ace_senaa
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ace_senaa, Blogger, Amman.
19/04/2026
Feeling good in black...
09/09/2025
Abay
04/02/2025
🦅
29/06/2024
A simple life
26/03/2024
Crosis✊
24/10/2023
Be back never ...
13/10/2023
07/10/2023
Good vibes only..
30/09/2023
Quietly confident...
11/01/2022
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ውለታዎች! ከኢትዮጵያ እስከ ዓለም ጠረፍ ድረስ።
ና ተከተለኝ ቋቅ እስኪልህ እውነታዎችን ላስቆጥርህ። ሁሉም ነገር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ገጸበረከቶች ናቸው። ይዘኽ የመጣኸው ቅንጣት የለህም። ቁጠርልኝ አንተው!
✔️የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ፊደል ቀርጻ ሆሄያት ደርድራለች።
✔️ የቀን መቁጠሪያ ቀመር ቀምራለች።
✔️ ዘመናዊ ትምህርት ባልነበረበት "ሀ" ግዕዝ "ሁ" ካዕብ እያለች ዋርካ ስር ፊደል አስቆጥራለች።
✔️ አ ቡ ጊ ዳ ሄ ው ዞ እያለች የሆሄ ንባብ አስተምራለች።
✔️መልዕክተ ዮሃንስን በጥበብ እያስጠናች ስድ ንባብን አሰልጥናለች። /ዛሬም ድረስ ዓለም ይኼንን እና ከላይ የተጠቀሱትን የትምህርት ዘዬዎች ይከተላል።/
✔️ የክርስቶስ የልደት ቀንን ከማንም ከምንም በላይ አስልታ ደርሳበታለች።
✔️ የክርስቶስን ግማደ መስቀል በግሸን አስቀምጣለች።
✔️ ስለህዋ ጥልቅ ጥናት አድርጋ ጥንት ከትባ አኑራለች።
✔️ ዘመናዊ ህክምና ሳይመጣ በባህላዊ ህክምና ትውልድን አገልግላለች። ለዘመናዊው የህክምና ዘርፍም አስተዋጽኦዋን አበርክታለች።
✔️ የአገር መሪዎች ለህዝብ ባይመቹ እየሻረች፣ ቢያጠፉ እየገሰጸች ዘመናትን አሻግራለች።
✔️ ወራሪ ጠላት ቢመጣ ታቦት ይዛ በመውጣት ምዕመናኑን አስከትላ ድንበር አስከብራለች።
✔️ እግዚአብሔር ለሙሴ የሰጠውን ጽላት በክብር ይዛ አስቀምጣለች።
✔️ አርሳ፣ ዘርታና አጭዳ ትውልድ መግባለች።
✔️ እጸዋትን እየተከለች የልምላሜ ፊትአውራሪ ሆናለች።
✔️ ለአገራችን የኪነጥበብ እድገት /ትወና/ መሰረት ነች።
✔️ ለአገራችን የሙዚቃ ልህቀት ዕልፍ ዜማዎችን አበርክታለች።
✔️ለአገራችን የስዕል ጥበብ መሰረት ነች።
✔️ ዓለም ላይ ትልቅ ተጽዕኖ የፈጠረው የሬጌ ሙዚቃ ምትና ቅኝት ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቅዳሴ የተቀዳ ነው።
✔️የአገራችን የቱሪዝም ገቢ ከ80% በላዩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ኃብቶች ናቸው።
✔️ ከኢትዮጵያ በዩኔስኮ ከተመዘገቡ፥ የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ቅርጾች ውስጥ 95% የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነው።
✔️ ዓለማችን ላይ ለሚነሱ በሽታዎች የሚቀመሙ /የሚመረቱ/ የመድኃኒቶችን ቀመር ከትባ ያኖረች ነች።
✔️30 ቀናትን ደርድራ፣ ለ13 ወራት በአግባቡ ስም ሰይማ፣ የሳምንቱን ቀናቶች በተናጠል ያስጠናች ነች።
✔️ በኢትዮጵያ ብዙ ንዋያቶችን አፍስሳ ታላላቅ ቤተመቅደሶችን በማነጽ ትልቅ የልማት ስራን ሰርታለች።
✔️ብዙ የረቀቁ ኪነ-ህንጻዎችን በመገንባት ለከተማ ውበትና የገበያ ማዕከላትን አስፋፍታለች። ይኼ ደግሞ ለአገር ሌላኛው ትልቅ የገቢ ምንጭ ነው።
✔️ በኃይማኖታዊ ዘርፍ የቱሪስት መስህቦች ተብለው የሚጎበኙት 99% ያህሉ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ኪነ ህንጻዎች ናቸው።
✔️ በገጠራማ ስፍራዎች የጥርጊያ መንገዶችን በማሰራት ውሃና መብራት በማስገባት ለብዙ ከተሞች እድገት ሆናለች።
✔️ሆስፒታልና ትምህርት ቤት በማይገኙባቸው ስፍራዎች መዋጮ በማሰባሰብና እራሷም ድጋፍ በማድረግ ብዙ አልምታለች በብዙ አስተምራለች።
✔️ግዕዝን ከጥንት ጀምሮ እስከ አሁን አኑራለች።
✔️የአለባበስ፣ የአመጋገብ፣ የጋብቻና የለቅሶ ስርዓቶችን ደንግጋለች።
ከዚህም በላይ የኔ አዕምሮ ቆጥሮ የማይጨርሰው እልፍ ውለታዎችን ለኦርቶዶክስ እምነት ተከታዩም ይሁን ለአህዛቡ ሁሉ ግልጋሎት ይሆን ዘንድ ከማንም ከምንም በላይ አበርክታለች። "ከሰኞ-እሁድ" ብትጠራ ስያሜው የ'ርሷ ነው። "ከመስከረም- ጷጉሜ" ብትል የወሩ ቅርጽ የ'ርሷ ነው። ዛሬ ቀኑ "7" ነው ብትል ቅድስት ሥላሴ ምስክሬ ናቸው የቀን ቀመሩም የ'ርሷ ነው። ታዲያ ሁሉን ለሰጠችህ ሁሉን ለቸረችህ ዝቅ ብለ ብታመሰግን ምን ይቀርብኃል? ከድንቁርና አላቀቀችህ እንጂ ምን አጎደለችብህ? እኔ ግን ሁሉን ለሰጠችኝ ቅድስት ቤተክርስቲያን ሁሉን እሆንላታለሁ።
እስኪ እናንተ በየሀይማኖታችሁ ለኢትዮጵያ ህዝብ ምን አረጋችሁ??????
Click here to claim your Sponsored Listing.