Kesis Tagay Tadele
Secretary-General of Inter-Religious Council of Ethiopia - IRCE.
14/07/2026
"አብርሐም አብርሐም ፃእ እምብሔርከ ወተፈለጥ እማዝማድከ "
እንኳን ለሥሉስ ቅዱስ (ቅድስት ሥላሴ ) ክብረ በዓል እንኳን አደረሳችሁ።
በዓሉን በአሳደገን ደብር በአጋሮ ማህበረ ሰላም ቅድስት ሥላሴ ከምወደው ሕዝብ ጋር በድምቀት አክብረናል።
24/05/2026
ሀይማኖታዊ እሴታችን ለዘላቂ ሰላማችን በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀው ሀገር አቀፍ የፀሎት መርሀ-ግብር ለይ የጉባኤው መልዕክት
የተከበራችሁ የነገዋ ኢትዮጵያ መሪ የሆናችሁ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ ትካዮች ፣
የዚህ ታላቅና ቅዱስ መድረክ ባለቤት የሆናችሁ፤ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ፣ የክብር እንግዶች እንዲሁም በዚህ ስፍራ የተገኛችሁ የኢትዮጵያ ወዳጆች በሙሉ፤
ከሁሉ አስቀድሜ በእንደዚህ አይነት ሀገራዊ የፀሎት መርሀ ግብር የፈጣሪን ፍቃድ ለመጠየቅ እድል ስላገኘሁ እንዲሁም የዚህ ደማቅ እና ልዩ ታሪክ ተካፉይ መሆን በመቻሌ እግዚአብሔር አመሰግናለሁ።
እንኳን ደህና መጣችሁ ።
እንደ አይን ጥቅሻ ተለዋዋጭ የሆነው አለም አቀፍ ነባራዊ ሁኔታ ይዞት በመጣው ፈተና እና እድል ፊት ለፊት እንገኛለን። በመሆኑም ይህንን ነባራዊ ሀቅ በልኩ በመረዳት እኛ ኢትዮጵያውያን ሁላችንንም በሚያሰባስበው ጥላ በአካልም በመንፈስም ባዋሃደን የሀገር ፍቅር ተሳስረን ልዩነታችን አጥር ሳይሆን በህብር ቀለም ውበት ደምቀን ኢትዮጵያ ስለምትባል የጋራ አጀንዳችን ዘላቂ ሰላም ፣ዘመናትን የተሻገረው ጠንካራ ሀይማኖታዊ እሴቶቻችንን ለማፅናት እዚህ ተገናኝተናል።
እኛ ከየ98 በመቶ በላይ የአማኝ ህዝብ መገኛ ፣ዘመን ተሻጋሪ የፅኑ ታሪክ ባለቤት ነን። ይህም እምነታችን በፈተና ወቅት መሻገሪያ፣ በጨለማ ጊዜ መሪ ብርሃን ሆኖ የኖረ እውነት ስለመሆኑ የፈጣሪን ስም ጠርተን በጋራ እንጀራ መቁረስ ብቻ ሳይሆን በሀገር ጉዳይ ለመጣ የፈጣሪን ስም ጠርተን በጋራ ለሞት ነፍሳችንን ለመስጠት እንኳ የማንሰስት ህዝቦች ለመሆናችን የቆምንባት ምድር፣ የረገጥነው አፈር ፣የአባቶቻችን አፅም ፣በደም የተጻፈው ታሪካችን ምስክር ነው።
የኢትዮጵያዊነት ብልጫው፣ የማሸነፍ ሚስጥር በፀሎት የፈጣሪን ፍቃድ መጠየቅ ስለመሆኑ ታሪካችን ምስክር ነው። እኛ ምድራችን ዝናብ ስታጣ የሰማይ መስኮቶች እንዲከፈቱ ፣ በህብረት ሆነን ወደ ፈጣሪ የጮኸን ህዝቦች ነን ።ጠላት ዳር ድንበራችንን ሲደፍር በራችንን ሲያንኳኳ በፀሎትና ተንበርክከን፣ በፅናት ቆመን ፣ድልን የተቀዳጀን ወደቁ ስንባል የምንነሳ፣ ፈረሱ ስንባል የምናብር፣ ጅራት ናቸው ሲሉን ራስ ሆነን የምንገኝ ፡አለም በቅጡ ያልተረዳን የመለኮት ድጋፍ ያልተለየን ለጠላት ግንእንቆቅልሽ የሆንን ህዝቦች ነን ።
ዛሬም እንደ ትላንቱ አንድነታችንን ለማፅናት ፣ሰላማችንን ለመጠበቅ እንደ ግለሰብም ሆነ እንደ ተቋም የምናደርገው ጥረት ሳናቋርጥ የፈጣሪ ፈቃድ ለመጠየቅ የፀሎት ጉልበት እንደሚያስፈልገን እንምናለን።
ሰላም የኔ ከምንለው የፖለቲካ አመለካከት፣ ከራስ ጥቅምና ፍላጎት የሚቀድም የጋራ አጀንዳችን ነው በመሆኑም ይህንን መሰረት በማፅናት ህብረ ብሔራዊ አንድነትን በማጠናከር ለሁሉም ኢትዮጵያዊ የምትበቃ አዲሲቷን ኢትዮጵያ ለመገንባት የሚደረገውን ጥረት ማገዝ እና የፈጣሪን በመጠየቅ ሁሉም የድርሻውን በመወጣት አዲስ የአርበኝነት ገድል እንድንፅፍ እኛ የሀይማኖት አባቶች አደራ ማለት እንፈልጋለን።
ዛሬ ይህ የፀሎት መርሀ ግብር እኛን ከፈጣሪ ጋር ብቻ የሚያገናኝ ሳይሆን አንዱ ከሌላው ጋር የልብ ትስስር እንዲፈጥር የሚረዳ በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጪ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን የሚያቀራርብ የመንፈስ አንድነት ድልድይ እንደሚሆን እናምናለን።
ክቡራትና ክቡራን፣
ኢትዮጵያዊነት የማይደፈር የክብር ተራራ፣ የነፃነት አርማ፣ የማይደበዝዝ የታሪክ አሻራ ነው።
ይህ አንድነት በመከራ ጊዜ ይበልጥ የሚፀና፣ በደስታ ጊዜ እንደ ተዋበ እንቁ የሚደምቅ፣ በጦርነት አውድማ ላይ ደግሞ ወደ ብረት መከታነት የሚቀየር ነው።
እኛ በቋንቋ፣ በባህልና በኃይማኖት ብንለያይም፣ በኢትዮጵያዊነት ጥላ ስር ግን አንድ አካል፣ አንድ አምሳል አለ። እሱ ፣እሷ ኢትዮጵያዊ ናት ተብለን ከሩቅ የምንለይበት በደማችን ውስጥ የፈሰሰ፣ ከአያት ቅድመ አያቶቻችን የተረከብነው፣ ልንሸሽገው የማንችለው ፣ልዩነትን በእርቅ የሚፈታ ፣ኩርፊያን እንደማለዳ ጤዛ በሚያስረሳ ህያው ፍቅር የተገነባን፣ የማይጠፋ እሴት ባለቤት ነን ።
ኢትዮጵያ ለኛ የማትቆረስ የስስት እንጀራ ናት። አንድ እናት ለልጇ ያላትን የማይለወጥ ፍቅር ፣ አንድ ልጅም ለእናቱ ያለውን ክብር ፣ኢትዮጵያን በልቡ የተሸከመ ሁሉ የሚረዳው ሀቅ ነው በመሆኑም ኢትዮጵያዊነት ለነገ ቸል የማንለው የልብ ምታችን እንደሆነ ወዳጅም ጠላትም ያውቀዋል ።
ዛሬም ስለ ሀገራችን ዘላቂ ሰላም፣ አብሮነት እንዲሁም የኢትዮጵያን እድገት የማዋለድ ጉዞ ሽግግር ሾተላይ እንዳያገኘው የፈጣሪን ፍቃድ እና እርዳታ በፀሎት ለመጠየቅ በአንድነት በፈጣሪ ፊት ቆመናል ።
በመሆኑም ይህ ልዩ እና ታሪካዊ መርሀ ግብር የሀገር አንድነትን የሚያስቀድም፣ለሰው ልጅ ክብር ብልጫ የሚሰጥ፣ ከሰፈር አጥር ተሻግሮ በኢትዮጵያዊነት ማህተም የደመቀ እንደሚሆን ፅኑ እምነት አለኝ።በመሆኑም ድህነትን በመዋጋት የሀገርን እድገት ለማረጋገጥ በፀሎትም በስራ ትጋትም እንድንበረታ በዚህ አጋጣሚ አደራ ማለት እንፈልጋለን ።
ሁላችንም ከጥላቻ ንግግር ይልቅ የሃሳብ የበላይነትን፣ ከመለያየት ይልቅ አብሮነት ላይ ማተኮር ይኖርብናል። የኢትዮጵያ ህዝብ የሚፈልገው ሰላም፣ ልማትና ፍትህ ማረጋገጥ እንጂ፣ የትላንትን ስብራት እያስታወሰ ተስፋ የሚያስቆርጠውን ቁስሉን የሚያክበትን ገል የሚያቀብለውን አይደለም።
በመጨረሻም ጸሎት የብርሃን ድልድይ የአንድነታችን ጉልበት በመሆኑ ቂምን በይቅርታ፣ ጥላቻን በፍቅር፣ ጥርጣሬን በመተማመን በመቀየር ኢትዮጵያን ያስቀደመ ለኢትዮጵያ መጻኢ ብሩህ ተስፋ የሚሆን በታሪክ ማህደር በበጎ የሚወሳ አሻራ እንድናናኖር መንፈሳዊ ጥሪያችንን ከአደራ ጋር እናቀርባለን።
ሰላማችንን በማጽናት፣አብሮነታችንን በማጠናከር የአባቶቻችንን አደራ እንጠብቅ እጆቻችንን ለጸሎትም ለስራም እንዘርጋ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ
19/05/2026
01/05/2026
የመገናኛ ብዙሃን ባለሥልጣን አንድ ምእራፍ ወደፊት ያስፈነጠረውን አዲስ ቴክኖሎጂ በAI አበለጸገ።
በዛሬው ዕለት ይፋ በተደረገው በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የታገዘ የተቀናጀ የሚዲያ ሬጉላቶሪ እና አስተዳደር ሥርዓት ይፋ ማድረጊያ ሥነ-ሥርዓት ላይ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን መልዕክት አስተላልፈዋል።
አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እንደገለጹት፣ ሥርዓቱ የመገናኛ ብዙኃን ተቋማትን ግልጸኝነት የሚያሰፍን፣ የዜጎችን ተሳትፎ የሚያሳድግና በመንግሥትና በሕዝብ መካከል መተማመንን የሚፈጥር ነው።
ቴክኖሎጂው ለሚዲያ ተቋማት ግልጸኝነትን በመፍጠር ፍትሕን ከማስፈን ባለፈ፤ የባለሥልጣኑን ሠራተኞች የሥራ ጫናና የጤና ስጋት የሚቀንስ መሆኑንም አንስተዋል።
አምባሳደር ሬድዋን አክለውም፤ "የቴክኖሎጂ ሥርዓቱ ውሳኔዎች በዘፈቀደ ሳይሆን በመረጃና በማስረጃ ላይ የተመሠረቱ እንዲሆኑ ያደርጋል" ብለዋል።
ይህም የዜጎችን ቅሬታ በመቀነስ፣ አገልግሎትን በማዘመንና ተጠያቂነትን ለማስፈን እንደሚያስችል ገልጸዋል።
ሥርዓቱ ቀደም ሲል የነበሩ የአሠራር ወጣገ-ባነቶችን በማስቀረት ዛሬን በትክክል በመሥራት ነገን በጽኑ መሠረት ላይ ለመገንባትና ተወዳዳሪ ተቋም ለመፍጠር ፋይዳው የጎላ መሆኑን ጠቁመዋል።
ከዓመታት በፊት መሰል ሙከራዎች ተጀምረው ሳይሳኩ መቆየታቸውን ያስታወሱት አምባሳደር ሬድዋን፣ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት አመራሮችና ባለሙያዎች ፕሮጀክቱን በአጭር ጊዜ ውስጥ በማሳካታቸው አመስግነዋል።
በቴክኖሎጂ የበለጸገው ይህ ሥርዓት የሚዲያ ጥቆማ፣ የቅሬታ ማቅረቢያና መከታተያ የሞባይል መተግበሪያን እንዲሁም የዌብ ፖርታል አማራጮችን ያካተተ መሆኑ ተገልጿል።
29/04/2026
የ800 ዓመት እድሜ ጠገቡ የወንጪ ቅዱስ ቂርቆስ ገዳም ታሪካዊነቱና ቀጣይ በጎ ዕድል ።
በኦሮሚያ ክልል በደቡብ ምዕራብ ሸዋ በወንጪ ዙሪያ ወረዳ የሚገኘው እድሜ ጠገቡን የወንጪ ቅዱስ ቂርቆስ ገዳም ለዘመናት በብትህውናና በምናኔ የቆየውን ያህል በቅርቡ በክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በገበታ ለሀገር ኢኮ ቱሪዝም አቧራውን በማራገፍ የትውልድ አሻራ ተቋዳሽ መሆን ችሏል።
ይህ ታሪካዊ እና ጥንታዊ የተፈጥሮ ጸጋዎች የተለገሱለት መልካምድር ሐይማኖታዊ እሴቶቹን እንደጠበቀ ለአከባቢው ተጨማሪ እድል ይዞ መጥቷል።
1, ሃይማኖታዊ ቱውፊቱን የጠበቀ ሕንጻ ቤተ መቅደስ
2,ደረጃቸውን የጠበቁ ሙዚየም
3,, የአብነት ት/ ቤቶች
4,የመጠመቂያ ቤት
5, ለጸሎትና ለንባብ ምቹ አጸድ
6, ከ1000 ሜትር በላይ የውስጥ ለውስጥ የወክ ማድረጊያ መንገድ
7, የጀልባዎች መዳረሻ ወደብ እና ሌሎችም ትላልቅ ፕሮጀክት በፍጥነትና በጥራት በመገንባት ላይ መሆኑን ተመልክተናል።
ይህ በቀጣይ አጭር ወራት ተጠናቅቆ ለምረቃና ለአገልግሎት ክፍት ሆና እንጠቀምበታል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ ።
ዛሬ በሥፍራው በመገኘት የሥራውን ጥራትና ፍጥነት በአስቸጋሪ የትራንስፖርት ሁኔታ ውስጥ ሳይበገሩ የግንባታ ቁሳቁስ በጀልባ በማመላለስ ይህን አኩሪ ታሪክ አሻራ በማስቀመጥ እያሰሩ ላሉ ሁሉ ልባዊ ምስጋናዬን ለማቅረብ እወዳለሁ።
ሚያዝያ 21/2018 ዓም
ምዕራብ ሸዋ፣ ወንጪ
27/04/2026
የኢትዮጵያ_የሃይማኖት_ተቋማት_ጉባኤና_የኢፌዲሪ_ጤና_ሚኒስቴር_ከፍተኛ_የሥራ_ኃላፊዎች ።
==================
በኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸኃፊ ሊቀ ትጉኃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ የተመራ የልዑካን ቡድን ከኢፌዲሪ ጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር መቅደስ ዳባ እና ከሚኒስቴሩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በዛሬው ዕለት በሁለቱ ተቋማት ትብብር በጋራ በሚሠሩ ሥራዎች ላይ ፍሬዓማ ምክክር አደረጉ፡፡
የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከኢፌዲሪ ጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የማህበረሰብን ጤና ለማስጠበቅ እና ወረርሽኖችን ፈጥኖ ለመቆጣጠር የሚረዱ በርካታ ውጤታማ ሥራዎች መሠራታቸውን ገልጸናል፡፡
በቀጣይ ባሉት ጊዜአት ትብብራችንን ይበልጥ በማጠናከር የሕዝብን ጤና ከመጠበቅ አንፃር በተለይም ግንዛቤ በማጎልበት እና በየደረጃው ያሉ የጤና ተቋማትን ከጉባኤው ቅርጫፍ መዋቅሮች ጋር በመስተሳሰር በርካታ ውጤታማ ሥራዎች መሥራት እንደሚያስፈልግ ተገልጿል፡፡
ይህንንም ተግባራዊ ለማድረግ ሚኒስቴሩ ሁኔታዎችን እንዲያመቻች ጥያቄ ቀርቧል፡፡
በተጨማሪም የአትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከጤና ጋር በተያያዘ እየሰራቸው ያሉትን ዋና ዋና ሥራዎች አስመልክቶ ለክብርት ሚኒስትር እና ለሚኒስቴሩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ሰፊ ገለፃ የተደረገ ሲሆን ማብራርያ በሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ዙርያም ጠቃሚ ማብራርያ ተሰጥቷል፡፡
የኢፌዲሪ ጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር መቅደስ ዳባ በበኩላቸው ከኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጋር በመተባበር የተሰሩት ሥራዎች ውጤታቸው ከፍ ያለ መሆኑን አስታውሰው ለአብነትም የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ከመከላከል እና የማርበርግ ቫይረስ ስርጭትን ከመግታት አንፃር የተሰራውን ሥራ አንሰተዋል፡፡
በቀጣይም ሀገራችን በራስ አቅም የተሟላ የጤና አገልግሎት ለመስጠት እያደረገች ያለውን እንቅስቃሴ የሃይማኖት ተቋማት እሴታቸውን ጠብቀው እንዲደግፉ ጠይቀዋል፡፡
በተያያዘም ክብርት ሚኒስትር ዜጎች በራስ አቅም ጤናማ ሕይወት መምራት ይችሉ ዘንድ በማሳሰብ እንዲሁም አስፈላጊውን ግንዛቤ እንዲያገኙ በማድረግ ሀገራችን የያዘችውን በራስ አቅም የተሟላ የጤና አገልግሎት የመስጠት እንቅስቃሴ ውጤታማ እንዲሆን ከጉባኤው ጋር በቅርበት መሥራት አስፈላጊ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
በመጨረሻም ክብር ሚኒስትር በቀጣዩ የበጀት ዓመት ከሚሠሩት ሥራዎች ውስጥ ከጉባኤው ጋር የሚሠሩትን ሥራዎች በዝርዝር በመለየት ከኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር ያለንን ትብብር በማጠናከር የተሻለ ሥራ እንዲሰራ ለሚመለከታቸው የሥራ ኃላፊዎች አቅጣጫ እና መመሪያ ከሰጡ በኋላ የዕለቱ የምክክር መድረክ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል፡፡
26/04/2026
ዛሬ በመጋቤ በረከት ግርማ ደምሴ መታሰቢያ በልጆቻቸው የተገነባ ሕንጻ ለአሰላ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ሙዚየም ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሱማሌ ጀግጅና ምስራቅ አርሲ አህጉረ ስብከት ጳጳስ ,ዶ/ር አካለ ወልድ ተሰማ (ቀሲስ) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መገናኛ ብዙኃን ዋና ሥራ አስኪያጅ ፣ የሀገረ ስብከቱ የሥራ ሓላፊዎች ፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ፣ የመጋቤ በረከት ግርማ ደምሴ ቤተሰቦችና ጓደኞች በተገኙበት መርቀናል ሕንጻውም የመጋቤ በረከት ግርማ ደምሴ አጽም ያረፈበት መካነ መቃብርና ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሚውሉ ቢሮዎች እና ሙዚየም መሆኑን ቤተሰቦቻቸው ገልጸዋል መጋቤ በረከት ግርማ ደምሴበሕይወት አርአያ የሚሆኑ አባት ነበሩ ::
ነፍስ ይማር
ሚያዝያ 18 ቀን 2018 ዓ.ም አሰላ)
20/04/2026
የጅማ መንበረ ጵጵስና ደብረ መዊዕ መድሃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን
አዲስ ለሚያስገነባው ታሪካዊው እና ዘመናዊው በ3800 ካ.ሜ ላይ የሚያርፍ እና ሥራው የብዙ ኦርቶዶክሳውያን እገዛ የሚጠይቅ መሆኑን በትናንትናው እለት በአካል ተገኝቼ ተረድቻለው ።
በሀገር ውስጥም በውጭ አገር የምትገኙ ሁላችሁም ትብብርና ድርብርብ ይጠይቃል።
የሕንፃው ሥራ መጠናቀቅ ለጅማ ከተማ ተጨማሪ ውበትን ያጎናጽፋል ተብሎ ይጠበቃል።
ሚያዝያ 12/2018 ዓም
ጅማ
ሀገር አቀፍ የሠላም ና የመከባበር ኮንፈረንስ ላይ የቀረበ መልእክት ።
ቤኒሻንጉል ፣አሶሳ
ሚያዝያ 8/2018 ዓ.ም
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the organization
Telephone
Website
Address
Https://goo. Gl/maps/fccaRpXKLTKqA2hP 9
Adama
1000