ETH RUN

ETH RUN

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ETH RUN, Sports Team, Addis Ababa.

22/03/2026

Ethiopia 🇪🇹 🇪🇹 🇪🇹 🇪🇹

02/03/2026

Super coach team አሰልጣኝ ሃጂ አደሎ

Photos from ETH RUN's post 01/03/2026

Tokyo marathon 2026 results
በወንዶች ኢትዬጵያዊው ታደሰ ታከለ ሲያሸንፍ በሴቶች ኬንያ ኮስጌ አሸንፉለች. እንካን ደስ አላቹሁ

22/02/2026

አትሌት ማሬ ዲባባ በጃፓን ኦሳካ ማራቶን አሸነፈች።
።።።።።።።።።።።።።።።።።

በሴቶች
1ኛ ማሬ ዲባ 2:21:44 (CR)
4ኛ አፍራ ጉዳፋይ - 2:23:28

በወንዶች
2ኛ ይሁንልኝ አዳነ 2:05:33

በደቡብ ኮሪያ 25ኛው የዴጉ ማራቶን

በሴቶች
2ኛ መሰረት በለጠ 2:19:52

በወንዶች
2ኛ ጪምዴሳ ጉደታ 2:08:09
5ኛ ገርባ ቢታ 02:10:02
7ኛ ጉሳ አምበሉ 02:10:55
8ኛ ደገነር መገርሳ 02:11:07
እንካን ደስ አላችሁ

22/02/2026

Ethiopian drill

21/02/2026

Sprint finished 50 meter for Ethiopian athlete's
Please this page 🙏🏃‍♂️🏃‍♂️🏃‍♂️🏃‍♂️

20/02/2026

Shura kitty's split

Photos from ETH RUN's post 20/02/2026

✍️ በፈረንሳይ ሊዬቨ በተካሄደ የቤት ውስጥ ውድድር በ3000 ሜትር 🇪🇹አትሌት ፍሬወይኒ ኃይሉ እና አዲሱ ይሁኔ አሸነፉ።

👉 በሴቶች የ3000 ሜትር ውድድር ኢትዮጵያዊቷ ፍሬወይኑ ኃይሉ በርቀቱ የአመቱን ፈጣን ሰአት 8:24.59 በማስመዝገብ አሸንፋለች።

በቅርቡ በፍሎሪዳ ታልሃስ በተካሄደው የአለም አገር አቋራጭ ሻምፒዮና በግሏ 5ኛ ደረጃን ይዛ የጨረሰቸው እና በቡድን ለኢትዮጵያ ወርቅ ያስገኘቸው አትሌት አለሺኝ ባወቀ በቤት ውስጥ ውድድር የመጀመሪያ ተሳትፎዋ በ8:26.29 ሁለተኛ ደረጃን ይዛ ጨርሳለች።

በ2025 የቶኪዮ አለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ5ሺ እና 10ሺ ሜትር ለጣሊያን የነሃስ እና የብር ሜዳሊያ ያሸነፈችው ናዲያ ባቶችሌቲ በ8:26.44 በርቀቱ የሃገሯን ሪከርድ በማሻሻል ሶስተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።

በውድድሩ ላይ የተሳተፉት ሌሎች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ሂሩት መሸሻ 5ኛ ፣ ሃዊ አበራ 6ኛ፣ የኔዋ ንብረት 9ኛ፣ ብርቱካን ሞላ 10ኛ፣ ሺቶ ጉሚ 11ኛ፣ ፋንታዬ በላይነህ 13ኛ እና አስቴር አሬሪ 14ኛ ደረጃን በመያዝ ጨርሰዋል።

በፈረንሳይ ሊዬቨ በ3000 ሜትር የነገሰችው አትሌት ፍሬወይኒ ኃይሉ፤ በአለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና በ2024 ግላስጎው ላይ በ1500 ሜትር፤ በ2025 ናንጂንግ ላይ በ3000 ሜትር ርቀቶች ለኢትዮጵያ ሁለት የወርቅ ሜዳሊያዎችን ማሸነፏ ይታወሳል።

👉በወንዶች በተካሄደ የ3000 ሜትር ውድድር ኢትዮጵያዊው አትሌት አዲሱ ይሁኔ የግል ምርጥ ሰአቱን 7:33.58 በማስመዝገብ አሸንፏል።

ኬንያዊው ጃኮብ ክሮፕ በ7:34.68 ሁለተኛ ደረጃን ሲይዝ፤ ኢትዮጵያዊው ጌትነት ዋለ በ7:35.44 በሶስተኛነት ውድድሩን ጨርሷል።

👉 በሴቶች የ800 ሜትር የአጭር ትራክ ውድድር የታላቋ ብሪታኒያ አትሌት ኬሊ ሆጅኪንሰን የርቀቱን የአለም ክብረወሰን በመስበር በ1:54.87 አሸንፋለች።

የሴቶች 800 ሜትር የቤት ውስጥ ውድድር ክብረወሰን ኬሊ ሆጅኪንሰን በተወለደችበት እለት፤ እአአ በመጋቢት 2002 በስሎቬንያዋ አትሌት ዮላንዳ ቼፕላክ ኦስትሪያ ቪዬና ላይ 1:55.82 ነበር የተመዘገበው።

የፓሪስ ኦሊምፒክ የ800 ሜትር ሻምፒዮኗ ኬሊ ሆጅኪንሰን በነገሰችበት ውድድር፤ የስዊዘርላንዷ ኦድሪ ዌሮ በ1:58.38 ሁለተኛ፤ ኢትዮጵያውያኑ አትሌቶች ጽጌ ዱጉማ እና ንግስት ጌታቸው 1:58.83 እና 1:59.54 በማስመዝገብ ሶስተኛ እና አራተኛ ደረጃን ይዘው ጨርሰዋል።

👉 በሴቶች የ1500 ሜትር ውድድር ፓሪስ ኦሊምፒክ ላይ በ1500 ሜትር ነሃስ፤ ቶኪዮ አለም ሻምፒዮና ላይ በ800 ሜትር የብር ሜዳሊያ ያሸነፈቸው፤ የታላቋ ብሪታኒያ አትሌት ጆርጂያ ሃንተር ቤል 4:00.21 በማስመዝገብ በአንደኛነት አጠናቃለች።

ኢትዮጵያውያኑ አትሌቶች ብርቄ ኃየሎም በ4:01.17 እና ሳሮን በርሔ በ4:01.51 ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።

አትሌት ወርቅነሽ መሰለ እና ሃረገወይን ካላዩ 4:06.91 እና 4:08.43 በማስመዝገብ 9ኛ እና 10ኛ ደረጃን ይዘው ሲጨርሱ፤ አትሌት ዶርሲቱ ቦራማ ከ900 ሜትሮች በኋላ ውድድሯን አቋርጣለች።

👉 በሴቶች 2000 ሜትር ውድድር አውስትራሊያዊቷ ጄሲካ ሃል በ5:26.68 አሸናፊ ሆናለች። ሳሎሜ አፎንሶ ከፖርቱጋል እና አጋቴ ጉዊልሞ ከፈረንሳይ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል።

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ኬና ቱፋ 5ኛ፣ ባይሴ ቶሎሳ 10ኛ እና ገላ ሐምበሴ 11ኛ ደረጃን ይዘው ውድድራቸውን ጨርሰዋል።
በቀጣይ የመጨረሻ ዙሩ በፖላንድ ይደረጋል

19/02/2026

Our Legends kenenisa bekele

19/02/2026
Photos from ETH RUN's post 17/02/2026

RAK HALF MARATHON Results

Want your business to be the top-listed Gym/sports Facility in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Culinary Team

Attire

Website

Address

Addis Ababa