Yetneberk Tadele
Fact based insights on Ethiopia’s politics, economy & society. Open dialogue via comments & messages NB: Please read our RULES before commenting on this page
1.
No hate speech is allowed
2. Do not use obscene, rude, crude, or insulting nicknames towards the admin of this page.
3. Do not harass, threaten, embarrass, swear at, sexually harass or abuse another participant.
4. For your safety, please do not post personal information like (ID number, phone number, smart card number) on our wall or in the comments.
5. One-liner comments that are negative, def
13/06/2026
Beautiful game. Bravo USA 🇺🇸
09/06/2026
ይህቺ የልጆቼ እናት ነች:: የሕይወቴ አጋር፣ በደስታም በፈተናም ከጎኔ የቆመች ልዩ ሰው። ብዙ ችግሮችንና ፈተናዎችን አብረን አልፈናል፤ አንድም ቀን ቅሬታ ሳታሰማ፣ በትዕግሥት፣ በፍቅር እና በጽናት ከጎኔ ቆማለች። ለመስዋዕትነቷ፣ ለትዕግሥቷ እና ለማይናወጥ ፍቅሯከልቤ አመሰግናለሁ። እግዚአብሔር ይባርክሽ፤ እወድሻለሁ። ❤️🙏
05/06/2026
ይህ ልክ የዛሬ 11 አመት - የሙሽርነት ሳምንት (ጫጉላ) ላይ የተነሳነው ፎቶ ነው። የዛሬ 11 አመት እንኳን ለትዳርና ለወደፊት ኑሮ የሚሆን ንብረትና ሀብት ሊኖረን ይቅርና እኛ ራሳችን ሀገር አልባ ስደተኞች ነበርን። ህይወት ወዴት እንደምትወስደን የማናውቅ፣ ሀገራችንን ጥለን የተሰደድን ባይተዋሮች። ከሳምንት በላይ ቢበዛ ከወር በላይ ማቀድ የማንችል ምስኪኖች (ድሆች)....ፍቅራችን ብቻ ነበር ተስፋችን፣ መዋደዳችን ብቻ ነበር በውሎ አዳራችን ውስጥ የነገን ተስፋ አጮልቀን ማየት እንድንችል የሚያግዘን። ....... ይህ የጭላንጭል የተስፋ ህይወት ደግሞ አንድ አመት ብቻ ቢሆን ባልከፋ፣ ሁለትም ቢሆን ጥሩ ነበር፣ ሶስት አመትም አልሆነም......ብዙ አመታት ነጎዱ.....ብዙ ክረምቶች፣ ብዙ የጸደይ ወራት ተቀምጠን አለፉ!! የሙሽርነታችን ዘመን እየራቀ በስደት ውስጥ ልጆች እየተወለዱ፣ ህይወት እንደ ሜዳ ላይ ሰንበሌጥ እያወዛወዘችን፣ ተስፋችንን ያዝነው ጨበጥነው ስንል እየራቀን .... “ነገን ያለ እግዚአብሄር ማን ያውቃል?” እያልን ብቻ ጥርሳችንን ነክሰን አንጀታችንን አስረን ውሎ ማደሩን ለመድነው። ለስደተኛ ከፈጣሪ ውጪ ማንም የለውም!..... ከተከበብንበት የዘመድ አዝማድ፣ ከነበርንበት የዝና ማማ፣ ከተወለድንበት ቄሄና አድባር ተሽቀንጥረን ቁልቁል ተጥለን እርስ በእርስ ብቻ አይን ለአይን እየተያየን፣ በሰለለና በሚደጋገም ድምጽ “አይዞህ! አይዞሽ!” እየተባባልን በመጨረሻም አቀበቱን ገፍተን ደመናውን ገምሰን፣ ውቅያኖሱን ከፍለን እግዚአብሄር “ወደዚህ ሂዱ..” ብሎ ወዳሰማራን ስፍራ፣ “እንኳን በሰላም መጣችሁ” ብሎ የሚቀበለን ህዝብ መሀል ሰፈርን። .... በዝያም ልጆችም ተጨመሩልን፣ የጎደለ የመሰለን ሁሉ በእጥፍ ተካስን፣ ያጣነው የመሰለንን ነገር ሁሉ አገኘነው። በእርግጥ ተስፋ ያደረግነው ነገር ሁሉ ምንም ሳይቀር አንድ በአንድ እየተቆጠረ ተሰጠን። - ነፍስህ እስካለች ድረስ በህይወትህ ውስጥ የማይለወጥ ምንም ነገር የለም!....... እግዚአብሄር ታማኝ ነው አይረሳም! እግዚአብሄር ቀን አለው!! እንደ ተባለው ግን እግዚአብሄር ተስፋህን ሊፈጽም ባዘጋጀው ቀን ወደ አንተ ሲቀርብ አንተ ከስፍራው አትጥፋ! ኑር!
በተስፋ ኑር!
በእምነት ኑር!
በሕይወት ኑር!!
01/06/2026
ባለፈው ሰሞን አንዲት የአራተኛ አመት የፋርማሲ ተማሪ በመመረቂያ አመቷ የትምህርት ቤት ክፍያ አጣሁ በማለት ራሷን አጠፋች የሚል ዜና አየሁ:: በወቅቱ የኢኮኖሚ መንገራገጭ ሳቢያ ችግር ላይ የወደቁ: ያሰቡበት መድረስ አልቻልንም የሚሉና ጊዝያዊ ችግራቸውን ዘላለማዊ አድርገው ያሰቡ ብዙ ወጣቶች በአሳዛኝ ሁኔታ በለጋ እድሜያቸው ይህችን ምድር በገዛ ፈቃዳቸው ተሰናብተዋል:: ዛሬም ተመሳሳይ ፍላጎት ያላቸው በሶሻል ሚዲያ ለሞት ሲያንገራግሩ ይሰማል። እኔ በሁሉም ላይ ለመፍረድ ፍላጎት የለኝም:: ነገር ግን እኔ እንደ እናንተ አስቤ በነበረ ኖሮ ገና በአስራዎቹ እድሜዬ ራሴን አጥፍቼ ተዘንግቼ ነበር…..
የ12ኛክፍል ማትሪክ የወሰድኩት በ16 አመቴ ነበር:: አባቴ የመፈተኛ አመት ላይ ምንም ዝግጅት አለማድረጌን ሲመለከት ደግመህ ተማር አለኝ:: እምቢ አልኩት:: ከቤት አባረረኝ:: የጓደኛዬ ቤተሰቦች ጋር ተጠግቼ ማትሪክ ተፈተንኩ:: አባቴ እንደፈራው ውጤት ሳይመጣልኝ ቀረ:: አንድ አጎቴ ይሰራበት የነበረ የነዳጅ ማደያ ተቀጥሬ እያጠናሁ ድጋሚ ለመፈተን ማጥናት ስጀምር የማደያው ባለቤት ወዲያው አባረረኝ:: መሄጃ ጠፋኝ:: ገዳም ልገባ ጠፍቼ ሄድኩ:: ሁለት ወር ቆይቼ ልጅ ነህ ብለው አሰናበቱኝ::
የት ልሂድ? አንድ የረሳሁት አጎት ሩቅ ሀገር እንዳለኝ ትዝ አለኝ:: ትራንስፖርት እየለመንኩ ከዝያም የ12 ሰአት የእግር መንገድ 20 ወንዝ ስችል እየዋኘሁ ሳልችል ወደ ፈለገበት ይግፋኝ እያልኩ ረሀብ እየጠበሰኝ እንደ ማስቲሽ እግር ላይ የሚጣበቅ ጭቃ አቆራርጬ ደረስኩ:: እዚህ ጋር መሞት እችል ነበር:: የምሄድበትን አላውቅም ድካምና ረሀብ አንገላቶኛል፤ ተስፋ የለኝም፤ ነገ ምን እንድምሆን አላውቅም:: እዝያው ወንዝ ውስጥ ስምጥ ፀጥ ብዬ ብቀር እችል ነበር::
እዝያ ጭልም ያለ ጫካ ውስጥ በማላውቀው ባህልና ቋንቋ ውስጥ ጥቂት ወራት ቆየሁ:: መኪና የለም: መብራት የለም: ቴሌቭዥን የለም፣ ስልክ የለም፤ አዲስ ነገር የለም:: ዥውው ያለ ገጠር:: እንዳልመለስ ያንን የመጣሁበትን የስቃይ መንገድ ያንን ወንዝ ፈራሁ:: ቆይ ውሀው ይጉደል እየተባልኩ እዝያው ሰነበትሁ::
በዚህ መሀል አንድ ጽናቴን ያየ የትምህርት ቢሮ ሀላፊ ታሪኬን ሰምቶ አዘነልኝና ያለቋንቋ ፈተና ደባብቆ መምህርነት ስልጠና እንዳገኝ አመቻቸልኝ:: ..... እፎይ!!
ኮሌጁ ስደርስ ግን ውጤቴ ቢያስገባኝም እድሜዬ ለመምህርነት ቁመቴም ለሰሌዳ እይመጥንም በማለት ለሚቀጥለው አመት ተመለስ ተባልኩ:: ... ወደ ማን እመለሳለሁ? በምን ሳንቲም እመለሳለሁ? ..... ለተማሪዎች ዶርም ተሰጠ የካፌ ካርድ ተስጠ:: እኔ በረሀብ እየተቆራመድኩ በብርድ እየተጠበስኩ ሁለት ቀን ከቢሮው ደጅ እያደርኩ ዲኑን በለቅሶ እያስቸገርኩ ቆየሁ:: እግዜር ይስጠው ተለመነኝ። ተመርቄ መምህር ሆንኩ::
ሌላ የሚቀበለኝ ስለሌለ እዝያው የላከኝ ቦታ ተመልሼ አንድ እመት አስተማርኩ:: ከዝያ በላይ አልቻልኩም:: ወደ ትውልድ ስፍራዬ ተመልሼ በመምህርነት ቅጠሩኝ ብዬ እመለከትኩ:: ቋንቋውን እችላለሁ: እንግሊዘኛም በደንብ ማስተማር እችላለሁ አልኳቸው:: ካለህበት ቦታ መልቀቅያና መሸኛ አምጣ አሉኝ:: ጊዜ ሳላጠፋ አመጣሁ:: …..ሳቁብኝ:: ችግሩ ከስምህ ነው ስምህንም ቀይረው ብለው አፌዙብኝ:: ደነገጥኩ:: ቅስሜ ተሰበረ:: ተስፋ ቆረጥኩ:: እዚህም ጋ መሞት እችል ነበረ:: ዘመድም ሀገርም አጣሁ፣ ጨላለመብኝ::
አፈር ግጬ አፈር በልቼ እንደገና ተማርኩና ስጨርስ ወደ አዲስ አበባ አመራሁ:: እዝያም ገብቼ እንዳይደላኝ ብዬ ቀን እያስተማርኩ ማታ እየተማርኩ ተመረኩ:: በተመረቅሁበት ሙያ ስራ አግኝቼ ተቀጠርኩ:: ብዙም እልቆየሁ ከአንዴም ሁለት ጊዜ የግድያ ሙከራ ተፈጸመብኝ:: ከባለስልጣናት እስክ ፖሊስ ተደራጁብኝ:: በስለት ተወግቼ ተጣልኩ:: የቀጠረኝ ድርጅት እንኳ የት ወደቀ ብሎ ሳይፈልገኝ ጅብ ይብላው ብሎ ሸሸኝ፣ ሞቴን አድበስብሶ አለፈው:: ጉዳዩን የሚያውቁ የሙያ አጋሮቼም ሰምተው እንዳልሰሙ ሆኑ:: ሀገሬን ጥዬ ተሰደድኩ:: .... ሌላ የጭንቀት ህይወት አሳለፍኩ::
ሳልሞት ቀረሁ:: እግዚአብሔርም አልገደልኝም: የዛቱብኝም ሊገድሉኝ ሳይችሉ ቀሩ። እኔም ተስፋ ቆርጬ ነፍሴን አላጠፋሁዋትም::
ቀን ያልፋል፣ ጊዜ ይለወጣል፣ ኢኮኖሚ ይሻሻላል፣ ተስፋ አስቆራጮች ሁሉ ያልፋሉ፣ .......ትልቁ ነገር አንዲት ነፍስን ጠብቆ በትዕግስትና በጽናት መጓዝና ነገን ተስፋ ማድረግ መቻል ነው። ከሁሉ በላይ ደግሞ ፈጣሪ ያለ ምክኒያት አልፈጠረኝም ብሎ ማመን ነው።.....
እኔ ዛሬ ያ ሁሉ መከራና ስቃይ አልፎ ከምፈልገው በላይ ብቻ ሳይሆን መሸከም ከምችለው በላይ ተደርጎልኝ፣ በፍቅርና በትዳር ተሰብስቤ፣ በልጆች ተከብቤ፣ በልጅነቴ ተመኝቼ ያጣሁትን ትምህርት አለም አለኝ ብላ ከምትኮራባቸው ታላቅ የትምህርት ተቋም ውስጥ እየተማርኩ፣ ዘመኑ ከፈጠራቸውና የቴክኖሎጂ የመጨረሻው የተባለለትን መኪና እያሽከረከርኩ፣ ፈጣሪዬን እያመሰገንኩ በደስታ እኖራለሁ። ነገ ከዛሬ በእጅጉ የተሻለ ሰው ሆኜ ማን ያውቃል ሀገሬንና ህዝቤን እንደገና ለማገልገል እበቃ ይሆናል። እኔስ ባልበቃ ልጆቼ......
ተስፋ ቆርጬ ቢሆን ኖሮስ? ሞቼ ቢሆን ኖሮስ?......
እንኳን ፈጣሪ በሰጠኝ ህይወት ይቅርና ራሴ ባቀድኩት ነገር እንኳ ተስፋ ቆርጬ ወደ ሁአላ ተመልሼ አላውቅም!!..... ወጣቶች ሁሉም ነገር በነበረበት አይቀጥልም እና ዛሬ በዋላችሁበትና ባደራችሁበት ልክ ብቻ እያሰባችሁ በነገ ላይ ተስፋ አትቁረጡ! በነፍስ አይጨከንም። ነገን ማን ያውቃል?...ማንም!!! ከመኖር ተስፋ አለ! ካለ መኖር ምን አለ? - ምንም የለም!!
ቅኝ ግዛት ትንሽ አልበዛም?
አምላኬ ቶሎ ናና ውሰደኝ 😀 😀
24/05/2026
ሰሞኑን ወደ ኢትዮጵያ ጎራ ካሉት ኢንግሊዛውያን መካከል እንስቷ (ሴቷ) ያጋራችው ቪዲዮ እጅግ ስሜት ይነካል። እንዲህ ትላለች፦
~ "I thought we are going to Ethiopia."
~ "What makes you say this isn't Ethiopia?"
"ኢትዮጵያ የመጣን መስሎኝ?"
"ታዲያ ይሄ ኢትዮጵያ አይደለም ያለሽ ማነው?"
... አዎ! ይሄ የሚሊየን ሳይሆን የቢሊየን የአለማችን ህዝብ ሊለው የሚችለው እውነታ ነው። ኢትዮጵያ ለማኝ፣ ደሀ፣ ረሀብተኛ፣ በድንቁርናና በሁአላ ቀርነት የምትታወቅ፣ አለም ረሀቧን ሊያስታግስላት እየዞረ የሚለምንላት፣ ከጦርነት በቀር ሰላምና ደስታ የሌላት ችጋራም ሀገር ነች.... ብሎ ያስባታል።
ኢትዮጵያ ..... የማያውቋት ቀርበው እስኪያይዋት፣ ዳሰው እስኪረዷት ድረስ አዎ የተሰጣት ስምና የተጻፈላት የአለም ታሪክ ይሄው ነው።.....እሱ ብቻ አይደለም የራሷ ዜጎች፣ ራሳቸው ኢትዮጵያውያኑ ከችጋሯ በቀር፣ ከልመናዋ በቀር፣ ከጦርነቷ በቀር፣ ከቆሸሸው መንደሯ በቀር መልካም ነገሯ እንዲወራ አይፈልጉም፣ ሰላምም እንዳላት፣ መልካም ገጽታም እንዳላት፣ ዛሬም ብዙ አስደሳች ገጸ በረከቶች እንዳሏት አለም እንዲያውቅ የማይፈልጉ ብዙ የራሷ ዜጎች አሉ።......
..ለዚህ ነው ወደ ኢትዮጵያ ድንገት ጎራ ያሉ የሌላው አለም ሰዎች "ይሄማ ኢትዮጵያ አይደለም፣ አውሮፕላኑ በስህተት ነው አውሮፓ የጣለን" ብለው እስኪደነጋገሩ ድረስ ግራ የሚጋቡት፣...እንጂማ ሀገሬ ችግሯን ብቻ እናስብ፣ ድህነቷን ብቻ እናስታም ካላልን በቀር ውብ ሀገር፣ የምድር ገነት ነች!!!
22/05/2026
ዘንድሮ ራሷን ለአለም ለማስተዋወቅ እንደ አዲስ አበባ የሶሻል ሚዲያን አቅም አሟጦ የተጠቀመ ያለ አይመስለኝም። ብዙዎች ሞክረውታል፤ እነ ኬኒያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ናይጄሪያ፣ ዱባይ ራሷ፣ አልፎ አልፎም አንዳንድ የአውሮፓ ሀገራት በሶሻል ሚዲያ ለመታየት ያደረጉትን ጥረት ያህል እንደ አዲስ አበባ ገነውና ገዝፈው ለመውጣት አልቻሉም። በዚህ ወቅት ሶሻል ሚዲያን በፎሎወር ብዛት የሚዘውሩ በርካታ ዝነኞች ወደ አዲስ አበባ እየተመሙ ነው፣ ብዙዎች ደግሞ ቀነ ቀጠሮ ይዘዋል፣ ሌሎች ደግሞ በሚያዩትና በሚሰሙት ነገር አፋቸውን በእጃቸው ጭነዋል። እንዲህ ያለ ነገር ከኢትዮጵያ አንጠብቅም ነበር የሚሉ ብዙ የፖድካስት ውይይቶችን እየሰማን ነው።....... በጥቅሉ እኛን ፍቅር ነሳን፣ ሰላም አጣን እንጂ ያለን ነገር የሚታየው ሁሉ ለሌላው አለም በእጅጉ የተወደደና የሚያስጎመጅ መሆኑን አያስተዋልን ነው።
19/05/2026
ኢትዮጵያውያን የአርሰናል ደጋፊዎች እንኳን ደስ ያላችሁ! ይገባችሁዋል!!
17/05/2026
የሄኒን ኢንተርቬው ሰማሁት። ሄኖክ በየዋህነት ተነሳስቶ፤ በኢትዮጵያ ታሪክ ተሰምቶ በማይታወቅ ሁኔታ "ህዝብ በገንዘቡ የሚሳተፍበት አንድ ፊልም" ለመስራት አልሞ የገንዘብ እርዳታ ጠየቀ። የጊዜው የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሁኔታ የትናንቱን መቶ ሺህ ብር ዛሬ የመቶ ብር ያህል እንኳ ዋጋ እያሳጣ ቃል የማያስጠብቅ ለዕቅድ የማይመች ሆኖ ፈረጃ የተባለውን ፊልም ለማውጣት ከህዝብ የሰበሰበው ሶስት ሚሊየን ብር የሶስት መቶ ሺህ ብር አሽቆልቁሎበት ክፉኛ ተሰቃየ።
ሄኖክ በቃለ መጠይቁ ላይ በሰፊው እንደ ገለጸው በእጅጉ የጎዳው የገንዘብ እጥረቱ ብቻ ሳይሆን የኛ ሰው "የሀበሻ" ኮሜንት (ዘለፋና ስድብ) ነበር። --- ገንዘብ ከለገሰው ይልቅ ዳር ቆሞ የተመለከተው ነበር በስድብ ሲያጥረገርገው የሰነበተው። ልጁ ግን ለአላማው ቁርጠኛ፤ ለቃሉም ታማኝ ነበርና ቃሉን በተግባር ተርጉሞ ፊልሙን ለእይታ አበቃ።
.. የኛ ሰው (ሀበሻ) እጅግ ከባድ (አስቸጋሪ) ከሚባሉ የአለም ህዝቦች ዋነኛው ይመስለኛል። ሰው ሲያገኝም ከስር ከስር መገዝገዝ፣ ቀን ሲዘምበትም ምሳር (መጥረቢያ) ይዞ ለመጣል መሯሯጥ። ....ይህ የሆነው ደግሞ በዚህ ዘመን የተፈጠረው (ቀለም ገብቶኛል፣ ሰለጠንኩ) ያለው ትውልድ በተነሳበት መሆኑ ደግሞ በእጅጉ አስገራሚ ነው።.....
ብቻ ሄኖክ ወንድሙ ለብዙዎቻችን በብዙ መልኩ ምሳሌ ሊሆን የሚችል አርቲስት ነው። ወንድማችን የሞራል ስብራት ሳይደርስበት፣ የማንም ስድብና ማጥላላት ተስፋ ሳያስቆርጠው ህልሙን ለስኬት ማብቃቱ በእጅጉ የሚደነቅ ምናልባትም በሲኒማው ኢንዱስትሪ ስሙን በደማቅ ቀለም ለመጻፍ የቻለ በመሆኑ ለአምስት አመታት የለፋበትን ፈረጃ ፊልሙን ለማየት እንጓጓለን!
Click here to claim your Sponsored Listing.