለገጠማቸው እና ለታሰሩ ሰዎች ከጎናቸው በመቆም አስፈላጊውን እገዛ እናድርግላቸው። ብዙ ወጣቶች ቆስለው በህክምና ላይ ናቸው። በርካታ ወጣቶች በጅምላ ታፍሰው ዛሬም ድረስ በእስር ላይ ይገኛሉ። በህመም እና በእስር ላይ የሚገኙ ወጣቶች ከፍተኛ እገዛ ያስፈልጋቸዋልና ጉዳዩ የጋራችን በመሆኑ እንደ ሙስሊም ማህበረሰብ ኃላፊነታችንን እንወጣ። በዚህ አጋጣሚ ከሙስሊም ወንድሞቻቸው ጎን በመቆም አብሮነታቸውን መስዋእትነት በመክፈል ጭምር በጎነታቸውን ላሳዩን ክርስቲያን ወገኖቻችን እጅግ የላቀ ምስጋና እያቀረብን ሙስሊሙ ማህበረሰብ አስፈላጊውን ህክምና እንዲያገኙ ከጎናቸው እንዲሆን ጥሪ እናቀርባለን።
በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ላይ እየተፈፀመ ያለውን ግፍ መንግስት በአስቸኳይ እንዲያስቆመው፣ የሙስሊሙ ንብረት የእምነት ተቋማት እና ሰብአዊ መብቶች እንዲከበሩ መንግስት ኃላፊነቱን እንዲወጣ አጥብቀን እንጠይቃለን።
የአዲስ አበባ ሙስሊም ወጣቶች ማሕበር
26/05/2023
በአዲሱ የሸገር ከተማ በመንግስት የፈረሱና እየፈረሱ የሚገኙ በርካታ መስጊዶችን ጉዳይ በተመለከተ በዛሬዉ ዕለት በተለያዩ መስጊዶች ድምጻቸዉን ባሰሙ ሙስሊሞች ላይ በተወሰደዉ የሀይል እርምጃ በደረሰዉ የሞትና የመቁሰል አደጋ የተሰማኝን ጥልቅ ሀዘን እየገለጽኩ ለሞቱት ጀነትን፣ ለቆሰሉት ፈዉስን፣ ለቤተሰቦቻቸዉም መጽናናትን እመኛለሁ፡፡
የተከበሩና የተቀደሱ ቤተዕምነቶችን ቅጽር ጥሶ መግባትና የዕምነት ተቋማትን በዚህ ልክ መዳፈር ከዘመነ-ኢህአዴግ በስተቀር በየትኛዉም የሀገራችን የመንግስት ሥርዓት ታሪክ ተፈጽሞ የማያዉቅ ሲሆን፣ ዉጤቱም ለማንም የማይበጅና በዉስብስብ ፈተናዎች ዉስጥ እያለፈች ባለችዉ ሀገራችን ላይ ተጨማሪ የመከራ ሸክም መጫን በመሆኑ የሚመለከተዉ አካል ነገሩን ቆም ብሎ ሊያጤነዉ ይገባል፡፡
አላህ ሀገራችንን ሠላም ያድርግልን!!!
Ambassador/Ustaz Hasen Taju
https://t.me/hassentaju
23/05/2023
ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን!!💔
አሏህ ያሻውን ሰሪ…የወደደውን ፈረደ!
ለዓመታት የቀጥባሬን ሐድራ ያጋፈሩት፣የመውሊዱ አበባ የነበሩት፣ የራቲባው ድምቀት፣ የነዝሙ የመደዱ ዘዋሪው… ሸይኽ ሰልማን ወደ አኼራ ሒደዋል። የቀጥባሬን መስጂድን ለዘመናት በዒማምነት አገልግለዋል። ሸይኽ ሰልማን ለነፍሳቸው ምቾት እና ዱንያዊ ተድላ ሳይጓጉ፣ ከሼኾች ሐድራ ሳይርቁ ዘውትረው ኺድማቸውን ፈፅመዋል። በሺዎች የሚቆጠሩ ደረሶችን አቅርተዋል። ብዙዎችንም ለትልቅ ዓሊምነት አብቅተዋል። የቃጥባሮች ኮኮከብ ዛሬ ሌሊት ወደ አኼራ ቤታቸው ተሻግረዋል።
ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን!
የሸይኻችን ስርዓተ ቀብር ነገ ማክሰኞ ከዙሁር ሶላት ስግደት በኋለ በቃጥባሬ ሐሪማ ቅጥር ግቢ ይፈፀማል።
መድረስ የቻልን ለቀብር ኹላችንም እንድረስ። ያልቻልነው ደግሞ በያለንበት ዒማማችንን በፋቲሃ እናውሳቸው!!💔
ተተኪያቸውን አላህ አያሳጣን
21/05/2023
ኢና ሊላሂ ወኢነ ኢለይሂ ራጂኡን 😥
#የገደባኖ (ወለኔ) ሼህ የሆኑት ሼህ መሀመድ ሼህ ከድር ሼህ አብድሽኩር ወደ አኼራ ሄደዋል አላህ ጀነተል ፍርዶስን ቤታቸውን ያድርገው 🤲
20/05/2023
#ሐይቅ
ሐይቆች ለወሀ^ብያ የሚከፈት ምንም አይነት በር የለም እያሉን ነው!
የዛሬው ስብስብ የ*ፖለቲካና የጥቅም አባዜ የተጠናወታቸው ሰዎች ከሚያደርጉት ስብስብ የራቀና የተለየ ነው።
ይህ ስብስብ ትክክለኛ አንድነት በነብዩ፣ በሶሐበቶች ብሎም የርሱን አደራ ጠብቀው ባቆዩት የመሻይኾች መንገድ መሆኑን በተግባር የሚያሳይ ስብስብ ነው።
©️ ኩፋ መልቲሚዲያ
06/05/2023
የህገወጡ የአዲስ አበባ መጅሊስ ኃላፊ አቶ ሱልጣን አማን የአዲስ አበባን ሙስሊም ሰላም እየነሳ ሽብር እየፈጠረ ነው።
ሱልጣን አማን የሚያሰማራቸው ጎረምሶች በታላቁ አንዋር መስጊድ ከ2 አስርት አመታት በላይ ከአሱር ሰላት በኋላ በመስጊዱ ማይክ የሚደረገው ዳእዋ ካልቆመ እርምጃ እንወስዳለን ብለው ሰሞኑን አንዋር መስጊድን የሁከት ማእድ ለማድረግ ከርቀት ቦታ እየተጠራሩ በመምጣት ችግር እየፈጠሩ ሁከት ቀስቃሽ ድርጊቶችን እየፈፀሙ ይገኛል።
በነገው እለት ሚያዝያ 28/2015 በጉለሌ ሙስሊም መቃብር መስራች ሸህ ሀሰን በቱል ስም የሚዘጋጀው ዓመታዊ መውሊድ አይከናወንም በማለት በሱልጣን አማን የሚመራው ህገወጡ መጅሊስ በማዘዙ የሸህ ሀሰን በቱል የልጅ ልጆች ያዘጋጁትን ዓመታዊ መውሊድ ፖሊስ አታደርጉም ብሎ እክል እየፈጠረ ያለበት ተጨባጭ ላይ እንገኛለን።
ይህ ሁሉ እየተፈፀመ ያለው የአዲስ አበባን ሙስሊም ወደ ሁከት በማስገባት ህዝበ ሙስሊሙን ለማጋጨት ሆን ተብሎ የተጠነሰሰ ሴራ ነው። መንግስትና ህዝብ የህገወጡ መጅሊስ መሪ አቶ ሱልጣን አማን እና አጋፋሪው አቶ መሀመድ አባተ የሚፈፅሙትን የሽብር ተግባር የማስቆም ግዴታ አለባቸው። ያ ሳይሆን ቀርቶ በታላቁ አንዋር መስጊድ እና በጉለሌ ሙስሊም መቃብር ግጭት ቢነሳ ለሚፈጠረው ችግር አቀነባባሪዎቹ የህገወጡ መጅሊስ አመራሮች እንደሚሆኑ መታወቅ አለብት።
የአዲስ አበባ ሙስሊም ወጣቶች ማሕበር
05/05/2023
ዛሬ ሶለዋት እናብዛ ሱረቱል ካህፍ እንቅራ
🌴 ጁመዓ ሙባረክ 🌴
05/05/2023
ፒያሳ በሚገኘው በኑር (በኒ) መስጂድ የሚሰጠው በረመዷን ፆም ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የአባታችን የክቡር ዶ/ር ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጅ ዑመር እድሪስ የቁርዐን ተፍሲር ፕሮግራም አላህ ካለ ዛሬ ጁመአ ይጀምራል ።
ፕሮግራሙም በሳምንት አራት ቀን ሰኞ፣ ማክሰኛ፣ ጁመዐ እና ቅዳሜ ከመግሪብ እስከ ኢሻ ይካሄዳል። የእውቀት ማእድ በሚፈስበት ቦታ በመገኘት ተጠቃሚ ይሁኑ ።
04/05/2023
"እንደ አይን ብሌን የምንሳሳላቸው መስጂዶቻችን በህገወጡ መጅሊስ አይመለከተኝም ባይነት ፈርሰው ሊያልቁ ነው "
በሸገር ከተማ ስም ከ11 በላይ መስጂዶች ፈርሰዋል ሙስሊሞች ተፈናቅለዋል ሙስሊሞች ቤታቸው በመፍረሱ ምክንያት ለአክፍሮት ሀይላት ተጋልጠዋል ጠንካራ የተባለው ኡማውን አባት አጣ አባት ይሁነው የተባለው ህገወጡ መጅሊስ ልጓሙ ተይዝዋል!!
በክቡር አባታችን ዶ/ር ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ዑመር እድሪስ አስተዳደር ጊዜም ሆነ ከሳቸው በፊት በነበሩት መጅሊሶች መስጂዶችና ሙስሊሞች እንደዚህ ተሸብረው ተንቀው ተዋርደው አያውቁም
በክቡር አባታችን ጊዜ መስጂዶች ሲፈርሱ ቤትኛውም የሀገሪትዋ ክፍል ለምን ብለው ለኡማው ጥብቅና ይቆሙ ነበር ሞጣ ላይ መስጂድ የተቃጠለ ጊዜ ሸይኽ ቃሲም ታጁዲን ሚድያዎችን የተቹበት ሁኔታ በጎንደሩ ክስተት ክቡር አባታችን ከብት ነው ወይ የምትጠብቁት ብለው መንግስትን የተቹበት ሁኔታ ይታወሳል መሻይኾቻችን ስለሀቅ እንጂ ማጎብደድ እነሱ ጋር ከቶ የለም
ጠንካራ አካታች አቃፊ ተብሎ በተጫነብን በህገወጡ መጅሊስ ጊዜ ዑለማዎች ታስረዋል ኡስታዞች በደህንነት ከመስጂድ ተባረዋል የሴት ሙስሊም ተማሪዎች ሂጃብ ተደፍሯል በመላው አዲስ አበባ ዙርያ ሸገር ሲቲ በሚባለው ከተማ እና ኦሮሚያ ላይ ከ10 መስጂዶች በላይ ዶግ አመድ ሆነው አንዳንድ ለሆድ ያደሩ የመጅሊሱ ተከፋይ አክቲቪስቶች እና መሰሎቻቸው መጅሊስን ለመከላከል የሄዱበት ርቀት ስንት ቢከፈላቸው ነው እንዲህ በዲናቸውን የሚሸቅጡት ለወንበራቸው ዋስትና ያደረጉት እንደዚህ ባለ ሁለት ቢላ የሆኑት የሚለው ግራ አጋቢ ነው
ከሁሉ የሚገርመው የአፍራሾቹ የልብ ባልደረባ ናቸው የሚያስብለው ነገር አቶ አህመዲን ጀበል ኢብራሂም ቱፋ ከመንግስት ጋር እየተወያዩ ነው ብሎ አጀንዳ ለማስቀየር የሄደበት መንገድ እራሱን ኡስታዝ ነኝ ከሚል አካል አይደለም ካድሬ እራሱ እንደዚህ አይነት ቲያትር ይሰራል ተብሎ አይጠበቅም
ሌላው የሚገርመው ነገረ ሀጅ ነው ሀጅን ይህ ህገወጥ ቡድን ህልም ሊያደርገው ይመስላል ካላመሰገናችሁ አያያዜ የበረታ ነው የሚለው የጀሊሉ ንግግርና በእጅ ያለ ወርቅ የሚለው የሀገሬ ሰው አባባል እዚህ ጋር ይሰራል ትላንት 98,000 ብር ሆነ ሀጅና አይወጅብም ያለን አካል ዛሬ 465,000 ብር ሲገባ በሂጅራ ባንክ አስገቡ ተበድራችሁ ሀጅ አድርጉ ሲለን ታዘብን የጭንቅላት ድርቀት ይህ ነው ሀጅ በብድር አቅሙ ላልቻለ ሰው መሄድ እኮ ክልክል ነው
ለምሳሌ አንድ ሰው ተበድሮ ሀጅ ቢያደርግና እዛው ቢሞት ሚስትና ልጅ እዳ እየከፈሉ ሊኖሩ ነው ? ትላንት ዘራፊ እያለ ሲጮኽ የነበር ቡድን በዚህ ያህል ዘረፋ ውስጥ ተዘፍቆ ሲታይ ጉድ ያስብላ ሌላው ህዝቡን ጉድ ያሰኝው እስር ቤት የነበሩ ግለሰቦች በአንድ ጀንበር በከተማችን ውድ የሚባሉ አካባቢዎች ላይ ውድ ህንፃ ሲገዙ ስትመለከት ከሰማይ ወርዶላቸው ካልሆነ በስተቀር የዚሁ የዘረፋ ውጤት እንጂ ሌላ ምንም ሊሆን አይችልም
በተጨማሪም #የበደል #ሱሰኞች
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10ልዩ ስሙ ብሔረ ፅጌ ኸውፈላህ ተብሎ በሚጠራው መስጅድ ህገ ወጡ የኢብራሂም ቱፋ እና የሱልጣን አማን ቅጥረኞች የመስጅዱ ዋና ኢማም ሸይኽ አብዱልከሪም በየእለቱ ከመግሪብ አስከ ኢሻዕ የተፍሲር የፊቂህ የሰለዋት ፕሮግራማቸውን በማስቆም ከዚህ ቀደም ከሚሰጡት የደረስ አትሰጡም በማለት ኢማሙን በማመናጨቅ ገፍተዋል የአካባቢው መስሊም ማህበረሰብ ለምን ይሆናል ብሎ ህገ ወጥ ከሱልጣን አማን ቅጥረኞች ጋር በተነሳ ፀብ ቀድሞ ከፖሊስ ጋር የተመሳጠረው ህገ ወጥ የህዝብ ተቀባይነት የሌለው የወሀቢያ ቡድን የመስጅድ አባቶች ወጣቶችን አሳስረዋል አስከ አሁኑ ሰዓት ድረስ ችሎት አልቀረቡም
በተጨማሪም በሲኤም ሲ አል ዒምራን መድረሳ ከ 300 በላይ የአፍተር ስኩል ቂርዓትን ኡስታዞቹን በማባረር በእኛ ካልሆነ(በወሀቢያ )አመለካከት መቅራት የተከለከለ ነው በማለት ተማሪዎችን በትነዋል
ፍትህ ለኸውፈላህ መስጅድ ሙስሊም ማህበረሰብ!!!
በዳዮች ረዳት የላቸውም !!
እውነት ያሸንፋል !!
21/02/2023
ዛሬ ምሽት ከ2:30_4:00 የትዊተር ዘመቻ ይኖረናል። ተዘጋጅተን እንጠብቅ፣ ትዊተር ያልከፈተ ይክፈት!
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Addis Ababa