Fidel Tube
Welcome to my Channel
ፊደል Tube
02/12/2020
በመቀሌ ከተማ የአገር መከላከያ ሰራዊት የማያውቀው የመሳሪያ ማከማቻ ዲፖ ተገኘ
የልዩ ዘመቻ 2ኛ ብርጌድ 3ኛ ሬጅመንት አዛዥ ሌተናል ጀነራል ሳድቅ አህመድ እንዳሉት መቀሌ ላይ መከላከያ የማያወቀው የመሳሪያ ማከማቻ ዲፖ ተገኝቷል።
የጁንታው ቡድን ውጊያውን መቋቋም ሲሳነው ትጥቁን እያራገፈ ፈርጥጧልም ብለዋል።
ከዚህ ውስጥ ሰራዊቱ የማያውቀው የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች የተከማቹበት ዲፖ ተገኝቷል ብለዋል
የሰሜን እዝ አመራሮችን ጠይቀን ስለዲፖው እንደማያውቁ ገልጸውልናል ያሉት ሌተናል ጀነራሉ፤ በቀጣይም ተመሳሳይ የመሳሪያ ማከማቻወችም ሊገኙ እንደሚችሉ ገልፀዋል።
በመሆኑም እነዚህ ከቀላል እስከ ቡድን መሳሪያዎች ወንጀል እዳይፈጸምባቸው የፍተሻ ስራው ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
ኢዜአ
07/06/2020
27/05/2020
Ethiopian Body builder Tsega Worku Full Body at Home Workout ቤታችን ውሥጥ መስራት የምንችለው ቀለል ያለ እስፖርት
24/05/2020
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 4048 የላብራቶሪ ምርመራ 88 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።
በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ተጨማሪ 88 ሰዎች ተገኙ
ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 4048 የላቦራቶሪ ምርመራ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ተጨማሪ 88 ሰዎች ተገኝተዋል፡፡
አዲስ የተገኙትን ጨምሮ ባጠቃላይ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 582 ደርሷል፡፡
ቫይረሱ የተገኘባቸው ግለሰቦች የእድሜ ክልላቸው ከ 8 እስከ 75 ዓመት ሲሆን 51 ወንዶች እና 37 ሴቶች ናቸው፡፡
ሁሉም ኢትዮጵያውያን መሆናቸውንም የገለጹት ሚኒስቴሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ
73 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 8 ሰዎች ከትግራይ ክልል ፣ 4 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል ፣ 1 ሰው ከሀረር ክልል ፣ እንዲሁም 2 ሰዎች የድንበር ተሸጋሪ አሽከርካሪዎች ናቸው ብለዋል፡፡
ከ88ቱ ግለሰቦች 13ቱ የውጭ ጉዞ ታሪክ ያላቸው፣ 20ው በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የነበራቸው፣ 55ቱ ደግሞ የጉዞም ይሁን የግንኙነት ታሪክ የሌለው እንደሆነ ሚኒስትሯ በሪፖርታቸው አካተዋል፡፡
በሌላ በኩል 1 ሰው ከኦሮሚያ ክልል ከቫይረሱ ያገገመ ሲሆን አጠቃላይ ያገገሙት ቁጥርም 152 ደርሷል፡፡
22/05/2020
በኢትዮጲያ 30 ተጨማሪ ሰዎች ላይ የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው‼️
በአጠቃላይ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 429 ደርሷል፡፡
የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ፡-⬇️
~ ባለፉት 24 ሰዓት ዉስጥ ለ3645 ሰዎች ምርመራ ተደርጎ 30 ኢትዮጲያዉያን ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል፡፡
~ 26ቱ ወንዶች ሲሆኑ 4ቱ ደግሞ ሴት ናቸው።እድሜያቸዉ ከ15 እስከ 60 ዓመት የሆኑ ናቸዉ።
~ የመኖሪያ ስፍራቸዉ 18 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣4 ሰዉ ከአሮሚያ ክልል(ጅግጅጋ ለይቶ ማቆያ )፣ 3 ሰዎች ከአፋር ክልል ፣3 ሰዉ ከትግራይ ክልል፣2 ሰዉ ድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪ
~ 9 ሰዎች የውጭ ሀገራት የጉዞ ታሪክ ያላቸው ናቸው፡፡
~ 17 ሰዎች በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት አላቸዉ፡፡
~ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የሌላቸዉ 4 ሰዎች ናቸው።
ተጨማሪ መረጃ ፦
~ አጠቃላይ ምርመራ የተደረገላቸው ሰዎች ቁጥር 73,164 ደርሷል።
~ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 5 ሰዎች አገግሟል።
~ አጠቃላይ ያገገሙ ግለሰቦች 128 ደርሰዋል።
~ በጽኑ ህሙማን ማከምያ ዉስጥ የሚገኝ ታማሚ የለም ፡፡
~ በለይቶ ህክምና ውስጥ ያሉ 294 ናቸው።
~ የአምስት ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡
10/05/2020
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 29 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል!
ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 2,171 ላቦራቶሪ ምርመራ 29 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያቸው ተረጋግጧል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 239 ደርሷል።
04/05/2020
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 5 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል!
ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 1,758 ላቦራቶሪ ምርመራ 5 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያቸው ተረጋግጧል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 140 ደርሷል።
25/04/2020
እስክንድር ነጋ በአሁን ሰዓት ኮልፌ ፖሊስ መምሪያ እንደሚገኝ ፓርቲው አስታውቋል
የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲፕሬዝዳንት አቶ እስክንድር ነጋ ዛሬ ሚያዚያ 17/2012 ዓ.ም ጠዋት ጀምሮ ከቤታቸው እንደወጡ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ኮማንድ ፖስት የእስር ትዕዛዝ መታሰራቸውን በፌስቡክ ገጹ ያስታወቀው የፓርቲው ቃል አቀባይ አቶ ስንታየሁ ቸኮል “በአሁን ሰዓት ኮልፌ ፖሊስ መምሪያ እንዳለ አረጋግጠናል” ሲል በድጋሚ አስታውቋል፡፡
አቶ እስክንድር “…ኮልፌ ቀራኒዮ ወረዳ 05 የድሆችን ቤት ፈረሳን አስመልክቶ ለምን ተገኘህ…” በሚል እንዳሰራቸውም ነው ቃል አቀባዩ በገጻቸው ያሰፈሩት፡፡
21/04/2020
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 3 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!
በኢትዮጵያ ባለፋት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገ 745 የላብራቶሪ ምርመራ ሶስት (3) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ተረጋግጧል። በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 114 ደርሷል።
የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦
ታማሚ 1 - የ42 ዓመት ቻይናዊ የመኖሪያ ቦታው ሰበታ ዞን ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የለውም፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያለው ግንኙነት በመጣራት ላይ ነው።
ታማሚ 2 - የ22 ዓመት ኢትዮጵያዊ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የለውም፤ በስራው ባህሪ ለበሽታው ተጋላጭነት ያለው።
ታማሚ 3 - የ22 ዓመት ኢትዮጵያዊ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ፤ ከሳዑዲ የመጣና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።
20/04/2020
ልዩ የስራ ጠባይ ላላቸውና ድጋፍ ለሚሹ የይለፍ ፍቃድ እየተሰጠ ነው
ከኮድ-2 ተሽከርካሪዎች የፈረቃ እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ ልዩ የስራ ጠባይ ላላቸውና ልዩ ድጋፍ ለሚሹ የተሽከርካሪ የይለፍ ፍቃድ እየሰጠ መሆኑን የፌዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣን አስታውቋል፡፡
ከዛሬ ጀምሮ እንዲተገበር ሆኖ ከወጣው የፈረቃ እንቅስቃሴ መመሪያ ጋር በተያያዘ ጥያቄ ያላቸው አካላት ወደ ባለስልጣኑ እየመጡ ነው ያሉት የባለስልጣኑ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ይግዛው ዳኘው በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በተቀመጠው የልዩ ድጋፍ አሰጣጥ መመሪያ መሰረት እየተስተናገዱ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ለጤና እና ፋርማሲ ባለሙያዎች፣ ለሚዲያ አካላት እንዲሁም ለአካል ጉዳተኞች አዋጁን ለማስፈጸም በወጣው የትራንስፖርት ስምሪት መመሪያ አንቀጽ 10 ንዑስ አንቀጽ 3 መሰረት በተቋቋመው የቴክኒክ ኮሚቴ እየታየ የይለፍ ወረቀት እየተሰጣቸው እንደሆነም ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡
ምንጭ:አላይን አማሀሪክ
20/04/2020
ጃክ ማ ሶስተኛ ዙር የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ቁሳቁሶችን ለአፍሪካ ሃገራት ሊልኩ ነው
የአሊባባ ፋውንዴሽን መስራችና ዋና ስራ አስፈጻሚ ጃክ ማ ሶስተኛ ዙር የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ቁሳቁሶችን ለአፍሪካ ሃገራት ሊልኩ ነው።
ጃክ ማ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ በርካታ የህክምና ቁሳቁሶችን ለሶስተኛ ጊዜ ለአፍሪካ ሃገራት ሊልኩ መሆኑን አስታውቀዋል።
በዚህም 4 ነጥብ 6 ሚሊየን ማስኮች፣ 500 ሺህ ናሙና መውሰጃ እና መመርመሪያዎች፣ 300 የመተንፈሻ መሳሪያዎች፣ 200 ሺህ አልባሳትና 200 ሺህ የፊት መሸፈኛዎች ለሃገራቱ ይላካሉ።
ከዚህ በተጨማሪም 2 ሺህ የሙቀት ኘመለኪያዎች፣ 100 የሰውነት መለኪያ መሳሪያዎች እንዲሁም 500 ሺህ ጥንድ የእጅ ጓንቶችም የሚላኩ ይሆናል።
ጀክ ማ ከዚህ ቀደም ለአፍሪካ ሃገራት የኮሮና ቫይረስ መከላከያ በሁለት ዙር ድጋፍ ማድረጋቸው ይታወሳል።
ምንጭ ፋና
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Website
Address
Opening Hours
| 00:00 - 12:00 |