Ethio Times
""የእኔ ዑማ ከሁሉም ዑማ በላጭ ነው""
(ረሱል ﷺ)
����
"መታደል እኮ ነው የሙሀመድﷺ "ዑማ" መሆን"
24/05/2026
🙄😏 አርሴናል ድል በማድረጉ ፈታ እያሉ ነው!
24/05/2026
በአርሰናል ጉዳይ መንግስት ጣልቃ ካልገባ ሰላም አናገኝም በቃ 😭😭😭
22/05/2026
ወደ ሀሰን አንጃሞ መካነ መቃብር
---
ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም የታላቁን ጀግና የሀሳን አንጃሞን መካነ መቃብር ጎበኘሁት ይለናል፡፡ በኢማሙ የታሪክ አሻራዎች ያደረገውን ቆይታ እንዲህ ተርኮልናል፡፡ / ከሄኖክ ስዩም በድሬቲዩብ
--
ትንሽ መንደር ናት፡፡ ውብና ለም፤ ግዙፍ ሁለት ጎጆዎችን ሾልኬ ገባሁ፡፡ ምሁር አክሊል የሚባለው ወረዳ ውስጥ ነኝ፤ ቀበሌዋ ሴባ ትባላለች፡፡ መንገዱን የሚመራው የሀሰን አንጃሞ የልጅ ልጅ ልጅ ነው፡፡ አራተኛው የኢማሙ ትውልድ፤
ስብሐት ገብረ እግዚአብሔር እኔ ወጣት ብሆን ሀሳን አንጃሞን ፊልም አደርገው ነበር ያለለትን ጀግና ብርቱ ታዋጊ በመሆን ይታወቃል፡፡ ጀግንነቱ ዛሬም ድረስ በስነ ቃሎች ይሞካሻል፡፡ ታሪክ ከማይረሳቸው ብርቱ ጦረኞች አንዱ ነው፡፡ ኢማም ሀሰን አንጃሞ፤
ከሃድያ እስከ ስልጤ ከእነሞር እስከ ቀቤና ከወለኔ እስከ ሊቢዶ ያሰባሰበው ጦር ከሸዋ ሠራዊት ጋር በጀግንነት እንዲዋጋ የመሪነት ብቃቱን የሚወስድ ስመ ጥር የጦር ጀግና ነው፡፡ ለዲኑ ብሎ ቢሰደድም ብዙዎችን አስከትሏል ይላሉ የወለኔው ሼህ ስለ ኢማሙ በጻፉት ጽሁፍ፤
ጥሮነ ሼህ ኡመር ሼህ በሽር የጻፉት ዜና መዋዕል ነው፡፡ አብዱልፈታህ አብደላህ ለአማርኛ አንባቢያን እንዲደርስ አድርጎታል፡፡ ሰውዬው ኢማም ሀሰን አንጃሞን በተመለከተ ከ150 ዓመት በፊት በጻፉት ጽሑፍ ቁመቱ ረዥም እንደሆነ ይነግሩናል፡፡
እንደ ሼህ ኡመር ገለጻ ኢማም ሀሰን አንጃሞ ብዙ መብላትና መጠጣትን የማይወድ፣ ጥቁር ሆኖ ቆንጆ፣ በሙያው ማንም የማይደርስበት፣ ፈረሰኛና ጀግናና ሲበዛ ቸር ነበር ይሉናል፡፡
እየሄድሁ ያለሁት ወደዚሁ ጀግና መካነ መቃብር ነው፡፡ ጡሃ መሀመድ ኺያርሺፋ ሀሰን የመካነ መቃብሩን ቅጥር ከፈተው፡፡ ወደ ውስጥ ገባን፡፡ ዛፎች የከበቡት አረንጓዴ ስፍራ ነው፡፡ ኢማም ኺያር፣ የሀሰን አንጃሞ አያትና አባትን ጨምሮ የኢማሙ መቃብር ይገኝበታል፡፡
ኢምሬትስ ፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴ ሀብቴ አባ መላን በጻፉበት መጽሐፍ ኢማም ሀሰን ኢንጃሞ ለእነ ራስ ጎበና ባስቸገረ ሁኔታ ፈተና መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የጀብዱ ሜዳ ጦርነት የሚባለውም በኢማም ሀሰን አንጃሞ በሚመራው የቀቤናና ሃድያ ሠራዊትና በራስ ጎበና መሪነት በሚመራው የዐፄ ምኒልክ ሠራዊት መካከል የተደረገ ነበር፡፡ በዚህ ጦርነት ድል ለራስ ጎበና ሠራዊት ቢሆንም ታላቁ የጦር መሪ የራስ ጎበና ልጅ መርእድ ጎበና ተሰውቷል፡፡ ኢማም ሀሰን አንጃሞም ከሠራዊቱ መፈታት በኋላ ወደ ጅማ ሸሽቷል፡፡
ራስ ጎበናም ከድሉ በኋላ የነበራቸው እድሜ የቀናት ብቻ ነበር፡፡ ተደጋጋሚ ጦርነቶችን ድል አድርጎ በመጨረሻም በንጉሠ ነገሥቱ ስመ ጥር የጦር መሪ የተረታው ኢማም ከዚያ በኋላ ሀሰን አንጃሞ የጀግንነት ምልክት ሆነ ስሙ ገኖ ተወደሰ፡፡
21/05/2026
21/05/2026
21/05/2026
በአዲስ አበባ-ደብረ ማርቆስ መስመር
34 ተሳፋሪዎች በታጣቂዎች ታገቱ
ከአዲስ አበባ ተነስተው ወደ ደብረ ማርቆስ በ"ኤፍ ኤም" የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ሲጓዙ የነበሩ 34 መንገደኞች በሰሜን ሸዋ ዞን በታጣቂዎች ታገቱ። እገታው የተፈጸመው ግንቦት 11 ቀን 2018 ዓ.ም. በገብረ ጉራቻ እና በፊቼ ከተሞች መካከል "ዓሊዶሮ" ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ሲሆን፣ ታጣቂዎቹ አውቶቡሱን በኃይል አስቁመው ተሳፋሪዎቹን ወደማይታወቅ አካባቢ ይዘዋቸው ተሰውረዋል። ከተሳፋሪዎቹ መካከል እስካሁን የደረሱበት የሚታወቀው የሦስት ግለሰቦች ብቻ ሲሆን፣ ጥቃቱን የፈጸሙት ታጣቂዎች ማንነትም ሆነ ከመንግሥት አካላት የተሰጠ ይፋዊ መግለጫ እስካሁን የለም።
ይህ አሰቃቂ ድርጊት በአዲስ አበባ–ደብረ ማርቆስ የትራንስፖርት መስመር ላይ አሳሳቢ እየሆነ የመጣውን የጸጥታ መደፍረስ ይበልጥ ያጎላ ሲሆን፣ በአካባቢው ተመሳሳይ ድርጊቶች በተደጋጋሚ መፈጸማቸው ተገልጿል። ከአራት ወራት በፊት በተመሳሳይ መስመር ላይ ሌላ አውቶቡስ ታግቶ የነበረ ሲሆን፣ እ.ኤ.አ. በመጋቢት 2025 ደግሞ በተመሳሳይ ዓሊዶሮ አካባቢ ታጣቂዎች በአውቶቡስ ላይ ተኩስ በመክፈት ከ56 በላይ ተሳፋሪዎችን አፍነው መውሰዳቸውን የዐይን እማኞች አስታውሰዋል። ታጣቂዎቹ በተሽከርካሪው ጎማዎች ላይ ተኩስ በመክፈት ካቆሙ በኋላ፣ ተሳፋሪዎችን እየደበደቡና እየጎተቱ ገደላማ ወደሆኑ ራቅ ያሉ ቦታዎች እንደወሰዷቸው ይነገራል።
በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች ዋና ዋና አውራ ጎዳናዎች ላይ የሚፈጸሙት እነዚህ ተደጋጋሚ ጥቃቶችና እገታዎች በሕዝብ ትራንስፖርት ፍሰትና በዜጎች የመንቀሳቀስ መብት ላይ ከፍተኛ ስጋት ደቅነዋል። ከዚህ ቀደምም በሰኔ 2016 ዓ.ም. ከአማራ ክልል ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ የነበሩ ከ100 በላይ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በገብር ጉራቻ ከተማ አቅራቢያ ታግተው ከፍተኛ የገንዘብ ክፍያ ተጠይቆባቸዋል። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) እና የተለያዩ የዜና ምንጮች በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች ውስጥ ከቀጠለው ግጭት ጋር ተያይዞ ለገንዘብ ማግኛ የሚፈጸሙ መሰል እገታዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመሩ መምጣታቸውን በተደጋጋሚ አስጠንቅቀዋል።
ምንጭ አዲስ አድማስ
19/05/2026
አክራሪ ክርስቲያኖች በአሜሪካ ካሊፎርኒያ ግዛት ሳንዲያጎ በሚገኝ መስጂድ ላይ በተከፈተ የተኩስ እሩምታ 3 ሰዎች ተገደሉ!
• ሀሩን ሚዲያ | ግንቦት 11 ቀን 2018 ዓ.ል
በአሜሪካ ካሊፎርኒያ ግዛት ሳንዲያጎ ከተማ በሚገኝ መስጂድ እና ኢስላማዊ ማዕከል ላይ ትላንት ሜይ 18 ቀን 2026 ቀትር አካባቢ በተፈጸመ የሽብር ጥቃት፣ የመስጂዱን ጥበቃ ጨምሮ እስካሁን 3 ሰዎች መገደላቸው እና ሌሎች በርካቶች ቆስለው ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸው ተገለጸ።
ጥቃቱ የተፈጸመው ዕድሜያቸው ከ17 እስከ 19 በሚገመት ሁለት ወጣቶች ሲሆን፤ በመስጂዱ አቅራቢያ ተኩስ በመክፈት ጥቃት ለማድረስ በሞከሩበት ወቅት የመስጂዱ ጥበቃ የነበረው አሚን አብዱላሂ ከፍተኛ የመከላከል ስራ በመስራት የብዙዎችን ህይወት ካተረፈ በኋላ በተኩሱ ህይወቱ አልፏል። የ8 ልጆች አባት የሆነው አሚን አብዱላሂ የህጻናቱን ህይወት ጨምሮ በርካታ ሰዎችን ከሞት መታደጉን የአካባቢው ፖሊስ በይፋ ገልጿል።
ጥቃት በተፈጸመበት በዚህ የኢስላማዊ ማዕከል ውስጥ በአልረሺድ ትምህርት ቤት የመድረሳ ትምህርት የሚማሩ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ህጻናት የነበሩ ቢሆንም፤ በህጻናቱ ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት ሳይደርስ በፍጥነት ደህንነቱ ወደተጠበቀ ስፍራ እንዲዛወሩ ተደርጓል።
የአሜሪካው የፌደራል ምርመራ ቢሮ (FBI) እና የአካባቢው ፖሊስ የተፈጸመውን ጥቃት "ሊኖር የሚችል የጥላቻ ወንጀል" (Possible Hate Crime) በሚል መነሻነት ጥልቅ ምርመራ የጀመሩ ሲሆን፤ በጥቃት አድራሾቹ ቁሳቁሶች ላይ ፀረ-እስልምና ጽሑፎች እና የናዚ ምልክቶች መገኘታቸው ጥቃቱ ከእስልምና ጥላቻ ጋር በቀጥታ የተያያዘ ለመሆኑ ማሳያ እየሆነ ይገኛል።
ክስተቱን ተከትሎ የአሜሪካ-ኢስላማዊ ግንኙነት ምክር ቤት (CAIR) ባወጣው መግለጫ፤ በሀገሪቱ የዕምነት እና የጸሎት ቦታዎች ደህንነት አለመጠበቅ እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ጠቁሟል። በአሁኑ ወቅት ከጥቃቱ በኋላ በመስጂዱ ዙሪያ የፖሊስ ጥበቃ በከፍተኛ ሁኔታ ተጠናክሮ እንደሚገኝ ተነግሯል።
📅 ዙል-ሒጃ 2 ቀን 1447 ዓ.ሂ
© ሀሩን ሚዲያ
Click here to claim your Sponsored Listing.