Torque Auto Garages

Torque Auto Garages

Share

Precision. Performance. Passion. Your trusted experts in auto repair, tuning & performance upgrades.

01/12/2025
30/11/2025

ቶርክ አውቶ ጋራጅ
Torque auto garage

Photos from Incredible Work's post 23/11/2025
23/11/2025

Photos from Abiy Ahmed Ali's post 23/11/2025
31/10/2025
31/10/2025

ከጥቂት ሕገ ወጥ ነጋዴዎች በስተቀር አብዛኛው ነጋዴ ከቀረጥና ከጉምሩክ ገቢውን የሚሰውርበትና የሽያጭ ደረሰኝ የማይቆርጡበትን ምክንያት ለመረዳት የራስን ተቋማትን ጓዳ የመፈተሽ ስራ፣ ሕግንና ቁጥጥርን ከማጥበቅ በፊት በጥብቅ ሊሰራበት ይገባል።

ነጋዴው ገዢም ሻጭም እንደመሆኑ መጠን እንደ ዜጋው በርካታ ውስብስብ ችግሮች የተዘፈቀ ነው። ተገቢውን የጉምሩክ፣ የገቢዎች፣ የውጭ ምንዛሪ አገልግሎት ለማግኘት፣ ምርት ለማምረት፣ ሸቀጡን ለማጓጓዝ፣ ከሽፍታ ለመሰወርና ኬላ ለማለፍ በደረሰኝ የማይወራረዱ ሕጋዊ ርዕስ የሌላቸው በርካታ ወጭዎች አሉበት።

በአብዛኛው የውጭ ምንዛሪ በሕጋዊ መንገድ ለማግኘት ማስፈቀጃ መክፈል አለበት። ከሶስተኛ ወገንና ከጥቁር ገበያ የውጭ ምንዛሪ ለመግዛት የደላላና ጨምሮ ሌሎች ክፍያዎች አሉበት። እለት በእለት የሚንሩ በውጭ ምንዛሪ ላይ የሚጣሉ የባንክ ቻርጆች ለመገመት የሚያዳግቱና ላልተጠበቀ ወጭ የሚዳርጉት ናቸው።

የጉምሩክና የገቢዎች ሕጎች፣ መመርያዎችና ደንቦች ተለዋዋጭ የማይገመቱ፣ እርስ በርሳቸው የተጠላለፉና ነጋዴው መብቱንና ግዴታውን በቅጡ ተረድቶ ሕግ ማክበር፣ ማስከበር እንዳይችል በማድረግ በቂ መረጃ የሌለውን ነጋዴ በማሸማቀቅ ጉቦ ለመጠየቅና በጥቅሉ ነጋዴውን ለሕገወጥ አሰራር የሚጋብዙና ለከፍተኛ ደረሰኝ አልባ የማይወራረድ ወጭ የሚዳርጉት ናቸው።

ነጋዴው ሸቀጡን ከአንድ አካባቢ ወደ ሌላ አካባቢ፣ ከጉምሩክ ወደ መጋዘን ከዛም ወደ መደብሩ ሲያጓጉዙ ጥቂት ለማይባሉ ደፋርና ሕገ ወጥ ደንብ አስከባሪዎች፣ ለወረዳ፣ ለክፍለ ከተማ ሰራዊቶች፣ ለሽፍታዎች፣ ለኬላ አስከባሪዎች፣ ለሚሊሻዎች፣ ለወፈ ሰማይ ጫኝና አውራጅ፣ ለጥገኛ ደጀ ጠኝና በእጄ በሉኝ ባይ ሁላ በየኪሳቸውና በየሂሳባቸው ገንዘብ መሸጎጥ አለበት። ለነገዴው ሌላ ደረሰኝ የማይቆረጥበትና የማይወራረድለት ወጭ ነው።

የልመና መዝገቡ ርዝመት ደግሞ ለጉድ ነው። በየሰበቡ ለሚከናወን የፓርቲ ድግስ፣ የውሎ አበል፣ አልባሳትና መጓጓዣ እጁን መዘርጋት አለበት። ለበዓል የዱቄት፣ የዘይት ኮታ ይጣልበታል። ለመንግስትና ሕዝባዊ ተቋማት ጥገናና ግንባታ፣ ለአካባቢ ጥበቃና ልማት ምጽዋት ይጠየቃል። ይህም በደረሰኝ የማይወራረድለት ሌላ የወጭ ርዕስ ነው።

ነጋዴው ይህንን ሁሉ የማይወራረድ ደረሰኝ የማይሰጥበት ወጭ ተሸክሞ ትርፉን በሕገ ወጥ መንገድ ከገቢዎች ሳይሰውር፣ ሸማች ላይ ሳይቆልልና ሂሳብ ሳያወራርድ እንዴት አድርጎ የእቃ ዋጋ ይተምን? ትርፍስ ያትርፍ? ስራውንስ ያስፋፋ? ጥሪትስ ይቋጥር? እንዴትስ አድርጎ ለሸቀጥና ለምርቱ ትክክለኛ ዋጋ ተምኖ ቫትና የሽያጭ ደረሰኝ ይቁረጥ? በህጋዊ መንገድ ገቢውንስ አሳውቆ ግብር ይከፈል?

ችግሩ ይቀጥላል። በየመንገዱ ላይ ከተማውን ያጥለቀለቀው አባትና እናቱ የማይታውቅ ሸቀጥ ምንጩ ኮንትራ ባንድ ነው። በኮንትራ ባንድ የሚገባው ሸቀጥ ግብር የማይከፈልበት፣ ቀረጥ ያልተቀረጠበት፣ ቫት የማይጎበኘውና ኪራይ የማይከፍሉ ሰዎች በሕጋዊ መንገድ ከሚገባው ዋጋ በረከሰ ደረጃ በየጎዳናው ላይ የሚቸረችሩት ስለሆነ ነጋዴውን ከገበያ የሚያስወጣ ነው። ለአንድ ዓይነህ ምርትና አገልግሎ በተለያየ ዋጋ መቀረጥም ለውድድር መታጣትነሠ ትርፍና ገቢ ስወራ መንሰኤ ነው።

አብዛኛው ነጋዴ ከዚህ ሁሉ ተቋማዊ፣ ድርጅታዊ ፈተና ባሻገር ከለላና ሽፋን ካላቸው ጥቂት ስርዓት አልበኛ ነጋዴዎች ጋር ታግሎ ትርፍ አትርፎ ስራውን ማስቀጠል ካልቻለ መክሰርና ከንግድ ስርዓቱ መሰረዝ እጣ ፈንታው ሌላው ፈተና ነው። እናስ፦ ሌሎች ጥቂት ነጋዴዎች ሕገ ወጥ ስለሆኑ ሁሉም ነጋዴ በሕገ ወጥ መንገድ መነገድ አለበት ማለት ነው?! ንግድን ከጽድቅና ከሞራል ባሻገር ካሰብነው ጥያቄው የሚሊየን ብር ጥያቄ ነው ?

ትርፍን ፍለጋ ወረቱን ያፈሰሰ ታታሪ ነጋዴ ሕግና ቁጥጥር ቢጠብቅም ለጥቂት ሕገ ወጥ ነጋዴዎች ሲባል በሚከፈተውና በማይዘጋው ቀዳዳ አጮልቆ በመማተር ንግዱን እንደሚያጧጡፍ አለመገመት እርስ በርሱ የሚጣፋ የዜሮ ድምር ጨዋታ ነው። እስከ ዛሬ ድረስም በዚህ አሸናፊ በሌለበት የአይጥና የድመት ድብብቆሽ መንገድ መቀጠሉ ተጎጂውም ሆነ የድብብቆሹ፣ የግብይይነትና የውድድር መታጣት ያስከተለው ምስቅልቅል ተሸካሚ ሕዝቡን እንዳደረገው ቀጥሏል።

በጥቅሉ ጥቂት የማይባሉ ነጋዴዎች አቅደውና አስልተው በሕገ ወጥ መንገድ በመመሳጠር፣ ትርፍ በማጋበስ፣ የተእታና የሽያጭ ደረሰኝ ባለመቁረጥና ገቢያቸውን በመሰወር ምዝበራ አልፈጸሙም ለማለት አልችልም። የዚህ ሁሉ ውጥንቅጥ መንስኤም እነዚሁ ነጋዴዎች እንደሆኑ ለመገመትም አዳጋች አይደለም።

በዛው ልክ አብዛኛው ነጋዴ ግን ወደ ሕወጥ የንግድ ስርዓት የሚገፋው ከላይ የጠቀስኳቸው ፈተናዎች ከገበያ የማስወጣት ፈተና ስለሚደቅኑበት እንደሆነ ማወቅ ተገቢ ነው። ስለዚህም በጥቂት ነጋዴዎች የተቀናጀና የተደራጀ ሕገወጥ አሰራር ሁሉም ነጋዴ መወቀስና ያለማቋረጥ መረበሽ የለበትም። ነጋዴው መረጋጋት በተሳነውና በተረበሸ ቁጥር የሸቀጥ እቃ ዋጋ መናር፣ የአቅርቦት መመናመን፣ የምርት እጥረትና የገበያ መናጋት በተደጋጋሚ ታይቷል። እድሉን ለሚጠብቁ ተቋማትና ነጋዴዎችም የዘረፋ መረብ ሲያዘረጋና የሕገ ወጥነት በር ሲያስከፍት አይተናል።

ችግሩ ሰ፣ ጥልቅና ውስብስብ ነው። ዋጋ የማረጋጋትና ግብር ሀገርን የመከፈል ገዳይም ያንዣብብበታል። ሕዝቡንና ታታሪውን ነጋዴ ለመታደግ ሕግ ከማውጣት በላይ የሁሉንም ርብርብና ስራን የሚጠይቅ ለመሆኑም ጥርጥር የለውም። ሕግ እየጠበቀና የሕገ ወጥነት በር እየተዘጋ በመጣ ቁጥር ሌሎች አዳዲስ የሕገ ወጥነት በርና ቀዳዳ የሚከፈትላቸው ወንጀለኛ ነጋዴዎችና ተቋማዊ ግብረ አበሮቻቸው ሕግ እንዲያከብሩና እንዲያስከብሩ እራስንና ውስጥን በመፈተሽ ስራ እስካልተሰራ ደረስ በየጊዜው የሚወጡ ሕጎችን ተከትሎ ለሕገ ወጥ ነጋዴዎች በሚከፈቱ አዳዲስ ሕገ ወጥ በርና ቀዳዳዎች ለመሹለክ፣ ቀሪዎቹ ነጋዴዎች መትመማቸው ደመነፍሳዊ የሕልውና ትግል ሆኖ መቀጠሉ የማይቀር ነው።

©ሙሼ ሰሙ

Want your business to be the top-listed Media Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Address

Addis Ababa
1000

Opening Hours

Monday 07:00 - 19:00
Tuesday 07:00 - 19:00
Wednesday 07:00 - 19:00
Thursday 07:00 - 19:00
Friday 07:00 - 19:00
Saturday 07:00 - 19:00