East Gojjam Zone Disaster Risk Management Office

East Gojjam Zone Disaster Risk Management Office

Share

ለአደጋ የማይበገር እና የምግብ ዋስትናው የተረጋገጠ ማህበረሰብ ለመፍጠር ተግተን እንሰራለን!

Photos from South Gondar Disaster Risk Managment's post 05/06/2026
Photos from Disaster Risk Management Commission  የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን's post 05/06/2026
Photos from ማዕከላዊ ጎንደር ዞን ኮሙዩኒኬሽን-Central Gondar Zone Communications's post 05/06/2026
Photos from የሰሜን ሸዋ ዞን አደጋ ስጋት ሥራ አመራር  ጽ/ቤት's post 04/06/2026
Photos from Central Gondar Zone Disaster Risk  Management Office's post 04/06/2026
Photos from የእሳትና አደጋ  ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን Fire and Disaster Risk Management Commission's post 04/06/2026
04/06/2026

በምሥራቅ አፍሪካ የሚጠበቀው ከመደበኛ በታች የዝናብ መጠን አማራ ክልልን ምን ያህል ያሰጋዋል?

ባሕር ዳር: ግንቦት 26/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ትናንት በመጭው ክረምት ማለትም ከሰኔ እስከ መስከረም ባሉት ወራት በምሥራቅ አፍሪካ ከሚጠበቀው በታች የዝናብ ኹኔታ እንደሚኖር የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ኢጋድ የአየር ንብረት ትንበያ እና መተግበሪያ ማዕከል በቅርቡ መግለጹ ይታወቃል።

በምክኒያት የተነሳው ደግሞ የኢልኒኖ ተጽዕኖ ነው።

✍️ክስተቱ አማራ ክልልን ምን ያህል ያሰጋዋል?

በኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዮት የምዕራብ አማራ ሚቲዎሮሎጂ አገልግሎት ማዕከል የሚቲዮሮሎጂ ሳይንስ ረዳት ተመራማሪ እንደግ አንለይ
ከክልሉ ከዓመታዊ የዝናብ መጠን ውስጥ ከ65 እስከ 90 በመቶ የሚኾነው ድርሻ በክረምት ወቅት የሚሸፈን በመኾኑ ለክልሉ ግብርና እና ኢኮኖሚ ወሳኝ ጊዜ ነው ብለዋል።

ይኹን እንጂ የዘንድሮው የክረምት ወቅት በአብዛኛው ከቀላል እስከ መካከለኛ በኾነ የኢልኒኖ ተጽዕኖ ሥር እንደሚቆይ ነው ባለሙያው የገለጹት።

ይህም በዝናብ ሥርጭቱ እና መጠኑ ላይ የራሱ የኾነ አሉታዊ ጫና ይኖረዋል ብለዋል።

#ነገር ግን በአማራ ክልል አብዛኛዎቹ አካባቢዎች የሚኖረው የዝናብ መጠን ከመደበኛ ጋር የተቀራረበ እንደሚኾን ይጠበቃል ነው ያሉት።

🚫በሰሜን ወሎ፣ በደቡብ ወሎ፣ በዋግኽምራ እና በኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ግን ክረምቱ ቀድሞ የመውጣት ኹኔታ ሊኖር እንደሚችል ገልጸዋል።

በእነዚህ አካባቢዎች ዝናቡ ከመደበኛው መጠን በታች የመኾን እድሉም ከፍተኛ መኾኑን በመረዳት በተለይ አርሶ አደሮች አስፈላጊውን ዝግጅት ሊያደርጉ ይገባል ብለዋል።

👉በሌላ በኩል በሰሜን፣ በደቡብ እና በማዕከላዊ ጎንደር አካባቢዎች በአንጻራዊነት መደበኛ የዝናብ ሥርጭት እንደሚኖር ቢጠበቅም በሰኔ እና በመስከረም ወራት የደረቅ ቀናት ሊከሰቱ ይችላሉ ነው ያሉት።

ይህ ኹኔታ የሰብል እርጥበት እጥረት ሊያስከትል ስለሚችል አርሶ አደሮች የሚገኘውን እርጥበት በአግባቡ የመያዝ እና የማቆር ሥራዎችን በልዩ ትኩረት ሊያከናውኑ ይገባል ብለዋል።

በአጭር ጊዜ የሚደርሱ የሰብል ዝርያዎችንም መዝራት እንደሚገባ መክረዋል።

🚫አጠቃላይ የዝናብ መጠኑ ከመደበኛ በታች ይኾናል ተብሎ ቢጠበቅም በሐምሌ እና በነሐሴ ወራት ውስጥ አልፎ አልፎ በሚከሰት ከባድ ዝናብ ምክንያት ድንገተኛ የጎርፍ አደጋ ሊከሰት እንደሚችልም አስጠንቅቀዋል።

ስለዚህ ለጎርፍ ተጋላጭ የኾኑ አካባቢዎችን በመለየት የመከላከያ ሥራዎችን ማከናወን ይገባል ብለዋል።

#ከኢንስቲትዩቱ የሚወጡ አዳዲስ መረጃዎችን እና ማሻሻያዎችን በንቃት በመከታተል አስፈላጊ የጥንቃቄ ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባም መክረዋል።

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Photos from ANRS Disaster Risk Management Commission's post 04/06/2026
Want your organization to be the top-listed Government Service in Debra Markos?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Website

Address

Debra Markos