Orthodox negn
Orthodox lij negn
20/10/2025
ታማልዳለች ስለኛ ታለቅሳለች😢
ድንግል ሆይ በጎለጎታ በተወደደ የልጅሽ መቃብር ላይ ስለኛ ስለኃጢአተኞች ያነባሽውን እንባ አስቢ!።
ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማሕፀኔ የተሸከምሁህን አስብ። በወለድሁህ ጊዜ ያገኙኝን ችግሮች የሌሊት ቁር የቀን ሐሩር አስብ። ከወለድሁህም ቡሀላ የማስተኛበት ቤት ስላጣሁ ቅጠል አልብሼ በከብቶች በረት ያስተኛሁህን አስብ። . . . በኩር ልጄን ከሚገሉ እኔን አስቀድመው ይረዱኝ ብዬ ለዮሴፍ የነገርሁትን አስብ። ልጄ ሆይ በጐዳና ስንሄድ ወንበዴዎች ባገኙን ጊዜ እነርሱን ሸሽቼ የምገባበት ቦታ አጥቼ መጨነቄን አስብ። ልጄ ሆይ ስለአንተ የተቀበልኩትን ረኀብና ጥምች ግርና ሀዘን መከራና ግፍ አስብ። ልጄ ሆይ በመስቀል ተሰቅለህ በሞትህ ጌዜ ያለቀስሁት ልቅሶዮን ዕንባዬን አስብ። ልጄ ሆይ ስለአንተ የደረሰብኝን ሁሉ አስብ። አሁንም በመማፀን ስሜን ለሚጠሩ ሁሉ ማራቸው።
በእውነት በእመብርሃን ፀሎት ይማረን።🙏🙏🙏
ልጇ ወዳጇም የወለድሽኝ ያዘልሽኝ እናቴ ደስ ይበልሽ ያሳደግሽኝ እናቴ ሆይ ደስ ይበልሽ አንቺ ምህረት የምትለምኝ ነሽ እኔ ይቅር ባይነኝና። ( ወበእንተዝ እገብር ለኪ ኩሎ ዘሰአልክኒ እምየ ወእፌጽም ለኪ ኩሎ መፍቅደኪ ) ስለዚህ የወለድሽኝ እናቴ የለመንሽኝን ሁሉ አደርጋለሁ ፈቃድሽንም ሁሉ እፈፅምልሻለሁ እናቴ ሆይ በመማፀን ስምሽን የጠራውን በመታመን መታሰቢያሽን ያደረገውን ሰው ሁሉ ስለአንቺ እምረዋለሁ አድነዋለሁ።
እመቤታችንም ይህንን ሁሉ የምህረት ቃልኪዳን ለሰጠኸኝ ለአንተ ለባህርይ አባትህ ለአብ ለባሕርይ ሕይወትህ መንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ስግደት ይገባል አለችው ለዘላለሙ አሜን።
ድንግል ማርያም ከጭንቅ ከመከራ ታውጣችሁ🙏🙏
በድንግል ማርያም አማላጅነት ያመነ እናትነቷን ያልካደ አሜን
መፅሐፈ ኢዮብ
የጌታዬ እናት ማርያም ማርያም ማርያም የምንለው ለኔ #ሰላም #ጤና ከመስጠት አልፎ ስምሽ ቤቴን #በበረከት ስለሚሞላው ነው
#ኦርቶዶክስ #ኦርቶዶክሳዊ ゚viralシfypシ゚viralシalシ
#ማርያም
የስሟ ትርጉም #ማርያም ዓይናችን ነሽ ማርያም የድንግል ማርያም ልጅ
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
1000