WMCC
AddisWalta - AW
አዲስ ዋልታ
Walta Media and Communication Corporate Who We Are
Walta Media and Communication Corporate S.C.
(WMCC) is a broadcast media company based in Addis Ababa, the political capital of Africa. The company which owns TV and Radio Stations aspires to become a pan African media company currently disseminating information in local and international languages. Walta has built its reputation through covering all aspect of Ethiopia and beyond in its professional news, documentary and programs reporting.
13/04/2026
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ለላይቤሪያ ፕሬዚዳንት አቀባበል አደረጉ
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለላይቤሪያ ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ንዩማ ቦአካይ አቀባበል አድርገዋል።
የላይቤሪያ ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ንዩማ ቦአካይ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ዛሬ ምሽት አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ÷ ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ንዩማ ቦአካይ የነገ ብሩህ ተስፋ እየተሰራባት ወደ ምትገኘው ምድረቀደምት ኢትዮጵያ እንኳን በሰላም መጡ ብለዋል።
በቆይታዎ እጅግ ፍሬያማ ወይይት እንደሚኖረን እምነቴ ነው ሲሉም ገልጸዋል።
13/04/2026
በጎሮ ጉቱ ወረዳ በትራፊክ አደጋ የ9 ሰዎች ሕይወት አለፈ
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሐረርጌ ዞን ጎሮ ጉቱ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የዘጠኝ ሰዎች ሕይወት አልፏል።
አደጋው ከአዲስ አበባ ወደ ድሬዳዋ ከተማ ሲጓዝ በነበረ ኮንቴነር የጫነ ተሽከርካሪ ላይ መድረሱን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል፡፡
በተከሰተው አደጋም እስካሁን የዘጠኝ ሰዎች ሕይወት ማለፉ ነው የተገለጸው፡፡
13/04/2026
በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ እየተካሄደ ያለው የመራጮች ምዝገባ በምስል፡-
13/04/2026
ጋሞ ጨንቻ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አደገ
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ "ሀ" እየተሳተፈ የሚገኘው ጋሞ ጨንቻ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ማደጉን አረጋግጧል።
ዛሬ በጅማ ስታዲየም ጨዋታውን ያደረገው ጋሞ ጨንቻ ቡራዩ ከተማን 3 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
ውጤቱን ተከትሎም ጋሞ ጨንቻ ወደ 2019 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ማደጉን አረጋግጧል ።
13/04/2026
በነጻ የንግድ ቀጣናዎች የተሰማሩ ባለሃብቶች ከገቢ ግብር ነጻ እንዲሆኑ ተፈቀደ
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በነጻ የንግድ ቀጣናዎች ውስጥ ተሰማርተው ግብዓቶችንና ምርቶችን ለገበያ በማቅረብ ስራ ላይ የተሰማሩ ባለሃብቶች ከገቢ ግብር ነጻ እንዲሆኑ ተፈቅዷል አለ የገንዘብ ሚኒስቴር።
ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ÷ የሀገር ውስጥ ኢንዱስትሪ ልማትን ወደኋላ የሚይዙ የካፒታል እጥረት፣ የግብዓት አቅርቦት ችግር እና የባለሙያ እጥረት ደረጃ በደረጃ በማቃለል ረገድ በርካታ ስራዎችን እየሰተራ እንደሚገኝ ገልጿል።
ከነዚህም መካከል አስመጪዎች ግብዓቶችንና ምርቶችን ቀረጥና ታክስ ሳይከፍሉ ወደ ሀገር ውስጥ አስገብተው ለግብዓቱ ወይም ለምርቱ ገበያ ባገኙ ጊዜ ቀረጥ እና ታክሱን የሚከፍሉበትን አሰራር የሚፈቅድ የነጻ የንግድ ቀጣና አሰራር መዘርጋቱ ይታወሳል።
አሁን ደግሞ የንግድ ቀጣናዎች ባለሃብቶችን የበለጠ የሚስቡ እንዲሆኑ ለማድረግ በነጻ የንግድ ቀጣናዎች ውስጥ ተሰማርተው ግብዓቶችን እና ምርቶችን ለገበያ በማቅረብ ስራ ላይ የተሰማሩ ባለሃብቶች ከገቢ ግብር ነጻ እንዲሆኑ መፈቀዱን አመልክቷል።
ባለሃብቶቹ እድሉን በመጠቀም በነጻ የንግድ ቀጣናዎች ውስጥ እንዲሰማሩ ሚኒስቴሩ ጥሪ አቅርቧል።
13/04/2026
ሸገር ከተማ እና ነገሌ አርሲ አቻ ተለያዩ
13/04/2026
ኢራን በየትኛውም ማስፈራሪያና ዛቻ አትንበረከክም - የሀገሪቱ ፓርላማ
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የኢራንን ወደቦች ከዛሬ ጀምሮ እንደሚዘጉ ይፋ አድርገዋል፡፡
አሜሪካና ኢራን የመካከኛው ምስራቅ ጦርነትን ለማስቆም ከ47 ዓመታት በኋላ በፓኪስታን ያካሄዱት የፊት ለፊት የሰላም ውይይት ያለስምምነት መጠናቀቁ ይታወቃል፡፡
ይህን ተከትሎም ፕሬዚዳንት ትራምፕ በኢራን ላይ የሚወሰደው ሁለንተናዊ ርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል፡፡
ከዛሬ ጀምሮም በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ የሚከናወንን የመርከብ እንቅስቃሴ እንደሚያግዱ ገልጸው ÷ ለዚህም የሜሪካ ጦር ዝግጁ ነው ብለዋል፡፡
የፕሬዚዳንቱን ማስጠናቀቂያ ተከትሎም የዓለም የነዳጅ ዋጋ በድጋሚ በበርሜል ከ100 ዶላር በላይ ማሻቀቡን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
የኢራን ፓርላማ አፈ ጉባዔ ሞሃመድ ባጋር ጋሊቢፍ በበኩላቸው ÷ቴህራን አሜሪካ በየጊዜው በምታስተላልፈው የትኛውም ዘቻ እና ማስፈራሪያ እጅ አትሰጥም ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
የኢራን አብዮታዊ ዘብ ወደ ሆርሙዝ ወሽመጥ የሚጠጉ የጦር መርከቦች ላይ አስፈላጊውን ርምጃ ለመውሰድ በተጠንቀቅ ላይ ይገኛልም ነው ያሉት፡፡
ሀገራቱ በዓለም ቁልፍ የነዳጅ መተላለፊያ መስመር በሆነው ሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ የገቡበት እሰጣገባም በዓለም የተፈጠረውን የነዳጅ ቀውስ ይበልጥ እንዳያባብሰው ተሰግቷል፡፡
በመላኩ ገድፍ
13/04/2026
ፋና መድረክ!
የሀገርን ሁለንተናዊ መልክ በሚወስኑ ርዕሰ ጉዳዮች የሚያደርገው የፖለቲካ ፓርቲዎች የክርክር መድረክ ቀጥሏል!
ርዕሰ ጉዳይ፡- የቋንቋ እና ባህል ፖሊሲ
በተጠቀሰው ርዕሰ ጉዳይ ተከራካሪ ፓርቲዎች ኢትዮጵያ ሊኖራት የሚችለው የስራ ቋንቋ ብዛትና አይነት፣ እንደ ሀገር ብሔራዊ ቋንቋ ይኑር ወይንስ አይኑር፣ የትምህርት ስርዓቱ በምን ቋንቋ ይሁን? በሚሉና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ፖሊሲያቸው ተዳስሰዋል።
በዚህም፡-
👉ብልጽግና ፓርቲ
👉ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት
👉የኢትዮጵያ ዜጎች ለማሕበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)
👉ሕዳሴ ፓርቲ የፖሊሲ አማራጫቸውን አቅርበዋል።
ባቀረቡት የፖሊሲ አማራጭም በፋና መድረክ ተሞግተዋል፤ የሌሎች ፓርቲዎችን አማራጭ ሃሳብም ሞግተዋል።
አርብ ምሽት በፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ቴሌቪዢንና በማሕበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይጠብቁን!
13/04/2026
ማንቼስተር ዩናይትድ ከሊድስ ዩናይትድ…
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ32ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ማንቼስተር ዩናይትድ በኦልድትራፎርድ ምሽት 4 ሰዓት ላይ ሊድስ ዩናይትድን ያስተናግዳል።
ሊጉ ለሀገራት ጨዋታ ከመቋረጡ በፊት የመጨረሻ መርሐ ግብሩን በአቻ ውጤት ያጠናቀቀው ማንቼስተር ዩናይትድ ወደ ድል ለመመለስ ከበርካታ ቀናት በኋላ ወደ ሜዳ ይገባል።
ያለፉትን አምስት ተከታታይ ጨዋታዎች በሊጉ ማሸነፍ ያልቻለው ተጋጣሚው ሊድስ ዩናይትድ በበኩሉ÷ ወደ አሸናፊነት ለመምጣት ብርቱ ፉክክር ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።
ሁለቱ ቡድኖች እርስ በርስ ካደረጓቸው ያለፉት አምስት ጨዋታዎች ማንቼስተር ዩናይትድ ሁለቱን ሲያሸንፍ በሦስቱ አቻ ተለያይተዋል።
ትናንት በተደረጉ የሊጉ ጨዋታዎች ማንቼስተር ሲቲ ቼልሲን 3 ለ 0፣ ሰንደርላንድ ቶተንሃም ሆትስፐርን 1 ለ 0፣ ክሪስታል ፓላስ ኒውካስል ዩናይትድን 2 ለ 1 ሲያሸንፉ፣ አስቶን ቪላ ከኖቲንግሀም ፎረስት 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት መለያየታቸው ይታወቃል።
ሊጉን አርሰናል በ70 ነጥብ ሲመራው ማንቼስተር ሲቲ በ6 ነጥብ ዝቅ ብሎ ይከተላል።
ማንቼስተር ዩናይትድ በ55 ነጥብ 3ኛ እንዲሁም አስቶንቪላ በተመሳሳይ 55 ነጥብ በግብ ክፍያ አንሶ 4ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
በወንድማገኝ ጸጋዬ
13/04/2026
በሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ አራት ጨዋታዎች ይደረጋሉ
በሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ አራት ጨዋታዎች ይደረጋሉ
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ27ኛው ሳምንት ሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ዛሬ አራት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።
ቀን 7 ሰዓት በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ሸገር ከተማ እና ነገሌ አርሲ የሚገናኙ ሲሆን÷ በተመሳሳይ ስታዲየም ቀን 10 ሰዓት ላይ አርባ ምንጭ ከተማ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
የሊጉ መርሐ ግብር ቀጥሎ ሲካሄድ ቀን 9 ሰዓት ላይ መቐለ 70 እንደርታ ከወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ይገናኛል።
እንዲሁም በተመሳሳይ ስታዲየም አመሻሽ 12 ሰዓት ላይ ሀዋሳ ከተማ እና ምድረ ገነት ሽረ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
13/04/2026
ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ተመዝግበው ካርድዎን ወሰዱ?
13/04/2026
የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ጉዞ አዲስ ምዕራፍ እየተራመደ ይገኛል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ጋር ባደረጉት የሁለት ክፍሎች ቃለምልልስ ኢትዮጵያ የአዲሱ ዘመን የኢንዱስትሪ መስፋፋትን እንዴት እየበየነች እንደሆነ አብራርተዋል።
የመጀመሪያውን ክፍል ማክሰኞ ሚያዚያ 6 ቀን 2018 ዓ.ም ከምሽቱ 2:30 ይጠብቁ።
Click here to claim your Sponsored Listing.