Yared Computer's
We have Brand new and brand used Personal computer's and Laptop's with a fair Price.....
06/01/2026
04/12/2022
ብራቮ ፑቲን👏
04/11/2022
#በቃን
14/03/2022
Lenovo think pad
14.1” screen size
Core i3
5th generation
4gb ram
500gb hdd
3-4hours battery 🔋 life
Look like new
13/05/2021
07/01/2021
መልካም የገና በዓል ይሁንልዎ!!!!!!
03/11/2019
ዘረኛ ይውደም
ከኮተቤ ነፃ አውጪ ግንባር የተሰጠ መግለጫ
We are an old school freaks በ 1970 ዎቹ ተወልደን በ 1990 ዎቹ የፈነዳን ፅድድድድት ያልን!! ጋንዲ እና ዘውዲቱ ሆስፒታል የተወለድን ጥቁር አንበሳ ፣ ደጃዝማች ወንድይራድ፣ ፀሐይ ሮሺን፣ ቦሌ ፣ አዲስ ከተማ ፣ አሳይ ፣ ምስካየዙናል ፣ አቃቂ ሚሽን ፣ ካቴድራል ፣ ሴንጆ በ1980ዎቹ ትምህርት የጀመርን ጠዋት ጠዋት ትምህርት ከመጀመራችን በፊት የኢትዮጵያ ብሄራዊ መዝሙር የዘመርን መንገድ ላይ ሆነን መዝሩን ከሰማን እንደ ጨው አምድ ባለንበት የቆምን የተማሪ ዩኒፎርም በ ሁሉም ት/ቤቶች ያስጀመርን በ ስጋጃ ቦርሳ ፣ በሪንግ ቡክ ፣ በDino ቦርሳ ደብተር ይዘን የተማርን... በ ባለ 50 ፣ 32 ፣ 16 ሉክ ደብተሮች ለብደን የተማርን የስዕል ደብተር በ ልሙጥ ሉክ ሰፍተን የሰራን ጋዝ ቀብተን አስደግፈን ስዕል የሳልን ሙዚቃ ፣ እጅ ስራ ፣ እርሻ ፣ ኑሮ በዘዴ ፣ woodwork ፔሬድ የተማርን በአጥር ፎርፌ የገጨን እጅ በጆሮ /የሞት ቅጣት/ የተቀጣን የ መማርያ መፅሃፍ የ መጀመርያው ገፅ ላይ ኢትዮዽያ ትቅደም ብለን ትምህርት የጀመርን የ ሳይንስ የፊት ገፅ መፅሃፍ ላይ የ እባብ ስእል ያየን እነ አብዲሳ አጋ ፣ የቡልቻ ልብ ፣ ታታሪው አየለ ፣ ሽልንጌ ሽልንጌ ፣ Ahmed has two wives በሚሉ የመማርያ መፅሃፎች የተማርን አርት እና ሳይንስ የመረጥን ሃይስኩል ስንጨርስ አውቶግራፍ ያስፈረምን ግቢ ክላስ ቀጥተን ፑል የተጫወትን በጣት በ ሚቆጠሩ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እና ኮሌጆች በ 5 ኢን ዋን ደብተር ተማረን የጨረስን በ መጀመሪያዎቹ የግል ኮሌጆች ተምረን የተመረቅን የካልሲ ኳስ ያንቀረቀብን ኳስ ተጫውተን በ ብርቅርቅ ሲጋራ ልጣጭ የተጠቀለለ የቅል ዋንጫ የበላን በረኪና እቃ ዋንጫ እስክንጋጋጥ ኳስ የተራገጥን እርግብ ማርባት የምንወድ ለፓሎኒ ኳስ መግዣ ብር ያጠራቀምን ፓሎኒ ኳስ ጎሚስታ ወስደን ያስለጠፍን ያስነፋን ለ ሰፈር ቡድን ማልያ ዋንጫ ይዘን በ የቤቱ የለመንን
እርግጫ የተጫወትን ብይ ፣ ጠጠር ፣ ሱዚ ፣ ፔፕስ ፣ ዲሞ የተጫወትን ማሪዮ እና ስኔክ ጌም ነፍሳችን የነበረ ዱቤ ዱቄት ፣ በካኪ ሚመጣው ረጅም ፓስታ ፣ ጋሌጣ ፣ ኮቾሮ ፣ ኦፖፕ ፣ ፊዚዝ ፣ ጦር ማስቲካ ፣ ጠጠር ከረሜላ ፣ ጉንፋን ከረሜላ ፣ ዱላ ከረሜላ ፣ ሜንት ከረሜላ ፣ ሎሚ በከረሜላ የበላን ጀላቲ ፣ ማይክል ዳቦ ፣ ፓስቲ ፣ በ ከለርድ ያበድ ዳቦ ቆሎ ተደብቀን የገዛን አንባሻ ቤት ተደብቀን የገባን ከተያዝን በርበሬ የታጥንን በ ሳማ ፣ በ አለንጋ ፣ በቀበቶ ፣ በሲሊፐር ተገርፍን በቁንጥጫ ፣ በኩርኩም የተቀጣን ፖስታ ሳጥን ቁጥር የ ነበረን የፍቅር ደብዳቤ የተፃፃፍን የብእር ጏድኛ የነበረን ገርል ፍሬንዳችንን በጩጬ አስጠርተን በር ላይ የጀነጀንን ብዙ ስልክ ቁጥር በቃላችን የሸመደድን በ ናሽናል ቴፕ ሪከርደር ሙዚቃ የሰማን በ ካሴት አዲስ እልበም የ ገዛን ካሴት ደምሰስን ከ ሬድዮ እንግሊዘኛ ዘፈን የ ቀዳን እንዳይደመሰስ ከኃላ ያለችውን አራት መአዘን ነገር በስኪብርቶ የሰበርን እንደገና ለመቅዳት ቀዳዳውን በ ሶፍት የደፈንን በስኪቢርቶ ካሴት ያጠነጠንን
በጥፍር ቀለም የተበጠሰ ካሴት የሰራን እቤታችን JVC ዴክ የነበረን VHS ካሴት የተከራየን VHS ካሴት ማጠንጠኛ ይዘን ያጠነጠንን ከ ብላክ ኤንድ ዋይት ቲቪ ወደ ከለርድ ቲቪ ያስቀየርን 21 ኢንች ከለርድ ናሽናል እንጨት የ ሚመስለው ቲቪ ወይም NEC ቲቪ ወይም 14 ኢንች ቲቪ ቤታችን የነበረ የ ከሰል ካውያ ወደ ኤሌክትሪክ ካውያ ያስቀየርን ስጋጃ ምንጣፍ ቤታችን የነበረ ወይም ጣውላ ወለል በሰም አሽተን ጉልበታችን እስኪዝል በበርኖስ ያሸን ሞ አንበሳ ባለው ትሪ ከቤተሰብ ጋር ተሰብስበን የ በላን
በቡታ ጋዝ ሻይ የተፈላልን ሰፈር ውስጥ የ ቡታ ጋዝ ክር ወደ ውስጥ ገብቶ ፈንድቶ ቤት ያቀጠለብን ሽርርር የሚለው ስልክ የነበረን ስልክ የተቆለፈብን ጠቅ ጠቅ ጠቅ አድርገን የደወልን ስም በተፃፍበት የ አባቶቻችን የ ቆዳ ቀበቶ የተገረፍን ለድግስ ቤታችን ዋይት ሆርስ ፣ ሬድ ሌብል ፣ ሄግ ዊስኪ የተገዛ ወይም እንግዳ ይዞልን የመጣ ታላቅ ፊልም ላይ ሺና ፣ ጋድ መስት ቢ ክሬዚ ፣ ዘ ስሪ ኮማንዶስን ያየን ፍሬንድስ ፣ ቢል ኮዝ ቢ ምንወዳቸው ሲት ኮም የነበሩ ቫንዳም ፣ ቻክኖሪስ ፣ ሸዋዚንገር ፣ ሻሩኬ ፣ ማክጋይቨርን የምንወድ በ እንግዳዘር ፣ አለባቸው ፣ ልመንህ ፣ አበበ በለው ፣ ደረጀ እና ሃብቴ ፣ ተስፋዬ ካሳ ቀልዶች የሳቅን.. ጂሚ ጂሚ ሃጃ ሃጃ ብለን የዘፈንን won't you take me to funky town የሚለውን ዘፈን ኮቱም ጃኬቱም ቆሽሿል እያን የዘፈንን በ 50 ሳንቲም ቪዲዮ ቤት ገብተን ፊልም ያየን እሁድ እሁድ ከ 8-10 ሰዓት 120 እያየን የተደበርን
space 1999 / ማያ / ፣ ፋዘር ዶሊንግ ፣ ጄክ ኤንድ ፋትማን ፣ አካፑልኮ ፣ ነፃ ትግል ፣ ቲቪ አፍሪካ ፣ ቅዳሜና ማክሰኞ ማታ ህበረት ትርዒት ፣ አርብ ከያቅጣጫው ቅዳሜ ማታ ታላቅ ፊልም ያየን...
አንዳይነት ባንዳይነት ፣ በፍሬዘር ሱሪ ፣ የጫማ ስእል ከነማሰርያው ጀርባው ላይ ባለው ጂንስ ጃኬት ፣ ካራቴ ጫማ ፣ ራንግለር ጂንስ ፣ አንበሳ ጫማ ፣ ሰንደል ጫማ ፣ ዶክተር ሹዝ ፣ ክሬሽን ቱታ ፣ ሆት ፓንት ፣ ስምንት ቅድ የዘነጥን...
ትዊንስ አራዳ ላይ ፣ ሄርሞን ፒያሳ ፣ ኮስሞስ ስቴድየም ፣ ለገሃር ሚኒ ፣ ቦሌ ሮድ ሮቢ ፣ ፐርፕል ፣ ፓራዲዞ ፣ ቦሌ ሚኒ ፣ ድንበል ዶም ቺኮቻችንን ቀጥረን ተቆራጭ እና ማኪያቶ አዘን 2 ሰዓት የጠበቅን... ኩዊንስ በርገር የበላን ፒዛ ዴሌ ሮማ ፒዛ የበላን ብሩኖስ አይስክሬም የበላን ፒያሳ ማሃሙድ ጋር ቺክ የቀጠርን ትሬን ሃውስ ፣ ሃራምቤ ፣ ኢንተር ላንጋኖ ሄደን የተሳሳምን አራት ኪሎ ጊርጊሮ እና ብሄራዊ ሥጋ ቤት ፣ ዶሮ ማነቅያ በቀለ ሥጋ ቤት ፣ መስቀል ፍላወር ሙሉ ሸዋ ስጋ ቤት ፣ ዱከም ምሥራቅ በር ሥጋ ቤት ፣ ናዝሬት ይልማ ሥጋ ቤት አዋጥተን ሄደን ቁርጥ እና ጥብስ የበላን በ አካል-ፀ ፣ ብላክ ላየን ፣ ድሪምስ ፣ ዛንዚባር ፣ ሲዱ ፣ ዴጃቩ ፣ ዲቫይን ፣ ፋንከን ፣ ሚልክ ሃውስ ፣ ሮሚና ፣ አሊዜ ፣ የጨስን በቢጎዲን ፀጉራችንን የጠቀለልን ፣ ስኒ ላይ በ ሻማ ጭስ ኩል በመስራት የተኳልን /የ ስር ኩል/ እንደ ኬሊ ሮውላንድ ስታይል ደረጃ ቁርጥ ፀጉራችንን የ ተቆረጥን ፣ የ አሊሺያ ኪስን ሹሩባ የተሰራን ፓንክ ፣ ቱፓክ ቁርጥ ፀጉራችንን ተቆረጥን ካተርፒለር እና ቲምበርላንድ ግድንግድ ጫማ አድርገን ፣ ሰፋፊ ቲሸርት ለብሰን ፣ ዎክ ማን በትልቅ ሄድፎን ሙዚቃ እየሰማን ነጠር ነጠር እያልን የሄድን ክረምት ክረምት ትልልቅ ቴፕ ይዘን ብሄረ ፅጌ ፣ አንበሳ ግቢ ፣ ባቦጋያ ፣ ሶደሬ ፣ ላንጋኖ ትሪፕ የሄድን የማይክል ጃክሰን ፣ ባብ ማርሊ ፣ ቱፓክ ፣ ኖቶሪየስ ቢ አይ ጂ ፣ አር ኬሊ ፣ ማክሲ ፕሪስት ፣ አሸር ፣ ቦይዝ ቱ ሜን ፣ ባክስትሪት ቦይዝ ፣ ማይክል ቦልተን ፣ ክሬግ ዴቬድ ፣ ሾን ፖል ፣ ዊትኒ ሂዮስተን ፣ ሴልን ዲዮን ፣ ማሪያ ኬሪ ሙዚቃ የ ሰማን...
ሪተርን ኦፍ ዘ ማክ ፣ ኬንት ተች ዚስ ፣ ዘፈኖችን በአማርኛ የዘፈንን ሃው ዊል አይ ኖ ፣ ሊን ኦን ሚን ለፍቅረኞቻችን የጋበዝን
የ አበበ ተካን
"አዬ ጉዷ መላመዷ
አዬ ጉዴ መላመዴ" ን ብለን አብረን የዘፈንን
ታይታኒክ ፣ ዘ ቦዲ ጋርድ ፣ ዘ ቻምፕ ፣ ፎረሰት ጋምፕ ፣ ብሬቭ ሃርት ምንወዳቸው ፊልሞች የ ነበሩ የ ነቀዘች ህይወት ፣ ጉዲ ፈቻ ፣ ቀዝቃዛ ወላፈን ፊልሞች ሲኒማ ገብተን ያየን ሳቤላ ፣ ብርቅርቅታ ፣ ፍቅር እስከ መቃብር ትረካ እሁድ ማታ ያዳመጥን አምልጦን ሰኞ ጠዋት ትምርት ቤት አርፍደን የደገምን እሁድ ጠዋት ከ 4-5 ሰዓት አብዬ ዘርጋውን ፣ ግዞ ፣ ባይከዳኝን እንዲሁም የመአበል ዋናተኞች ለመስማት የጏጏን..
የቅዳሜ ከሰዓት የሬድዮ ድራማዎች በ ማይክል ጃክሰን ዘፈን ክላሲካል ታጅቦ ያዳመጥን...
ቅዳሜ ቅዳሜ በ ኢቲቪ ፕሪሚየር ሊግ ቤታችን ያየን ሮማሪዮ ፣ ቤቤቶ ፣ ትልቁ ሮናልልዶን ያደነቅን... በሮናልዲኒሆ ጥበበኛ እግሮች የፈዘዝን ለዚዳን ብቃት ቆመን ያጨበጨብን በ ቤክሃም አቋም የተማረክን.. ሺረርን የጎል ማሽን ያልን... ስብሃት ገ/ እግዚአብሄር ፣ አዳም ረታ ፣ በውቀቱ ስዩምን ፣ ሲድኒ ሸልደን ፣ ዳንኤላ ስቴላ ፣ አጋታ ክርስቲ መፅሃፍ ያነበብን
ከ አዲስ ነገር ጋዜጣ እወቀት የሸመትን ..........
ጎጥ፣ ብሔር፣ ጎሳ የሌለን በኢትዮጵያዊነታችን የምናምን የአዲስ አበባ ልጆች እንዲህ ነን፡፡ ዘረኝነት ይብቃ
Click here to claim your Sponsored Listing.
Contact the business
Telephone
Website
Address
Addis Ababa
251911973232
Opening Hours
| Monday | 09:00 - 18:00 |
| Tuesday | 09:00 - 18:00 |
| Wednesday | 09:00 - 18:00 |
| Thursday | 09:00 - 18:00 |
| Friday | 09:00 - 18:00 |
| Saturday | 09:00 - 18:00 |