My notice
One day I will seccess 1 mehone leAndinet enji lemeleyayet aydelem
ከተዋህዶ ድምጽ የተወሠደ
ሚሚ ብትናገር
13 መጋቢት · PUBLIC
50 Reads
ትንሿ ሚሚ ብትናገር ኧረ ምን ምን ትል ነበር
ምን ማለቴ እንደሆነ እስኪ ታሪኩን ልናገር
ቀኑ እሁድ ጠዋት ሰዓቱ ዘጠኝ ሰዓት
በዚያን ጊዜ ነበረ ትንሿን ሚሚን ያየሗት
ጸጉሯን በሪባን አስይዛ ተከትላ ጓደኞቿን
ቁርባን ልትቀበል መጣች እንዳጣመረች እጆቿን
በዚያን ጊዜ ተቆጣሁ እኔ አዋቂ ተብየዋ
በሚሚም ተበሳጨሁ ስርአት ባለማክበሯ
ከዚያም ወደ እርሷ ጠጋ ብየ ጎተትኳትና ከሗላ
አሁኑኑ በይ አዉጭ አፍሽ ዉስጥ ካለ የሚበላ
ደግሞም ቁርባን እንዳትቆርቢ በደንብ ሳትለብሽ ያን ነጠላ
ብየ ስጮህባት ሚሚ ኣየችኝ ቀና ብላ
እኒያ የሚያማምሩት ዓይኖቿ አንድ ስሜት ያሳያሉ
ኀዘን ይሁን ትዝብት አላዎኩም ብቻ ግን ያስፈራሉ
“ የኔን ይቺን የህጻን ስህተት አስቀድመሽ ሳታይ
ያንችን የተበላሸ ሕይወት እስኪ መጀመሪያ አስተካክይ ” ብላ የምትል
መሰለኝ
እርሷ ግን ምንም አላለች ብቻ አየችኝ እና ደንግጣ ወደ ሗላዋ
ተመለሰች
እርሷ ወደ ሗላ ስትመለስ አይኗ ግን ዉስጤ ቀረ
ለምን እንደዚያ አስደነገጥኳት ለምንስ ንግግሬ መረረ
ምን ብላኝ ይሆን በልቧ ለምንስ እንደዚያ አየችኝ
ብየ ማሰብ ጀመርኩኝ ሚሚ ዉስጤን ረበሸችኝ
ቅዳሴም ካበቃ ቡሃላ ልቤ እረፍት አልሰጥ አለኝ
የሚሚ ሁኔታዋ በህሊናየ እየታየኝ
አልተናገረችኝ እርሷ ከቶ አናዳችም ነገር
ግን ብትናገር ኖሮ ምን ምን ትለኝ ነበር
ስለኛስ ስለ ሁላችን ሚሚ ምን ትናገር ይሆን
አፍ ብትፈታ ብታዎራ እድሜዋ ትንሽ ባይሆን
እያልኩ ሳለ ሚሚ መጣች ደግሞ አሁን በሃሳቤ
ከህሊናየ ጋር ትግል ጀመርኩ ጸጸት ስለገባዉ ልቤ
ሚሚ ዛሬ ምን ሆነሽ ነዉ እንደዚያ በሃዘን ያየሽኝ
መናገር ብትችይስ ኖሮ ዪሄኔ ምን ነበር ያልሽኝ
ብዬ በዉስጤ ጠየኳት የርሷም ተከፈተ አንደበቷ
ንግግሯንም ጀመረች በመናገር ስለ ህይዎቷ
“ዛሬ እንግዲህ በህልምም ቢሆን ከሰጣችሁኝ አንደበት
እስካሁን የተሰማኝን እስኪ ልናገርበት
ትንሿ ሚሚ እባላለሁ እድሜዬም 5 ዓመት
ቤተ ክርስቲያን እመጣለሁ ሑሌ እሁድ እሁድ እለት
ሌሎችም ቦታዎች ቢሆን ከእናቴ ጋር እሄዳለሁ
ታዲያ እኔም እንደ አቅሜ ብዙ እታዘባለሁ
ሰዉ ሁል ጊዜ አሸንጉሊት ዪዠ ስታገል ሲያየኝ
በጆሮየ የማልሰማ ይመለስዋል በአይኔም የማዪታየኝ
ግን እኮ አስተዉላለሁ እናት እና አባቴ ሲጣሉ
እኔን ከወንድምሽ ጋር አትጣይ እያሉ
አባዬም እየጠጣ ሁሌ ቤቱን ይረብሻል
አትረብሽ እያለ ግን እኔን ሁሌ ይቆጣል
የእናቴም ጓደኞቿ ሁልጊዜ እቤት ይመጣሉ
እኔን ከፊታቸዉ አስቀምጠዉ መጥፎ ነገር ያወራሉ
ሁሌ ሰዉን ሲያሙ ሰዉን ሲሰድቡም እሰማልሁ
እኔም ይሄን ቁጭ ብዬ ከእነርሱ እማራለሁ
ታዲያ ሌላ ከየት ልማር ገና ህጻን ነኝ እኔ
ከዎላጆቼ ነዉ እንጂ ከእነርሱ ስር በመሆኔ
ምን ተማርሽ ብሎ ማን ከቶ ሊጠይቀኝ
ቴሌቪዥን ሆኗል ወዳጀ ቋንቋን እንኳን የሚያስተምረኝ
ደግሞም ክርስቲያን ነሽ ብላኛለች የክርስትና እናቴ
ግን ፀሎት አይፀለይ መዝሙር አይሰማ በቤቴ
የክርስቶስን ስም አይጠሩ ቤተሰቦቸ ክርስቲያን ሆነዉ
የኛ ቤት ፀሎት ደግሞ እገሌን አጥፋልን ነዉ
ታዲያ ምኑንም ሳልማረዉ ምኑንም ቀድሜ ሳላዉቀዉ
ሗላ ባህሏን ሐይማኖቷን ተወች ብለዉ ሊቆጡኝ ነዉ
የትኛዉን ልተዉ እና የትኛዉን ልከተለዉ
ኢትዮጲያዊት መባሉም እኮ አሁና እያሳፈረኝ ነዉ
ክርስቶስ ሁሉን ዉደዱ አለ ጠላታችሁንም ጭምር
ብሎ አይደል ሰባኪዉ የሚሰብከዉ ዘማሪዉስ የሚዘምር
እናንተ ግን ለዎገን እንኳን የላችሁም ንፁህ ፍቅር
ሰወች እኛ ቤት መጥተዉ አማራ፣ኦሮሞ፣ጉራጌ፣ትግሬ ተባብለዉ
ሲያቀርቡና ሲያርቁት ሰዉን በዘሩ ከፍለዉ
ይሄንንም እሰማለሁ! እና ማንነቴ ምንነቴ ጠፍቶኛል እኮ ለእኔ
ሳይሻል አይቀርም መሰል አሜሪካዊት መሆኔ
ከቤታችን ዉስጥ እኮ ወንዱ አያቴ ይሻላሉ
ከቶ ክፉ አይናገሩም ሰዉንም ይወዳሉ
እርሳቸዉም እንዲህ ይላሉ ያሳለፉትን ህይወት ያወራሉ
በአንዲት ጎጆ ቤት ዉስጥ ሁሉን እየተካፈሉ
ከወገናቸዉ ጋር አብረዉ እየጠጡ እየበሉ
የእገሌ ልጅ የእገሌ ዘር ሳይባባሉ ከቶ
ሁሉ ተጋግዞ ተማክሮ ተሳስቆና ተጫዉቶ
ልጅ ወላጁን ወላጅ ልጁን አጥብቆ እያከበረ
እግዚአብሔርን አመስግኖ መኖር ብቻ እንደነበረ
የዱሮዉን እያነሱ ብዙ ታሪክ ይነግሩኛል
ግን ያንን ዛሬ ስለማላይ ተረት ተረት ይመስለኛል
እንግዲህ ወደ አንች ልመለስ…….!
ነጠላ በደንብ ሳትለብሽ አትቆርቢም ዛሬ ያልሽዉ
አንች ነጠላ በደንብ ለብሰሻል ግን የታለ የቆረብሽዉ?
በአለባበሴ በኩል ልክ ነሽ ተሳስቻለሁ
ግን ያ.. እኮ ትንሽ ስህተት ነዉ ወደፊት እመለሳለሁ
እናንተ አዋቂወቹ ግን በሌላዉ መፍረድ ቀርቶባችሁ
እራሳችሁ አትድኑም በንስሃ ታጥባችሁ
ለኀጢያተኞች እማይደል ጌታ የተሰቀለዉ?
እኔ የ5 ዓመቷ ህፃን ምን ኀጢያት ኖሮብኝ ነዉ?
በእርግጥ ከትላንት ዎዲያ ብርጭቆ ሰብሪያለሁ
ባለፈዉ ሳምንት ከወንድሜ ከረሚላ ቀምቻለሁ
ግን እናንተ አዋቂወች ስንት በደል ያለባችሁ
ለካ የሌላዉን በደል ነዉ የምታስቡ በልባችሁ
እናም ታላቋ እህቴ ቢገባሽ ኖሮ ምስጢሩ
የመስቀሉ፣የቁርባኑ፣የትምህርቱ፣የመፅሃፉ
አያስቆጣሽም ነበር የእኔ ነጠላ መዛነፉ”
አዎ………!!
ትንሿ ሚሚ ብትናገር
ይህንን ትለኝ ነበር
ጌታችንም ለካ ለዚህ ነዉ የነገራችሁ ሐዋርያቱን
ልቡ እንደ ሚሚ ያልሆነ እንደማይወርሰዉ መንግስቱን
እርሷ በዉጭ ብትሳሳት ልቧ እኮ ንፁህ ነበር
ደግሞም ተመልሳለች አንደበቷም ባይናገር
እኛ ግን አዋቂዎቹ ዉጫችንን ስናጠራ
ዉስጣችን ቆሽሾ ቀረ ዋናዉን ስራ ሳንሰራ
ብየ ያኔ ብንን አልኩኝ
ወደ ራሴም ተመለስኩኝ
የትንሿም ሚሚ ሃሣብ ከህሊናዬ ዉስጥ ወጥቶ ሲበር
የቤተ ክርስቲያን ትምህርት አልቆ መዝሙር እየተዘመረ ነበር
እኔ ግን ቀስ ብየ ወጣሁ በሗለኛዉ በር
ከህፃናቶችም ክፍል ገባሁ ሚሚን ልፈልጋት
ከአንድ ወንበር ላይ ተቀምጣ ብቻዋን አገኘሗት
ከዚያም ወደ እርሷ ተንደረደርኩ
ይቅርታ አልኳት ከእግሯ ወደኩ
ሚሚ ከእኔ እንደምትበልጥ ዛሬ ገና በደንብ አወኩ{2}
ወስብሃት ለእግዚአብሔር፡፡
ምንጭ፡ ድምፀ ተዋህዶ
አይኔን ብጨፍንሥ
✍★ዓይኔን ጨፍኜ ብፀልይስ?★
"""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""
ምእመናን የምንፀልየው አይኖቻችንን ከፍተን ወደ ላይ ወደ
ሰማይ አቅንተን ነው፡፡ ምክንያቱም እንዲህ መፀለይ የቅዱሳን
አበው ስርዐት ነውና፡፡ይህንን በተመለከተ ቅዱስ ዳዊት
‹‹ዓይኖቼን ወደ ሰማይ አቀናሁ ብሉአል›› መዝ 120፣1
በተጨማሪም ‹‹በሰማይ የምትኖር ሆይ ዓይኖቼን ወደ ተራሮች
አነሳሁ፡፡እነሆ የባሪያዎች ዓይኖች ወደ ጌታቸው እንዲሆኑ
የባሪያይቱም ዓይን ወደ እመቤቲቱ እጂ እንደሆነ እንዲሁ
እስኪምረን ድረስ አይናችን ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሄር
ነው፡፡›› ብሉአል፡፡መዝ122፣1-2 ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም
ያስተማረን ዓይንን ከፍቶ ወደ ሰማይ አቅንቶ መፀለይን ነው፡፡ዮሐ
11፣41 ፤ 17፣1 ፡፡ ከዚህም የተነሳ የሃዲስ ኪዳን ምእመናን
ሁሉ የሚከተሉት ይህንኑ የፀሎት ስርአት ነው፡፡ለምሳሌ ቅዱስ
እስጢፋኖስ በአይሁድ እጅ በድንጋይ እየተወገረ እርሱ ግን
ዓይኑን ከፍቶ ፣ ወደ ሰማይ አቅንቶ ‹‹ጌታ ኢየሱስ ሆይ ነፍሴን
ተቀበል›› እያለ ይፀልይ እና ይማልድ ነበር፡፡ሐዋ 7፣54
ነገር ግን አንዳንድ ሰዎች ሃሳቤ ተተሰብስቦ መፀለይ የምችለው
አይኔን ስጨፍን ነው፤ የሚል አስተሳሰብ አላቸው ግን ዓይን
ስለተጨፈነ ሃሳብ አይሰበሰብም ፣ልቡናም አይረጋጋም፡፡
ምክንያቱም ዓይንን በመጨፈን ሃሳብ የሚሰሰብ ቢሆን ኖሮ
ዓይኖቻቸው የጠፋባቸው ወገኖቻችን ሁሉ ለፀሎት በተነሱ ጊዜ
ልቦናቸው አይበተንባቸውም ያሰኝ ነበር፡፡ምናልባትም‹‹ነገር
በዓይን ስለሚገባ ነው›› ይባልም ይሆናል፡፡ይሁን እንጂ ነገር
በጆሮም ይገባል፤ ታዲያ ስንፀልይ ጆሮአችንን በጥጥ ልንዎትፍ
ነው?ነገር እኮ ከልቦናም ይመነጫል ይህንንስ እንዴት ልናደርግ
ነው?
እኛ በስሜታዊነት በአንድ ጊዜ ከመንፈሳዊ ህይወት ጫፍ ላይ
ለመውጣት፣በአንድ ጊዜ ከ ፍፁምነት ማዕረግ ለመድረስ
ስለምንፈልግ እንጂአሳብን ሰብስቦ በተረጋጋ ልቡና መፀለይ
በአንድ ጊዜ የሚደረስበት ፀጋ አይደለም፡፡ምክንያቱም መንፈሳዊ
ሕይዎት ደረጃ አለው፡ ፡በመሆኑም በብዙ ገድል ከአንዱ ደረጃ
ወደ ሌላኛው ደረጃ በእግዚአብሄር ቸርነት ይደረስበታል እንጂ
ቁጭ ብሎ ስለተፈለገ ብቻ የሚገኝ አይደለም፡፡ስለዚህ
በምንፀልይበት ጊዜ የሚረብሹን ብዙ የሃሳብ ውጣውረዶች
ቢኖሩም ከእነርሱ ጋር በእምነት እየተጋደልን እስከመጨረሻው
መፅናት አለብን፡፡በዚህን ጊዜ እነዚያ የሚያስቸግሩን ነገሮች
በሙሉ በእግዚአብሄር ፈቃድ እየጠፉልን ይሄዳሉ፡፡ ስለሆነም
ክርስትና የገድል ህይዎት መሆኑን ማወቅ አለብን፡፡ቅዱስ
ጰውሎስም ‹‹መልካሙን ገድል ተጋድያለሁ›› ያለው በከንቱ
አይደለምና፡፡2ጢሞ4፣7 እግዚአብሄር ሁላችንንም ይርዳን፡፡
አእሜን።
13/07/2015
08/02/2015
Melkam negern hulu madreg yasdestegnal
Cliquez ici pour réclamer votre Listage Commercial.