Awel Digital Engineering & Logistics
Electro-Mechanical Engineering Solutions | Installation • Commissioning • Troubleshooting | Cranes & Industrial Systems | Mojo, Ethiopia
15/05/2026
13/05/2026
ክሬን የሚወድቀው በአጋጣሚ አይደለም — በቸልተኝነት ነው!
እስካሁን ባየኋቸው የኢትዮጵያ የክሬን አደጋዎች ሁሉ አንድ ዓይነት ምክንያት አለ:
❌ ክሬን ሳይፈተሽ ሥራ ይጀምራል
❌ ያልሰለጠነ ኦፕሬተር ይሰራዋል
❌ Safety limit ሲደርስ ኦፕሬተሩ ያሽረዋል
❌ LMI (የጭነት መቆጣጠሪያ) ሳይጣራ ይሰራል
ውጤቱ? → አዲስ አበባ ጉርድ ሾላ፣ መገናኛ፣ ኮምቦልቻ፣ አሶሳ...
እነዚህ አደጋዎች ሊታወቁ እና ሊቀሩ የሚችሉ ነበሩ! 😔
ክሬን ያለ ሰለጠነ ኦፕሬተር → መሣሪያ ሳይሆን አደጋ ነው።
Share ♻️ — ግንዛቤ ሕይወት ያድናል!
#ኢትዮጵያ
12/05/2026
🚨 በኢትዮጵያ ክሬኖች ለምን ይወድቃሉ? — ከዘርፉ Expert የቀጥታ ትንተና
በአዲስ አበባ ጉርድ ሾላ፣ መገናኛ፣ በወሎ ኮምቦልቻ፣ እና በቢንሻንጉል ጉምዝ አሶሳ የደረሱት የክሬን አደጋዎች ያስታወሱናል:
❝ ችግሩ ክሬኑ አይደለም — ስርዓቱ ነው ❞
🔴 የቻይና ክሬኖች (Zoomlion / XCMG / Sany)
✔️ ዋጋ ርካሽ ነው
✔️ ልምድ ባለው ሰው ሊሰራ ይችላል
✔️ ጥገናው ቀላልና ቁሳቁሱ ቶሎ ይገኛል
✖️ Safety system ደካማ ነው
✖️ ኦፕሬተሩ የ safety limit ቢጥስ ክሬኑ አይቆምም
✖️ አደጋ ሲጠጋ ወዲያው አይጠቁምም — ሰዎች ሲጎዱ ወይም ሲሞቱ ነው የሚታወቀው
🟢 የአውሮፓ/አሜሪካ ክሬኖች (Grove, Liebherr, Rigo)
✔️ CAN Bus የሚባል digital network ሁሉም sensors ያስተሳስራል
✔️ LMI (Load Moment Indicator) ከ interlock ጋር ይሰራል
✔️ አደጋ ሊደርስ ሲል ክሬኑ ራሱ ይቆማል — ሰው አይጎዳም
✔️ EN 13000 እና ASME B30.5 international standard certified
✖️ ችግር ሲፈጠር ለማስተካከል ልዩ software እና ስልጠና ይፈልጋል
✖️ የሚያውቆቸው ቴክኒሻን ስለሌሉ ብዙዎቹ ኢትዮጵያ ውስጥ ለረጅም ጊዜ ሳይሰሩ ይቀራሉ
💡 በቀላል ቋንቋ ማብራሪያ:
የቻይና ክሬን = ቀላሉ መኪና
→ Brake ሲበላሽ ይሮጣል — አደጋ ይደርሳል
የአውሮፓ ክሬን = Airbag + ABS + electronic ያለው ዘመናዊ መኪና
→ አደጋ ሲቃረብ ቆሞ ያስጠነቅቃል
→ ግን ሲበላሽ ያለ trained mechanic ማስጠገን አይቻልም
⚠️ ኢትዮጵያ ምን ታጣለች?
1️⃣ የሰለጠነ crane operator — ስልጠና ሳይሰጥ crane ቁልፍ ይሰጣሉ
2️⃣ Licensed crane technician — European system የሚያውቅ ባለሙያ ያስፈልጋል
3️⃣ የሀገር ውስጥ crane safety certification — አሁን ድረስ የለም
4️⃣ Pre-lift inspection culture — ብዙ site ላይ ምንም check ሳይደረግ ሥራ ይጀምራል
እኔ ማን ነኝ?
በሁለቱም ስርዓቶች ሰርቻለሁ — Grove GMK 55T & 80T, Liebherr, Rigo 60-65T truck-mounted crane, እና Zoomlion, XCMG, Sany ክሬኖች ላይ።
በአውሮፓ ደረጃ international crane training አጠናቅቄ የሁለቱን ስርዓቶች ልዩነት ከቅርብ አይቻለሁ።
ዓላማዬ:
→ ኢትዮጵያ ውስጥ የክሬን ደህንነት ግንዛቤ ማሳደግ
→ አደጋ ከደረሰ በኋላ ሳይሆን አደጋ ከመድረሱ በፊት ለመናገር
Share ♻️ አድርጉ — ሕይወት ሊታደግ ይችላል!
#ኢትዮጵያ #ግንባታ
Reliable Engineering | Smart Diagnostic Solutions
Your trusted partner for engine, electrical, and hydraulic diagnostics delivering precision and performance every time.
📍 Modjo City, Ethiopia
📞 +251 934 858 484
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Mojo