Digital Hakim

Digital Hakim

Share

Physicians activist

24/06/2026

👍

24/06/2026

የታጠፈው ክንፍ፣ የጠፋው ፈገግታ፦ የጤና ባለሙያዎች እምባ
ŠŠŠ
በሆስፒታሉ ኮሪደር ላይ የሚሰማው የእግር ኮቴ እንደወትሮው ፈጣንና በልበ-ሙሉነት የተሞላ አይደለም፤ የድካም፣ የሐዘንና የባዶነት እንጂ። የነጭ ጋውኑ ክብር በውስጡ ያለውን የተሰበረ ሰብዕና ሊደብቀው አልቻለም። የሰዎችን ሕይወት ለመታደግ ሌሊቱን ሙሉ በብርድና በጭንቀት ሲዋትቱ ያደሩት የእነዚያ እጆች ዛሬ በራሳቸው ሕይወት መዛባት ምክንያት ይንቀጠቀጣሉ።

ከስድስት ወራት በላይ... ሙሉ ግማሽ ዓመት! ለአንድም ቀን ሳያቋርጡ፣ የታካሚን እምባ እየጠረጉ፣ የትርፍ ሰዓት (ዱቲ) ክፍያቸውን ግን በአየር ላይ ቀርቷል። ከቤት ሲወጡ የልጆቻቸውን ፍላጎት ማሟላት ያቃታቸው፣ የቤት ኪራይ መክፈያ አጥተው በየቀኑ በባለቤቶቻቸው ፊት አንገታቸውን የሚደፉ፣ ለትራንስፖርትና ለዕለት ምግብ የሚበደሩ የሕክምና ባለሙያዎችን ማየት የኢትዮጵያን ሕክምና ትልቅ የሐዘን ማኅደር አድርጎታል።

"ሌሎችን አድናለሁ፤ እኔን ግን ማን ያድነኛል?" የሚለው የውስጥ ጥያቄያቸው ምላሽ አጥቶ በየማዕዘኑ ያስተጋባል። ይህ በደል በባለሙያዎቹ ላይ ብቻ ሳይሆን በመላው የጤና ሥርዓት ላይ የሚከተሉትን አስለቃሽና አስከፊ ክስተቶች ይዞ እየመጣ ይገኛል፦

1. የሞራል መሰባበርና የውስጥ እምባ
በጭንቀትና በረሃብ የዛለ አእምሮ ይዞ የቀዶ ጥገና ክፍል መግባት ምንኛ ከባድ ነው? በአንድ በኩል የታካሚው ሕይወት፣ በሌላ በኩል ደግሞ በዕዳ የተተበተበው የራስ ሕይወት። ባለሙያው በሽተኛውን እያከመ በውስጡ ግን ስለ ራሱ ምስቅልቅል ሕይወት ያለቅሳል። ይህ ስሜታዊ ስብራት በስራ ጥራት ላይ የሚያሳድረው ጥላ እጅግ አስፈሪ ነው።

2. የፍቅርና የርኅራኄ መድረቅ
ሕክምና የዕውቀት ብቻ ሳይሆን የርኅራኄ ጥበብ ነው። ነገር ግን የራሱ መሠረታዊ መብት የተነፈገው፣ ክብሩ የተረገጠውና የተራበው ባለሙያ ውስጡ ሲደማ፣ ለታካሚው የሚሰጠው ፈገግታና ተስፋ አብሮ ይደርቃል። በሆስፒታሎች ውስጥ የሚታየው መፅናናት በጥላቻና በብስጭት መተካት ይጀምራል።

3. የባለሙያዎች ስደትና የጤና ተቋማት ባዶነት
ለዓመታት የተደከመባቸው፣ በከፍተኛ የሕክምና ዕውቀት የበለጸጉ ስፔሻሊስቶች፣ ጠቅላላ ሐኪሞችና ነርሶች ተስፋ ሲቆርጡ አገራቸውንና ተቋማቸውን ጥለው ይሰደዳሉ። ወይ ወደ ግል ተቋማት አለያም ሙሉ በሙሉ ሙያውን ወደ መተው ያመራሉ። ይህ ደግሞ ነገ በሆስፒታሎቻችን ውስጥ አዋላጅና ቀዳጅ ማጣትን ያስከትላል።

4. በድሆች ላይ የሚዘንበው መከራ
የዚህ ሁሉ በደል የመጨረሻ ሰለባ የሚሆኑት ወደ ግል ሕክምና መሄድ የማይችሉ ምስኪን የገጠርና የከተማ ድሆች ናቸው። ባለሙያው ሲደክም፣ ሲያዝንና አልጋውን ጥሎ ሲወጣ፣ የነፍስ ማዳኑ ሰዓት ይረዝማል። በሆስፒታል ደጃፍ ላይ የሚፈስሰው የንጹሐን እምባና ሕይወት ደግሞ የዚህ ቸልተኝነት የመጨረሻው መራራ ፍሬ ነው።

የዝምታው ዋይታ

"ነጭ ጋውን ለብሰን፣ በውስጣችን ግን ጥቁር ሐዘን ተቀምጧል። ሰውን ስናድን እያደርን፣ እኛ ግን በቁማችን እየሞትን ነው። ክፍያችን የበጎ አድራጎት ስጦታ ሳይሆን፣ በደምና በላባችን የገዛነው መብታችን ነበር።"
— ከተማረረ የጤና ባለሙያ የተደመጠ

የነገው ተስፋችን እንዳይጨልም፣ የሕዝባችን ነፍስ በባለሙያዎች መጎሳቆል ምክንያት እንዳትቀጠፍ፣ የክልሉ መንግሥትና የሚመለከታቸው አካላት ጆሯቸውን ወደነዚህ ምስኪኖች ድምፅ ሊያዞሩና ፈጣን መፍትሔ ሊሰጡ ይገባል። ያለበለዚያ የምናጣው ገንዘብን ብቻ ሳይሆን፣ ዳግም የማይተካውን የሰዎች ሕይወትና የሀገርን የሕክምና ምሰሶ ይሆናል።

24/06/2026

ከነጭ ጋውን ጀርባ ያለው የዕንባ ታሪክ — ክፍል አንድ

​ከአስር ዓመታት በፊት ነበር... በጤና መኮንንነት (Health Officer) ተመርቄ ስራ የጀመርኩት። የነጩ ጋውን ክብር፣ ሰዎችን የመርዳት ፍላጎት ህሊናዬን ይሞላው ነበር። ስራ በጀመርኩ በአመቴ ግን ህይወቴን የሚቀይር ትልቅ የውጭ ሀገር እድል ደረሰኝ። ሻንጣዬንክ አዝጋጅቼ፣ የተሻለ ህይወት ፍለጋ መብረር እችል ነበር። ነገር ግን በውስጤ የሚጮህ አንድ ትልቅ ህልም ነበረኝ—"ሀኪም መሆን!"

​ለዚያ ህልሜ ስል፣ ያንን ሁሉ ወርቃማ የውጭ እድል ረግጬ የህክምና ትምህርት ቤት (Medical School) ተቀላቀልኩ።

​ያሳለፍኳቸው አመታት ግን አልጋ በአልጋ አልነበሩም። እንቅልፍ አልባ ሌሊቶች፣ የፈተና ውጥረት፣ የኢኮኖሚ መጣበቅ... ብዙ ውጣ ውረዶችን አሳለፍኩ። በመጨረሻም ከብዙ ትግል በኋላ በጥሩ ውጤት ተመረቅኩ! ያኔ ደስታው የኔ ብቻ አልነበረም። የቤተሰቦቼ፣ የጓደኞቼ፣ የዘመድ አዝማድ ሁሉ ነበር። "እንኳን ደስ አለህ፣ ዶክተር ቤተሰብ አገኘን!" የሚለው የደስታ እልልታ ዛሬም በጆሮዬ ያቃጭላል።

​ነገር ግን ያ ሁሉ ደስታ ወደ መራራ ሀዘን ለመቀየር አንድ አፍታ ብቻ ነበር የፈጀው።

​የመጀመሪያ ወር ደመወዜ በቴክስት ስልኬ ላይ ሲገባ ስልኩ ጓደኛዬ እጅ ነበር። ስክሪኑ ላይ ያለውን አሀዝ ሲያየው ማመን አቃተው። በድንጋጤ አይኖቹን አፍጥጦ ጠየቀኝ። እውነታውን አረጋገጥኩለት።

​ጓደኛዬ ቀና ብሎ አየኝና በቁጭት፥ "ይቅርብህ! ይሄን ያህል አመት ተምረህ ይሄ ነው ደመወዝህ? ይቅርብህ!" አለኝ። እኔ ግን ያሳለፍኩት አመታት፣ የፈሰሰው ድካሜ፣ የወደፊት ተስፋዬ እና ለህክምና የነበረኝ እብደት የሚመስል ፍቅር ተደምረው የጓደኛዬን ምክር እንድገፋው አደረጉኝ። ከዚያ በኋላ ለሁለት እና ሶስት ጊዜ ይህንን ስራ እንድተወው በወዳጆቼ ተለምኛለሁ... እኔ ግን አሻፈረኝ አልኩ።

​ግን ጊዜው እየሄደ ሁኔታዎች ይባስ እየከፉ መጡ። እንደጠበቅኩት አልሆነም። ህይወት ወደ አጣብቂኝ ውስጥ ከተተችኝ።

​የዱቲ (Duty) ክፍያ መከፈል ቀረ።

​በትርፍ ሰዓት የግል ተቋም እንዳልሰራ የሚከለክል ደብዳቤ ደረሰኝ።

​በዚያች ደመወዝ ከወር ወር መድረስ የማይታሰብ ሆነ።

​ለሰባት ወራት ያህል በቤተሰብና በጓደኛ ድጎማ በትዕግስት ኖርኩ። የዶክተርነቱ ክብር በኪስ ባዶነት ተሸረሸረ።

​በዚህ ሁሉ ጨለማ ውስጥ ግን አንድ የመጨረሻ ተስፋ ነበረኝ። አሁን ከምሰራበት ሆስፒታል ቤተሰቦቼ ወዳሉበት ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በዝውውር መሄድ። "እዚያ ከሄድኩ ቢያንስ የቤት ኪራይና የምግብ ወጪ ይቅልልኛል" በሚል ሙሉ ተስፋ ቀኑን እጠብቅ ነበር።

​በመጨረሻም ቀኑ ደረሰ... የዝውውር ስም ዝርዝር ተለቀቀ። ልቤ እየመታች PDF ከፈትኩት። ከተዘዋወሩት ሀኪሞች ስም ዝርዝር ውስጥ አይኖቼ የኔን ስም መፈለግ ጀመሩ።

​ከላይ... ከመሀል... ከታች... የምፈልገው ስም የለም!

​ድንጋጤዬ ጨመረ። አይኖቼን ወደ ታች ሳወርዳቸው ግን፥ "አልተዘዋወሩም" ከሚሉት መሀል ስሜ በጉልህ ተፅፎ አገኘሁት። ያኔ ውስጤ ዝብርቅርቅ አለ። ሰማዩ ተደፋብኝ። ለሁለት ቀናት ሙሉ እንቅልፍ በአይኔ ሳይዞር አደረ። በአዕምሮዬ ውስጥ አንድ ቃል ብቻ ያስተጋባ ነበር፥ "ልቀቅ... ልቀቅ... ልቀቅ..."

​ነገር ግን ወዴት እሄዳለሁ?

​በዚህ መሀል ነበር ስልኬ ላይ "ትንሽ" መልዕክት የገባችው። የቅርብ ጓደኛዬ ነበር። መልዕክቱ አጭር ግን የጉዞ መስመር ቀያሪ ነበረች፡ "እባክህ ይህንን ስራ ልቀቅ!" የሚል።

​በዚያች ቅፅበት ውስጤ የነበረው ፍርሃት ወደ ድፍረት ተቀየረ። ወሰንኩ! በሁለተኛው ቀን ጠዋት... ያንን በደምና በላብ ያገኘሁትን ሙያ የሚሸኘውን የስራ መልቀቂያ ደብዳቤ አስገባሁ።

​ነጩን ጋውን አውልቄ ስወጣ ምን ተሰማኝ? ከስራ መልቀቂያው በኋላስ ህይወት ወዴት ትወስደኝ ይሆን? ለሙያዬ የነበረኝ ፍቅር አበቃለት?

ይቀጥላል.....

24/06/2026

ለዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ንግስት እሌኒ መሐመድ መታሰቢያ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል

ለሚመለከተው የሥራ ኃላፊ ሁሉ

ሆሳዕና

​ጉዳዩ፦ የትርፍ ሰዓት (ዱቲ) ውዝፍ ክፍያ ጥያቄን እና የአገልግሎት ማቆም ውሳኔን ስለ ማሳወቅ

​እኛ የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ንግስት እሌኒ መሐመድ መታሰቢያ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የጤና ባለሙያዎች፣ ለህዝባችን ካለን የላቀ የሰብአዊነት እና የሙያ ግዴታ በመነሳት ላለፉት 6 (ስድስት) ተከታታይ ወራት ያለምንም የትርፍ ሰዓት (ዱቲ) ክፍያና ማበረታቻ አገልግሎት ስንሰጥ መቆየታችን ይታወቃል። ይህ በመሆኑም በባለሙያውና በቤተሰቦቻችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ህይወት ላይ ከፍተኛ ጫና እና ጉዳት እያደረሰ ይገኛል።

​ተቋማችን በጥራት፣ በቅንነት እና በታማኝነት የሚያገለግሉ የተመሰከረላቸው ዕንቁ ባለሙያዎች የሚገኙበት ሆስፒታል እንደመሆኑ መጠን፣ ላለፉት ወራት ያቀረብናቸው ህጋዊና አስተዳደራዊ ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ ባለማግኘታቸው ምክንያት በአሁኑ ወቅት ሰራተኛው ለከፋ የእለት ተእለት ኑሮ ችግር ተዳርጓል። አሁን ያለንበት የሰኔ ወር የበጀት ዓመት ማጠቃለያ (መዝጊያ) ወቅት በመሆኑ፣ ለወራት የተከማቸው ውዝፍ ክፍያ በአስቸኳይ ሊፈጸም ይገባል።

​ባለሙያው ላለፉት ስድስት ወራት ያሳየው እጅግ ከፍተኛ ትዕግስት እና የሙያ ስነ-ምግባር አክባሪነት እንደ ድክመት ሊቆጠር አይገባም። መደበኛ የሥራ ሰዓታችንን በታማኝነትና በሃላፊነት ስሜት የምንወጣ ቢሆንም፣ ያለአግባብና ያለክፍያ ከተደነገገው መደበኛ የሥራ ሰዓት ውጭ እንድንሰራ የሚደረግ ማንኛውም አይነት አስተዳደራዊ ጫናም ሆነ ተጽዕኖ ተቀባይነት የሌለውና የሰራተኛውን መሠረታዊ መብት የሚጥስ መሆኑን በጥብቅ ለማሳሰብ እንወዳለን።

​በመሆኑም፣ መላው የሆስፒታሉ የጤና ባለሙያዎች በአንድ ድምፅ ባስተላለፉት ውሳኔ መሠረት የሚከተሉትን የአቋም መግለጫዎች እናሳውቃለን፦

​ለወራት የተከማቸው የትርፍ ሰዓት (ዱቲ) ውዝፍ ክፍያ ሙሉ በሙሉ እስከ ሰኔ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ እንዲፈጸም እንጠይቃለን።

​ይህ ጥያቄያችን በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ተገቢውን ምላሽ ካላገኘ፣ ከሰኔ 20 ቀን 2018 ዓ.ም (ከምሽቱ 11፡30 ሰዓት) ጀምሮ ማንኛውንም የማታ፣ የዕረፍት ቀናት (ዊኬንድ) እና የሕዝብ በዓላት የትርፍ ሰዓት (ዱቲ) አገልግሎቶችን የምናቆም መሆኑን እናሳውቃለን።

​ከተጠቀሰው ቀን በኋላ መፍትሄ ባለመሰጠቱ ምክንያት ለሚፈጠረው ማንኛውም አይነት የአገልግሎት መቋረጥ ኃላፊነቱን የሚወስደው ጥያቄያችንን በወቅቱ መፍታት ያልቻለው የሚመለከተው የአስተዳደር አካል መሆኑን እናረጋግጣለን።

​ለሙያችን እና ለህዝባችን ያለንን ክብር በድጋሚ እየገለጽን፣ የተፈጠረው አስገዳጅ ሁኔታ ታይቶ አስቸኳይና አስተማማኝ መፍትሄ እንዲሰጠን እንጠይቃለን።

​ከአክብሮት ሰላምታ ጋር!

​የደብዳቤው አቅራቢዎች፦

የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ንግስት እሌኒ መ/መ/ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የጤና ባለሙያዎች

Photos from Digital Hakim's post 21/06/2026

የመሃል ሜዳ ጠቅላላ ሆሥፒታል ሠራተኞች እና ህሙማኖች ከትርፍ ሠአት ክፍያጋ በተያያዘ ሥለቀጣይ ሁኔታዎች የጋራ ዉይይት አደረጉ

Photos from Digital Hakim's post 21/06/2026

Internal Medicine graduates of Addis Ababa University, 2026.

21/06/2026

በሲዳማ ክልል ሀንጣጤ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ድምፅ ሁኑን

21/06/2026

የመንግሥት ውዝፍ ደመወዝን በሕግ እንዴት ማስከፈል ይቻላል? (በአዲሱ አዋጅ ቁጥር 1332/2016 መሠረት)

ሰላም የ "ዳኛ እና ፍትህ" ቤተሰቦች! የመንግሥት ሠራተኞች መብትና ግዴታን የሚደነግገው አዋጅ በቅርቡ ተሻሽሎ አዋጅ ቁጥር 1332/2016 ሆኖ መውጣቱን ያውቃሉ? በዚህ አዲስ አዋጅ መሠረት ውዝፍ ደመወዝን መጠየቅ የሚቻልበትን መንገድ እንደሚከተለው አቅርበነዋል።

ዋና ዋና ነጥቦች፦

1️⃣ የቅሬታ አቀራረብ ሥርዓት

በአዲሱ አዋጅ መሠረት፣ ማንኛውም ሠራተኛ በመብቱ ላይ ቅሬታ ሲኖረው መጀመሪያ ለመሥሪያ ቤቱ የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ማቅረብ አለበት። መሥሪያ ቤቱ በውስጥ አሠራሩ ምላሽ ካልሰጠው ወደ ክስ መሄድ ይችላል።

2️⃣ የይርጋ (Statute of Limitation) ጊዜ (አንቀጽ 103)

ይህ በጣም ሊታወቅ የሚገባው ነጥብ ነው! በአዲሱ አዋጅ አንቀጽ 103 መሠረት፦

ማንኛውም የደመወዝ ክፍያ ጥያቄ መብቱ ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ በ6 ወር ጊዜ ውስጥ ካልቀረበ በይርጋ ይታገዳል።

ነገር ግን መሥሪያ ቤቱ ዕዳውን በጽሑፍ አምኖ ከሆነ ወይም ሠራተኛው በወቅቱ እንዳይጠይቅ ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት ካጋጠመው የይይርጋው ጊዜ ሊቆጠር ይችላል።

3️⃣ የአስተዳደር ፍርድ ቤት ሥልጣን

በአዲሱ አዋጅ መሠረት፣ በደመወዝ እና ተያያዥ ጥቅማጥቅሞች ላይ የሚነሱ ክርክሮችን የማየት ሥልጣን ለአስተዳደር ፍርድ ቤት ተሰጥቷል። የዚህ ፍርድ ቤት ውሳኔ በመሠረታዊ የሕግ ስህተት ምክንያት ካልሆነ በቀር የመጨረሻ ይሆናል።

4️⃣ ተጠያቂነት እና አፈጻጸም አዋጁ

የመንግሥት ሠራተኞች መብት እንዲከበር እና ተገቢው ክፍያ በወቅቱ እንዲፈጸም ያዛል። ፍርድ ቤት የወሰነውን ክፍያ መሥሪያ ቤቱ ለመፈጸም ፈቃደኛ ካልሆነ፣ ዓቃቤ ሕጉ ለሕግ የበላይነት ሲባል ውሳኔው እንዲፈጸም የማድረግ ግዴታ አለበት።

ማጠቃለያ፦

በአዲሱ አዋጅ 1332/2016 መሠረት መብትዎን በወቅቱ ይጠይቁ። የ6 ወር የይይርጋ ጊዜው እንዳያልፍባችሁ ጥንቃቄ አድርጉ!

ፍትህን እና ሕግን በቀላል ቋንቋ ለማድረስ እንተጋለን!

መኮንን ጫኔ

Photos from Digital Hakim's post 21/06/2026

ቀድሞ የወጣው የ pharmacy መውጫ ፈተና

እኛ የፋርማሲ ተማሪዎች ነን
ሰኔ 10/2018 የመውጫ ፈተና ተፈትነን። የክብደት blueprint ከመጣስ በተጨማሪ፣ ይህ ፈተና አስቀድሞ ተሰርቋል። ስለዚህ ለእኛ ድምጽ ይሁኑ ፍትህ ለፋርማሲ ተማሪዎች

Photos from Digital Hakim's post 21/06/2026

በፋርማሲ ዘርፍ የመውጫ ፈተና ላይ የቀረበ ቅሬታ‼️
▬▬
በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሲዘዋወሩ የተገኙት እነዚህ ሁለቱ ደብዳቤዎች ከአምቦ ዩኒቨርሲቲና ከወለጋ ዩኒቨርሲቲ ናቸው!
▬▬▬
Ministry of Education Ethiopia አጣርቶ ውሳኔ ይሰጣል ብለን እንጠብቃለን።
▬▬

🙄

Want your practice to be the top-listed Clinic in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Address

Kazanchis
Addis Ababa