BeZera

BeZera

Share

Invest in Our Farms. Harvest Our Future.

Photos from BeZera's post 25/08/2025

ላለው ይጨመርለታል ሚባለው ውሸት አይደልም ፍጹም እውነት እንጂ። ምስኪኑ ገበሬ በማይረባ ትርፍ እየሸጠ ሲጎዳ ህዝቡም በከፍተኛ ዋጋ ተማሯል። ብቸኛው ተጠቃሚ መሃል ላይ ያለው አትራፊው ነጋዴ ነው።

ይህን ነገር ሊስተካከል የሚችልበት መንገድ አለ ወይ?

መልሱም በሚገርም ሁነታ ኣዎ ነው።

እንዴት፥ በማንና መች?

ይሀንን ሃገር ኣቀፋዊ ጥያቄ ሊመልስ የሚችለው BeZera ነው። ስራችህንን ከነመፍትሄው በቅርቡ ይጠብቁን። የተሰበረውን ስርዐት በጋራ እንጠግነው።

24/08/2025

በገበያ ውስጥ እህል ዋጋው በየደቂቃው፣ በየሰአቱና በየቀኑ ወደላይ እየጨመረ ይገኛል። እናንተም ከሌለቹ ላይ እያወጣቹ በመግዛት ነገ አንዴት እሆናለው በሚል ጭንቀት ውስጥ ትሆናላቹ። እነዚህን እህሎች የሚያቀርቡት ገበሬዎች ግን ከክስረት ራሳቸውን ማዳን አልቻሉም። በራሳቸው መሬት ላይ ቢሠሩም በፋይናንስ እጥረት ምክንያት በተሻለ ዘዴ ማስተዳደር አይችሉም። በዝያም ምክንያት ስግብግቡ ነጋዴ ይሀንን እድል በመጠቀም ትልቅ ትርፍ በማትረፍ ምስኪኑን ገበሬና ኣማራጭ ያጣውን ህዝብ ለትርፉ ሲል ይጎዳል።

በዚህ ሰአት ነው በዘራ(BeZera) ለጥቅም ሚውለው፡ ገበሬዎች የሚያስፈልጋቸውን የፋይናንስ ድጋፍ በመስጠት፣ መሳሪያ እና ቴክኖሎጂ በማቅረብ፣ የሰብል ምርታማነት እንጨምራለን። እንዲሁም small-holder farmer ብለን ምንጠራቸውን ገበሬዎች በቂ የሆነ ስልጠና በመስጠት ወደ ገበያ አናስገባለን። ይህ የገበያ ዋጋ አንዲቀንስ ይረዳል፣ እናንተም ነገ እንዴት እሆን የሚለውን ጭንቀታችሁ ይቀራል፣ ገበሬዎችም በገንዘብ እና በክብር ይኖራሉ።

በቀላሉ፣ ዛሬ በገበያ ላይ መቆም የሚችል ገበሬ፣ ነገ ለህዝቡ የምግብ ዋጋ የሚቀንስ ነው። ይህን ድርጊት ለመፈጸም በBeZera ላይ እንገናኝ።

BeZera

#ኢትዮጵያ #ገቢ

Want your business to be the top-listed Finance Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Address

Addis Ababa