Muhe shash
ሚኒም አየነተ ዘናዎቺን ላኩለን ኢንፎርማቲኦን ላኩለን
05/08/2024
የስራና ክህሎት ሚኒስትር ወደ ሁለት የአውሮፓ ሀገራት ዜጎችን ለስራ ስምሪት ለመላክ ዝግጅቱን ማጠናቀቁ ገለፀ!.
ሐምሌ 29/2016).
የውጭ ሃገር የሥራ ስምሪት የዜጎችን መብት፣ ደህንነት እና ጥቅም የሚያስጥብቅ እንዲሁም በከፊል የሰለጠነ የሰው ሃይል ብቻ ሳይወሰን የሰለጠነ የሰው ሃይል ስምሪትን የሚያካትት እና የዘመነ አገለግሎት እንዲሆን ባስቀመጥነው የሪፎርም አቅጣጫ መሰረት ወደ አውሮፓ (Sweden and Norway) ገበያ ለመግባት ቀደም ብሎ በተጀመረ ጥረት የዝግጅት ምዕራፍ ተጠናቆ ወደ ተግባር መግባቱን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስታውቋል።
በመሆኑም በስምምነቱ መሰረት የተጠየቁ የሞያ ዘርፎች የሚከተሉት ናቸው።
1- ካርዲዬሎጂስት
2- የማርኬቲንግ ባለሙያ
4- ኬሚካል ኢንጅነር
5- ባስ ድራይቨር
6- አርክቴክት
7- አካውንታን
8- አውቶሞቲቭ ቴክኒሽያን ባለሙያ
9- የላብራቶሪ ቴክኒሺያን
10- የአይ ቲ ባለሙያ
11- የፋርማሲ ባለሙያ
12- የሽያጭ ባለሙያ
13- የሶፍትዌር ባለሙያ
14- ሜዲካል ዶክተር
15- የኮምፒተር ጥገና ባለሙያ
16- ነርስ
17- ግራፊክስ ዲዛይነር
18- የፀጉር ባለሙያ
19- የደንበኛ አገልግሎት ባለሞያ
በመሆኑም አስፈላጊውን ስልጠና እና ሌሎች መመዛኛዎችን በሟሟላት የዚህ ዕድል ተጠቃሚ መሆን የምትፈልጉ ዜጎች በኢትዮጲያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት (https://lmis.gov.et) በመመዝገብ የዚህ ዕድል ተጠቃሚ እንድትሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጥሪ አቀርቧል።
05/08/2024
!!
ዜና እረፍት ሻሸመኔ
በዛሬውለት አንድ ታዳጊ የሻሸመኔ ወጣት በድንገተኛ መኪና አደጋ ወደማይቀርበት ወደ ዳሩል አኬራ ሄዷል።
ሐምሌ 29 /11/2016
ይሆ ወንድማችን ሙሉ ስሙ (አል አሚን ታምራት) ይባላል መኖሪያ አድራሻው 010 ካ አሌሉ ከገበያው ጀርባ ሲሆን የኡስታዛ መርየማ ሰኢድ ልጅ ነው ኡስታዛ መርየም በተለያዩ ቦታዋች ቁርአን ና ኪታቦችን የምታስቀራ ትታቃለች።
አሁንም 010 አሌሉ አከባቢ በሚገኝው አል ፈትህ መስጂድ የሴቶች ጀመአ ታስቀራለች አሁንም በማስቀራት ላይ ትገኛለች።
ይሄ ወንድማችን ትለንትና ሐምሌ 28/11/2016 የፈጅር ሰላት ከመድረሱ በፊት ከደሎመና በ10ኪሎ ሜትር ላይ በምትገኛው ቢደር ከተማ ላይ በመኪና አደጋ አርፏል።
ይሂወንድማችን በ 1987 ተወልዶ በ27 አመቱ አርፏል።
አላህ ጀነተል ፍርደውስ ይወፍቀው
#ለመላ ቤተሰብ ዘመድ አዝማድ አላህ ሰብር ጥንካሬ ይስጣችሁ።
ሁላችንንም ከእንደዚህ አይነት አደጋ አላህ ይጠብቀን።🤲
ለዚች እናታችንም ሶቢሩን ጥንካሬውን ይስጣት🤲
የሆነ ቀን ድንገት ሁሉም ነገር ያበቃል፤ ከሞት ጋር ፊት ለፊት እንጋፈጣለን፤ የማናሸንፍበትን ትግል ታግለን ላንመለስ እንሄዳለን! 💔😭
ጌታችን ሆይ! በዛ ቀን እዘንልን 🤲
የዚህ ወንድማችን የቀብር ስነስራት ዛሬ ሐምሌ 29/11/2016/ ሰኞ 010 እዛው አካባቢ በሚገኘው መስጂድ ሰላቱል ጀናዛ ከተሰገደበት በኋላ አለሉ የሙስሊሞች መካነ-መቃብር የቀብር ነ ርዓቱ ተፈጽሟል።
ሁላችሁም ይህንን ወንድማችን በዱአችሁ አትርሱት።🤲
Click here to claim your Sponsored Listing.