GLN
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from GLN, College & University, Awassa.
14/08/2021
ኢትዮጵያ የቆዩ ፈንጂዎችን ሙሉ ለሙሉ ለማፅዳት ዓለም አቀፍ ትብብር ጠይቃለች !
ኢትዮጵያ ከውጭ ከመጡ ጠላቶችና በአገር ውስጥ በተደረጉ ጦርነቶች መሬት ውስጥ ተቀብረው የቆዩ ፈንጂዎችን፣ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ሙሉ ለሙሉ ለማፅዳት ዓለም አቀፍ ትብብር እየጠየቀች መሆኑ ተገለጸ፡፡
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የፈንጂ ማምከን ቢሮ ኃላፊ ኮለኔል አበራ አዘናው ፥ ኢትዮጵያ በካናዳ እ.ኤ.አ. በ2004 የፈረመችውን የፀረ ሰው ፈንጂ ማውደም ስምምነትን በተያዘለት እ.ኤ.አ. በ2020 አስወግዳ ባለማጠናቀቋ፣ ሁለተኛ የማራዘሚያ ጊዜ በኖርዌ ኦስሎ እ.ኤ.አ. 2020 እንደገና ለአምስት ዓመት ጠይቃ እስከ 2025 እንደተራዘመላት ለሪፖርተር ጋዜጣ ተናግረዋል፡፡
በ5 ዓመታት ውስጥ አፅድታ እንድትጨርስ በስምምነቱ መሠረት ፈቃድ የተሰጣት ቢሆንም፣ ኢትዮጵያ ያሏት የፈንጂ ማምከኛ መሣሪያዎች ኋላ ቀር በመሆናቸውና በፋይናንስ ችግር ሳቢያ የዓለም አቀፍ ማኅበረሰቡን ትብብር መጠየቋ ተገልጿል፡፡
የድጋፍ ሁኔታዎችን አስመልክቶ የፈንጂ ማምከን ቢሮ የኢፌዴሪ ሰላም ሚኒስቴር፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴርንና ሌሎች አካላትን ጨምሮ ከኤምባሲዎችና ከዓለም አቀፍ ድርጅቶች ድጋፍና ትብብር ለማግኘት ግንቦት 12 ቀን 2013 ዓ.ም. ዝግ ውይይት ተካሂዷል፡፡
የፈንጂ ማምከን ቢሮ ኃላፊው፥ አገሪቱ ምንም እንኳ በትግራይ፣ በአፋር ፣ በቤኒሻንጉል ጉምዝ፣ በኦሮሚያ፣ በሶማሌና በጋምቤላ ክልሎች መሬት ውስጥ የተቀበሩ ወይም ተከማችተው የሚገኙ ፀረ ሰው ፈንጂዎች እንዳሉ ቢታመንም የፈንጂዎቹ ትክክለኛ መገኛ ቦታ አይታወቅም ሲሉ ለ ተናግረዋል።
የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ነገ ይፋ ይደረጋል።
የ2012 የ12ኛ ክፍል ፈተናን በተመለከተ ዛሬ በሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ዲላሞ ኦተሪ የተሰጠው መግለጫ በአጭሩ ሲጠቃለል ፦
- ከተፈተኑት ከግማሽ በላይ ተማሪዎች ከ350 በላይ አምጥተዋል።
- ፈተናውን ከወሰዱ አጠቃላይ ተፈታኞች ውስጥ 55.7 ፐርሰንቱ ከ350 በላይ አምጥተዋል።
- ከ600 በላይ ያመጡ ተማሪዎች 702 ናቸው።
- የዓመቱ ከፍተኛ ውጤት 669 ሆኖ ተመዝግቧል።
- #ከነገ ጀምሮ ተማሪዎች ውጤታቸውን በሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች ኤጀንሲ ድረገፅ እና በአጭር የፁሁፍ መልዕክት 8181 የፈተና መለያ ቁጥራቸውን በማስገባት መመልከት ይችላሉ።
- ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ጊዜን እና ማለፊያ ነጥብን በተመለከተ ከሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ጋር እየተሰራ ነው።
08/03/2021
የአማሮ ልዩ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ኃላፊ ተገደሉ።
የአማሮ ልዩ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ በተከፈተባቸዉ ተኩስ ህይወታቸዉ አለፈ።
የልዩ ወረዳዉ ዋና አስተዳዳሪ ቆስለዉ አርባ ምንጭ ሆስፒታል እንደገቡ ተሰምቷል።
ጥቃቱ የተፈፀመው በፀረ ሰላም ኃይሎች (የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች) ነው ብሏል የወረዳው መንግስት።
እንደ አማሮ ወረዳ መረጃ በተከፈተው ተኩስ የቡዙሃን ህይወት አልፏል፤ በርከት ያሉ ሰዎች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል።
እስከ አሁን ባለው መረጃ የ 8 ሠላማዊ ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን በጫካ ውስጥ የተበታተኑ እና ያልተገኙ ስለላሉ ቁጥራቸው ከዚህ ሊበልጥ ይችላል ተብሏል።
ጥቃቱ የተፈፀመው በአማሮ ወረዳ እና በምዕራብ ጉጂ ዞን አጎራባች ቀበሌያት መካከል ሠላማዊ ስብሰባ እየተካሄደ በነበረበት ወቅት ነው ሲል የልዩ ወረዳው ኮሚኒኬሽን ገልጿል።
Click here to claim your Sponsored Listing.