Gratia Gospel Ministry

Gratia Gospel Ministry

Share

Gratia Gospel Ministries envisions great impacting generation on this earth which is built and revealed by the life of the LORD.

23/05/2026

ዓለም ሁሉ ይስማ፦ ኢየሱስ አዳኝ ነው፣ ፈዋሽ ነው፣ በመንፈስ ቅዱስ ያጠምቃል፣ ወደ ዓለም ተመልሶ የሚመጣው የዓለም ሁሉ ነጉስ ነው።

18/05/2026

መዝሙር 20:7
እነዚያ በሰረገላ እነዚያም በፈረስ ይታመናሉ፤
እኛ ግን በአምላካችን በእግዚአብሔር ስም ከፍ ከፍ እንላለን።

10/05/2026

የኢየሱስ ክርስቶስ ደም
የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከአማኞች እለታዊ ሕይወት ጋር ያለው ግንኙነት (ተዛምዶ)
ቁልፍ ጥቅስ፦ ራዕይ 1:5-6
ቅዱስ ደሙ ከኃጢአት አጥቦናል (አንጽቶናል)
… ለወደደን ከኃጢአታችንም በደሙ ላጠበን፥ መንግሥትም ለአምላኩና ለአባቱም ካህናት እንድንሆን ላደረገ፥ ለእርሱ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ክብርና ኃይል ይሁን፤ አሜን። (ራዕይ 1:6)

I. መግቢያ፦
የፈሰሰው የክርስቶስ ኢየሱስ ደሙ የአንድ ጊዜ ክስተት ብቻ አይደለም። ይህ ደም የአማኞች ሁሉ መንፈሳዊ ኃይል እና የድላቸው ምንጭ ነው። ደሙ በአማኞች ዕለታዊ ኑሮ ውስጥ ከፍተኛ ስፍራ እአልለው።
II. ከዚህ ቀጥሎ 3 ዋና ዋና ነገሮችን እንመለከታለን፦
1. ደሙ ከሞተ ስራ ህሊናችንን ያነጻል (ዕብ. 9:13 - 14)
በየቀኑ ለእግዚአብሔር ንጹህ አምልኮ እንድናቀርብ ያስችለናል፣
2. ደሙ በየእለቱ ከፍተኛ ድል ይሰጠናል (ራዕይ 11:12)
ደሙ የድል ጋሻችን ነው፣
3. ደሙ በየቀኑ በብርሃን እንድንመላለስ ያደርገናል (1ዮሐ 1:5-10)
ከእግዚአብሔር እና እርስ በእርሳችን መልካም ህብረት እንዲኖረን ያደርጋል።
III. አማኞች ማድረግ ያለባቸው ጥንቃቄዎች (ዕብ. 10:26-31፣ 1ጴጥ. 1:13-21)
ወደን እና ፈልገን ኃጢአት መስራት የለብንም፣
በቅድስና መኖር አለብን፣
ደሙ የእግዚአብሔር ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ደም መሆኑን ሁልጊዜ አጥብቀን መረዳት አለብን፣
ክርስቶስ ሌላ ደሙ ሌላ እንደሆነ መቁጠር የለብንም፣
ምናልባትም ደሙን እንደ ልዩ ምትሃታዊ ነገር መቁጠር የለብንም።

አሜን ሃሌሉያ!
ግንቦት 2/2018

Spiritual Notes 05/05/2026

Spiritual Notes 167 likes, 4 comments. "HOW CHRIST GOT INTO MY FAMILY -Reinhard Bonnke"

27/04/2026

1) የጳውሎስ ልምምድ፣ (1ኛ ቆሮ. 14:18)

2) በልሳን ስንጸልይ እራሳችንን እናንጻለን፦ 1ቆሮ. 14፥4

3) በልሳን ስንጸልይ ለምልጃ ጸሎት ብርቱ ኃይል ይኖረናል (ሮሜ 8: 26 - 27) ፣

4) በልሳን ስንጸልይ በውስጣችን ላለው የእግዚአብሔር መገኘት ንቁ እንድንሆን ያደርገናል (ማቴዎስ 28፥19-20)፣

5) በልሳን ስንጸልይ እምነታችን ያድጋል እንዲሁም በእግዚአብሔር ፍቅር ውስጥ ዘወትር እንመላለሳለን (ይሁዳ 1፥20፣ ሮሜ 5፥5)፣

6) የምንጸልየው ልሳን ሲተረጎም መልዕክት ይሆንና ጉባኤው ይታነጻል፣ ይመከራል፣ ይጽናናል፣ (1 ቆሮ. 14፥5 )

7) በልሳን መጸለይ በደስታ ለሆነ አምልኮ እና ውዳሴ ማቅረቢያ መንገድ ነው፦ ( ዮሐንስ 4፥24)

ማጠቃለያ፦ ኑ አሁን በመንፈስ ቅዱስ ተሞሉ!!! በልሳን ጸልዩ!!! ሃሌሉያ።

ላምምምምትምህርት 7 : የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች

ታላቅ የሆነ የመንፈስ ቅዱስ መነቃቃት በዓለም ላይ እየሆነ ነው። ይህ የአዲስ ኪዳን የመጨረሻው የመንፈስ ቅዱስ መነቃቃት ዘመን ነው።

በመጀመሪያዋ ዘመን ቤተክርስቲያን የነበሩ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች ቀስ በቀስ እየከሰሙ የሄዱበት ዘመን ነበር።

ከቤተክርስቲያን ታሪክ እንደምንረዳው 1906 (እ.አ.አ .) የመንፈስ ቅዱስ ሪቫይቫል (መነቃቃት) እንደገና የጀመረበት ዘመን ነበር።

አሁን በ21ኛው ክፍለ ዘመን እስከ ጌታ ዳግም ምጽአት ጊዜ የተለየ የመንፈስ ቅዱስ መነቃቃት ይሆናል ብለን እናምናለኑ። ይህም ደግሞ ምንም የማይቀለብሰው እውነት ነው።
ኢዮኤል 2፥28
የሐዋ. 2: 1-4
የሐዋ. 2፥38 - 39

በመጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ እጅግ ብዙ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች በዝርዝር ይገኛሉ።
እነእርሱም፦ ሮሜ 12:6 - 8፣1ቆሮ. 12:7-11 ፣ 28-30፣ ኤፌ. 4:11- 12፣ ያሉት ሲሆኑ እነዚህንም በሚገባ ለመረዳት እያንዳንዳቸውን በጥልቀት ማጥናት ይኖርብናል።
ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ የምናጠናቸው የሚከተሉትን ዘጠኝ ስጦታዎችን ብቻ ናቸው፦
1) የንግግር ስጦታዎች፦
በልሳንመናገር
በልሳን የተነገረውን መተርጎም
ትንቢት መናገር

2) የመገለጥ ስጦታዎች፦
የጥበብ ቃል ሥጦታ
የእውቀት ቃል ስጦታ
መናፍስትን የመለየት ስጦታ

3) የማድረግ ስጦታዎች፦
የእምነት ስጦታ
የፈውስ ስጦታ
ታምራት የማድረግ ስጦታ ናቸው።

ከዚህ በላይ ከተዘረዘሩት የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች ውስጥ ጥቂቶችን ብቻ እንመለከታለን፦

7.1 በልሳን መናገር
በልሳን መናገር ሦስት ደረጃዎች አሉት። እነእርሱም፦
# የምልክት ልሳን፦ #ማር. 16:17
“ያመኑትንም እነዚህ ምልክቶች ይከተሉአቸዋል፤ በስሜ አጋንንትን ያወጣሉ፤ በአዲስ ቋንቋ ይናገራሉ፤ እባቦችን ይይዛሉ፥”
ይህ ስጦታ በክርስቶስ ኢየሱስ ላመኑት ሁሉ የሚሰጥ ነው። ለእያንዳንዱ በግል እንዲታነጽበት ይሰጣል። ላመኑት ደግሞ ምልክት ነው። ሁሉም በአንድ ጉባኤ መናገር ይችላሉ #የሐዋ. 10:48። ብዙ ጊዜ የሚተረጎም አይደለም፣

# # በልዩ ዓይነት ልሳን መናገር፦ #1ቆሮ.12:10
“ለአንዱም ትንቢትን መናገር፥ ለአንዱም መናፍስትን መለየት፥ ለአንዱም በልዩ ዓይነት ልሳን መናገር፥ ለአንዱም በልሳኖች የተነገረውን መተርጎም ይሰጠዋል፤”
ለአንዳንዶች በክርስቶስ አካል ውስጥ ለሆኑት መንፈስ ቅዱስ እንደፈቀደ የሚሰጠው ስጦታ ነው።
የሚተረጎም ነው። ማህበሩን እና ግለሰቦችን ያንጻል፣ ተናጋሪውንም ያንጻል። 1ቆሮ.14:4፣ 27-28፣
ሲተረጎም ሁለት ወይም ሦስት ሆነው በየተራ ይናገሩ፣ አንዱ ይተርጉም።
የሚተረጉም ባይኖር በጉባኤ መካከል ጸጥ ይበል እና ለራሱና ለእግዚአብሔር ይናገር። እንዲተረጉምም ይጸልይ። 1ቆሮ. 14:13፣28፣

# # # ልዩ ልዩ ዓይነት ልሳኖች፦ #1ቆሮ. 12:28
“እግዚአብሔርም በቤተ ክርስቲያን አንዳንዶቹን አስቀድሞ ሐዋርያትን፥ ሁለተኛም ነቢያትን፥ ሦስተኛም አስተማሪዎችን፥ ቀጥሎም ተአምራት ማድረግን፥ ቀጥሎም የመፈወስን ስጦታ፥ እርዳታንም፥ አገዛዝንም፥ የልዩ ልዩ ዓይነት ልሳኖችንም አድርጎአል።”
ለእያንዳንዱ ወይም ለጥቂቶች በክርስቶስ አካል ውስጥ ላሉት የሚሰጥ ነው።
ከአገልግሎት የጸጋ ሥጦታዎች ይመደባል። ይህ የጸጋ ሥጦታ ለቤተክርስቲያን መታነጽና ለወንጌል ስርጭት ይጠቅማል። ለማያምኑም ምልክት ይሆና። #1ቆሮ. 14:22፣
ልሳን ሲተረጎም ቤተክርስቲያንን ያንጻል። ለወንጌል ስርጭት የሚጠቅመው ተናጋሪው ሳያውቀው አዳማጩ ግን ሲያውቀው ጌታን መቀበል ይችላል ።
“የቀርጤስና የዓረብ ሰዎች፥ የእግዚአብሔርን ታላቅ ሥራ በልሳኖቻችን ሲናገሩ እንሰማቸዋለን።” #የሐዋ. 2:11

# # # # በልሳን መናገር ስጦታው እና አጠቃቀሙ፦
“እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ምንድር ነው? በምትሰበሰቡበት ጊዜ ለእያንዳንዱ መዝሙር አለው፥ ትምህርት አለው፥ መግለጥ አለው፥ በልሳን መናገር አለው፥ መተርጐም አለው፤ ሁሉ ለማነጽ ይሁን።” #1ኛ ቆሮንቶስ 14፥26
በግል በአምልኮ እና በጸሎት ጊዜ እያንዳንዱ በልሳን ቢጸልይና ቢዘምር ይታነጻል፣ ይባረካል። በህብረት አምልኮ ጊዜ ማንም ሳይታወክ መናገር ይቻላል።
“ስለዚህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ትንቢት ለመናገር በብርቱ ፈልጉ፥ በልሳኖች ከመናገርም አትከልክሉ፤” “ነገር ግን ሁሉ በአገባብና በሥርዓት ይሁን።” #1ኛ ቆሮንቶስ 14፥ 39-40
የሚተረጎም ልሳን ካለ ወደ ፊት ወጥቶ ቢነገር መልካም ነው። ይህም ከመሪዎች በመነጋገር ይሆናል።

# # # # # በልሳን የተነገረውን የመተርጎም ስጦታ፦
ይህ ስጦት በልሳን ከመናገር ስጦታ ጋር በቀጥታ የተገናኘ ስጦታ ነው።

ይህ ስጦታ ከተፈጥሮ በላይ የሆነ ከመንፈስ ቅዱስ የሚሰጥ ብቃት ሲሆን በሌላ ልሳን የተነገረውን ቋንቋ ጉባኤው ወደ የሚያውቀው ቋንቋ መተርጎም ነው።

ይህ ስጦታ በተፈጥሮአዊ እውቀት አንድን ቋንቋ ወደ ሌላ ቋንቋ የመተርጎም ችሎታ አይደለም።
በመንፈስ ቅዱስ ስጦታ የተነገረን ልሳን በመንፈስ ቅዱስ በሚሰጠው የመተርጎም ስጦታ ለጉባኤው በመተርጎም መናገር ነው።

ይህ የመተርጎም ስጦታ የሚሰጠው መንፈስ ቅዱስ እንደ ፈቀደ ሲሆን ማንኛውም በመንፈስ ቅዱስ የተሞላ አማኝ የሚተረጎመው ልሳን ሆነ ትርጉሙም ለራሲ ሊሰጠው ይችላል።

እነዚህ ሁሉ የዚያው የአንዱ መንፈስ ስጦታዎች ሲሆኑ፣ ለእያንዳንዱ ሰው መንፈስ ቅዱስ ራሱ እንደ ፈቀደ ይሰጠዋል። 1 ቆሮንቶስ 12:11

በልሳን የሚናገር ሰው እንዲተረጉም ይጸልይ። “ስለዚህ በልሳን የሚናገር እንዲተረጉም ይጸልይ።” # 1ኛ ቆሮንቶስ 14፥13

ልሳናት በሚነገሩበት ስዓት ትርጉሙ የሚሰጠው አማኝ ከራሱ ምንም አሳብ ሳይጨምር የተሰጠውን ብቻ መናገር አለበት። ጉባኤው ደግሞ ትርጉሙን አድምጦ በመፈተን መልእክቱን መቀበል ይኖርበታል።

7.2 ትንቢት የመናገር ስጦታ፦
“ለአንዱም ትንቢትን መናገር፥ ለአንዱም መናፍስትን መለየት፥ ለአንዱም በልዩ ዓይነት ልሳን መናገር፥ ለአንዱም በልሳኖች የተነገረውን መተርጎም ይሰጠዋል፤” 1 ቆሮ. 12፥10

“ትንቢትን የሚናገር ግን ለማነጽና ለመምከር ለማጽናናትም ለሰው ይናገራል።” 1 ቆሮ. 14፥3

“ሁላችሁ በልሳኖች ልትናገሩ እወድ ነበር፥ ትንቢትን ልትናገሩ ግን ከዚህ ይልቅ እወዳለሁ፤ ማኅበሩ ይታነጽ ዘንድ ንግግሩን ባይተረጐም በልሳኖች ከሚናገር ትንቢትን የሚናገር ይበልጣል።” 1ቆሮ.14፥5

በ1ቆሮ. 14:31 መሰረት አማኞች ሁሉ መንፈስ ቅዱስ እንደፈቀደ ትንቢት የመናገር ስጦታ ሊኖራቸው ይችላል። ምክንያቱም፦

“ሁሉም እንዲማሩ ሁሉም እንዲመከሩ ሁላችሁ በእያንዳንዳችሁ ትንቢት ልትናገሩ ትችላላችሁ።” # 1ኛ ቆሮንቶስ 14፥31

ትንቢት ተናጋሪዎች ከጌታ የተቀበሉትን ትንቢት በየተራ መናገር ይገባቸዋል። በአንድ ጉባኤ ተናጋሪዎቹ ከሶስትም መብለጥ የለባቸውም። 1ቆሮ.14:29-33።

የትንቢት ስጦታ ዓላማ፦
1) ቤተክርስቲያንን ለማነጽ፣
2) ቤተክርስቲያንን ለመምከር እና
3) ቤተክርስቲያንን ለማጽናናት ነው።

ነገር ግን ትንቢት ማለት ስብከት ማለት አይደለም። ትንቢት እና ስብከት ሁለቱ የተለያዩ ናቸው። ትንቢት ሲቀርብ የተቀበለውን መናገር ብቻ እንጂ እንደ ስብከት መብራት የለበትም።

የትንቢት ስጦታ የአገልግሎት ትኩረቱ በማነጽ፣ በማበረታታት እና በማጽናናት ላይ እንጂ የወደፊቱን በመናገር ላይ ትኩረት የለውም።

የወደፊቱን የመናገር ስጦታ ከዕውቀት እና ከጥበብ ስጦታ ጋር የሚያያዝ ነው።

ሌላው ጥንቃቄ የትንቢት ስጦታ ለግለሰብ ምሪት የሚሰጥ መሆን የለበትም። አንድ አማኝ በትንቢት ሳይሆን መመራት ያለበት ምሪትን መጠየቅ ያለበት ከጌታና ከመንፈስ ቅዱስ ብቻ ነው።
“በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመሩ ሁሉ እነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸውና።” # ሮሜ 8፥14

ምሪት የምንቀበለው ቃሉን በማጥናት እና በመረዳት፣ እንዲሁም በመንፈስ ቅዱስ የውስጥ ምስክርነት ነው።

ሆኖም አንድ ትንቢታዊ መልዕክት የሚነገረን ከሆነ ቀደም ሲል እኛ ከጌታ የተረዳነውን ለማረጋገጥ ይሆናል።

በዚህ ዘመን ትንቢትን ከእግዚአብሔር ቃል እና ከመንፈስ ቅዱስ የውስጥ ምስክርነት በላይ አድርገን መውሰድ የለብንም። ይህ ከባድ መንፈሳዊ አደጋ አለው። ብዙዎች በዚህ መንገድ በመሄድ ስተዋል።።

(*** የሌሎቹ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች ይቀጥላሉ)

14/04/2026

እግዚአብሔርን በመምሰል በሙላት ማደግ የምንችለው እንዴት ነው?
ክፍል 1

14/04/2026

እግዚአብሔርን በመምሰል በሙላት ማደግ የምንችለው እንዴት ነው?
ክፍል 1
መግቢያ፦
በእግዚአብሔር ህያው ቃል እና በጸሎት ካልሆነ በስተቀር እግዚአብሔን በመምሰል የምናድግበት መንገድ የለም።
ቅዱስ ቃልን በመመገብ፣ በተግባር በመለማመድ፣ በግል ህይወት በመኖር የእግዚአብሔርን ህይወት በውስጣችን በየቀኑ ልንገነባ ይገባናል። በዚህ ውስጥ ልብ ማለት ያለብን ቃሉ እና ጸሎት የማይለያዩ መሆናቸውን ነው።

#1 “እንግዲህ እንደ ተወደዱ ልጆች እግዚአብሔርን የምትከተሉ ሁኑ፥ ... ።” ኤፌሶን 5፥1-2

#2 “ነገር ግን በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እውቀት እደጉ። ... ።” 2ኛ ጴጥሮስ 3፥18

#3 “የእግዚአብሔር ቃል በሙላት ይኑርባችሁ፤ ... ” ቆላስይስ 3፥16

ትርጉም፦ በእግዚአብሔር ባህርይ ማደግ ማለት ምን ማለት ነው ?
የመዝገበ ቃላት ትርጉሙ፦ እጅግ በጣም ከፍ ያለ የሞራል ልዕልና ማለት ሲሆን ይህ ዓይነቱ መጽሐፍ ቅዱሳዊው የባህርይ ልዕልና ምንጩ የእግዚአብሔር ቃል እና ከእግዚአብሔር ጋር ያለን የማያቋርጥ ህብረት እና አንድነት ነው።
የባህርያችን እድገት መለኪያ እና እውነተኛ ምሳሌአችን ጌታችን ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።

እንዲሁም በእውነት ክርስቶስ ኢየሱስን የሚከተሉ አማኞች ሁሉ ይህ እጅግ ከፍ ያለው መንፈሳዊ የሞራል ልዕልና እንዲኖራቸው በከፍተኛ ደረጃ የሚጠበቅባቸው ሆኗል።

“እኛም ሁላችን በመጋረጃ በማይከደን ፊት የጌታን ክብር እንደ መስተዋት እያብለጨለጭን መንፈስ ከሚሆን ጌታ እንደሚደረግ ያን መልክ እንመስል ዘንድ ከክብር ወደ ክብር እንለወጣለን።” 2ኛ ቆሮ 3፥18

ዛሬ ሁላችንም እንደምናውቀው ዓለም በከፍተኛ የሞራል ውድቀት ውስጥ እጅግ በከፋ ሁኔታ ትገኛለች። ቤተክርስቲያንን ከቀን ወደ ቀን እያሰጋት ያለው ይኸው ከባድ የባህርይ ወይም ያሞራል ውድቀት ነው።

ነገር ግን ይህ አይነቱ አምላካዊ (godly charactur) ባህርይ በአንድ ለሊት የሚገነባ ሳይሆን ብዙ ድካም እና ብዙ ስራ እንዲሁም ብዙ ልምምድ ይጠይቃል። ይህም ብቻ አይደለም ትላንትና ካለፈው ውድቀታችን ብዙ መማርን ይጠይቃል።

“ነገር ግን ለዚህ ዓለም ከሚመችና የአሮጊቶችን ሴቶች ጨዋታ ከሚመስለው ተረት ራቅ። እግዚአብሔርን ለመምሰል ግን ራስህን አስለምድ።” 1ኛ ጢሞቴዎስ 4፥7

20/01/2024

የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ዋና ዓላማ ምንድን ነው?
የመጀመሪያው የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ዋና ዓላማ የክርስቶስ ምስክር ለመሆን ነው፦

ሐዋሪያት እና ወንጌላውያን እንዲሁም ሌሎች ወንድሞችና እህቶች መንፈስ ቅዱስን የተሞሉት የክርስቶስ እውነተኛ ምስክር ለመሆን ነው፣ የሐዋ. 1: 4-8፣

ወንጌላዊያንና ሚሲዮናዊያን ሁሉ ሁል ጊዜ በመንፈስ ቅዱስ ሙላት ክርስቶስን ይመሰክራሉ፣

እስጢፋኖስ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል የተሞላ ሰው ነበር፣ ህይወቱ እስኪሰዋ ድረስ ክርስቶስን መስክሯል። የሐዋ. 6:8-10፣ የሐዋ. 7:55፣

ፊሊጶስ በመንፈስ ቅዱስ ሙላት ለሰማራዊያንን ክርስቶስን ሰበከ፣ የሐዋ. 8:5-8

ጴጥሮስ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ ክርስቶስን በሙላት ሰብኳል፣ የሐዋ. 2:14-40፣ የሐዋ. 4:8

ጳውሎስ በመንፈስ ቅዱስ ኃይልና ስልጣን ከኢየሩሳሌም ጀምሮ እስከ አልዋሪቆን ድረስ ክርስቶስን ሰብኳል፣ የሐዋ. 13:4-9፣ የሐዋ. 15:18-19፣

የቆጵሮስና የቀሬና ሰዎች የጌታ እጅ (መንፈስ ቅዱስ) ከእነርሱ ጋር ነበርና ክርስቶስን ሰብከዋል፣ የሐዋ.11:19-24

በህይወታችሁ እጅግ ደስተኞች መሆን ከፈለጋችሁ ክርስቶስን በመንፈስ ቅዱስ ኃይል በመስበክ መከሩን ሰብሰቡ።

ዛሬ ባለው አረዳድ የመንፈስ ቅዱስ ሙላት ዓላማ መስመሩን የሳተ በመሆኑ ቤተክርስቲያን ችግር ውስጥ ወድቃለች።

ወደ እውነተኛው የመንፈስ ቅዱስ ሙላት ዓላማ በመመለስ የክርስቶስን ወንጌል እንስበክ። አሜን።

ሳሙኤል ከበደ ብሩ (ፓስተር)

20/12/2023

አንዲት እውነተኛ የክርስቶስ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን መሰረታዊ የመንፈስ ቅዱስ ትምህርት እና ልምምዶቹ ከሌላት ጤነኛ ቤተክርስቲያን አይደለችም።

I Was Homeless And Hated God, Until This Happened… 17/12/2023

I Was Homeless And Hated God, Until This Happened… Christina Baker was homeless and hated God, until this happened...

Want your place of worship to be the top-listed Place Of Worship in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address


Addis Ababa