MY PATH

MY  PATH

Share

my purpose is to share my social life experience and comments to people.

የሊቢያ ሰማዕታት የመጨረሻ ደቂቃዎች | ሐይማኖትን መካድ ወይም መሞ*ት | ከ10 ዓመት በፊት ይህ ተከስቶ ነበር | @gedamattv Documentary 26/05/2026

ዛሬ በአጋጣሚ እነዚያ ወገኖቸ ሲሰየፉ፣ የቅርብ ዘመዶቹ ታስረውበት ሲጨነቁ ከነበሩት ፣ መሃል አንድ ሰው አገኝቸ ፣ ዘመዱ ተርፋ የነገረችውን ፣ የነበረውን አጫዎተኝ አጫወተኝ። ስለዚህ እኔም ደግሜ ለጠፍኩላችሁ።

ዛሬ ይህን ቪዲዮ ድንገት አገኘሁት፣ ይህ ከመፈፀሙ ጥቂት ቀናት ቀደም ብሎ እነዚህ ወገኖቻችንን አሸባሪዎች አሰልፈዋቸው የመጀመሪያውን ተሰላፊ ሲቀሉት በህለሜ ጌታ አሳየኝ። እኔም ጌታ ሆይ ይህን ማየት አልችልም ብየ አቀርቅሬ አልቀስ ነበር። ጌታ ቦታውን "ፉት" ነው ብሎ ነገረኝ። እነዚህ ሊሰየፉ ሲወሰዱ ሌሎች ደግሞ በእስር ቤት ውስጥ በጭንቀት ላይ ናቸው አለኝ። እየተንሰቀሰቅሁ ሳለቅስ የራሴ ለቅሶ ከእንቅልፌ ቀሰቀሰኝ። በቤተክርስቲያናችን በወቅቱ የመሪዎች ኮሚቴ ሰብሳቢ ስለ ነበርኩ ይህንኑ ነግሬአቸው ፀለይንላቸው። ስንፀልይም ለቅሶየን መቆጣጠር አልቻልኩም ነበር። ለቤተክርስቲያናችን አመራሮች ጌታ ቦታውን "ፉጥ" ነው ብሎኛል ብያቸው ነበር። ድርጊቱን የዓለም ህዝብ ይሰማዋልም ብሎኝ ነበር። ድርጊቱ ከተፈፀመ በኋላ ቪዲዮኑን ሳይ ያው በህልሜ ያየሁት ቦታ ነበር። ጌታ "ፉት" ሲል የሰማሁትን ግን "ፑንት ላንድ"፣ ነው ብየ ነበር የነገርኳቸው። እኔ ከተናገርኩት ጋር የቦታ ሥም ልዩነት በመፈሩ ተደናገርኩ። ኋላ ላይ ቆይቶ ያ ሥፍራ ጥንት "ፉጥ /phut " እንደሚባልና በሊቢያና ግብፅ መካከል ይገኝ የነበረ ቦት እንደሆነ መፅሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ላይ አነበብኩ።
በግፍ የተገደሉትን ሰማዕታት አስቀድሞ እግዚአብሔር ያውቅ ነበር። በመሠዊያው ሥር በሰማይ ሆነው አምላካቸውን ፣ "እስከመቸ ፍርድህ ይዘገያል፣" ከሚሉት መሃል ይሆናሉ ብየ አስባለሁ። ሠውን በግፍ ለምትገሉ ግፈኞች ሁሉ ወየውላችሁ !!!!!!!!!
ከሰማይ ግፍን የሚያይ አምላክ አያንቀላፋምና።
Google _The name "Put (or Phut)" is used in the Bible for Ancient Libya,

የሊቢያ ሰማዕታት የመጨረሻ ደቂቃዎች | ሐይማኖትን መካድ ወይም መሞ*ት | ከ10 ዓመት በፊት ይህ ተከስቶ ነበር | @gedamattv Documentary 🌟 የሊቢያ ሰማዕታት የመጨረሻ ደቂቃዎች | ሐይማኖትን መካድ ወይም ሞ*ት | ከ10 ዓመት በፊት ይህ ተከስቶ...

19/05/2026

ዛሬ በፕሮጀክታችን የታቀፈ ህፃን ቢሯችን ከናቱ ጋር በመጣበት አጋጣሚ የትምህርት ውጤቱ መቀነሱን አወቅን። እናቱን ለምን ትምህርቱ ቀነሰ፣ ጎበዝ አልነበረም ወይ? አልኳት። የሽንኩርት መፍጫ እሰራልሻለሁ እያለ ጥናቱን ቀንሶ ነው፣ አለችኝ። እኔ በልጅነቴ አባቴ የመከረኝን ምክር መክሬ አሰናበትኩት። ለናተም ከዓመታት በፊት የለጥፍኳትን ገጠመኘን ካለችበት ፈልጌ ለጠፍኩላችሁ፠

“ የበሽር ጦሮች”
8ኛ ዓመቴን ላገባድድ 4 ወር ገደማ ሲቀረኝ ከደሴ /ጢጣ ጦር ካምፕ ወደ ሀረርጌ/ ጉርሱም አውራጃ ፉኛን ቢራ ከተማ ሄድን። አባቴ ተከራይቶ የጠበቀን ቤት ከተማው ዳርቻ ነበር። የ3ኛ ክፍል ተማሪ ነበርኩ። አንድ ቀን ሠፈራችን በሽር የተባለ ቀጥቃጭ (ቱምቱ ) በሥራ ቦታው ብረቱን በከሰል እሳት እያጋለ ፤ መጥረበያ፣ ሜንጫ፣ ጦር ፣ ወዘተ ሲሰራ አይቸ እጂግ ተደነቅሁ። ከዚያም ይህን ከምትሰራ ለምን ሽጉጥና ጠመንጃ አትሰራም እይልኩ እጨቀጭቀው ጀመር። እሱም ልጅ ነው ብሎ ከእኔ ጋር መለፋለፍ የፈለገ መሠለኝ፣ ቆይ የጀመርኩትን ሥራ ልጨርስና የምትለውን እሰራልሃለሁ፣ ይለኛል። እኔም እውነት መስሎኝ ቶሎ የጀመረውን ሥራ ጨርሶ ሽጉጥና ጠመንጃ እንዲሰራ በወናፍ እሳቱን ማናፋት ለምጀ ሳናፋለት መዋል ጀመርኩ። ከትምህርት ሰዓት ውጭ በሽር ጋር መዋሌን ቤተሰቤ አያቅም።
የበሽር ሚስት፣ ሐለማ፣ ከቡና ገለባ የምትሰራውን ሆጃ ቀን ቀን በማንቆርቆሪያ አያመጣች በጌባ( ከቅል የተሰራ ሆጀ፣ ሻይ መጠጫ እቃ ) እያጠጣችን ሱሰኛ አደረገችኝ። ወራት ካለፉ በኇላ ግን በሽር ለእኔና ለአባቴ እንደ መጠናችን ያማሩ ጦሮች ሰርቶና ከጦር ዘንግ ጋር አዋዶ ማስታወሻ ሰጠኝ። እኔም ደስ ብሎኝ ወደ ቤታችን ወስጀ ለአባቴ፣ ለሱ የተላከለትን ጦር፣ ሰጠሁት። ነገር ግን ያለጠበቅሁት ፈተና ገጠመኝ። እንዴት ጦሮቹን ሊሰጥህ ቻለ ብሎ እጄን እየጎተተ በሽር ሥራ ቦታ ድረስ ወሰደኝ። በሽርንም ሲጠይቀው ሁሉንም ነገረው።
አባቴም ተገርሞ፣ በል ሁለተኛ እዘያ እንዳትሄድ፣ ትምህርትህን ተከታትለክ ካደግህ በኇላ አንተ ራስህ ሽጉጥና ጠመንጃ ትሰራለህ፣ ብሎ መከረኝ። አድጌ የሶሲዮሎጂ ምሩቅ ብሆንም ብርቱ የቴክኒክ ዝንባሌየ እስከዛሬም አልተለየኝም።
በ 12 ዓመቴ ፣ 5ኛ ክፍል ስደርስ፣ አባቴ ወደ ኦጋዴን (ቀብሪደሃር) ተዛውሮ ሲሄድ፣ እኛን፣ ቤተሰቡን ግን ጉርሱም ትቶን ሄደ፡፡ እትየ ፣ ያሳደገችኝ ደጓ እናቴ፣ አቶ ብርሃኑ የተባሉ ዳኛ ቤት ተከራይታ ሠፈር ቀየርን፡፡ መደዳውን የተሰሩና 3 ባለ 2 ክፍል ቤቶች ሲሆኑ፣ የእኛ ቤት ከዳር፣ ቀጥሎ ፣ጠበቃ ማነየ ከሚስቱ ጋር የሚኖሩበትና ክፍሎችና በጨረሻ ዳኛው ከነቤተሰባቸው የሚኖሩበት ቤቶች ነበሩ፡፡ ማናየ ወዳጅ አድርጎኝ፣ ማታ ማታ የወንጀለኛ መቅጫ ህግ ያስጠናኝ ነበር፡፡ ከመሸ እየፈራ ከቤት መውጣት አይወድም፡፡ ማታ ማታ ከሚስቱ ጋር ከልኳንዳ ሥጋ ገዝታችሁ ኑ እያለ ይልከንና እራታችንን የሥጋ ጥብስ እንበላለን፡፡ ሚስጢረኛውም አድርጎኝ ውሽማው የወለደችለትን ወንድ ልጅ፣ በአራስነት እተኛችበት ቤቷ ድረስ ወሰወዶ አሳይቶኛል፡፡
በኋላ ግን የማነ ጠላኝና ዐይንህን ለአፈር አለኝ፡፡ ከትምህርት ቤት ስመለስ ቤታችን በር ላይ ቆሞ እንዳልገባ ይከለክለኛል፡፡ እኔንም እትየንም ግራ ገባን፡፡ የዳኛው ሚስት ወ/ሮ በዙ፣ ይህን አንድ ፍሬ ልጅ ምን አድርገኝ ነው የምትለው፣ ብለው ቢቆጡትም ከበር አላላቸውም፡፡ ምርር ያለኝ ቀን፣ ለዳኛው፣ ቤታቸው ገብቸ በደሌን መናገር ጀመርኩ፡፡ ነገር ግን ገና መናገር ስጀምር እልህና ሲቃ ተናንቆኝ ተንሰቅስቄ እያለቀስኩ፣ እርሰዎ ይተውት፣ እኔ እራሴ እበቃዋለሁ፣ ብያቸው እየሮጥኩ ከቤታቸው ወጣሁ፡፡ በሽር የሰራልኝን ጦሬን ከቤታችን አውጥቸ እየወዘወዝኩ፣ ስማ የማነ፣ ከዛሬ ጀምሮ አኔ ነኝ የማሳድድህ፡፡ ጦሬን በደረትህ ላይ ሳልቀበቅብብህ እጄን አትይዘኝም፣ አልኩት ፡፡ ዳኛው ከቤት ወጥተው የማነን ቢቆጡትም፣ ቁጣቸው ስሚት አልሰጠኘም ፡፡ የማነ ከስራ ሲመለስ ተራየን በሩ ላይ ጦሬን ያዠ እየጠበቅኩት አበሳውን አሳየሁት፡፡ ኳስ ጨዋታ ስሄድም ጦሬ አትለየኝም፡፡ በመንገድ ሲመጣ ካየሁት መንገዱን ዘግቸ አቅጣጫ አስቀይረዋለሁ፡፡ ተው ተብየ ብመከር አልሰማ አልኩ፡፡ አውሬ አደረገኝ። የማነ ችግሩን ለጓደኞቹ እየነገራቸው፣ እምጫወትበት ሜዳ ድረስ ይመጡና ህፃን ሆኜ ሲያገኙኝ እሱኑ እየሰደቡት ይመለሳሉ፡፡
አንድ ቀን እትየና ወ/ሮ በዙ የየማነን ሚስት ማድቤት አሰገብተው የጠባችንን ምክንያት እንድትነግራቸው ሲጨቀጭቋት እውጭ ሆኜ ሰማሁ፡፡ ከብዙ ውትወታ በኋል ተናገረች፡፡ አያድርስ ነው፣ እኔን ከዚህ አንድ ፍሬ ልጅ ጠርጥሮኝ እኮ ነው፣ አለች፡፡ እትየና ወ/ሮ በዙ ደንግጠው ሲጮሁ ሰማኇቸው፡፡ እኔንም ነገሩ ሲገባች ተፀይፌ አቅለሸለሸኝ፡፡ እትዬ ልጄን ይገልብኛል ብላ ቤቱን ለቀን ሠፈር ቀይረን ጦር ካምፕ ውስጥ መኖር ጀመርን፡፡
በአስተማሪነት 7 ዓመት ሠርቼ ዩንቨርሲቲ ልገባ ስል በልጅነት በደስታ ያደኩባትን የጉርሱም ከተማን ላይ ሄድሁ። በሽር በጣም ናፍቆኝ ስለነበር ላየው ሥራ ቦታው ነበር መጀመሪያ የሄድኩት። የስራ ቦታው ምንም ለውጥ አላየሁባትም፣ ያው ዳስ ነበረች። አጥቸው ስመለስ መንገድ ላይ ተገናኘን። ረስቶኛል። ሐሊማስ?ብለው እንባው በጉንጮቹ ላይ እየወረዱ እንደሞተችበት ነገረኝ። የኔም እንባ መፍሰሱ አልቀረም። ስላላወቀኝ ተስፋ ቆርጨ ተሰናብቸው 100 ሜትር ያህል እንደራቅሁ፤ ኃየሉ ብሎ ሲጣራ ሰምቸው ፊቴን ወደ ኇላ አዞርኩ። በሽር አስታውሶኝ ወደ እኔ እየሮጠ ነበር። ጠብቄው ሲደርስብኝ እላየ ላይ ተጠምጥሞ ይስመኝ ነበር። በሂወት ከቆየንና አገራችን ሰላም ስትሆን በሽርን እንደገና ሄጀ አየዋለሁ።
እነ ወ/ሮ በዙ ቤትም ሄጀ ነበር። እኩያየ የነበረችውን የምስራች ብርሃኑን እና እናተን ወ/ሮ በዙን አገኘኇቸው። እነሱም ፈፅመው ረስተውኝ ነበር። በብዙ የትዝታ ገጠመኞቻችን፣ የኔና የየማነን ጠብ ጨምሬ እንዲያስታውሱኝ ብነግራቸውም ትዝ ልላቸው አልቻልኩም። ተሰናብቻቸው ከቤት ወጥቸ ከራቅሁ በኇላ ከኇላየ ጥሪ ሰማሁ። ዘወር ስል ሁለቱም ወደ እኔ እየሮጡ ነበር። እላየ ላይ ተጠምጥመው ይስሙኝ ጀመር። ከነሱ ጋር ተመልሸ እንዳድር በለምነኝም ጊዜ ስላልነበረኝ አሽ ሳልላቸው ቀረሁ። ትንሽ የነበረችውን በለጡ ብርሃኑን ግን ዩንቨርሲቲ አገኘኇት።
ጉርስሞች ይህ ፅሁፈ ከደረሳችሁ ለነምስራች ብርሃኑ አስነብቡልኝ።

18/05/2026

ጌታ! አትመጣም ወይ?"
የነገርከን ሁሉ አንዳቸውም ሳይቀር
ሁሉም ተከናውኗል ተፈፅሟል በምድር
እንደ ኖህ ዘመን ሠው በዝሙት ወድቋል
ገሞራም አልቀረ ወንድ ከወንድ ይጋባል
በእውቀትም ተራቆ ሠው ጨረቃ ደርሷል
አለማት ታስሰው ሚስጢር ይፋ ሆኗል
ሂዋን እደፈጠርክ ከአዳም አጥንት
ሠው ጀምሮልሃል ሊፈበርክ ሂወት
ጦርነትም በዝቷል የመምጫህ ምልክት
ጎርፍና ድርቅ፣ በርሃብም መሞት
ቸነፈር በሽታ በምድር ላይ መብዛት
ሁሉም ተከናውኗል አልቀረም በያይነት
ሥጋ የሚያበሰብስ የሞት መቅሰፍት
እሱም ተፈብርኳለ ሞልቷል በያለበት
የተበተነው ህዝብ በዓለም ጥግጋት
ህየወት አልባ ክምር የዋሻ አፅማት
ህያው ሆኖ ቆሟል በሀገሯ ቅድስት
የቤተ መቅደሱ ግንባታ ግብዓት
ተጠናቋል አሉ ተመርቶ በፍጥነት
መቅደሱ ውስጥ ገብቶ እኔ ነኝ የሚለው
ይመለካል አሉ ሃውልቱን ገንብተው
ቀያይ ጊደሮች ሊሆኑ መስዋዕት
ተራብተዋል አሉ በብርቱ ዝግጂት
ነብዩም ተገልጧል የውሸት አባት።
ሁለቱ ወይራዎች ሞትን ያልቀመሱት
ዳግም ሲመለሱ ለምስክርነት
ዓለም ይሰማቸዋል ተሰርቷል ኢንተርኔት።
ግንባራችን ላይ ሊመታ ምልክት
ላንገዛ ላንሸጥ ላይኖር ግብይይት
ካርድና ሞባይል የወቅቱ ማሳያ
ድንበር ሳይከላቸው ሠፍነው በዓለም ዙሪያ
እንድንሸማምት በሁሉም ገበያ
ሞግዚት ሆነውናል ለምልክቱ
ማህተም አሰኪመታ ሁሉም በያአናቱ።
ፍቅራችን ቀዝቅዟል
ግለኝነት ብሷል
ሠው ራሱን ወዷል
ስግብግብ ሴሰኛ ከንቱ ፍጡር ሆኗል
አርተፈሻል አስተውሎ ስለኛ ያስባል
ማንነት ተነጥቀን እንግዳ ሆነናል
መወሰን ተነጥቀን እሱ ይመራናል።
እንግዲህ ምን ቀረ ያልከን ሁሉ ሆኗል
ጌታ አትመጣም ወይ? ዘመኑ እንደሁ አልቋል።

20/04/2026

ነብዩ ኖህ ቁራን ለመላክ ለምን መረጠው ?
ቁራዎች በቅርቡ እስራኤልን ለምን ወረሯት፣ ባንዲራዋንስ ከሰንደቁ ላይ ለምን ፈተው አወረዱት?
Gemini ስለ ቁራ የሚለውን ቀጥሎ ለጠፍኩላችሁ።

የቁራዎች አስደናቂ ብልህነትና ችሎታ
Conversation with Gemini
ቁራ ስለተባለው የአዕዋፍ ዝርያ ብልህ ተፈጥሮ መረጃ ሊሰጡኝ ይችላሉ?

ቁራዎች በአዕዋፍ ዓለም ውስጥ ካሉ ዝርያዎች ሁሉ በብልህነታቸውና በማስተዋላቸው ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛሉ። ሳይንቲስቶች እንደሚሉት ከሆነ የቁራዎች የአዕምሮ ብስለት ከሰባት ዓመት ህፃን ልጅ ጋር ሊመጣጠን ይችላል።
ስለ ቁራዎች ብልህ ተፈጥሮ ጥቂት አስገራሚ ነጥቦች እነሆ፦
1. መሣሪያዎችን የመሥራትና የመጠቀም ችሎታ
ቁራዎች ለተፈለገው ዓላማ የሚሆኑ መሣሪያዎችን ፈብርከው መጠቀም ይችላሉ። ለምሳሌ፦

ጠባብ ቀዳዳ ውስጥ ያለን ምግብ ለማውጣት እንጨቶችን ይገነጥላሉ፣ ወይም ሽቦን በማጠፍ እንደ መንጠቆ (Hook) ይጠቀማሉ።

ለውዝ ወይም ጠንካራ ገፅ ያላቸውን ምግቦች ለመስበር መንገድ ላይ ያስቀምጡና መኪና እንዲፈጨው ያደርጋሉ። ከዚያም መኪናው ሲያልፍና ትራፊክ ሲቆም ሄደው ይበላሉ።

2. የሰውን ፊት የመለየትና የማስታወስ ብቃት
ቁራዎች ለረጅም ጊዜ የማይረሳ ትውስታ አላቸው።

ጓደኛና ጠላትን ይለያሉ፦ ጉዳት ያደረሰባቸውን ሰው ፊት ለዓመታት አይረሱም። እንዲያውም ያ ሰው ሲመጣ ለሌሎች ቁራዎች የማስጠንቀቂያ ድምፅ በማሰማት "ጠላት መጣ" ብለው ይነግራሉ።

መረጃ ያስተላልፋሉ፦ በአንድ ቁራ ላይ መጥፎ ነገር የፈፀመ ሰውን ሌሎች ያላዩት ቁራዎች እንኳ እንዲጠሉትና እንዲሸሹት የማድረግ "የማህበራዊ ግንኙነት" ችሎታ አላቸው።

3. ችግርን የመፍታት ስልት (Problem Solving)
ቁራዎች አንድን ግብ ለመምታት ደረጃ በደረጃ ማሰብ ይችላሉ።

በአንድ ታዋቂ ሙከራ ላይ፣ ቁራዎች በአንድ ጠባብ ብርጭቆ ውስጥ ያለን የውሃ መጠን ከፍ ለማድረግና ምግቡን ለማግኘት፣ ድንጋዮችን እየለቀሙ ብርጭቆው ውስጥ በመጨመር የውሃውን መጠን ከፍ ሲያደርጉ ታይተዋል። ይህ የመፈናቀል ሕግን (Displacement) በተግባር የመረዳት ችሎታቸውን ያሳያል።

4. ለወደፊት ማቀድ
ቁራዎች እንደ ሰው ለነገ ብለው ያስባሉ።

ምግብ አትርፈው ከቀበሩ በኋላ ሌላ ቁራ ሲያያቸው ካስተዋሉ፣ የተቀበረውን ምግብ ቦታ በመቀየር ሌላ ቦታ ይደብቁታል። ይህ የሚያሳየው ሌላው ቁራ ሊሰርቃቸው እንደሚችል አስቀድመው መገመታቸውን ነው።

5. ጨዋታና ቀልድ
ቁራዎች ለመዝናናት ብቻ ሲሉ የተለያዩ ድርጊቶችን ያከናውናሉ። በበረዶ ላይ መንሸራተት፣ ሌሎች እንስሳትን (ለምሳሌ የድመትን ጭራ) በመጎተት መቀለድና መሮጥ ይወዳሉ። ይህም ከፍተኛ የአዕምሮ እድገት ያላቸው ፍጥረታት መገለጫ ነው።

ባጭሩ፦ ቁራዎች ዝም ብለው የሚበሩ አዕዋፍ አይደሉም፤ በአካባቢያቸው ያለውን ሁኔታ ተረድተው ውሳኔ የሚያሳልፉ፣ የሚማሩና መረጃን የሚያጋሩ እጅግ ብልህ ፍጥረታት ናቸው።

03/04/2026

"ልጠይቅህ ሚስጢር "

በሠማይ በምድር የሞላህ እግዚሔር
አንዳችም በፊትህ ከቶ የማይሰወር
ኤልሻዳይ ነህና ልጠይቅህ ሚስጢር።
እንዴት ነው በሰማይ የገነቱ ስፍራ
ደግሞም የሲኦሉ ሠውን የሚያስፈራ
ቦታው አልጠገበም በዚህ ሁሉ ተጓዥ ሂያጁ በየተራ?
ነገሩን ባነሳም የተገረምኩበት
ሌላ ነው ጥያቄው የተጨነኩበት።
በዚች በምድራችን በምንኖርባት
ግፉ ሞልቶ ተርፎ በገነፈለበት
እልፍ አላአፍቱ በሚታጨዱባት
ግራና ቀኝ ያለዩ አበባ ህፃናት
በግፈኞች እብሪት ሲረግፉ በጥይት
ባዋቂ ተደፍረው ሲሞቱ በስቃይ
ይህን ሁሉ ክፋት እያየህ ከሠማይ
ግራ ስላጋባኝ የዝምታህ ነገር
አፌን በጄ ጭኜ ልጠይቅህ ሚስጢር።
ፃድቃን ከመሰዊው ሥር ለፍርድ ሲጠይቁህ
ቀሪው እስኪታረድ ጠብቁ እንዳልህ
ለዚህ ይሆን እንዴ የበዛው ዝምታህ
ኮታው እስኪሞላ የሚሞተው ህዝብህ
አይተህ እንዳላይ እንደህ ዝም ማለትህ?
በግፈኞቹ ላይ ያልነደደው ቁጣህ ?
ብለህ ይሆን እንዴ መምጫ ድልድይ ነው
በሞት ነው መንገዱ ወደኔ የሚመጣው ?

02/04/2026

"የአባቴን ቅሬታ በፍለጋ ስዳክር ኖርኩ"

( ካለፈው የቀጠለና መጨረሻ)
አባቴ ግን ከአብራኩ የወጣ ልጆቹን ሳያይ ነበር የተሰዋው፡፡ ባዩሽን በ5 ዓመት ዕድሜዋ ላሳድጋት ወሰድኳት ፡፡ የዩንቨርሲቲ ተማሪ በመሆኔ ለእጮኛዬ በአደራ አስረከብኳት፡፡ እናቷ አድራሻዋን ቀይራ እንዳትጠፋብኝ ስጋት ነበረብኝ፡፡ ዩንቨርሲቲ ስማር እረፍት ሳገኝ ደግሞ ወደ ሲግናል ሠፈር ሠፈር እየሄድኩ ወንድሜን ስፈልግ እውል ነበር፡፡ ሲወለድ ላየው የሄድኩበት ቦታና ምልክቶች ሁሉ ጠፉብኝ፡፡
4ኛ ዓመት ስደርስ፣ በፍለገዬ ተስፋ እየቆረትኩ መጣሁ፡፡ አባቴ አንቺን ከማግባቱ በፊት ወንድ ልጅ ወልዶ እንደነበረ ነግሮሽ ነበር፣ ብየ የባዩሽ እናትን፣ ማዕለድን አንድ ቀን ጠየቅኇት፡፡ እሷም በአጋጣሚ እንዳገኘችውና እንደምትጠይቀው፣ መልኩም ቁርጥ አባታችሁን ይመስላል አለችኝ፡፡ ከእሷ ያልጠበቅሁትን የምስራች ስሰመማ ደስታና የአባቴ ትዝታ ተደበላልቆብኝ መናገር ተሳነኝ።
አንድ ቀን፣ ማዕለድ ወንድሜ የሚገኝበትን አድራሻ በምልክት ነግራኝ ሲጊናል ሰፈር ወንድሜን ለመፈለግ ብቻየን ሄድሁ፡፡ ህፃናት የታጠረ ክፍት ሜዳ ውስጥ ኳስ ይጫወታሉ፡፡ ህፃናቱ የወንደሜን ሥም ሲጠሩ ሥመቸ ተከታትዬ የሚጠራውን ህፃን ለይቸ አወቅሁት፡፡ ነገር ግን አባቴን አይመስልም፡፡ ሞክሸው ሊሆን ይችላል ብየ አሰብኩ፡፡ ከልጆቹ መረጃ ለመሰብስባ እንዲመቸኝ፣ ጋዜጠኛ ነኝ ብየ አጠገቤ የተቀምጡትን ህፃናት ተዋወቅኋቸው፡፡ ጫዋታችሁን መዘገብ እንድችል እንደገና በቡድን ተደራጂታችሁ ተጫወቱ፤ በመጨረሸ አሸናፊውንና ተሸናፊውን ቡድን ገንዘብ እሸልማችኇለሁ፣ አልኳቸው፡፡
ወንድሜ የቡድን አምበል ሆኖ ተጫዋቾችን ለመምረጥ ከሥሬ ዘሎ ተነሳ፡፡ ቁርጥ አባቴን ነው፡፡ ሠውነቱ የፈረጠመ፣ ትካሻውና አጥንቶቹ ሰፋፊ፣ አፍንጫ ጎራዳ፣ የአባቴ ቅጂ ነው፡፡ከበዩሽ ጋር ቁርጥ ተመሳሳይም ናቸው።
እንባየን ተቆጣጠርኩት፡፡ አቅፌ እንዳልስመው ችግር ሆነብኝ፡፡ የተቀራኔ ቡድን ተጫወቾችን እየበረጋገድ ደጋግሞ ጎል አስገባ፡፡ የያዝኩላቸው የጊዜ ገደብ ሲያበቃ በከፍተኛ የግብ ልዩነት በወንድሜ ቡድን አሸናፊነት ተጠናቀቀ፡፡ ሁለቱም ቡድኖች ተሰልፈው ሊሸለሙ በዓምበሎቻቸው መሪነት ከፊቴ ቀረቡ፡፡
ከወንድሜ ጋር ፊት ለፊት ተፋጠጥን፡፡ ኮከብ ግብ አግቢ ነህ ብየ በሰበብ አቀፌ ሳምኩት፡፡ ጋዜጠኛ ነኝ ብያለሁና በየተራ ቃለ መጠይቅ አቀረብኩላቸውና ስለ እራሱና ስለቤተሰቡ እየጠየቅሁት መረጃ ሰበሰብኩ፡፡ አገሩ ሄዶ አያቅም፤ ደብረብርሃን ቢሄድ ሳር ቅጠሉ የገብረፃድቅ ልጅ መሆኑን በመልኩ ያውቃል፡፡
ድንገት ብሞት እንኳን ባዩሸ ወንድሟን ሳታውቅ እንዳትቀር ፈራሁ፡፡ ልጃገረድ ስትሆን ጠብቄ አንድ ቀን ወንድሟን ላሳያት ሲጊናል ሠፈር ወሰድኳት፡፡ ሠፈር ስንደርስ ባለጠጅ ቤቷን አክስቱንና እናቱን አገኜናቸው፡፡ እሱ ግን ሠፈር ውስጥ አልነበርም፡፡ ከአባቱ ጋር በጣም ስለሚወደዱ ስለወላጅ አባቱ አንስተንበት አናቀም፣ አለችኝ እናቱ ፡፡ ብንነግረው በመሃላቸው ያለው መቀራረብ ያስጨንቀኛል፣ አለችኝ ፣ ጨመረችና፡፡ አመች ሁኔታ ከተፈጠረ ወደ ፊት ልናስተዋውቃቸው ተስማምተን ተለያየን፡፡
ባዩሽ ግን ወንድሟን ለማግኘት ጓጉታ ኖሯል፡፡ ከተመለስን በኋላ ሳታማክረኝ ለወንድሟ ስልክ ደውላለት እንተዋወቅ እህትህ ነኝ፣ አለችው፡፡ ነገሩ እንግዳ ሆኖበት ደናገጠ፡፡ ጓደኞቹን አስከትሎ ነበር ያገኛት፡፡ ስለሚመሳሰሉ ተጨማሪ መረጃ አላስፈለገውም፡፡ሁለቱም ያባቴ ቅጂ ናቸውና። ተቃቅፈው እንደተላቀሱ ባዩሽ ነገረችኝ።
ከ16 ዓመት በኇላ፣ የዛሬ 3 ዓመት፣ በርጂና ምክኒያት ከመሞቴ በፊት ወንድሜን ለማየት ከደሴ ወደ አዲስ አበባ ሄድሁ። አዲስ አበባ ድብልቅልቋ ስለወጣ ጭራሽ ሰግናል ሠፈርን ላውቃት አልቻልከም። በፍለጋየ ወቅት እዚያው የሚኖር የእህቴ ልጅ አብሮኝ ነበር። በ8:00 ሰዓት ለፍለጋ ወጥተን ፣ ከምሽቱ 1:00 ገደማ በሠፈሩ ሰዎች ርዳታ ቤቱን አገኘነው። የወንድሜ እናት በሽተኛ ሆና አለጋ ላይ አገኘኇት። በመጀመሪያ አስታውሳኝ በሰላም ጥቂት በጨዋታ አሳለፍን። ደግሞ ድንገት ፀባየዋ ተቀየረና፣ ቤቴን ለቃችሁ ውጡልኘ፣ ልጀ ቢኖር ኖሮ በሽጉጥ ግንባር ግንባራችሁን ይላችሀ ነበር፣ አለችን። የእህቴ ልጅ በንግግሯ ተገርሞ፣ አንቺ፣ እኔ ኮ የመንግሥተ ኮለኔል ነኝ፠ የምኖረውም እዘሁ ሠፈር ነው፣ የማንን ግንባር ነው በሽጉጥ የመታው?አላት። ኮለኔል ብትሆን ማን ይፈረሃል፣ በኖር ኖሮ አይለቅህም ነበር ፣ አለችው። ከቤት ስንወጣ ልጇ ተከትላን ሸኜችን። እባካችሁ የቅርታ አድርጉልን፣ አባታችን አና ትልቋ እህታችን ተከታትለው ከሞቱ በኇላ ድንገት እንዲህ ያደርጋታል ፣ አለችን። ሆዴ በሃዘኔታ እንደተሸበረ፣ የእነን ደጋፍ ባስፈለጋችሁ ጊዜ ደውይልኝ ብየ ስልክ ቁጥሬን ሰጥቻት ተሰናበትናት። ወንድሜ የተወለደው ሰኔ ወር ውስጥ 1967 ዓ.ም ነው። ወንድሜን መቼ ይሆን አቅፌ የምስመው ????

14/02/2026

" በመንፈሡ ተነድቼ "
ትላንት በህልሜ በመንፈሡ ተነድቼ
ተራጋሚዎች አደባባይ ተገኝቼ
አፌን ለርግማን ገና ስከፍት
ቃሉ ይለወጣል ሲነገር በኔ አንደበት
ርግማኑ ተለውጦ ወደ መልካም ይቀየራል
አንደበቴን ሳላዘው በራሱ ይማልዳል
ሌባውን ልረግም ስል ቃሉ ይቀየራል
ሠርቶ እንዲበላ ልቦና ስጠው ይላል
ጤና አጥቶ የሚለምነውን
ፈውሶት እንዲድን
አምራች ሆኖ ምርት እንደያፍስ
ከሡ ተርፎ ለሠው እንዲደርስ
ፈጣሪን እማፀናለሁ ቸርነቱን
ከሠው ዘር እንዲያጠፋ ማጣትን
ነፍስ ገዳዩ ልቦና እንዲገዛ
እማፀነዋለሁ ማስተዋል እንዲያበዛ ።
በጌታ መንፈስ ተነድቼ
ስማልድ በሡ ተመርቼ
ከተራጋሚዎች መሃል ተገኝቼ
ባይተዋር አደረጉኝ ወገኖቼ
እኔ ግን ቆምኩ በሂወት
ማዕበል ሲመጣ በድንገት
ተራጋሚዎች ሲጠፉ በቅፅበት።

14/02/2026

" ምን ዓይነት ትንግርት ነው "
እንደ ግብረ ጉንዳን ሲርመሰመሱ
በየሠው ቤት በፍለጋ ሲያስሱ
በብዛታቸው ታላቅነት ተገርሜ
መረመርኩ አካሄዳቸውን ደጋግሜ
በእጃቸው ምንም ነገር የለም
የያዙት አንዳች ለመፋለም
መዝመታቸው በባዶ እጃቸው
አልገባ ብሎኝ አላማቸው
ተደንቄ በዐይኔ እያየኋቸው
አንዳች ሳይከውኑ ጠፋ ደብዛቸው።

21/12/2025

" አብዮትና ሥነ- ሥርዓት "
(Gimini ርዕሱን ስለቀየረው እኔም ቀይሬዋለሁ)
በአገራችን የታዘብኩትን ከማንሳቴ በፊት ፣በቻይና አብዮታዊ የትጥቅ ትግል ወቅት፣ የተከሰተውን እንደ መንደርደሪያ ላንሳ።
የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ሠራዊቱን ከደቡባዊ ቻይና ወደ ሰሜን 1000 ማይል የእግር ጉዞ ያጓጉዝ ነበር። ይህን ታሪክ ፣ የአገሬ ተዋጊዎች፣ " THE RED STAR OVER CHINA " የተሰኘውን መፅሐፍ ፈልገው ለሚመሯቸው ተዋጊዎች ቢያስነብቧቸው ስለ ህዝባዊነትና ዲስፕሊን እንዲማሮ ስለ ሚጠቅማቸው መጠቆም እፈልጋለሁ።
ወደ ታሪኩ ቅንጫቢ ልመለስ።
የጉዞውን መራራና እልህ አስጨራሽ ፍልሚያውን በዐይነ ህሊናችሁ ተመልከቱልኝ። በጉዟቸው አንዲት ንግሥት የምታስተዳድረው ግዛት ደረሱ። አካባቢው በበግ እርባታ ይታወቃል። ማኦ ዜቱንግ ሠራዊቱን ሰብስቦ፣ በርሃብ እስከሞት ብትደርሱም የገበሬ በግ እንዳትነኩ፣ የአንድ በግ ህይወትና የአንድ አብዮታዊ ሠራዊት ዓባል ሂወት እኩል ይሆናል ፣አላቸው። ሠራዊቱ በርሃብ እየማቀቀና ሳርና ቅጠሉን እየተመገበ ጉዞውን ቀጠለ እንጂ አንድም የገበሬ ንብረት አልነካም ነበር። ማኦ ዜቱንግ እራሱ የሚያጨሰው ሲጋራ ስላጣ ፣ የደረቀ የዛፍ ቅጠል በወረቀት እየጠቀለለ ማጨስ ስለ ጀመረ ፣ ሠራዊቱ ድርጊመቱን በመቃወም በሠላማዊ ሰልፍ ተቃውሞ አስተውት።
ወደ አገራችን የ1983 ዓ.ም ትዝብቴ ልመልሳችሁ።
በወቅቱ ምዕራብ ሀረርጌ ፣ ጭሮ ከተማ እሠራ ነበር። ኢህአዴግ አገሪቱን የተቆጣጠረበት ጊዜ ነበር። መከረኛው አማራም በማንነቱ ይጨፈጨፍ ነበር ( የእንቁፍቱን ጭፍጨፋ ማስታወስ በቂ ይመስለኛል)። ከዚህ በፊት ፣ " አሚንን ልዘክረው" በሚለው ርዕስ ስር ወዳጀ አሚን በሚሰራበት መቻራ ከተማ ኦነጎችን ተጠግቶ በማማከር ግድያውን እንዲከላከል ለማድረግ እዚያው ድረስ ሄጀ ያደረግነውን ውጤታማ ተግባር በዚሁ ገፄ ላይ ለጥፌላችሁ ነበር። አሚንን፣ ለመሆኑ ወደ እዚች ከተማ የገቡት ምን ያህል የኦነግ ታጣቂዎች ናቸው፣ አልኩት። 38 ብቻ ነበሩ አለኝ። እነዚህ 38 ታጣቂዎች 3 ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ቁኒ የተባለች ከተማ ላይ ብቻ 17,000 መድረሳቸውን ሰማሁ። የቁኔ ከተማ ከጭሮ ከተማ 20 ኪ.ሜ ብትርቅ ነው። በዚያው ሰሞን ይህ ሠራዊት የጭሮ ከተማን ሌሊት ሌሊት እየከበበ ከተማዋ ላይ መትረየሱን ሲያንበቀብቅብን ያድር ጀመር። መብራትና ውሃ አቋርጦብን ቤተሰቤ ከአንድ ወር በላይ ንፍሮ እየበላና የወንዝ ውሃ እየጠጣ ቆይቷል።
አንድ ቀን ሌሊት በጨለማ ከቁኒ ከተማ በኦነግ የተማረሩ ገበሬዎች ሹልክ ብለው ጭሮ መጡና ኢህአዲግን ከኦነጎች ነፃ አውጣን ብለው ከተማዋን በሠላማዊ ሠልፍ አጥለቀለቋት። ምን ሆናችሁ ነው ፣ብንላቸው፣ ኦነግ የጉድጓድ ማሽላችንን እያወጣ ሠራዊቱን ቀለበበት፣ ሰንጋ በሬዎቻችንን እያረዳ አበላቸው፣ ስንት ሺህ ብር እንሸጠዋለን ያልነውን የጫት ተክል ምርታችንን እየቆረጠ ሠራዊቲን አቃመብን፣ የቀፎአችንን ማር እየቆረጠ ማሩን አስበላብን፣ አሉን። እንቁላል፣ ዶሮ፣ እንጨት ፣ወዘተ ጭሮ ሄዳችሁ ለነፍጠኛ እንዳትሸጡ ተብለው በመከልከላቸው ምርታቸውን ሸጠው በሚያገኙት ገንዘብ፣ ጋዝ፣ ዘይት፣ ጨው፣ መድሃኒት፣ ወዘተ እንዳይገዙበት አደረጓቸው።
ኢህአዴግ ተንኮሉ፣ ሠላማዊ ሰልፍ ከተደረገ በኋላ ለሠልፈኞቹ ምላሽ ሳይሰጣቸው ዝሞ፣ ጭጭ፣ አላቸው። ገበሬዎቹ ወደ ቁኒ እንዳይመለሱ ፣ ሠላማዊ ሠልፍ በማድረጋቸው ኦነግ የሚበቀላቸው መሆኑን ስለ ፈሩ ወደ ቁኒ ከተማ ሳይመለሱ እዚያው ጭሮ ከተማ ረሃብ እየቆላቸው ከሳምንት በላይ ቆዩ። ኢህአዴግ እንዴት ጥቃት እንደሚፈፅም ሲያጠና ኖሯል አንድ ሳምንት የከረመው። የሀረር ገበሬ ከጧት ጀምሮ እስከማታ ጫቱን ሲቅም ነው የሚውለው ( ስለ ዚህ ጉዳይ ክቡር ግርማቸው ተክለሃዋሪያት፣ "አርዓያ " ብለው የፃፉትን መፅሐፍ ያነበበ ያቀዋል )። ታዲያ እነዚህን ገበሬዎች የሚቅሙት ጫት የምግብ ፍላጎታቸውን ስለ ሚዘጋቸው ቀን ብዙም አይመገቡም። እነሱን ረሃብ የሚለቅባቸው ሲነጋጋ ነው። ይህን ረሃብ ፣ "ጭንንቶ" ይሉታል፣ በግርድፉ ሲተረጎም ሆድን ሞረሙር ፣ ወይም ሆድን የሚናከስ ርሃብ ፣ እንደማለት ነው። ታዲያ እነዚህ የገበሬ ጦሮች ሲነጋጋ ከምሻጋቸው እየወጡ ምግብ ፍለጋ ወደ ከተማ እንደሚወርዱ፣ ኢህአዴግ ይደርስበታል። ከሳምንት በኋላ ሌሊቱን ከጭሮ ከተማ ጦሩ ተነስቶ በጫካ በኩል በእግር ተጉዞ ሲነጋጋ ቁኒ ተማ የሚገኘው የኦነግ ምሽግ ይደርሳል። ያን ጊዜ ገበሬዎቹ ምግብ ፍለጋ ከምሽጋቸው ወጥተው ምግብ ፍለጋ ወደ ከተማዋ ሄደዋል። በለቀቁት ምሽግ የኢህሀዴግ ታጣቂ እየገባ ምሽጉን ተቆጣጠረው። ኢህአዴጎቹ ልክ እንደ ኦነግ ታጣቂዎች ፀጉራቸውን አበጥረውና ሚዶም በጎፈሬቸው ራይ ሻጥ አድርገዋል። ሽርጥም አገልድመው ተመሳስለው ነበር። የኦነግ ታጣቂዎች ጭንንቷቸውን አስታግሠው ወደ ምሽጋቸው ሲመለሡ፣ አቦ አንተ ማነህ? እኔ ምሽግ ተሳስተህ ነው የገባኸው፣ አቦ ወደ ራስህ ምሽግ ሂድ እንጂ ፣ ይላሉ። በዚህ ጊዜ ኢህአዴግ በክላሽ ጥይት ደረት ደረታቸውን እያሉ 30 ደቂቃ ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በትንሽ ሜዳ ላይ ከበባ አድርገው ማረኳቸው። አሁን እኔ ይኸን ጀግንነት ነው ብየ ማውራት አደለም አላማየ። የኔ አላማ ለሠላማዊ ሠልፍ ጭሮ የሄዱት ገበሬዎች ከፈፀሙት በቀል የዛሬ ታጣቂዎች ትምህርት እንዲወስዱ ማሳሰብ ነው። ሠላማዊ ሠልፈኞች ኢህአዴጎቹን ከኋላ ኋላ ተከተለዋቸው ከጭሮ ከተማ መጥተው ነበር። እንዴት እነዚህን ትማርካላችሁ፣ እያሉ ፣በትንሽ ቦታ ላይ በተሰበሰቡት ምርኮኞች መሃል ቦምብ እየጣሉ፣ ኢህአዴግ ካደረሰው ጉዳት የበለጠ ግድያ ፈፀሙ። እነ ማኦ ዜቱንግ እና ሠላማዊ ሠልፈኞች ከፈፀሙት ድርጊት ያልተማረ ታጣቂ፣ ከወዲሁ ፣ዋ ! ለኔ፣ ብሎ ቢጠነቀቅ መልካም ነው እላለሁ። ያገሬ ሠው፣ " ማወቅ እንኳን እናውቃለን፣ ብንናገር ግን እናልቃለን፣ ብለን ነው እንጂ፣ ይላል በሥነ - ቃሉ። የተበደለ ህዝብ ቀን ያጋጠመው ቀን የበደለውን እንደሚበቀል አውቆ መጠንቅቅ ማትረፍ ነው። በ"ፍቅር እስከ መቃብር" መፅሐፍ እንደ ተገለፀው ከአበጀ በለው ተከታይ ገበሬ ከከወነው ተግባር እና ኮ/ል መንግሥቱኃይለማሪያም፣ በሰሜኑ ጦርነት፣ "ህዝቡ በሠራዊታችን ላይ እንደ አንበጣ ይሠፍርበታል፣" ብለው ከተናገሩት ኩነት መማር ብልህነት ነው።

Telephone

Website

Address

Dessie